Telegram Group Search
ደብረ ምጥማቅ

ግብጽ በምትገኘው በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስም በተሠራችው ደብረ ምጥማቅ ቤተ ክርስቲያን ጉልላት ላይ ድንግል ማርያም ከግንቦት ፳፩ ጀምሮ እስከ ፳፭ ቀናት በተከታታይ በመገለጧ ሕዝበ ክርስቲያን በዓሏን ያከብራሉ፡፡

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ወደ ምድረ ግብጽና ኢትዮጵያ በተሰደደች ጊዜ በአሁኑ ጊዜ ደብረ ምጥማቅ ተብሎ በሚጠራው ቦታ ላይ ዐርፈው ነበር:: ጌታችንም ቦታውን ባርኮ የእርሷ መገለጫ እንዲሆን ቃል ኪዳን ገብቶላት ስለነበር ጊዜው በደረሰ ሰዓት ደብረ ምጥማቅ ተገድሞ የበርካታ መነኮሳት በዓት ሆነ:: በደብረ ምጥማቅም እመቤታችንም ቅድስት ድንግል ማርያም ብርሃን ተጎናጽፋና በሠራዊት መላእክት ታጅባ ተገልጣለች፤ በዚያን ጊዜም ሱራፌል ማዕጠንታቸውን ይዘው ሰገዱላት፤ እንዲህ እያሉም አመሰገኗት፤ ‹‹አብ በሰማይ አይቶ እንዳንቺ ያለ አላገኘም፤ ባንቺም ሰው ሆነ፡፡›› (መጽሐፈ ስንክሳር ግንቦት ፳፩ ገጽ. ፫፻፲፰)

ሰማዕታትም እንደየክብራቸው ማዕረግ ለእመቤታችን ድንግል ማርያም ሊሰግዱ ረቂቃን በሆኑ ፈረሶቻቸው ተቀምጠው ወደ እርሷ ቀረቡ፤ በመጀመሪያ ሊቀ ሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ ከሁሉም ቀድሞ ከሰገደላት በኋላ ሌሎቹም በተመሳሳይ መልኩ ሰገዱላት፡፡ ከዚህም በኋላ ቅዱስ መርቆሬዮስ በዱሪ ፈረስ ተቀምጦ ወደ እርሷ በመምጣት ሰገደላት፡፡ ጻድቃን በአንድነት ቀርበው ለክብሯ ሰገዱላት፤ ቀጥሎም በንጉሥ ሄሮድስ በግፍ የተገደሉት ሕፃናት ለእርሷ ሰገዱ፤ በደስታና በፍቅርም ተጫወቱ፡፡ በዚያ የተሰበሰቡትም ክርስቲያኖች፣ እስላሞችና አረማውያን ይህን በአዩ ጊዜ ደስታ ሞልቶባቸው በተለየ ዓለም ያሉ ይመስላቸው ነበር፡፡ (መጽሐፈ ስንክሳር ግንቦት ፳፩ ገጽ. ፫፻፲፰)

አባ ጽጌ ድንግልም በደብረ ምጥማቅ በታላቅ ክብር ለምእመናን የታየችው የአምላክ እናት የድንግል ማርያምን መገለጥ በማኅሌተ ጽጌ ድርሰቱ እንዲህ በማለት ገልጾታል፤ ‹‹አመ ትበርቂ በደብረ ምጥማቅ ኀምሰ ዕለታተ፣ ትእምርተ ገጽኪ ይርአይ እስከ ይትነሣእ ዘሞተ፣ሚ መጠነ ማርያም ታሥተፌሥሒ ትፍሥሕተ፣ ኅድጊሰ ጽጌ ፍቅርኪ በጊዜ ንቃሁ መዓልተ፣ ብፁዕ ዘርእየኪ በሕልሙ ሌሊተ፤ የፊትሽን መልክ ያይ ዘንድ የሞተ ሰው እስኪነሣ ድረስ በደብረ ምጥማቅ ለአምስት ቀናት ያህል በተገለጽሽ ጊዜ ማርያም ምን ያህል ደስ ታሰኚ ኖሯል! በቀን የታየው የፍቅርሽ አበባ ይቅርና ሌሊት በሕልሙ ያየሽ ምስጉን ነው፡፡›› (ማኅሌተ ጽጌ)

በደብረ ምጥማቅ ከተሰበሰቡት ሕዝብ መካከል እናትና አባታቸው፣ ዘመዶቻቸው እንዲሁም ባልንጀሮቻቸው የሞቱባቸው ሰዎች ቅድስት ድንግል ማርያም እንድታሳያቸው በለመኗት ጊዜ እንደ ቀደመ መልካቸው አድርጋ ታሳያቸው ነበር፡፡ አንዳንዶች ደግሞ መሀረባቸውን ወደ ላይ በሚወረውሩት ጊዜ እርሷ የወደደቻቸው እንደሆነ በእጅዋ ተቀብላ መልሳ ትጥልላቸዋለች፤ ሁሉም ለበረከት ይካፈሉታል፡፡ እነርሱም ወደ ቤታቸውም ለመሄድ በሚፈልጉ ሰዓት ተሰናብተውና በተባርከውም ይሄዳሉ፡፡ (መጽሐፈ ስንክሳር ግንቦት ፳፩ ገጽ. ፫፻፲፱)

የደብረ ምጥማቅና የአካባቢዋ ሰዎች እመቤታችን ድንግል ማርያምን ያዩባቸው ቀናት አረማውያኑ ያመኑበት፣ የበደሉት በምልጃዋ ቸርነትን ምሕረትን ያገኙበት፣ ያመኑት ደግሞ የተባረኩበት ዕለታት ነበሩ፡፡ ሕዝቡ እርሷን ተመኝተው ያጡት ወይንም ጠይቀው ያልተፈጸመላቸው ምንም ነገር አልነበረም:: ነቢያት፣ ሐዋርያት፣ ጻድቃን፣ ሰማዕታት፣ ደናግል፣ መነኮሳት መላእክትና ሊቃነ መላእክትም ለድንግል ማርያም ሲሰግዱ ይታዩ ነበር::

ነቢዩ ዳዊት ‹‹ወለገጽኪ ይትመሐለሉ ኲሎሙ አሕዛብ ብዑላነ ምድር፤ የምድር ባለጠጎች አሕዛብ ሁሉ በፊትሽ ይማለላሉ›› በማለት ትንቢትን እንደተናገረላት በርካት ቅዱሳን ሰዎች ቅድስት ድንግል ማርያምን ተገልጻላቸው ለማየት ተመኝተዋል፤ ልመናቸው ተሰምቶላቸው የአምላክ እናት ተገልጻላቸው ፊቷን ለማየትን ክብሯን  ለመግለጥ ቅዱሳን አባቶች፣ ጻድቃን ሰማዕታት በቅተዋል፡፡ ይህም የሆነው በፍጹም ልቡናቸው በመማፀናቸውና በፍጹም ትጋት የጌታቸውን እናት ሲያገለግሉ በመኖራቸው እንደሆነ የጻድቃኑ ገድል ምስክር ነው፡፡ እነርሱም ሌት ከቀን ምኞታቸው ይሳካላቸው ዘንድ በጸሎት ይማፀኑ ነበር፡፡ (መዝ. ፵፬፥፲፪)

እመቤታችን ድንግል ማርያምም ጸሎታቸውን ሰምታ ያሰቡትን ትፈጽምላቸው ነበር፤ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በደብረ ምጥማቅ ተገልጣ የሕዝቡን ምኞት እንደፈጸመችላቸው የእኛንም በጎ መሻት ትፈጽምልን፤ አሜን፡፡

ምንጭ:-ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል

https://www.tg-me.com/መዝሙር ዘዳዊት/com.mezmur_Zedawitt
“እመቤታችን በሁሉም እርምጃዎቿ  የተከበረች ነበረች እጅግ ትሁት ፤ የምትናገረው በጣም ጥቂት ሲሆን እሱም ለማድረግ አስፈላጊ በሚሆንበት ብቻ ነበር፤ በጣም ዝግጁ ሆና የምትሰማና በቀላሉ ንግግር ለማድረግ የምትችል ናት፤ ለእያንዳንዱ ሰው አክብሮትና ክብር (ሰላምታ) ትሰጣለች፤ ቁመቷ መኻከለኛ ነው፤ አንዳንዶች ግን ቁመቷ ከፍ ያለ እንደነበር ይናገራሉ፤ ከእያንዳንዱ ሰው ጋር ያለምንም ፍርሀት በግልጽነት ያለምንም ሳቅና መጯጯኽ ትናገራለች፤ በተለይ ፈጽማ ለቁጣ የምትጋበዝ አልነበረችም፤ መልኳ እንደ ደረሰ የስንዴ አዝመራ ያማረ ጸጒሯ ቀይማ ነው፤ ዐይኖቿ ብሩሃትና የዋህ የሆኑ ቀለማቸውም ፈዘዝ ያለ ቡናማ ሆኖ የዐይኖቿ ብሌኖች የዘይት-አረንጓዴ ይመስላል፤ የዐይኖቿ ቅንድብ (ሽፋሽፍት) ከፊል ክብና ደማቅ ጥቁር ናቸው፡፡ አፍንጫዋም ረዥም፣ ከናፍሮቿ ቀይና ምሉእ ሲሆኑ በቃሎቿ ጣፋጭነት የተመላባቸው ነበሩ፤ ፊቷ ክብ እንቁላልማ ዐይነት ቅርጽ ነበረው፡፡ እጆቿ ረዥምና ጣቶቿም በጣም ረዣዥም ነበሩ፤ ከማንኛውም ያልተገባ ኩራት ሙሉ በሙሉ የነጻች ስትሆን ግድ የለሽነት ፈጽሞ አልነበረባትም፤ የሚመጡትን ነገራት በፍጹም ትሕትና ትቀበል ነበር፤ ተፈጥሯዊ ቀለማት ያላቸው፤ ማለትም በቤት ድር የተሠሩ ልብሶችን ትለብስ ነበር፤ ይህም በእጅጉ አብሯት የሚሄደው አለባበስና ይህ እውነታ በራሷ ላይ በምታደርገው ቅዱስ ልብስ አሁን ቅሉ ሊረጋገጥ የሚችል እውነታ ነው፤ በመንገዶቿ ሁሉ በመለኮታዊ ጸጋ የተመላች ነበረች፤” ሲል ስለ ድንግል ማርያም ገልጿል፡፡

የቆጵሮሱ ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ
ግንቦት ፳፩
ደብረ ምጥማቅ


ከሠላሳ ሶስቱ የእመቤታችን በዓላት አንዱ ነው። ደብረ ምጥማቅ በግብፅ ሀገር በምኔተ ገምኑዲ አቅራቢያ የምትገኝ ቦታ ናት። እመቤታችን በስደት ሳለች ጌታ በዚህ ቦታ በስምሽ ዐብይ ቤተ ክርስቲያን ይታነጻል፤ ስሙንም ደብረ ምጥማቅ ይሉታል ብሎ ነግሯት ነበር። ይኸውም አልቀረ፤ በዚሁ ቦታ በእመቤታችን ስም ቤተክርስቲያን ታንጾ ስሙ ደብረ ምጥማቅ ተብሏል።

በዚህም ዕለት እመቤታችን ከፀሐይ ሰባት እጅ አብርታ ከጉልላቱ ላይ በመንበረ ብርሃን ተቀምጣ መላእክት ሊቃነ መላእክት ከበው ሲያመሰግኗት ነቢያት ሐዋርያት ጻድቃን ሰማዕታት እጅ ሲነሷት ታይታለች። “እንዘ ትበርቂ በደብረ ምጥማቅ ኃምሰ ዕለታተ” እንዳለ ደራሲ በልጇ የመለኮት ብርሃን አሸብርቃ መላእክት: ሊቃነ መላእክት: ኪሩቤል: ሱራፌል ከበዋት ነቢያት: ሐዋርያት: ሰማዕታት: ደናግላን: መነኮሳት ሄሮድስ ያስፈጃቸው ሕፃናት ይመጣሉ። ሱራፌል ማዕጠንት ይዘው በእያንዳንዱ እያመሰገኑ ያጥኑ ነበር። ከሰማዕታት ቅዱስ ጊዮርጊስ በነጭ ፈረስ ተከትሎ ቅዱስ መርቆርዮስ በጥቁር ፈረስ በየተራ እየመጡ ይሰግዱላታል።

ከፊቷ ብርሃን የተነሣ 5 ቀን ሌሊቱና ቀኑ አይታወቅም ነበር። በዚህ ጊዜ ልብሳቸውን ወደ ላይ ሲወረውሩላት የፈቀደችውን ተቀብላ ትልክላቸዋለች። ከዚያም ለበረከት ይካፈሉታል። ከተሰበሰቡትም እስኪ እገሌን አስነሺልን እያሉ ሲለምኗት አስነሥታ በሕይወተ ሥጋ ታሳያቸው ነበር። እንዲህ እየሆኑ በፍጹም ደስታ ሰንብተዋል። እስከ አምስት ቀንም ምዕመናኑን አረማውያኑንም አንድ ወገን አድርጋ ስትባርክ ሰንብታለች። ከዚህም በኋላ ምዕመናኑም አረማውያኑም በየዓመቱ እኚህን አምስት ዕለታት በደብረ ምጥማቅ ተሰብስበው የሚያከብሩ ሆነዋል። የበዓሉ መታሰቢያ ከግንቦት 21 እስከ 25 ቀን ነው።

ግንቦት 21 በደብረ ምጥማቅ በገሃድ ተገልጻ ታላቅ ተአምር ያደረገችበት፡፡

ግንቦት 22 በደብረ ምጥማቅ ለተሰበሰቡ ምእመናን በግልጽ በመታየት ትነጋገራቸው ነበር፡፡

ግንቦት 23 በደብረ ምጥማቅ ለተሰበሰቡ ምእመናን በግልጽ በመታየት ትነጋገራቸው ነበር፡፡

ግንቦት 24 እመቤታችን ተወዳጅ ልጇን ይዛ ከአረጋዊ ዮሴፍና ሰሎሜ ጋር በመሰደድ ግብፅ አገር የገባችበት ዕለት፡፡

ግንቦት 25 ተወዳጅ ልጇ የደረቁ በትሮችን ተክሎ በተአምራት ያለመለመበት ዕለት፡፡

በዚህ ዕለትም እናታችን፣ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በደብረ ምጥማቅ ለ5 ቀን በግልጽ መታየቷ የሞቱት መነሳታቸው ብርሃን መሆኑ ጨለማ መጥፋቱ የሰውን ልመና መቀበሏ ወዘተ ይነገራል። የቅድስት እናታችን ረድኤት በረከቷ አማላጅነቷ አይለየን፣ ጣዕሟን ፍቅሯን አይለይብን። የዓመት ሰው ይበለን፣ አሜን!
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
“ድንግል ሆይ በሁሉ አንደበት መመስገን የተገባሽ ስለሆነ በሰማይ ካሉ መላእክትና በምድር ከሚኖሩ ደቂቀ አዳም ሁል ጊዜ ምስጋና ይቀርብልሻል።” ቅዳሴ ማርያም

“ሰላም ለእለ ርእዩኪ ከመ ዐይነ ወለት ኀበ እማ፣
መዋዕል ኃምስ እስከ ይትፌጸማ፣
ማርያም ንግስት ዘደብረ ምጥማቅ ከተማ፣
ብፁዓት አዕይንት ዘነጸራኪ በግርማ፣
ወብፁዓት አእጋር ቅድሜኪ ዘቆማ።” እን ዐርኬ
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
ምንጭ፡ መዝገበ ታሪክ 2 ገጽ 87፣ መድብለ ታሪክ ገጽ 383

https://www.tg-me.com/መዝሙር ዘዳዊት/com.mezmur_Zedawitt
††† እንኩዋን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የስደት
በዓል በሰላም አደረሳችሁ †††

=>የአርያም ንግሥት: የፍጥረታት ሁሉ እመቤት ድንግል ማርያም የባሕርይ
አምላክ ልጇን አዝላ በዚህች ቀን ወደ ምድረ ግብፅ ወርዳለች::

+በወንጌል ላይ (ማቴ. 2:1-18) እንደተጻፈው ጌታችን በተወለደ በ2 ዓመቱ
የጥበብ ሰዎች (ሰብአ ሰገል) ወደ ቤተ ልሔም መጥተው ሰግደውለት: ወርቅ
እጣን ከርቤውን ገበሩ: አገቡለት::

+ንጉሥ ተወልዷል መባሉን የሰማ ሔሮድስ 144,000 ሕጻናትን ሲፈጅ በቅዱስ
ገብርኤል ትዕዛዝ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም 1 አምላክ ልጇን
አዝላ: በአንዲት አህያ ጥቂት ስንቅ ቁዋጥራ: ከዮሴፍና ከሰሎሜ ጋር ስደት
ወጣች::

+ከገሊላ ተነስታ በጭንቅ በመከራ: በረሃብና በጥም: በሐዘንና በድካም:
በላበትና በእንባ ተጉዛ በዚሕች ቀን ምድረ ግብፅ ገብታለች::

+የአምላክ እናቱ
*እሳትን አዝላ በብርድ ተንገላታለች::
*ለእኛ የሕይወት እንጀራን ተሸክማ እርሷ ተራበች::
*የሕይወትን ውሃ ተሸክማ ተጠማች::
*የሕይወት ልብስን ተሸክማ ተራቆተች::
*የሕይወት ፍስሐን ተሸክማ አዘነች::
*እመ አምላክ ተራበች: ተጠማች: ታረዘች: ደከመች: አዘነች: አለቀሰች:
እግሯ ደማ: ተንገላታች::

+ለሚገባው ይሕ ሁሉ የተደረገው ለእኛ ድኅነት ነው:: በእውነት ይህንን
እያወቀ ለድንግል ማርያም ክብር የማይሰጥ ሰይጣን ብቻ ነው:: አራዊት:
ዕፀዋትና ድንጋዮች እንኩዋ ለአመላክ እናት ክብር ይሰጣሉ::

+አረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍና ቅዱስ ሰሎሜ ደግሞ የክብር ክብር ይገባቸዋል::
ከአምላክ እናት ከድንግል ማርያምና ከቸር ልጇ ጋር መከራ መቀበልን
መርጠዋልና::

=>መድኃኔ ዓለም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለምን ተሰደደ?
ለምንስ ስደቱን ወደ ግብፅና ኢትዮዽያ አደረገ?

1.ትንቢቱን ይፈጽም ዘንድ:: በፈጣን ደመና ወደ ግብፅ እንደሚወርድ
ተነግሯልና (ኢሳ. 19:1, ዕን. 3:7)

2.ምሳሌውን ለመፈጸም:: የሥጋ አባቶቹ እነ አብርሃም: ያዕቆብ (እሥራኤል):
ኤርምያስ ወደዚያው ተሰደዋልና::

3.ከግብፅ ጣዖት አምልኮን ያጠፋ ዘንድ:: (ኢሳ. 19:1)

4.የግብፅና የኢትዮዽያ ገዳማትን ይቀድስ ዘንድ::

5.ሰው መሆኑ በአማን እንጂ ምትሐት እንዳልሆነ ለማጠየቅ:: ሰው ባይሆን
ኑሮ አይሰደድም ነበርና:: ሔሮድስ ቢያገኘው ደግሞ ሊገድለው አይችልም::
ያለ ፈቃዱና ያለ ዕለተ ዐርብ ደሙ አይፈስምና::

6.ስደትን ለሰማዕታት ባርኮ ለመስጠት:: እና

7.የአዳምን ስደት በስደቱ ለመካስ ነው::

=>ቸሩ መድኃኔ ዓለም የድንግል እናቱን ስደት አስቦ ከመንግስተ ሰማያት ስደት
ይሠውረን:: ከስደቱ በረከትም ያድለን::

=>ግንቦት 24 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ዕንባቆም ነቢይ
2.ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊና ቅድስት ሰሎሜ
3.ቅዱስ አብቁልታ ሰማዕት
4.ቅዱስ አልዓዛር ካህን (የአሮን ልጅ)

=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖት
2.ቅዱስ አጋቢጦስ (ጻድቅ ኤዺስቆዾስ)
3.ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
4.ቅዱስ ሙሴ ፀሊም
5.ቅዱስ ቶማስ ዘመርዐስ
6.ቅዱስ አብላርዮስ ታላቁ
7."24ቱ" ካኅናተ ሰማይ (ሱራፌል)
8.አቡነ ዘዮሐንስ ጻድቅ (ኢትዮዽያዊ)

=>+"+ ዘንዶውም ሴቲቱ በወለደች ጊዜ ሕጻኑዋን እንዲበላ ልትወልድ ባላት
ሴት ፊት ቆመ:: አሕዛብንም ሁሉ በብረት ዘንግ ይገዛቸው ዘንድ ያለውን ልጅ:
ወንድ ልጅ ወለደች:: ልጇም ወደ እግዚአብሔርና ወደ ዙፋኑ ተነጠቀ::
ሴቲቱም ሺህ ከሁለት መቶ ስድሳ ቀን በዚያ እንዲመግቧት በእግዚአብሔር
ተዘጋጅቶላት ወደ ነበረው ሥፍራ ወደ በረሃ ሸሸች:: +"+ (ራዕይ. 12:4-7)
https://www.tg-me.com/መዝሙር ዘዳዊት/com.mezmur_Zedawitt
ታላቁ ቅዱስ ባስልዮስ❤️  እንዲህ ያስተምረናል።

👉ማር ያልቀመሰውን የማርን ጣፋጭነት በቃላት መግለጽ እንደማይቻል

👉 እኛም ራሳችን ወደ ጌታ ቸርነት በኛ ቸርነት ዘልቆ መግባት ካልቻልን

👉 የእግዚአብሄርን ቸርነት በማስተማር መንገድ በግልፅ መግለጽ አይቻልም። የራሱን ልምድ.

ቅዱስ ሰሎዋን ዘ አቶናዊ ❤️ ደግሞ  እንዲህ ያስተምረናል።

👉ብዙ ባለጠጎች እና ኃያላን ሰዎች ጌታን ወይም እጅግ ንፁህ እናቱን ለማየት ብዙ ዋጋ ይከፍላሉ፣

👉 ነገር ግን እግዚአብሔር በሀብት አይገለጥም፣

👉ነገር ግን በትሑት ልብ... እያንዳንዱ ድሀ ሰው ትሑት መሆን እና እግዚአብሔርን ማወቅ ይችላል።

👉 እግዚአብሔርን ለማወቅ ገንዘብም ሆነ ስም አያስፈልገውም ነገር ግን ትህትና ብቻ ነው።

👉 የቱንም ያህል ብንማር እንደ ትእዛዙ እስካልኖርን ድረስ እግዚአብሔርን ማወቅ አይቻልም፤

👉 እግዚአብሔርን በመንፈስ ቅዱስ እንጂ በሳይንስ አያውቅም።

👉 ብዙ ፈላስፎች እና የተማሩ ሰዎች አምላክ መኖሩን ወደ ማመን መጡ, ነገር ግን እግዚአብሔርን አያውቁም ነበር.

👉እግዚአብሔር እንዳለ ማመን እና እሱን ማወቅ ሌላ ነገር ነው።

👉 አንድ ሰው እግዚአብሔርን በመንፈስ ቅዱስ ካወቀ፣ ነፍሱ ቀንና ሌሊት ለእግዚአብሔር ባለው ፍቅር ትቃጠላለች፣

👉ነፍሱም ከማንኛውም ምድራዊ ነገር ጋር ልትታሰር አትችልም።

ፈጣሪ እግዚአብሔር ❤️ከሁላችን ጋር ይሁን!!!
https://www.tg-me.com/መዝሙር ዘዳዊት/com.mezmur_Zedawitt
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን ፡፡ ✞✞✞

እንኳን አደረሳችሁ

❖ ሰኔ 1 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት

+"+ ቅዱስ_ዮሴፍ_ጻድቅ +"+

=>ቤተ_ክርስቲያን በዚህ ስም ብዙ ቅዱሳን አሏት:: በተለይ ደግሞ እስራኤል
የተባለ የቅዱስ_ያዕቆብ ልጅ ቅዱስ ዮሴፍ ከሁሉም ቅድሚያውን ይይዛል::
ታላቁ ቅዱስ_መጽሐፍ ላይ በስፋት ታሪካቸው ከተጻፈላቸው ቅዱሳን አንዱ ነው::

+ስለዚህ ቅዱስ ዝርዝር መረጃን
ለማግኘት ኦሪት_ዘፍጥረትን
ከምዕራፍ 39 እስከ 50 ድረስ ማንበብ ይኖርብናል:: ከዚህ በተረፈም በዜና ቤተ ክርስቲያን ስለ ቅዱሱ ብዙ ተብሏል::

+መጽሐፍ ቅዱስ ሲጀምር ስለ ቅዱስ ሰው አዳም ይነግረናል:: ቀጥሎም ስለ ቅዱሳኑ
ሴት
ሔኖክ
ኖኅ
ሴም
አብርሃም
ይስሐቅና
ያዕቆብ
ነግሮን ቅዱስ_ዮሴፍ ላይ ይደርሳል::

+ቅዱስ ዮሴፍ ያዕቆብ (እስራኤል) ከሚወዳት ሚስቱ ራሔል ከወለዳቸው 2 የስስት ልጆቹ አንዱ ነው:: ቅዱሱ ምንም
እናቱ ብትሞተበትም በአባቱና በፈጣሪው ፊት ሞገስ ነበረው::
ምክንያቱም ቅን: ታዛዥና የፍቅር ሰው ነበርና::
+እንዲያ አምርረው ለሚጠሉት ወንድሞቹ እንኳን ክፋትን አያስብም ነበር:: ይልቁኑ ለእነሱ ምሳ (ስንቅ) ይዞ
ሊፈልጋቸው በበርሃ ይንከራተት ነበር እንጂ::
+መንገድ ላይ ቢርበው አለቀሰ እንጂ ስንቃቸውን አልበላባቸውም:: የአባቶቹ አምላክ ግን ድንጋዩን ዳቦ አድርጐ
መግቦታል:: 10ሩ ወንድሞቹ ግን ስለ በጐነቱ ፈንታ ሊገድሉት ተማከሩ:: ከፈጣሪው አግኝቶ በነገራቸው ሕልም
"ሊነግሥብን ነው" ብለው ቀንተውበታልና::
+በፍጻሜው ግን በይሁዳ መካሪነት ለዐረብ ነጋድያን ሸጠውታል:: በዚህም ለምስጢረ ሥጋዌ (ለጌታ መሸጥና
ሕማማት) ምሳሌ ለመሆን በቅቷል:: ወንድሞቹ ለክፋት ቢሸጡትም ቅሉ
ውስጡ ፈቃደ እግዚአብሔር ነበረበትና በባርነት በተሸጠበት በዺጥፋራ
ቤት ፈጣሪው ሞገስ ሆነው::
+ወጣትነቱን በፍቅረ እግዚአብሔር ሸብ አድርጐ አስሮ ነበርና የዺጥፋራ ሚስት የዝሙት ጥያቄ አላንበረከከውም:: "ማንም አያየንም" ስትለውም "እፎ እገብር ኃጢአተ በቅድመ እግዚአብሔር" (ማንም ባያይስ እንዴት በፈጣሪየ ፊት ኃጢአትን አሠራለሁ?) በማለት ከበደል አምልጧል:: ስለዚህ
ፈንታም የእሥር ቅጣት አግኝቶታል::
+ጌታ ከእርሱ ጋር ቢሆን በእሥር ቤትም ሞገስን አገኘና አለቅነትን ተሾመ:: "ኢኀደረ ዮሴፍ ዘእንበለ ሲመት" እንዲል
መጽሐፍ:: ከዚያም የንጉሡን (የፈርዖንን) ባለሟሎች ሕልም ተረጐመ:: ቀጥሎም ንጉሡን በሕልም ትርጓሜ አስደመመ::
ፈርዖንም ቅዱሱን በግዛቱ (ግብጽ) ላይ ሾመው::
+ቅዱስ ዮሴፍ በምድረ ግብጽ ነግሦ ሕዝቡን ከረሃብ ታደገ:: ለቅዱስ አባቱ ለእሥራኤልና ክፉ ለዋሉበት ወንድሞቹም መጋቢ ሆናቸው:: አስኔት (አሰኔት) የምትባል ሴት አግብቶም
ኤፍሬምና ምናሴ የተባሉ ልጆችን አፍርቷል:: +በመንገዱ ሁሉ እግዚአብሔርን አስደስቶ: ከአባቱ
ዘንድም ምርቃትና በረከትን ተቀብሎ በ110 ዓመቱ በዚህች ቀን በመልካም
ሽምግልና ዐርፏል:: ወገኖቹም በክብርና በእንባ ቀብረውታል:: "አጽሜን አፍልሱ" ብሎ በተናገረው ትንቢት መሠረትም ልጆቹ (እነ ቅዱስ ሙሴ) ከግብጽ ባርነት ሲወጡ አጽሙን ወደ ከነዓን አፍልሠዋል::

+" ቅዱስ ለውንትዮስ ሰማዕት "+

=>ቅዱሱ የተወለደው በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን አካባቢ ሲሆን ሃገሩ ጠራብሎስ ትባላለች:: በወቅቱ በወታደርነት
ነገሥታቱን ያገለግል ነበር:: ድንግል: ደም ግባት የሞላለት ወጣት ስለ ነበር በሰዎች ፊት ሞገስ ነበረው::

+እርሱ ግን ምን ወታደር ቢሆን ጾምና ጸሎትን ያዘወትር ነበር:: በተለይ ደግሞ የዳዊትን መዝሙር እየመላለሰ ይጸልየው:
ይወደው ነበር:: ንግግሩ ሁሉ በመንፈስ ቅዱስ ጨውነት የታሸ ነውና ብዙ ጉዋደኞቹን ከክህደት ወደ ሃይማኖት:
ከክፋት ወደ ደግነት መልሷል::

+የመከራ ዘመን በደረሰ ጊዜም በገሃድ ስመ ክርስቶስን ይሰብክ ነበር:: ክፉ ሰዎች ከሰውት በመኮንኑ ፊት በቀረበ
ጊዜም አልፈራም:: ወታደሮቹ መሬት ላይ ጥለው እየደበደቡት:ደሙ እንደ ጐርፍ እየተቀዳ እርሱ ግን ይዘምር ነበር::

+በመጨረሻም ስለ ክርስቶስ ፍቅር አንገቱን ተሰይፏል::ቅዱስ ለውንትዮስ እጅግ ተአምረኛ ሰማዕት ነውና
በእምነት እንጥራው:: ቤተ ክርስቲያንም ዛሬ የቅዱሱን ተአምራት ታስባለች:: ቅዳሴ ቤቱም የተከበረው በዚሁ ዕለት ነው::

=>አምላከ ቅዱሳን ወርኀ ሰኔን የፍሬ: የበረከት: የንስሃና የጽድቅ አድርጐ ይስጠን:: ከሰማዕቱ ጽናትን: ጸጋ በረከትን
ይክፈለን::

=>ሰኔ 1 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ዮሴፍ ጻድቅ (የያዕቆብ ልጅ)
2.እናታችን አስኔት (የቅ/ ዮሴፍ ሚስት)
3.ቅዱስ ለውንትዮስ ክቡር ሰማዕት
4.ቅዱስ ቢፋሞን ሰማዕት
5.ቅዱስ ቆዝሞስ ሰማዕት

❖ወርኃዊ በዓላት
1፡ ልደታ ለማርያም
2፡ ቅዱስ በርተሎሜዎስ ሐዋርያ
3፡ ቅዱስ ሚልኪ ቁልዝማዊ
4፡ ቅዱስ ራጉኤል ሊቀ መላእክት
5፡ ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና

=>+"+ እንዲህም አላቸው:- "ወደ ግብጽ የሸጣችሁኝ እኔ ወንድማችሁ ዮሴፍ ነኝ:: አሁንም ወደዚህ ስለ ሸጣችሁኝ አትዘኑ:: አትቆርቆሩም:: እግዚአብሔር ሕይወትን ለማዳን ከእናንተ በፊት ሰዶኛልና . . . እግዚአብሔርም በምድር ላይ ቅሬታን አስቀርላችሁ ዘንድ: በታላቅ መድኃኒትም አድናችሁ ዘንድ ከእናንተ በፊት ላከኝ::" +"+ (ዘፍ.
45:4-8)

<<< ወስብሐት ለእግዚአብሔር >>>
https://www.tg-me.com/መዝሙር ዘዳዊት/com.mezmur_Zedawitt
#ብቻዬን_ተውከኝ

ከእለታት በአንድ ቀን እንዲህ ሆነ። አንድ ሰው በቤቱ ቁጭ ብሎ ያሳለፈውን ጊዜ ያስተውላል። በደስታው ጊዜ፣ በመሳቂያው ጊዜ፣ በእልልታው ሰዓት፣ ሁሉ በተመቻቸለት ጊዜ ዱካው አራት ሆኖ ያያል። በጣም ይገረማል በዚህ ሁሉ ጊዜ እግዚአብሔር አብሮኝ ነበር በማለት እግዚአብሔርን አመሰገነ። ሁለቱ ዱካ(ኮቴ) የራሱ እንደሆነ ሌሎች ሁለቱ ደግሞ የሚጠብቀው የእግዚአብሔር እንደሆነ ገብቶት እግዚአብሔር ሁሌ አብሮት ስላለ በመደነቅ እጅጉን አመሰገነው።

የችግሩ ጊዜ፣ የሀዘኑ ሰዓት፣ የህመሙ ጊዜ፣ የስቃዩ ጊዜ፣ የሰቆቃው ሰሞን፣ የለቆሱውን ዘመን፣ ሲመከት ግን ኮቴው ሁለት ብቻ ሆነ። በዚህ ምክንያት ወደ እግዚአብሔር ፊት ቀርቦ እንዲህ አለው። እግዚአብሔር ሆይ አንተ በደስታዬ እና በድሎቴ ጊዜ አብረኸኝ ነበርክ። ነገር ግን የችግሬን ጊዜ ብቻዬን ተውከኝ ይኸው የሚታየኝ ዱካ ሁለት ነው በማለት እግዚአብሔርን መውቀስ ጀመረ።

እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል መለሰለት። ልጄ ሆይ የውልህ የደስታህ ጊዜ አብሬህ መሆኔ ልክ ነው የችግርህ ጊዜ ችግርህን መሸከም አቅቶህ ነበር፣ ህመምህ ከአቅምህ በላይ ሆኖ ነበር፣ ብዙ ፈተናዎች ተደራርበውብህ ልትሸከመው ከምትችለው በላይ ሆኖብህ ስለነበር መራመድ አቅቶህ እኔ ተሸክሜህ ነበር። እና ያየኸው ሁለት ኮቴ የእኔ ነው። ልጄ እኔ ትቼህ አላውቅም ቢደክምህ እንኳን ተሸክሜህ ሁሉን አሻግርሃለሁ አለው።

እግዚአብሔር እኔ ጋር የለም ባላችሁበት በዛ ጊዜ እግዚአብሔር ግን እጅግ ቅርችሁ ሆኖ አተነፋፈሳችሁን እንኳን ይሰማል። ያለ እግዚአብሔር ያለፈ ዘመንና ዕለትም ጨርሶ የለም። በትጋት ተሻገርኩት ከማለት ይልቅ እግዚአብሔር አሻገረኝ ማለት እጅግ ማስተዋል ነው።

የሃሳብ ምንጭ:- አዲስ ህይወት መጽሐፍ

✍️ ዲያቆን ተስፋ መሠረት
አባ ገብረኪዳን ካስተማሩት። ሰምተን እያለፍንው ስላልተለወጥን ደጋግመን አንብበን እስቲ እንለወጥ

ጥያቄ? የሰው ልጅ ይህን ሁሉ ኑሮ እየኖረ ለምን ውድቀት መጣበት? የሰው ልጅ የሕሊና ውድቀት የመጣበት ሦስት ጥያቄዎችን ባለመመለሱ ነው። በምድር ላይ የሚኖር ሰው "ሰው" ለመባል የሚበቃው እነዚህን ሦስት ጥያቄዎች መመለስ ሲችል ነው።

እኔ ምንድን ነኝ? ሰው ነኝ። ክርስቲያን ነኝ። "አህያ ነኝ ወይ?" ዓለም የጫነችብኝን ኃጢያት ሁሉ የምጫነው? "ፈረስ ነኝ ወይ?" ያለ ሕግ በየሔድኩበት የምዘሙተው? "ውሻ ነኝ ወይ?" የተፋሁትን መልሼ የምልስ? ማለትም የተናዘዝኩትን ኃጢያት መልሼ የምሠራ? "ዘንዶ ነኝ ወይ?" ትልቁንም ትንሹንም የሚውጥ? እግዚአብሔርን፣ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን፣ ቅዱሳኑን ሁሉ የሚሰድብ? የሚያቃልል? በሬ ነኝ ወይ? አንዴ በፖለቲካ፣ አንዴ በሥርዓተ ትምህርት፣ አንዴ በዘረኝነት ቀንበር ማንም ጠምዶ የሚያርሰኝ? ተጎንብሰህ ያልተፈጠርከው ቀና ብለህ እንድትሔድ ሆነህ የተፈጠርከው የሰማይ ሀገር ስላለህ ነው። "እኔ እንቁራሪት ነኝ ወይ?" ስሔድ አቅጣጫ የሌለኝ? አንድ ቀን ዘማሪ፣ አንድ ቀን ዘፋኝ? አንድ ቀን ዘራፊ፣ አንድ ቀን መጽዋች?

ሰው የሕሊና ልዕልና እንዲኖረው ይህን ለራሱ ይመልስ። እኔ ምንድን ነኝ? ሰው። ሰው ማለት ምን ማለት ነው? 7፣ 7 ማለት ፍጹም፣ ፍጹም ማለት የሚያስብ፣ የሚኖር፣ ሰማያዊ ዜግነት ያለው፣ አርዓያ እግዚአብሔር ያለው። አምሳለ እግዚአብሔርነት ያለው፣ በደመ ክርስቶስ የተቀደሰ፣ በስመ ክርስቶስ የከበረ፣ የሥላሴ ልጅ፣ የቅዱሳን ወገን፣ የማኅበረ መላዕክት ሠራዊት፣ አንድነት፣ የቤተክርስቲያን፣ የክርስቶስ አካል፣ እንዲህ መሆናችንን ስለምንረሳ ሕሊናችን የወደቀው ለዚህ ነው።

በዓለም ላይ የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ሕሊናቸው የወደቀው፣ የሰውነት ክብር በቁስ ክብር ስለተተካ ነው። ቁስ ከሰውነት ስለበለጠ! "ማግኘት ከመገኘት ስለበለጠ" ነው። አሁን ሰው ስለ ማግኘት ነው የሚጨነቀው እንጂ ስለተገኘበት ክብር ማሰብ ትቷል።

ነፍስ በሥጋው ውስጥ ሕልው ሆና የምትኖርበትን ምግብ ከመስጠት፣ ነፍስን እም ሃበ አልቦ አምጥቶ መፍጠር አይበልጥም ወይ? ሥጋ ለብሶ የሚከብርበትን ልብስ ከመስጠት፣ ሥጋን ከአፈር አክብሮ መፍጠር አይበልጥም ወይ? አያችሁ? እግዚአብሔር ለሥጋና ለነፍስ ከሚሆነው ይልቅ፤ ስለ ሥጋና ስለ ነፍስ ክብር እንድናስብ አርቆ ወደ ተሻለ ክብር ነበር የወሰደን። ያንን ስለተውንው ነው ውድቀት የመጣው። ደስታችንም ትርጉም ያጣው።

እኔ ምን ላደርግ ወደ እዚህ ምድር መጣሁ? ሰማያዊ፣ መንፈሳዊ ንግድ ልነግድ። ሰው ከእንስሳት ይልቅ የተሻለ አዕምሮ የተሰጠው በሚሠራው በሚፈጥረው ነገሮች የሰማይ ሀገር እንዳለን ለምሥክርነት እንዲሆኑት ነው።

የሰማይ ሀገር መኖሩን፣ እግዚአብሔር መኖሩን፣ አንዱ ማስረጃው የሰው ልጆች ደስታ አላበቃ ማለቱ ነው። የሰው ልጆች መርካት አለመቻላቸው ነው። አንድ ሊቅ ሲናገር "ልባችን ለአንተ መቅደስነት ስለተፈጠረ አንተ እስከምትገባ ድረስ አይሞላም።" ይላል። እግዚአብሔር እስኪሞላ የሰው ልጅ አይሞላም። "የሰዎች እና የመላዕክት እውቀት እና ምኞት ሁሉ አንተን ሲያይ ያርፋል።" ይላል አረጋዊ መንፈሳዊ። እግዚአብሔርን በማየት ደስታ ሁሉ ይፈጸማል። እግዚአብሔርን በማግኘት ሀብት ሁሉ ይሞላል። መጨረሻው ይህ ነው። ወእጸግብ በርዕየ ስብሐቲከ እንዳለ ቅዱስ ዳዊት። ገጸ ምሕረትህን በማየት እጠግባለሁ። እግዚአብሔርን ስላጣ ሰው ውድቀት ጀመረ።

ወዴት እየሔድኩ ነው? ወደ ክርስቶስ። የት እደርሳለሁ? በምሠራው ሥራ ወደ ሲዖል ወይስ ወደ ገነት? በተገላለጠ አለባበሴ ወደ ዲያብሎስ፣ ወደ ዝሙት እደርሳለሁ ወይስ በመጎናጸፍ ወደ ድንግል ማርያም? 1ጴጥ 3፥1-7 እነ ሣራን ሲያመሰግን ከሰው በተሰወረ በልብ ጌጥ እንጂ ጸጉርን በመሸረብ አላጌጡም። የት እንደምንሔድ ስለማናውቀው።

ሁላችንም ወደ እግዚአብሔር እየሔድን መሆናችንን ስናስብ ሕሊናችንን ገዝተን የሕሊና ልዕልና ይኖረናል።
https://www.tg-me.com/መዝሙር ዘዳዊት/com.mezmur_Zedawitt
ዐረገ በስብሀት የእርገት መዝሙር Arege Besibhat
አረገ በስብሐት
የእርገት መዝሙር

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

     🔸 @Z_TEWODROS
🔸🔹🔸 @Z_TEWODROS
     🔸 @Z_TEWODROS

✍️Comment @Channel_admin09
👉 "ጌታ ኢየሱስም . . . ወደ ሰማይ ዐረገ በእግዚአብሔርም ቀኝ ተቀመጠ" - ማር. 16፥19

👉 "ዐርገ ወልድ በስብሐት ውስተ ሰማያት" - ዚቅ ዘዕርገት

👉 "ይህንም ከተናገረ በኋላ እነርሱ እያዩት ከፍ ከፍ አለ፤ ደመናም ከዓይናቸው ሰውራ ተቀበለችው። እርሱም ሲሄድ ወደ ሰማይ ትኵር ብለው ሲመለከቱ ሳሉ፥ እነሆ፥ ነጫጭ ልብስ የለበሱ ሁለት ሰዎች በአጠገባቸው ቆሙ፤ ደግሞም፦ የገሊላ ሰዎች ሆይ፥ ወደስማይ እየተመለከታችሁ ስለ ምን ቆማችኋል? ይህ ከእናንተ ወደ ሰማይ የወጣው ኢየሱስ ወደ ሰማይ ሲሄድ እንዳያችሁት፥ እንዲሁ ይመጣል አሉአቸው።" - ሐዋ. 1፥9-11

✝️"'ዐርገ በስብሐት ውስተ ሰማያት' በብርሃን በቅዳሴ በክብር በሥልጣን ወደ ሰማይ ዐረገ፤

✝️'ወነበረ በየማነ አቡሁ' በአባቱ ዕሪና ኖረ፤ ኖረ ማለቱ ንጉሥ የተጣላውን ሰናፊል አትታጠቅ በትር አትያዝ እንዲህ ካለ ቦታ አትቀመጥ ብሎ ሥርዓት እንዲወስንበት ሥርዐት የወሰነበት ሆኖ አይደለም፤ ምልአት ሲል ነው። 'እስመ ብሂል የማን ይመርሕ ኀበ ተዋሕዶቶሙ በክብር' እንዲል። 'ነበረ' የእንግድነት፣ 'የማን' የባለቤትነት ነው።

✝️'ዳግመ ይመጽእ በስብሐት' ዳግመኛ በብርሃን በሥልጣን በቅዳሴ ይመጣል፤

✝️'ይኰንን ሕያዋነ ወሙታነ' በሕያዋንና በሙታን ይፈርድ ዘንድ፤ አንድም ሕያዋንና ሙታንን ይገዛ ዘንድ ይመጣል፤ አንድም ሕያዋን ያላቸው ጻድቃን ናቸው በነፍስ ሕያዋን ናቸውና፤ አንድም በነፍስ ሕያዋን የሚሆኑበትን ሥራ ይሠራሉና፤ አንድም የሕያው የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ናቸውና፤  ሙታን ያላቸው ኃጥአን ናቸው በነፍስ ሙታን ናቸውና፤ አንድም በነፍስ ሙት የሚሆኑበትን ሥራ ይሠራሉና፤ አንድም የሙት የዲያብሎስ ማደሪያ ናቸውና፤ አንድም ኃጥአንን ሕያዋን አላቸው በዚህ ዓለም ሕያዋን ናቸውና። ጻድቃንን ሙታን አላቸው 'ምውት አነ በኀበ ዓለም ወዓለምኒ ምውት ይእቲ በኀቤየ' የሹትን አያገኙምና፤ አንድም ኃጥአንን ሕያዋን ሙታን ይላቸዋል ሕያዋን አላቸው እስከ ዕለተ ምጽአት፤ ሙታን አላቸው ከዕለተ ምጽአት በኋላ፤ አንድም ሕያዋን አላቸው በዚህ ዓለም፤ ሙታን አላቸው በወዲያኛው ዓለም፤ ሕያዋን አላቸው በሥጋ፤ ሙታን አላቸው በነፍስ፤ አንድም ጻድቃንን ሕያዋን ሙታን ይላቸዋል፤ ሙታን አላቸው እስከ ዕለተ ምጽአት፤ ሕያዋን አላቸው ከዕለተ ምጽአት በኋላ፤ አንድም ሙታን አላቸው በሥጋ፤ ሕያዋን አላቸው በነፍስ፤ አንድም ሙታን አላቸው በዚህ ዓለም፤ ሕያዋን አላቸው በወዲያኛው ዓለም።

✝️'ወአልቦ ማኅለቅት ለመንግሥቱ' ለመንግሥቱ ፍጻሜ የለውም፤ ዳዊትና ሰሎሞን ቢገዙ አርባ አርባ ዘመን ነው ሊያውም እስከ ዳንና እስከ ቤርሳቤህ ድረስ ነው። የዕሱ ግን ዘመኑ ፍጻሜ የለውም ግዛቱም ድንበር የለውምና 'እስመ ዚአየ ውእቱ ኩሉ ዓለም በምልዑ [ዓለምና ሞላው የእኔ ነውና]' እንዲል (መዝ. 49 (50)፥12)።"

ምንጭ፦
መጋቤ ሐዲስ ደምፀ አንበርብር፣ ውዳሴ ማርያምና ቅዳሴ ማርያም ጸሎተ ሃይማኖትና አቡነ ዘበሰማያት አንድምታ ትርጓሜ፣ ጸሎተ ሃይማኖት፣ ገጽ 435-436፣ 2007ዓ.ም

👉"ጌታ ኢየሱስም ከእነርሱ ጋር ከተናገረ በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ በእግዚአብሔርም ቀኝ ተቀመጠ።" - ማር. 16፥19

👉"እስከ ቢታንያም አወጣቸው እጆቹንም አንሥቶ ባረካቸው። ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየ ወደ ሰማይም ዐረገ። እነርሱም፤ ሰገዱለትና በብዙ ደስታ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ" - ሉቃ. 24፥50-52

👉"አምላክ በእልልታ፥ እግዚአብሔር በመለከት ድምፅ ዐረገ" - መዝ. 46 (47)፥5

👉"ወደ ላይ ዓረግህ፥ ምርኮን ማረክህ፥ ስጦታንም ለሰዎች ሰጠህ" - መዝ. 67 (68)፥18

👉"በምሥራቅ በኩል ወደ ሰማየ ሰማያት ለወጣ ለእግዚአብሔር ዘምሩ" - መዝ. 67 (68)፥33

ሰላም ለዕርገትከ ዘኢይትረከብ መጠኑ፤
ወለንብረትከ ሰላም ለአቡከ ውስተ የማኑ፤
ኢየሱስ ክርስቶስ እለ ኪያከ ተአመኑ፤
ቅዱሳነ ዘእምኀቤከ ወንጹሐነ ይኩኑ፤
ጰራቅሊጦስሃ መንፈስከ ፈኑ፠
- መልክአ ኢየሱስ - ሰላም ለዕርገትከ

ዐረገ በስብሐት ዐረገ በእልልታ፤
ሞትን ድል አድርጎ የሠራዊት ጌታ፤                                                                                                                                                                                                             ዐረገ በእልልታ።

መልካም በዓለ ዕርገተ ክርስቶስ ኢየሱስ እግዚእነ!
https://www.tg-me.com/መዝሙር ዘዳዊት/com.mezmur_Zedawitt
✝️ ጌታችን ለምን በ40 ኛው ቀን ዐረገ ?

-> ጌታችን ያረገው ሞትን በሥልጣኑ  ድል አድርጎ በተነሳ በ40 ኛው ቀን ነው (የሐዋ 1፥ 3 ) ።  ለምን 40 ቀን እስኪሞላ ጠበቀ ከ 40 በታች ወይም በላይ ለምን አልቆየም ?

1- አዳም የ30 0መት ጎልማሳ ሆኖ ተፈጥሮ በ40ኛው ቀኑ አግኝቶ ያጣትን ገነትን እንደመለሰለት ለማጠየቅ 40 ቀን ሲሆነው ዐረገ ::

2 - ሰው (ወንድም ሆነ ሴትም ) ተስእሎተ መልክዕ የሚሳልለት ከተጸነሰ በ40ኛው ቀኑ ነውና ተስዕሎተ መልክዕ ለተሣለለት የሰውል ልጅ ሁሉ ካሳን ፈጸምኩ ለማለት ዕርገቱን ከተነሳ በ40 ቀኑ አደረገው::

3- ሰጎን ጫጩቶቿን የምትፈለፍለው እንደ ሌሎቹ አዕዋፍ በመታቀፍ አይደለም፡፡ ለ40 ዕለት ያህል ተባዕቱም ሆነ እንስቲቱ ሰጎን እንቁላሉን ትክ ብለው ይመለከቱታል ፤ዕንቁላሉም ነፍስ ዘርቶ ይፈለፈላል ፤ለጥቂት ፊታቸውን ቢመልሱ ግን ዕንቁላሉ ይበላሻል ፡፡

ጌታችንም ከትንሳኤው በኋላ 40 ቀን እስኪሆን መቆየቱ ዘውትር እንደሚጠብቀን ፥ ከእኛም ዐይኑን እንደማያነሳ ምሳሌም ነው ።

©️ አምኃ ሥላሴ / መኩሪያ ተሰፋዬ
https://www.tg-me.com/መዝሙር ዘዳዊት/com.mezmur_Zedawitt
እንኳን አደረሰን
ሰኔ 12 - ዓመታዊ የቅዱስ ሚካኤል በዓል

አንድ አምላክ በኾነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ሰኔ ዐሥራ ሁለት በዚች ዕለት የከበረ የመላእክት አለቃ የመልአኩ የሚካኤል የመታሰቢያውን በዓል ያከብራሉ። የሚያከብሩበትም ምክንያት እንዲህ ነው፤

እስክንድርያ በምትባል ከተማ አክላወበጥራ የተባለች ንግሥት የንጉሥ በጥሊሞስ ልጅ ዙሐል በሚባል ኮከብ ስም ያሠራችው ታላቅ ምኵራብ ነበረና በየዓመቱ ሰኔ በባተ በዐሥራ ሁለት ቀን በዚያ ምኵራብ ሕዝቡ ተሰብስቦ ታላቅ በዓል ያደርጉ ነበር፡፡ በዚያም ምኵራብ ውስጥ ዙሐል የሚሉት ታላቅ የነሐስ ጣዖት ነበረና በዓሉ በሚከበርበት ዕለት ብዙ ፍሪዳዎችን ያርዱለት ነበር፡፡

አባ እለእስክንድሮስ እስከተሾመበት ዘመን ድረስ ለዚያ ጣዖት እንዲህ ሲያደርጉ ኖሩ፡፡ ይኸውም ሦስት መቶ ዓመተ ምሕረት ተፈጽሞ በአራተኛው ምዕት ውስጥ ነበር፡፡ አባ እለእስክንድሮስ በእስክንድርያ ከተማ ሊቀ ጵጵስና በተሾመ ጊዜ፣ ጻድቅ ቆስጠንጢኖስም በነገሠ ጊዜ የክርስትና ሃይማኖት ስለ ተስፋፋች ያን ጣዖት ሊሠብረው ወድዶ ሳለ ጐስቋሎች ሰዎች ከለከሉት፡፡ እንዲህም አሉት፤ ‹‹እኛ  በዚህ  ቦታ ይህን በዓል ማክበርን ለምደናል። እነሆ ከአንተ በፊት  ዐሥራ ስምንት ሊቃነ ጳጳሳት አልፈዋል፤ ይህን ልማዳችንንም
አልለወጡብንም፡፡ ››

አባ እለእስክንድሮስ ግን ገሠፃቸው፤ አስተማራቸው፡፡ ስሕተታቸውንም በመግለጥ እንዲህ አላቸው፤ ‹‹ይህ ጣዖት  የማይጎዳና የማይጠቅም ነው፡፡ እርሱንም የሚያመልክ  ሰይጣናትን ያመልካቸዋል፡፡ምክሬንስ ብትሰሙ ቀድሞ እንደ  ነበረ አድርጌ ይህን በዓል እሠራላችኋለሁ፤ ይኸውም ጣዖቱን እንድንሰብረው፣ ምኵራቡንም እንድንባርከውና በከበረ መልአክ በመላእክት አለቃ በሚካኤል ስም ቤተ ክርስቲያን አድርገን እንድንሰይመው ነው፡፡ እኛም ይህን ታላቅ በዓል እንሠራለን፡፡ የሚታረዱትም ላሞችና በጎች ለድኆችና ለጦም አዳራዎች፣ ለችግረኞችም በከበረው መልአክ ስም ምግብ ይኹኑ፡፡ እርሱ በእግዚአብሔር ዘንድ ባለሟልነት ያለው ስለ ኾነ ስለ እኛ ይማልዳልና፡፡›› ይህንንም ብሎ በዚህ በጎ ምክር አስወደዳቸው፤  እነርሱም ታዘዙለት፡፡ ከዚህም በኋላ ያንን ምኵራብ አድሰው በዚህ የከበረ መልአክ የመላእክት አለቃ ሚካኤል ስም ቤተ ክርስቲያን አደረጉት፡፡ በዚችም ዕለት አከበሩዋት፡፡ እርሷም የታወቀች ናት፡፡ እስላሞችም እስከ ነጉሡበት ዘመን ኑራ ከዚያ በኋላ አፈረሱዋት፡፡ ይህም በዓል ተሠራ፤ እስከ ዛሬም ጸንቶ ይኖራል፡፡

ዳግመኛም በዚች ዕለት እግዚአብሔር የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልን በነገዱ ውስጥ በመላእክት ዅሉ ላይ በብዙ ክብር ሾመው፡፡ ይህም የከበረ መልአክ ክብር ይግባውና በጌታችን ፊት ስለ ሰው ልጆችና ስለ ፍጥረትም ዅሉ ይለምናል፤ ይማልዳልም፡፡ የዚህ የከበረ የመላእክት አለቃ ሚካኤል ተአምራቱ ብዙዎች ናቸው፡፡ ከእነርሱም አንዱ ይህ ነው፤

እግዚአብሔርን የሚፈራ አንድ ሰው ነበረ፡፡ እርሱም የከበረ የሚካኤልን የበዓሉን መታሰቢያ በየወሩ በዐሥራ ሁለተኛው ቀን ይልቁንም በሰኔ እና በኅዳር ወር አብልጦ ያከብር ነበር፡፡ በጐረቤቱም ርኅራኄ የሌለው አንድ ባለ ጠጋ ሰው ነበረ፡፡ ይህን እግዚአብሔርን የሚፈራውን ሰው የከበረ መልአክ የሚካኤልን በዓል በሚያደርግበት ጊዜ ይጠላውና ያቃልለው ነበር፡፡ ለድኆች ስለ መራራቱም ይዘባበትበት ነበረ፡፡ የሕይወቱ ዘመንም ተፈጽሞ የሚሞትበትና ከዚህ ከኃላፊው ዓለም ድካምም የሚያርፍበት ጊዜ ሲቀርብ የክቡር መልአክ ሚካኤልን የበዓሉን መታሰቢያ ታደርግ ዘንድ፣ ምጽዋት ሰጭም ትኾን ዘንድ ሚስቱን አዘዛት፡፡ ከዚህም በኋላ ዐረፈና ገንዘው ቀበሩት፡፡
Forwarded from 🎤 ዜና ተዋህዶ ቻናል 🎤 (Ť€m€)
በዚህ ዓመት ለሚመረቁ ለዩኒቨርስቲ እና ለኮለጅ ተማሪዎች እንዲሁም የመውጫ ፈተና ጭንቀት ላይ ላላቸው ላኩላቸው

ተወዳጆች ሆይ የክርስቶስ ሰላም ከእናንተ ጋር ይሁን።

+ #ተማሪዎች ከፈተና በፊት ምን ብለው ይጸልዩ?

ቅዱስ ቄርሎስ ሳድሳዊ ከሚታወቁባቸው በርካታ በጎ ነገሮች አንዱ ለተማሪዎች የነበራቸው ልዩ ፍቅርና ቅርበት ነበረ፡፡ አባ ሚናስ ተብለው ይጠሩ ከነበረበት የምንኩስናቸው ዘመን ጀምሮ አቡኑ በተማሪዎች የተከበቡ ነበሩ፡፡ ከልዩ ልዩ ክፍለ ሀገራት ካይሮ ዩኒቨርሲቲ ሊማሩ ለሚመጡ ተማሪዎች የማደሪያ አገልግሎት በቅዱስ ሚናስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ይሰጡ ነበር፡፡ ይህ አገልግሎታቸውም በግብፅ ለዘመናዊው ቤተ ክርስቲያንን የሚያካትት የማደሪያ አገልግሎት(church- affiliated dormitory) መወለድ ምክንያት ሆኗል፡፡ የዚህ የማደሪያ አገልግሎት ተጠቃሚዎች የነበሩ ተማሪዎችም ቀሳውስትና ጳጳሳት የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ለመሆን በቅተዋል፡፡(ሊቀ ጳጳሱ አቡነ ሳሙኤልና ቅዱስነታቸው አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊተጠቃሽ ናቸው፡፡) በወቅቱ መነኩሴ የነበሩት አባ ሚናስ (አቡነ ቄርሎስ) ለእያንዳንዱ የቤተ ክርስቲያኑ ካህን በተማሪዎቹ መኖሪያ ውስጥ የሥራ ድርሻ ሰጥተው ነበር፡፡ የእርሳቸውን የሥራ ድርሻ ምን እንደነበረ ግን ማንም ሰው አላወቀም ነበር፡፡ በሌሊት በድብቅ የሚሠሩት ሥራ ካህናቱና በቤተ ክርስቲያኑ የሚኖሩ ተማሪዎች የሚጠቀሙበትን መጸዳጃ ቤት ማጽዳት ነበር፡፡

ይህ ለተማሪዎች ያላቸው በጎ አመለካከት በፓትርያርክነት ዘመናቸው አልተለያቸውም፡፡ ተማሪዎች ፈተና ሲደርስባቸው ወደ እርሳቸው እየመጡ ጸልዩልን ይሉአቸው ነበር፡፡ አንዳንድ ተማሪዎች ደግሞ የሚያጠኑበትን መጽሐፍ ይዘው መጥተው ያስባርኩ ነበር፡፡ ቅዱስ አባ ቄርሎስ አንዳንዴ መጽሐፉን ገለጥ ያደርጉና ‹ይህንን አጥኑ› ብለው ይሠጡ ነበር፡፡ የፈተናውም አብዛኛው ጥያቄ ከዚያ ገጽ ይወጣ ነበር፡፡ እንዲሁም ለተማሪዎች ፈተና በሚፈተኑበት ጊዜ የሚገጥማቸውን የመንፈስ ጭንቀትና የአእምሮ ውጥረት በመረዳት የሚከተለውን ከፈተና በፊት የሚጸለይ ጸሎት አዘጋጅተውላቸዋል፡፡

+ ጸሎት +

‹‹ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ

‹‹በችግርህ ቀን ጥራኝ ፤ አድንሃለሁ አንተም ታከብረኛለህ›› ብለህ የአንተን መጠጊያነት መፈለግን ስላስተማርከኝ አመሰግንሃለሁ!

አሁንም ጌታ ሆይ! በዚህ የፈተና ሰዓት ጥበብና ማስተዋልን ትሰጠኝ ዘንድ እማጸንሃለሁ፡፡

ይህን ፈተና በሰላም አልፍ ዘንድ ጸጋን (ሞገስን) ስጠኝ፡፡ ፈተናውን በምሠራ ጊዜ ጥልቅ የሆነ ሰላምህንና በረከትህን ስጠኝ፡፡

ጌታዬ ኢየሱስ ውጤት በሚሰጡኝ ጊዜ በመምህራኖቼ ዓይን መወደድን ትሰጠኝና ልባቸውን ታለሰልስልኝ ዘንድ እለምንሃለሁ፡፡ የከበርከው ጌታእኔ ኃጢአተኛ ነኝ ፤ ዓመቱን ሙሉ አንተን ደስ አላሰኘሁህም ፤ ውስጤንም ጭምር ፤ ነገር ግን ከልቤ ደንዳናነትና ከኃጢአቶቼ የተነሣ ሳይሆን ከምሕረትህ እና ከርኅርኄህ የተነሣ እንደትረዳኝ እለምንሃለሁ፡

ጌታ ሆይ ‹‹ለምኑ ይሰጣችኋል፣ እሹ ታገኛላችሁ፤ አንኳኩ ይከፈትላችኋል›› ብለሃል፡፡ እናም እነሆኝ እየለመንኩ ነው፤ የምሕረትህንም ደጅ እያንኳኳሁ ነው፡፡  ‹‹ወደ እኔ የሚመጣውን ከቶ ከእኔ አላወጣውም›› ብለሃልና ጸሎቴን አትናቅ፡፡በቅድስት ድንግልና በመላእክትህ ሁሉ አማላጅነት መልስልኝ!! አሜን!"

ታሪክ በማይረሳው የተወሳሰበ የትምህርት ዘመን አልፋችሁ ለምትፈተኑ ለዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪዎች እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን! የልባችሁን ዓይን ያብራላችሁ! ያጠናችሁትን ይባርክላችሁ የተማራችሁትን ያስታውሳችሁ! ባለቀ ሰዓት የሚደረግ ጥናት ከጭንቀት ውጪ ምንም አያተርፍምና ራሳችሁን በጸሎት አረጋግታችሁ ተፈተኑ::

https://www.tg-me.com/zena_tewahido
#ሳታቋርጡ_ጸልዩ

"ሥራ የሚሠራ ሰው ቀኑን ሙሉ በጸሎት ተጠምዶ መዋል አይችልም" አትበለኝ፤ ይችላል። በጸሎት የሚያስፈልገው ድምፅ ሳይሆን ሀሳብ ነው ፤ እጅ ሳይሆን እደ ልቦናን ማንሣት  ነው፤   አፍአዊ ሳይሆን ውስጣዊ አኳኋን ነው ።ይህን ለማድረግ ደግሞ ቦታም ጊዜም አይገድብህም። በጉልበትህ ባትንበረከክ፤ ደረትህንም ባትደቃ እንኳ መንፈስህ ትጉ ከሆነ ጸሎትህ ሥልጡን ነው ።

    #ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
https://www.tg-me.com/መዝሙር ዘዳዊት/com.mezmur_Zedawitt
በዓለ መንፈስ ቅዱስ / ጰራቅሊጦስ

ይህች ታላቅ ዕለት ከቅድስት ሥላሴ አንዱ አካል የሆነው እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ለቅዱሳን ሐዋርያት፣ ለቅዱሳን አርድእትና ለቅዱሳት አንስት የተገለጠባት ዕለት ናት፡፡ እነዚህ ሁሉ በጸሎት ተግተው በሚጸልዩበት ወራት መንፈስ ቅዱስ በተከፋፈሉ የእሳት ልሳን አምሳል የወረደበት ቅዱስ ቀን ነው፡፡ አስቀድሞ ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለቅዱሳን ሐዋርያት ደብረ ዘይት በተባለ ታላቅ ተራራ ላይ ሳሉ እንዲህ ብሎ አስተምሯቸው ነበር “ኃይልን ከአርያም እስክልክላችሁ ድረስ በኢየሩሳሌም በጸሎት ቆዩ፡፡”/ሉቃ 24፡36/ መቶ ሃያው ቤተሰብም በኢየሩሳሌም ሀገር በምትገኝ በቤተ መቅደስ በአንድነት ሆነው በጸሎት በመትጋት ቆዩ፡፡ 120ው ቤተሰብ የሚባሉት 12ቱ ሐዋርያት፣ 72ቱ አርድእት/አገልጋዮች/ እና 36ቱ ቅዱሳን አንስት/ሴቶች/ ናቸው፡፡

ከዕርገት በኋላ በአሥረኛው ቀን እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ሐዋርያት ወዳሉበት፣ በጸሎትና በምሥጋና ወደ ሚተጉበት ሥፍራ በእሳት አምሳል /ምሳሌ/ ወርዶ በእያንዳንዳቸው ላይ ተቀመጠባቸው፡፡ ይሄንንም ሁኔታ ተከትሎ ምስጢር ተገለጠላቸው፣ ይፈሩ የነበሩት ሐዋርያትም ወንጌልን ለማስተማር ደፋሮች ሆኑ፣ በተለያየ ቋንቋዎች እንዲናገሩ እውቀት ተሰጣቸው፤ የእግዚአብሔርንም ጸጋ ተቀበሉ፡፡ ይህንን ታላቅ ኀይል እና ሰማያዊ ስጦታን የሰጣቸውን እግዚአብሔርን በታላቅ ዝማሬና እልልታ አመሰገኑት፡፡

በዚያም ዕለት  በዓለ ሃምሳ የሚባለውን የአይሁድን በዓል ለማክበር ከተለያዩ ሀገራት የመጡ ቁጥራቸው በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የሐዋርያቱን ታላቅ የዝማሬና የእልልታ ድምፅ ሰሙ፡፡ ከመቶ ሃያው ቤተሰብ መካከል አንዱ የሆነው ቅዱስ ጴጥሮስ የተሰበሰቡት ሁሉም እንዲሰሙት ድምፁን ከፍ አድርጎ ቃለ እግዚአብሔርን እንዲህ ብሎ አስተማራቸው፡፡ “እናንተ የእስራኤል ሰዎች ሆይ እኛን የሰው ልጆችን ለማዳን እግዚአብሔር ኢየሱስ ክርስቶስ ሰው ሆኖ ወደ ምድር መጥቶ ከክፉ ሥራ ተመለሱ፣ ኀጢአትን አታድርጉ፣ በቅድስና ኑሩ፣ ወደ እኔም ተመለሱ ቢላችሁ፤ እናንተ ግን ምንም በደል ሳይኖርበት ገረፋችሁት፣ አንገላታችሁት፣ በመስቀል ላይም ሰቀላችሁት፡፡ እርሱ ግን እግዚአብሔር ነውና ሞትን ድል አድርጎ ተነሣ፡፡ እርሱ ግን አሁንም ይቅር ባይ ነውና ከኀጢአታችሁ ተመለሱ ንስሐም ግቡ፡፡” በማለት አስተማራቸው፡፡ የተሰበሰቡት ሰዎች ሁሉ ተገረሙ፡፡ ምክንያቱም ሐዋርያት በፊት የሚያውቁት አንድ ቋንቋ ብቻ ነበረ፡፡ በዚህ ሰዓት ግን ሰባ ሁለት ቋንቋን እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ገልጦላቸው ለሁሉም በየቋንቋቸው አስተማሯቸው፡፡ ይህንንም ድንቅ ተአምር ከተመለከቱት ብዙዎች እግዚአብሔርን አመሰገኑት፡፡ ወደ ሐዋርያትም ቀርበው “አባቶቻችን እናንተ የእግዚአብሔር አገልጋዮች ናችሁና ምከሩን፡፡ እንደ እናንተ የእግዚአብሔር ልጆች እንድንሆንና በቅድስና እንድንኖር ምን እናድርግ?” በማለት ጠየቁ፡ በዚያች ቀን ቁጥራቸው ሦስት ሺ ያህል ሰዎች በቅዱስ ጴጥሮስ ትምህርት አምነው ክርስቲያን ለመሆን ቀረቡ፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስም እንዲህ አላቸው፡፡ “እነሆ ሁላችሁም ንስሐ ግቡ፡፡ በአምላካችን በኢየሱስ ክርስቶስ የባሕርይ አምላክነት አምናችሁ ተጠመቁ፡፡” አላቸው በዚያው ዕለትም ሦስት ሺ ሰዎች ወደ ሐዋርያት በመቅረብ ኀጢአታቸውን ተናገሩ፤ ሐዋርያትም እግዚአብሔር ይፍታችሁ እያሉ ልጅነትን የሚያሰጣቸውን ጥምቀት አጠመቁዋቸው፡፡
ከዚያ ቀን ጀምሮም በየዓመቱ ይህችን ታላቅ የቤተ ክርስቲያን የልደት ቀን የምትባለውን በዓለ ጰራቅሊጦስን ክርስቲያኖች በታላቅ ደስታና ምሥጋና እናከብራታለን፡፡

በጽርሐ ፅዮን የወረደው የአብ በረከት፣ የወልድ ፍቅር ፣ የመንፈስ ቅዱስ አንድነት ከሁላችንም ጋር ይሁን!!!
https://www.tg-me.com/መዝሙር ዘዳዊት/com.mezmur_Zedawitt
2024/06/25 10:09:08
Back to Top
HTML Embed Code: