Telegram Group Search
“እፈልግሀለሁ”  ይህ ቃል ለአድማጩ ቀላል፣ ለተናጋሪው ደግሞ እጅግ ከባድ የሆነ ቃል ነው። ምናልባት ተናጋሪው የሚያሳፍረውና የሚያሳምመው ጉዳይ መሀል  ላይ የሚወጣ ቃል ነው።  ደካማነቱን ለመሸፈን የሚጥርበት ሌላ ዘዴም ይሆናል አንዳንዴ።  በዚህ ቃል የሚያናግሩን ሰዎች ትኩረት መስጠት ይኖርብናል።  ከጉዳያቸው መሀል እነርሱን ማንጠልጠል በደል ስለሚሆንብን።

@fuadkheyr
@fuadkheyr
መፅሃፍን ለፌስቡክ ልጥፍ በሚመች አጭር ይዘት ደግሞ የመፃፍ ውድድር ጀምረናል። ለመነሻ እንዲሆን ሰሞኑን ከታተመው የ ABX መፅሀፍ እንጀምራለን። "ሰባሐል ኸይር" እነሆ መፅሀፉን ሙሉ ለሙሉ ማንበብና መረዳት ግዴታ ነው። የመፅሃፉን ሀሳብ አሳጥሮ የተሻለ የፃፈ ይሸለማል።

ሽልማቱ ምንድነው?
1ኛ ለወጣ ሰው 3000 ብር
2ኛ ለወጣ 1500 ብር
3ኛ ለወጣ ደግሞ 1000 ብር
ከ4 እስከ 10 ደግሞ የተሻለ ለፃፉት ለጥሩ ተሳትፎ 200 ብር።
በተጨማሪም ለአስሩም ተሸላሚዎች "አልሂጃብ" የተሰኘ የመፅሃፍ ሽልማት ይኖራቸዋል። የኡማው ከንባብ መራቅ ያሳሰበው ወንድማችሁ ነው ይህንን ያቀረበው። ተሳተፉ። በዚህ የፌስቡክ አድራሻ ተሳተፉ
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=938051771373055&id=100055047226745&mibextid=Nif5oz


@Fuadkheyr
@fuadkheyr
የንፁሆች ስህተት ሁሉም ሰው እንደነሱ ስለሚመስላቸው ነው። አንዳንዶች…  እንደሞኝነት ያዩታል። አላህ በልባቸው ውስጥ ያስቀመጠው ንፅህና መሆኑን ግን አያውቁም። በዚህ መንገድ ግን በተደጋጋሚ መነደፍ የሙእሚን ባህሪ አይደለም።
@fuadkheyr
@fuadkheyr
የዛሬ መቶ አመት ታሪክ ነን። ወይ በፊደሎች መሀል የምንዘከር… ወይም ምድር የዘነጋችን ታሪክ።

@fuadkheyr
@fuadkheyr
መራቅ ገዳይ  ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ክብር እንደሌለህ ከሚሰማህ ቦታ ከመቅረብ  እልፍ ግዜ ይሻላል።  ምክንያቱም መከባበር ከሌለ አንተም የለህም።
@fuadkheyr
@fuadkheyr
ቁጥር አይደሉም። ሁሉም የራሳቸው ህይወት፣ ህልሞችና ወዳጆች ነበሯቸው።

@fuadkheyr
@fuadkheyr
“እና ከሁሉም ውድቀት በኋላ…  እጣፈንታችን  ህልማችንን  እንደማይመስል እንረዳለን።”
ደርዊሽ

@fuadkheyr
@fuadkheyr
"አትርገሙት… እርሱኮ አላህና መልዕከተኛውን ያፈቅራል።" ረሱል
በየጊዜው መጠጥ እየጠጣ የሚገረፍ ሰሓባቸውን አስመልክቶ የተናገሩት ቃል ነበር… ታውቃለህ? ጊዜ ያዳልጣል ፣ ትናንትና ዛሬ አንድ ላትሆን ትችላለህ… ስሜትህ አሸንፎህ ኃጢያት ውስጥ ትዘፈቅ ይሆናል… ምናልባት ለመቁጠር የሚያዳግት ኃጢያት ውስጥ…  ግን የአላህና የመልዕክተኛው ፍቅር ከውስጥህ አይለይ… መውደድህን ቀጥል… አንድ እለት ፍቅር በተግባር ይገለጣል… ውዴታህ ስሜትህን ያሸንፋል…

@Fuadkheyr
@fuadkheyr
ውድድሩ ተጀምሮአል… ያነበባችሁትን በአሪፍ መልኩ አጋሩን።

መፅሃፍን  ለፌስቡክ ልጥፍ በሚመች አጭር  ይዘት ደግሞ የመፃፍ ውድድር ጀምረናል። ለመነሻ እንዲሆን ሰሞኑን ከታተመው የ ABX መፅሀፍ እንጀምራለን። "ሰባሐል ኸይር" እነሆ መፅሀፉን ሙሉ ለሙሉ ማንበብና መረዳት ግዴታ ነው። የመፅሃፉን ሀሳብ አሳጥሮ  የተሻለ የፃፈ ይሸለማል።

ሽልማቱ ምንድነው? 
1ኛ ለወጣ ሰው 3000 ብር
2ኛ ለወጣ 1500 ብር
3ኛ ለወጣ ደግሞ 1000 ብር
ከ4 እስከ 10 ደግሞ የተሻለ ለፃፉት ለጥሩ ተሳትፎ 200 ብር።
በተጨማሪም ለአስሩም ተሸላሚዎች "አልሂጃብ" የተሰኘ  የመፅሃፍ ሽልማት ይኖራቸዋል። የኡማው ከንባብ መራቅ ያሳሰበው ወንድማችሁ ነው ይህንን ያቀረበው።  ተሳተፉ።  በዚህ የፌስቡክ አድራሻ ተሳተፉ
https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=938051771373055&id=100055047226745&mibextid=Nif5oz


@Fuadkheyr
@fuadkheyr
አንዳንድ ሰዎች አይንህን ብትሰጣቸው "ከነቅንድቡ አልሰጠንም" ብለው ያወራሉ።  እነዚህ ምንም ብታደርግላቸው መልካም ጎንህን ለመመልከት የሚከብዳቸው ሰዎች ናቸው።

@Fuadkheyr
@fuadkheyr
እና ከሁሉ ነገር በኋላ… ዱዓ የሌለበት ዓለም ከንቱ እንደሆነ ይገባሃል። በመጨረሻ… ስኬትም ስክነትም እዚህ መተናነስ ውስጥ እንደነበረ ትረዳለህ። አልሏሁመ!!

@fuadkheyr
@fuadkheyr
ድንገት አልነበረም። የቀደር መስመር ላይ ነው የተገናኛችሁት። በህይወትህ ላይ የሆኑ ትምህርቶችን ሰጥተውህ ያለፉት ሁሉ(ምናልባትም ክፉዎች)፣ ከዋክብቶች ሲሸሹህ ሰማይህን ሊያበሩልህ የመጡት ምርጥ ሰዎችህ ሁሉ… ለነርሱ የተወሰነላቸው የህይወት ዓለም ከተወሰነልህ የህይወት ዓለም ጋር እንዲነካካ ተፅፏል። ሌላ አይደለም።

@fuadkheyr
@fuadkheyr
“ጌታዬ ሆይ! ባምፅህም እወድሃለሁ።”
ታላቁ ሰሓባ ዐምር ቢን ዓስ

@fuadkheyr
@fuadkheyr
"አንዲት ሴት ለቤተሰቦቿ ምግብ ማዘጋጀቷ  ፆመኞችን የማስፈጠር አጅር ውስጥ ይካተታል።"
ሸይኽ ኻሊድ መስለህ
@fuadkheyr
@fuadkheyr
ሰዎችም እድል ናቸው። በሆነ አጋጣሚ የምናገኛቸው ወይንም የምናጣቸው። ሁል ጊዜ በነበረበት የምናገኘው አይኖርም። ምናልባት ዛሬ ለኛ የተገባ ሰው… ነገ ላይሆን ይችላል።

@fuadkheyr
@fuadkheyr
በዙሪያህ ያለውን ሁሉንም ነገር ለመረዳት አትሞክር። አንዳንድ ጉዳዮችን አለመረዳት ነው የሚሻለው። አንዳንዴ ነገሩን በመረዳትህ የሚመጣብህ የልቦና ቀውስና አንደበትህ ላይ የሰዎች ስም መመላለስ ብቻ ነው። …  በቃ ምናገባኝ ማለት አስፈላጊ ነው። በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ!

@fuadkheyr
@fuadkheyr
አቡበከር የቢላልን ያህል ድብደባ አላስተናገደም።  ድህነትም እንደአቡዘር አልፈተነችውም። ሰይፎች የኻሊድን ያህል ታዘውት በካሃዲያን አንገት ላይ አላሳረፈም። ግን  ከሁሉም የሚበልጥ ሰሓባ ነበር። ለነብዩ ልቡን ሰጥቷል። እንዳሻዎት ያድርጉኝ ብሏል። የልብ ሰው!!

@fuadkheyr
@fuadkheyr
ውስብስብ ጉዳዮቹን ለአላህ አደራ የሰጠ ሰው አይከስርም፣ አይፀፀትም።

@fuadkheyr
@fuadkheyr
ግብፃዊው ፀሓፊና ፈላስፋ አኒስ መንሱር “የሰዎችን ውስጣዊ ዓለም እንዴት ነው ማወቅ የምንችለው?" የሚል ጥያቄ ተጠይቆ ነበር። እንዲህ ሲል መለሰ፦
“ባል ሚስቱ በታመመች ጊዜ ይታወቃል። ሚስት ደግሞ ባሏ በደኸየ ጊዜ ትታወቃለች። በመከራ(ችግር) ወቅት የእውነት ጓደኛ ይበጠራል። ልጆች ወላጆቻቸው ሲሸመግሉ ይታወቃሉ። ወንድምና እህቶች የውርስ ጊዜ ይታወቃሉ። ዘመድአዝማድ በብቸኝነት ውስጥ እንግዳ ሆነህ ሲያገኙህ ታውቃቸዋለህ። የእውነት ፍቅር ደግሞ ጥቅም ሲያበቃ ይታወቃል። አማኝ በፈተና ወቅት ይለያል።”

@fuadkheyr
@fuadkheyr
በጣም መንገብገብ፣ በጣም ክፍት መሆን፣ በጣም ራስን መስጠት ብዙ ጊዜ በጣም ያዋርዳል። ሁለተኛ ሰው ወይም አማራጭ የሚታይበት ሰው ያስደርጋል። ሁሉንም ነገር ሰጥቶ አንድ ነገር እንዲሰጡት የሚለምን አይነት ሰው ያስደርጋል። ሰዎች ያልተዘጋጁበትና ያላሰቡት ዓይነት ቦታ ስትመጣላቸው ይኮራሉ። በእጅ ያለወርቅ እንደመዳብ የሚሉትን ዓይነት እንዲሆኑ እናደርጋቸዋለን… በራሳችን እጅ። አንዳንዴ "አይመቸኝም" ያስፈልጋል። አንዳንዴ "ፈልገው ይደውሉ" ብሎ መተውም ያስፈልጋል። … ሲመስለኝ።

@fuadkheyr
@fuadkheyr
2024/05/27 14:22:18
Back to Top
HTML Embed Code: