Telegram Group Search
isaac decor
ለ ሠርግ
ለ ሽምግልና
ለ ልደት
ለ ቤቢ ሻወር
ለ ብራይዳል እና
ለተለያዩ የምርቃት ፕሮግራሞች
በተመጣጣኝ ዋጋ ።
0923706960
0920313071
ልቤ ፊት... አትቅጣኝ
[ ]

ልትቀጣኝ አስበህ እንደሁ...
የመብረቅ ጅራፍ ገምደህ - ጀርባዬን ግረፍ ፤ ምታ፥
ቀላያትን ተርትረህ ለኔ ብቻ ክፈት ፤ ፍታ፥
ግን እባክህ...
ልቤ ፊት እንዳይሆን ጌታ።

ልቤንማ...
የተስፋ ድንጋይ አስነክሼው፥
አይዞህ እያልኩ እየገፋሁ፥
ከበረሀ ሐሩር መሐል
ስንቴ ሲያምነኝ ጥዬው ጠፋሁ።

ልቤንማ...
ዐይኖቹን በጨርቅ እያሰርሁ፥
ደሞ በጥፊ እያጣፈርሁ፥
"ማነው የመታህ?" እያልሁት ፥ ስስቅበት ፣ ስተፋበት፥
(ያውም'ኮ ከካደው ጋር
ያውም'ኮ ከሸጠው ጋር)፡ ስሳለቅ ስዘብትበት፥

በአእምሮዬ ተከልዬ፥
ከገዳዮቹ መሐል ቆሜ - 'ስቀለው ስቀለው' ብዬ'፥
መስቀሌን አሸክሜው፡ ጎለጎታዬን ሲወጣ፥
(በሰራሁት እንዳልቀጣ)
የምጥ ስቃዩን ሳጋፍር፥
ከሕዝቡ ጋር ስጨፍር፥
ስጣደፍ ሞቱን ለማክበር፥
አካሌ'ኮ አይመስልም ነበር።
ያሸከምኩት መስቀል ላይ ፥ እርቃኑን ቸንክሬ ብሰቀለው፥
ከሰዉ መሐል እያየኝ...
"የሚያደርገውን አያውቅም ፤ አባት ሆይ ይቅር በለው፥"
ብሎ ለኔው ለምኖህ ፥ ደጋግሞ እንደመሞቱ፥
ደሞ ቀና ቀና እያለ...
ሊጎበኘኝ በምህረቱ
አሁን ገና መነሳቱ
አሁን ገና መቃናቱ
አሁን ገና መበርታቱ...

ደሞ ዛሬ...
በአይታረም ገላዬ...
የሰጠኸኝን ትሩፋት፥
መልሼ በእጄ ስገፋት፥
እንደልጅ ልብሴን አውልቀህ ፥ ስትገርፈኝ በማጣት ሳማ፥
አፌን በእጅህ አፍንልኝ ፤ ጩኸቴን ልቤ እንዳይስማ።
በሺ ቁስል ተወርሬ ፥ ላዝግመው እንጂ ወደፊት፥
ይሄን አካል ተሸክሜ ፥ አልችልችልም መቆም እሱ ፊት።

ቅጣቴን ነው ጌታዬ...
አንክተኝ፡ ጣለኝ፡ ስበረኝ!
ግን በእናትህ..!
በድኔን እንዳያይብኝ፡
.........ከልቤ አርቀህ ቅበረኝ.....

[ ሚካኤል ምናሴ ]
ለምን እንደምንንቅህ ታውቃለህ?
ኤልያስ ሽታኹን
- - - - -

እሺ ባይ ምኑ ይከብራል?

ከወዳጆችህ ጀምሮ ሁሉም በስምህ ሲዋሽ ዝም አልክ?

የምትችለውን ሁሉ እንደማትችል ተቆጠርክ?

አንተን ለማየት የማይበቁ አንተን ለመግደል ሲበቁ አየን!

ትሁት አምላክ ዓለም የለውም

ሲናገር ሊቅ ዝም ሲል ድንቅ አምላክ አለም አያውቅም

“በስንት ሸጥከኝ?” የማትል በደለኛውን ያማታሳቅቅ

የቅኖች ውኃ ልክ

አይተኸን ሳይሆን ኖረኸን የተረዳከን

ለምን በዚህ ደረጃ ወደድከን?

ለምን በዚህ ደረጃ አፈቀርከን?

በስምህ ሌባ ስንሆን አየኸን?

ትሁት ነህና ይዘብትብሀል

ልክ ነህና ስህተት ይፈልግብሀል (ፈሪሳውያን እንዳደረጉት)

ጌታ ሆይ ዛሬም ላንተ ጊዜ የለንም::

አናሳዝንም?
👨‍🎨mintesnot tariku
live landscape painting
oil on canvas
20cm×40cm
🔴 sold
" ፈርተውም ፊታቸውን ወደ ምድር አቀርቅረው ሳሉ፥ እንዲህ አሉአቸው። ሕያውን ከሙታን መካከል ስለ ምን ትፈልጋላችሁ? ተነሥቶአል እንጂ በዚህ የለም።"
(የሉቃስ ወንጌል 24:5)

😊መልካም የትንሳኤ በዓል😊
እንሂድ እንሂድ ወደአልጋ
አያ ጊዜ ሳይመጣ
አያ ጊዜ አለህ?
<አዎ>
ምን እየሰራህ?
<እየሄድኩ >
ሳትመጣ?
<አለፍኩኮ>
በየት በኩል
< በደጅ...>
እንዴ...? ሳትበላን? ብላን እንጂ?
<ያልበሰለ አይበላም>
ምን ይበጀን? የት እንብሰል?

<ኧረ የምን መብሰልሰል?
መሄድ እንጂ ወደየ አልጋ...
ቀኑ መሽቶ እስኪነጋ። >

ትኝት...

አልጋ ምጣድ ፡ እስኪታሰስ
ግሎ ድንገት፡ ህልም እንዳይጤስ
እጤሰው ላይ፡ ደሞ ሊጡን
እስኪበስል፡ ከጎን ወጡን...
ውይ ውይ ... እሳቱሳ?
ተረሳ...
ያልጋገሩት መች ይበስላል?
በቃን በቃን እንነሳ..

ንቅት...

እንሂድ ከአልጋ እንውጣ...
አያ ጊዜ ሳይመጣ...
አያ ጊዜ አለህ?
<አዎ!>
ምን እየ...
<እየሮጥኩ>
እረፍ እንጂ...
<መች ደክሜ... ?>
ወይ ቁጭ በል...
<መቼ ቆሜ? >
ወይ ዝግ በል...
<ቸኩያለሁ...>
ወይ ተግ በል...
<ቀጥሬያለሁ... >
ማንን?
<የእናንተን ልክ...>
ብሎን ፍትልክ...

ንቃት በርሚል ፡ጠላ ጥንስስ
ጌሾ ውሎን ፡ በሳቅ ክልስስ
ተስፋ ድፍድፍ፡ ስጋት ድፍርስ
ቅራሪውን ቀድተን ችልስስስስ
ወየሁ ወየሁ! እስክስ እስክስ!
አፍ ደፈረ ፡ እግር ሰጋ...

እንሂድ እንሂድ...ወደአልጋ
አያ ጊዜ ሳይመጣ...
አያ ጊዜ አለህ?
ፀጥ...
እግር ቀጥ
ትንፋሽ ፀጥ...
ልብ ዝም...
የጠየቅነው አይመልስም
ከንጋቱ ንቃት ደርቋል
ከእንቅልፋችን ህልም ርቋል
አያ ጊዜም የለም አልቋል።

red-8
ይድረስ ለፀሀይቷ

ፀሀዬ!

እራስሽን ለምን ለፅልመት አሳልፈሽ ሰጠሽ?

አታውቂም! ናፍቆቴ እንደሆንሽ?
ትወጫለሽ?
ልጠብቅሽ?

ይህን ጨለማ ረተሽ ንጋት ላይ ከውብ ፈገግታሽ ጋር ትመጭልኝ ይሆን!!
እንጃ ጨለማው ግን እየፎከረብኝ ነው።
እባክሽ ከሰመጥሽበት ጉድጓድ ውጪ ከተራራው መሀል!!
ንጋት ስትወጪ በጉጉት አይኖቼ ይንከራተታሉ።
ዛሬ በየት አቅጣጫ ነው መውጫሽ?
በውብ ቀለማት በተበጀ ቬሎሽ ተሞሽረሽ ብቅ ስትዪ ጉጉቴ ያይላል በቀለማት በታጀበ ብሩሽ ሸራ ላይ ጠብብ ያሰኘኛል፤ግን ምን ጥበብ አለና ስጠበብ ብውል የእውነተኛው ሰአሊሽ ሞኝነት ይጠበብብኛል
ልፎካከር ሳስብ እራሱ ቅስሜ ይነክታል ለስብራቴም ጠገን የለውም እርሱ እራሱ ካላበጃጀኝ በቀር
ሆ!
እንኳንስ እና እንዲያ እንዴትስ ይታሰባል መሬት ተኩኖ ሰማይን መዳሰስ?!
ሆሆ!!
እሱው እንደሰራሽ ይመርብሽ እቴ!
ደሞ ደግሞ ብቅ ስትዪ ወረት በሌለበት ቢያ ፈገግታሽ እውነት ሰውነትን አልፎ ሁለመናን ይፈውሳል ግድ የለሽም አለንጋሽም ይሁነኝ እናቴም አይደለሽ።
ብቻ ነዪልኝ!
እጠብቅሻለሁ እስከ...

ምንተስኖት ታሪኩ

( እንቅልፍ አና ድካም ድንገት ተያይዘው በጠፉበት ለሊት
ፀሀዪቷን በመጠበቅ በቀን 6/7/2016
ከለሊቱ 8:30-10:10 የተፃፈ)
በሀጥያታችን ከምትቀስፈን
ስንበረታ ገድለህ አትርፈን።

ምንተስኖት ታሪኩ
8/7/2016
ጃስ!! ህያውን ከሙታን መካከል ስለምን ትፈልጋለህ? ምነዋ ግን እስከነ... ቆምክበት አለኝ እየሩሳሌም ያለሁ መስሎት

በቅፅበት የመቃብር ስፍራው እና ባዶ እግር ታወሰኝ፤ይህ በዚህ እንዳለ

ዛሬ አስቂኝ ታሪክ ሰማሁ
አንድ ሀሰተኛ አገልጋይ ክርስቶስ ነኝ እያለ አምልኮት ይቀበላል አሉ!
እናም ለዚህ ሰው ስለ ተአምሩ ሚስቱ ምስክር ነች
"ኢየሱስ ውሀውን ወደ ወይንጠጅ እንደቀየረው የኔም ባል ውሀውን ወደ ሻይ ቀይሮአል" ትላለች

እና ይሄ ጉዳይ ያሳሰበው ምዕመንም አንድ ሀሳብ አመጣ
በጉባኤው መሀል አንተ ክርስቶስ እንደሆንክ ከአብ ዘንድ ተልከህ እንደመጣህ እናውቃለን እነሆ እኛም ሙሉ ክብር ልናጎናፅፍህ እንገርፍሀለን እንገልሀለን አንተም በ 3ኛው ቀን ትነሳለህ ብለው በነገር ያዙት
እርሱም አስጥሉኝ ብሎ ኡኡታውን አቀለጠው።

እናም ወንድሜ/ እህቴ (ጐፔቾ/ኧተሙወና) ትልቁ ምስጢር ተአምራት አይደለም ከሞት መነሳት ነው።
ከክርስቶስ ጋራ ሞተናል?
ከሞትስ ተነስተናል?
ዳግም ተወልደናል?

ብቻ እናስብበት ለማለት ያክል ነው !
አላውቃችሁም ከመባል ያድነን!!

ምስሉ ላይ ያለሁበት ቦታ ወደ ቦሌ አትላስ አካባቢ ፒኮክ መናፈሻ ታስቦበት በድንገት የተነሳ ፎቶ ቢሆንም
ሳይታሰብ ከጊዜው ድባብ ጋር አንዳች ምልከታን ፈጥሮአል

(የሉቃስ ወንጌል ምዕ. 24)
----------
1፤ ነገር ግን ከሳምንቱ በመጀመሪያው ቀን ያዘጋጁትን ሽቱ ይዘው ከእነርሱም ጋር አንዳንዶቹ ወደ መቃብሩ እጅግ ማልደው መጡ።

2፤ ድንጋዩንም ከመቃብሩ ተንከባሎ አገኙት፥

3፤ ገብተውም የጌታን የኢየሱስን ሥጋ አላገኙም።

4፤ እነርሱም በዚህ ሲያመነቱ፥ እነሆ፥ ሁለት ሰዎች የሚያንጸባርቅ ልብስ ለብሰው ወደ እነርሱ ቀረቡ፤

5፤ ፈርተውም ፊታቸውን ወደ ምድር አቀርቅረው ሳሉ፥ እንዲህ አሉአቸው። ሕያውን ከሙታን መካከል ስለ ምን ትፈልጋላችሁ? ተነሥቶአል እንጂ በዚህ የለም።

6-7፤ የሰው ልጅ በኃጢአተኞች እጅ አልፎ ሊሰጥና ሊሰቀል በሦስተኛውም ቀን ሊነሣ ግድ ነው እያለ ገና በገሊላ ሳለ ለእናንተ እንደ ተናገረ አስቡ።

*ታዲያ የት እየፈለግነው ነው ንጉሱን የመቃብር ስፍራ? አንድከም!
አንድ ሚስጥር ልንገራቹ 

"ተነስቶአል እርሱ በዚያ የለም"

                              ምንተስኖት ታሪኩ
                                         2016 ዓ.ም
2024/05/31 06:06:31
Back to Top
HTML Embed Code: