Telegram Group Search
ቀሪ 100ኛ ቀን የተመራቂ ተማሪዎች በዓል በዛሬው እለት በደመቀ ሁኔታ ተከብሮ ውሏል።

በተለያዩ የመዝናኛ እና የበጎ አድራጎት ተግባራት ሲከናወን የዋለ ሲሆን በውድድሮች ተሸናፊ የሆነ ዲፓርትመንት በደብረብርሃን በስደት ላይ ያሉ ወገኖቻችንን ገንዘብ በማዋጣት ለመርዳት ተችሏል። እንዲሁም ዕለቱን ደም በመለገስ ታስቧል።

ቀሪ የምረቃ በዓሎችን እንዲሁ በደመቀ መልኩ ማክበሩ ይቀጥላል።

@DBU11
@DBU_ENTERTAIN
#MESA ተመልሷል!
ለሁሉም 1ኛ ዓመት ተማሪዎች በሙሉ

ልዩ የቲቶሪያል ስልጠና ጊዜ 26/07/2016 (ሐሙስ) ምሽት 12:00
ከ MESA ጋር

@DBU11
#ከእናንተው

ከቀን 17/07/2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 22/07/2016 ዓ.ም ብቻ በደብረብርሃን ቻይና ካምፕ ተጠልለው የሚገኙ ወገኖችን ለመርዳት በተሰበሰበ የገንዘብ እርዳታ በአጠቃላይ 83,000 ብር ሊሰበሰብ ተችሏል።

ይህም የተለያዪ የማሰባሰብ መንገዶችን በመጠቀም
ዶርም በመዞር፣ስፖንሰሮችን በመጠየቅ፣በአስተዳደር እና ዲፓርትመንት ቢሮዎች ቁሳቁሶችን ድጋፍ በመጠየቅ፣እንዲሁም በሶሻል ሚዲያ (Tiktok,Telegram) የዕለት ቁርስ በማስፈረም የተገኘ ነው።

ከዚህ በተጨማሪ ከ4503 ተማሪዎች ወጪ እንዲሆን የተፈረመ ቁርስ ከተማሪዎች ምግብ ቤት 1140 ዳቦ፣5 ድስት ፍርፍር ነው ወጪ የተደረገው።

ከግቢያችን ምግብ ቤቶች መካከል ማርካን (ቢኒ) ከ200 በላይ ለሚሆኑ ተፈናቃዮች በ2ዓይነት ምግብ ነፃ ድጋፍ አድርጓል።

በልብስ የተሰበሰበ 6 ቦንዳ ልብስ የተሰበሰበ ሲሆን

ከእናንተ የተገኘውን፣በስፖንሰር የተሸፈነውንም እሁድ 22/07/2016 ለስደተኛ ወገኖቻችን ሊደርስ ችሏል።

በዚህ የእርዳታ ስራ ላይ ስታስተባብሩ፣ስትደግፉ፣ስትረዱ በፍቃድም በተግባርም አብራችሁ ለተሳተፋችሁ ሁሉ ምስጋና ይግባችሁ።

@DBU11
የተማሪዎች ሃሳብ እንደወረደ

ጥቆማ    : በ  DBU   እየተሰጠ   ያለው   የአፈታተን   ስርዓት   ከታለመለት  አላማ   ውጪ   መሆኑን     መጠቆም  እወዳለሁ።  ማለትም   ኩረጃ   የሚባለውን  ነገር  ይበልጥ   ለማጠናከር  ታቅዶ   የተሰራ     የሚያስመስል     በርካታ  መገለጫውች  አሉት።  ይህም   ከsystem  እስከ   ፈታኝ   ድረስ  በተለይ    system  በጣም   ጥናት  የሚያስፈልገውና      በደንብ   የተረጋገጠ   ሙከራ  አልተሰራበትም።  ማለትም    ይህ  ስርዓት   ኩረጃን   ካላስቆመ   ምንድነው  ጥቅሙ   ......?

አባካችሁ   የሚመለከታችሁ    ሁሉ ይህ  ነገር      በጣም   አዛ  ነው።  ተማሪዎችም   የሚስጥር   ቁጥራቸውን  በመለዋወጥ    የፈተናን    ምዘና    ኢ_ፍትሀዊ     እያደረጉት   እንደሆነ   universty ሊያውቅ  ይገባል።

@DBU11
@DBU_ENTERTAIN
ለእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ መልካም በዓልን እንመኛለን!

ኢድ ሙባረክ!
@DBU11
#ዒድ_አልፈጥር

1445ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በግቢያችን በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በድጋሜ DBU DAILY እንኳን ለ የዒድ አልፈጥር በዓል አደረሳችሁ ይላል።

ዒድ ሙባረክ !

@DBU11
@DBY_ENTERTAINMENT
ለማንኛውም የህትመት እና ዲዛይን ስራዎች

ይደውሉ
0940219376
#update
ፋና አዲስ ትውልድ በደብረብርሃን ከተማ የሚገኙ ወጣቶች ላይ ያተኮረ የግንኙነት መረብ የሚያሰፋ ፕሮግራም አዘጋጀ።

የወጣቶች ስነተዋልዶና ጤና አጠባበቅ ላይ ያተኮረው ይህ ፕሮግራም በደብረብርሃን ከተማ ውስጥ የሚገኙ ወጣቶች ላይ ትኩረታቸውን አድርገው ከሚሰሩ የተለያዩ ተቋሟት ጋር የልምድ ልውውጥ አድርገዋል።

በልምድ ልውውጡ የወጣቶች ጤና አጠባበቅ ላይ መሰራት
አለባቸው ያሉትን የተለያዩ ስራዎች  ላይ ውይይት አድርገዋል።

በፕሮግራሙ የደብረብርሃን ከተማ ጤና መምሪያ፣ የሴቶችና ህፃናት መምሪያ  ፣ ቪክትሪ ኮሌጅ ፣ በደብረ ብርሃን ከተማ የሚገኙ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ና የመንግስት ሃላፊዎች በተገኙበት የከተማዋው እንዲሁም የዩኒቨርስቲ ወጣቶች ተሳታፊ ሆነዋል።

@DBU11
የስራ ቅጥር ማስታወቂያ

@DBU11
አዲስ ናሽናል አይዲ በደብረብርሃን ከተማ መመዝገብ ተጀምሯል

ምዝገባው የተጀመረው በደብረብርሃን ከተማ ሼል አካባቢ በሚገኘው የአልማ(አማራ ልማት ማህበር) ህንጻ 1ኛ ፎቅ ላይ ሲሆን በመረጃ አያያዝ ጉዳይ ተመዝጋቢዎች በያዙት ህጋዊ መረጃ መሰረት የሚካሄድ ይሆናል። ይህም የመጀመሪያው የቀበሌ መታወቂያ፣የዪኒቨርሲቲ አይዲ እንዲሁም መሰል መታወቂያዎች ለመረጃነት የሚያገለግሉ ሲሆኑ በናሽናል መታወቂያው ላይ የሚሰፍረው መረጃ ቅድሚያ ለምዝገባ በሰጡት መታወቂያ ላይ የተመሰረተ ነው። ማለትም እንደምሳሌ የአዲስ አበባን መታወቂያ የያዘ ሰው የናሽናል አይዲው መረጃ አዲስ አበባ ተብሎ ይመዘገባል። የዩኒቨርሲቲ መታወቂያም ከሆነ መታወቂያው ላይ የሚሰፍረው መረጃ የዩኒቨርሲቲው(ደብረብርሃን) የሚል ይሆናል።

በመሆኑም አዲስ መመዝገብ የምትፈልጉ በቢሮው በመገኘት ምዝገባውን መፈጸም የምትችሉ ሲሆን የፋይዳ ቁጥር እስከ 2 ቀን ባለው ጊዜ ውስጥ ይደርሳችኋል። የደረሳችሁን የፋይዳ ቁጥር የቴሌብር ሱፐር አፕን በመጠቀም ናሽናል ፋይዳ አይዲ በሚለው አማራጭ የመታወቂያ ፋይላችሁን በ ፒዲኤፍ ማውረድ ትችላላችሁ። በፒዲኤፍ የወረደውን የመታወቂያ ፋይልም በ @natiTG2 በመላክ ወደ ካርድ መታወቂያ በ150 ብር ማሳተም ትችላላችሁ።

መረጃን ማስተካከል የምትፈልጉ አሁን በደብረብርሃን አገልግሎቱ አልተጀመረም።

ለበለጠ መረጃ 0940219376
@NatiTg2
ከምዝገባ እና ከመረጃ ለውጥ ጋር ለተያያዘ ጥያቄ በ0940219376 ልታናግሩኝ ትችላላችሁ።
2024/04/20 10:16:24
Back to Top
HTML Embed Code: