tg-me.com/GAT_Tutorial/172
Last Update:
ለምን ጥቂት ተማሪዎች ብቻ ለድህረ ምረቃ ፕሮግራም ይታጫሉ?
ከ 30 ሚልዮን በላይ የሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ በትምህርት ዘርፍ ውስጥ ነው ያለው። በየዓመቱ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የመጀመሪያ ድግሪ ተማሪዎች ከተለያዩ ከመንግስት እና ከግል ከፍትኛ ት/ት ተቋማት ይመረቃሉ። ይሁን እንጅ የሁለተኛና የሶስተኛ ድግሪ ምሩቃን ቁጥር እምብዛም አይደለም። ለምሳሌ በ2012 - በ2013 አካደሚክ ዓመት ላይ 6,353 የምያህሉ ማስተርስ ተማሪዎች ከተለያዩ ዩኒቨሪቲዎች እና ኮሌጆች ተመርቀዋሉ። ይሄ በ 2008-2009 ዓ.ም ከተመረቁ የሁለተኛ ድግሪ ምሩቃን ቁጥር (3,574) ጋር ሲነጻጸር 75% ዕድገት አሳይቷል። እንደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ያሉ ተቋማት በየዓመቱ በሺዎች የሚቆጠሩ የሁለትኛ ድግሪ ተማሪዎችን ያስመርቁ ነበሩ።
የሶስተኛ ድግሪ ምሩቃን ቁጥር በሀገር አቀፍ ደረጃ እጅግ በጣም ዝቅተኛ ነው። ለምሳሌ በፈረንጆች 2020 ላይ ከ 3000 በላይ የሶስተኛ ድግሪ ተማሪዎችን የተለያዩ ከፍተኛ ት/ት ተቋማት ተቀብለዋሉ። በየዓመቱም ከ500 በላይ የዶክትሬት ድግሪ ምሩቃን ከተለያዩ ከፍተኛ ት/ት ተቋማት ይመረቃሉ። በፈረንጆች 2023 ላይ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲት ከ 300 በላይ የሶስተኛ ድግሪ ተማሪዎችን አስመርቆ ነበር።
በ2023 ለመጀመሪያ ጊዜ የብሄራዊ ድህረ ምረቃ ፕሮግራም መግቢይ ፈተና NGAT/GAT ከተመጀመረበት ጊዜ አንስቶ በተለያዩ ዙሮች ፈተናውን ከሚወስዱት 5% ተማሪዎች ብቻ እንድምያልፉት መረጃዎች ይጠቁማሉ። ከNGAT/GAT ፈተና በኋላ በየዓመቱ ምን ያክል የሁለተኛ እና ሶስተኛ ድግሪ ተማሪ ሊመረቅ ይችላል የሚለውን ከዚህ ዓመት ጀምሬን አብረን የምናይ ይሆናል።
ጥቂት ተማሪዎች ብቻ ስኬታማ ሆነው ወደሚገቡበት የድህረ ምረቃ ትምህርት ፕሮግራም ለመግባት NGAT/GAT ማለፍ የግዴታ ሆኗል። ከስራ ገበታችሁ ሳትርቁ ፥ ካላችሁበት ሆናችሁ እጅግ በጣም ቀላል፣ ግልጽ እና ለመረዳት ምቹ የሆኑ የGAT ቪድዮ ትምህርቶችን ፥ ሲሙዪለሽን እና የ NGAT/ GAT Solution በማግኘት በቀላሉ ማለፍ ትችላላችሁ።
ሼር: @GAT_Tutorial 🙏
ለመምዝገብ : ⤵️
@GATtutorialbot
BY GAT Tutorial Official
Warning: Undefined variable $i in /var/www/tg-me/post.php on line 283
Share with your friend now:
tg-me.com/GAT_Tutorial/172