Telegram Group Search
አሥ ሠላሙ ዐለይኩም ወራሕመቱላሂ ወበረካቱሁ

ያ ጀመዓህ! "የተደበቀው እውነት" የሚለው መጽሐፍ ለሁለተኛ ጊዜ ታተመ። በክርስቲያኖች ሚሽነሪዎች ከፍተኛ ተቃውሞ የደረሰበት ይህ መጽሐፍ በክርስቲያኖች ሚሽነሪዎች አስታዋዋቂነት"promotion" የተነሳ በታተመ በሳምንቱ አልቋል። ተወዳጁ ነቢያችን"ﷺ"፦ "አሏህ ይህንን ዲን ከፈለገ በከሃዲያንም ቢሆን ያጠናክረዋል" ስላሉን በእነርሱ አስታዋዋቂነት ለብዙ አንባቢያን እንዲዳረስ ምክንያት ሆኗል፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 1, ሐዲስ 212
አቢ ሁረይራህ"ረ.ዐ." እንደተረከው፦ "ነቢዩ"ﷺ" እንዲህ አሉ፦ "እነሆ ሙሥሊም የሆነች ነፍስ እንጂ ሌላው ጀነትን አይገባትም፥ አሏህ ይህንን ዲን ከፈለገ በከሃዲያንም ቢሆን ያጠናክረዋል"። ﻋَﻦْ ﺃَﺑِﻲ ﻫُﺮَﻳْﺮَﺓَ، ﺭﺿﻲ ﺍﻟﻠﻪ ﻋﻨﻪ ﻗَﺎﻝ ﻋﻦ ﺍﻟﻨَّﺒِﻲّ ﺻَﻠَّﻰ ﺍﻟﻠﻪُ ﻋَﻠَﻴْﻪِ ﻭَﺳَﻠَّﻢَ ﺃﻧﻪ ﻗَﺎﻝَ ﺃَﻧَّﻪُ ﻟَﺎ ﻳَﺪْﺧُﻞُ ﺍﻟْﺠَﻨَّﺔَ ﺇِﻟَّﺎ ﻧَﻔْﺲٌ ﻣُﺴْﻠِﻤَﺔٌ، ﻭَﺃَﻥَّ ﺍﻟﻠﻪَ ﻳُﺆَﻳِّﺪُ ﻫَﺬَﺍ ﺍﻟﺪِّﻳﻦَ ﺑِﺎﻟﺮَّﺟُﻞِ ﺍﻟْﻔَﺎﺟِﺮِ‏

የመጀመሪያው ዕትም በታተመ በ 20 ቀኑ ዛሬ ገበያ ላይ ውሏል። መጽሐፉን ለምትፈልጉ፦
፨፦ አዲስ አበባ መርካርቶ አንዋር መሥጂድ ኢሥላማዊ መጻሕፍት መደብር ውስጥ፣
፨፦ አዲስ አበባ ፒያሳ Abdu Book Delivery
0929574133
፨፦ አየር ጤና አንሷር መሥጂድ 0963796354

የበለጠ መረጃ ለማግኘት +251920781016 ዐብዱ ብለው ይደውሉ!

መጽሐፉ ተደራሽነት እንዲኖረው ባለው የማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃን ሼር በማድረግ ሠበቡል ሂዳያህ ይሁኑ!

ወጀዛኩሙላህ ኸይራ!

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://www.tg-me.com/ወሒድ የንጽጽር ማኅደር/com.Wahidcom
"የተደበቀው እውነት" በአፋን ኦሮሞ "Dhugaa dhokate" በሚል ኢንሻላህ በቅርብ ቀን ይጠብቁ!

እስከዛው በአፋን ኦሮሞ ለሟሟሻ ያክል መጣጥፍ ያንብቡ፦ https://www.tg-me.com/Wahidomar1/62
ኪርያ ላይሶን

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

5፥116 አላህም፡- «የመርየም ልጅ ዒሣ ሆይ! አንተ ለሰዎቹ፡- "እኔን እና እናቴን ከአሏህ ሌላ አማልክት አድርጋችሁ ያዙ ብለሃልን?» በሚለው ጊዜ አስታውስ ፡፡ وَإِذْ قَالَ اللَّهُ يَا عِيسَى ابْنَ مَرْيَمَ أَأَنتَ قُلْتَ لِلنَّاسِ اتَّخِذُونِي وَأُمِّيَ إِلَـٰهَيْنِ مِن دُونِ اللَّهِ

"ኩሪዮስ" κύριος ማለት "ወንድ ጌታ" "አባ ወራ" ማለት ሲሆን "ኩሪያ" κυρία ማለት ደግሞ "ሴት ጌታ" "እመቤት" ማለት ነው፥ ማርያም በኦርቶዶክስ፣ በካቶሊክ እና በአንግሊካን "ኩሪያ" κυρία ትባላለች። በአገራችን በግዕዝ "እግዚእ" ማለት "ወንድ ጌታ" "አባ ወራ" ማለት ሲሆን "እግዚእት" ማለት ደግሞ "ሴት ጌታ" "እመቤት" ማለት ነው፥ ኢየሱስን "ጌታችን" ለማለት "እግዚእነ" ሲሉ ማርያም ደግሞ "ጌታችን" ለማለት "እግዚእትነ" ይሏታል።

የአገራችን ኦርቶዶክስ ሰሙነ ሕማማት ላይ "ኪርያ ላይሶን" የሚሉት ማርያም እንጂ ኢየሱስ አይደለም።
"ኪርያ" የሚሉት "ኩሪያ" κυρία ለማለት ሲሆን "ላይሶን" የሚሉት የሚሉት ደግሞ "ኤልይሶን" ἐλέησον ነው፥ በጥቅሉ "ኩሪያ ኤልይሶን" κυρία ἐλέησον ወይም "ኪርያ ላይሶን" ማለት "ጌታችን ማሪን" ማለት ነው።
እውን ማርያምን በሌለችበት "ጌታችን ማሪን" ማለት አግባብ ነውን? ማርያምስ እንዲህ ያለ ሥልጣን እንደተሰጣት የሚያሳይ የባይብል ጥቅስ አለን? ቅሉ እና ጥቅሉ ግን ይህ ግልጽ ሺርክ ነው። ይህ አምልኮተ ማርያም ከልጇ የተገኘ ትምህርት ስላልሆነ አምላካችን አሏህ ኢየሱስን፦ "አንተ ለሰዎቹ፡- "እኔን እና እናቴን ከአላህ ሌላ አማልክት አድርጋችሁ ያዙ ብለሃልን? ብሎ ይጠይቀዋል፦
5፥116 አላህም፡- «የመርየም ልጅ ዒሣ ሆይ! አንተ ለሰዎቹ፡- "እኔን እና እናቴን ከአሏህ ሌላ አማልክት አድርጋችሁ ያዙ ብለሃልን?» በሚለው ጊዜ አስታውስ ፡፡ وَإِذْ قَالَ اللَّهُ يَا عِيسَى ابْنَ مَرْيَمَ أَأَنتَ قُلْتَ لِلنَّاسِ اتَّخِذُونِي وَأُمِّيَ إِلَـٰهَيْنِ مِن دُونِ اللَّهِ

እርሱም፦ "በእርሱ ያዘዝከኝን ቃል ጌታዬን እና ጌታችሁን አሏህን አምልኩት ማለትን እንጂ ለእነርሱ ሌላ አላልኩም" በማለት መልስ ይሰጣል፦
5፥117 በእርሱ ያዘዝከኝን ቃል ጌታዬን እና ጌታችሁን አሏህን አምልኩት ማለትን እንጂ ለእነርሱ ሌላ አላልኩም፡፡ مَا قُلْتُ لَهُمْ إِلَّا مَا أَمَرْتَنِي بِهِ أَنِ اعْبُدُوا اللَّهَ رَبِّي وَرَبَّكُمْ

"አምላክ" የሚለውም ቃል "መለከ" ማለትም "አመለከ" ከሚል የግዕዝ ቃል የመጣ ሲሆን "የሚመለክ" ማለት ነው። ከሣቴ ብርሃን ተሰማ የዐማርኛ መዝገበ ቃላት (2005) ገጽ 708)

ከዚህ አንጻር ዐበይት ክርስትና ማርያምን አያመልኳትምን? እንዴታ! ድብን አርገው ያመልካሉ። አንድ ሰው ፍላጎቱን አምላኩ አድርጎ ያዘ ማለት ፍላጎቱን አምላኬ ብሎ ጠራ ማለት ሳይሆን ለአምላክ የሚሰጠውን የአምልኮ ክፍል ለፍላጎቱ ቅድሚያ ሰጠ ማለት ነው፦
25፥43 ፍላጎቱን አምላኩ አድርጎ የያዘውን ሰው አየህን? አንተ በእርሱ ላይ ጠባቂ ትሆናለህን? أَرَأَيْتَ مَنِ اتَّخَذَ إِلَـٰهَهُ هَوَاهُ أَفَأَنتَ تَكُونُ عَلَيْهِ وَكِيلًا

የማርያምን አምላክ አርጎ መያዝ በዚህ ሒሳብ መረዳት ይቻላል። በተመሳሳይ ጳውሎስ፦ "ሆዳቸው አምላካቸው ነው" ብሏል፦
ፊልጵስዩስ 3፥19 መጨረሻቸው ጥፋት ነው፥ ሆዳቸው አምላካቸው ነው።

ያ ማለት ማለት ሆዳቸውን "አምላኬ" ብለው ጠሩ ማለት ሳይሆን ለአምላክ የሚሰጠውን የአምልኮ ክፍል ለሆዳቸው ቅድሚያ ሰጡ ማለት ነው፥ የማርያምን አምላክ አርጎ መያዝ በዚህ ስሌት መረዳት ይቻላል።
"እግዚእ ኦ" ማለት "ጌታ ሆይ! ማለት ሲሆን "እግዚእ ኦ" ተብሎ እና "አቤቱ" ተብሎ ሁሉም አቤቱታ የሚቀርብለት አምላካችን አሏህ ብቻ እና ብቻ ነው፥ ሐጃህ የሚሞላ የምጀንበት መጀን የእርሱ ስም ብቻ ነው። በዐበይት ክርስትና አምልኮተ ማርያም የተዘፈቃችሁ ካላችሁ ሞት ሳይመጣባችሁ አሊያም የፍርዱ ቀን ከመምጣቱ በፊት ወደ አሏህ በንስሓ ተመለሱ!
አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://www.tg-me.com/ወሒድ የንጽጽር ማኅደር/com.Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አንዱ በኮሜንት መጥቶ፦ "ትክክለኛው "ኩሪዬ ኤልይሶን" Κύριε ἐλέησον ወይም "ኪርዬ ላይሶን" ነው፥ ትርጉሙ በወንድ አንቀጽ "ጌታችን ማረን" ማለት ስለሆነ ለኢየሱስ እንጂ ለማርያም አይደለም" በማለት አስተያየቱን ሰጥቷል። ቅሉ ግን ከልጅነት እስከ ዕውቀት አብሮን ያደገው "ኪርያ ላይሶን" እየተባለ እንጂ "ኪርዬ ላይሶን" ሲባል አልሰማንም። ያያያዝኩትን ቪድዮ ስሙት!
በጉራጊኛ ደርሥ ተለቋል፦ https://www.tg-me.com/wahidcomguragiga/42
ጠባቂዎች

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

9፥116 ለእናንተም ከእርሱ በቀር ጠባቂም ረዳትም የላችሁም፡፡ وَمَا لَكُم مِّن دُونِ اللَّهِ مِن وَلِيٍّ وَلَا نَصِيرٍ

ማመናፈስ እና ማመቻመች የሚወዱ ሚሽነሪዎች ቀን ከሌሊት ወቃሽና ነቃሽ በመሆን ማኮሰስ እና ማራከስ ተያይዘውታል፥ የሃይማኖት ንጽጽር ላይ ያሉት ዐቃቢያነ እሥልምና ደግሞ የሚሽነሪዎችን የቆላ ሀሩር የደጋ ቁር ኢምንት እና ቀቢጽ ያክል ሳይቆጥሩ መልስ ይሰጣሉ። ከሚያንኳስሱትና ከሚያራክሱት ነገር መካከል፦ "ከአሏህ በቀር ጠባቂ የለም" ተብሎ በሌሎች አናቅጽ "መላእክት ጠባቂዎች ናቸው" መባላቸውን ነው። ይህንን የተውረግረገረገ መረዳት በሰከነ እና በሰላ አእምሮ እንየው፦
አምላካችን አሏህ ለአማንያን ጠባቂ ነው፥ ከእርሱ በቀር ጠባቂ የለም። ከእሳት ቅጣት የሚጠብቅ እርሱ ብቻ ነው፦
9፥116 ለእናንተም ከእርሱ በቀር ጠባቂም ረዳትም የላችሁም፡፡ وَمَا لَكُم مِّن دُونِ اللَّهِ مِن وَلِيٍّ وَلَا نَصِيرٍ
11፥113 ወደ እነዚያም ወደ በደሉት አትጠጉ፡፡ እሳት ትነካችኋለችና፡፡ ከአላህም ሌላ ጠባቂዎች የሏችሁም፡፡ ከዚያም አትረዱም፡፡ وَلَا تَرْكَنُوا إِلَى الَّذِينَ ظَلَمُوا فَتَمَسَّكُمُ النَّارُ وَمَا لَكُم مِّن دُونِ اللَّهِ مِنْ أَوْلِيَاءَ ثُمَّ لَا تُنصَرُونَ

"ከአላህም ሌላ ጠባቂዎች የሏችሁም" የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት! እሳት እንዳይነካን ከአሏህ ሌላ ጠባቂዎች የሉም። ቅሉ ግን አምላካችን አሏህ ለሰው ከክፉ የሚጠብቁት ተተካኪዎች መላእክት አድርጓል፦
13፥11 *"ለሰው ከስተፊቱም ከኋላውም በአላህ ትዕዛዝ ከክፉ የሚጠብቁት ተተካኪዎች መላእክት አሉት"*፡፡ لَهُ مُعَقِّبَاتٌ مِّن بَيْنِ يَدَيْهِ وَمِنْ خَلْفِهِ يَحْفَظُونَهُ مِنْ أَمْرِ اللَّهِ
86፥4 *"ነፍስ ሁሉ በእርሷ ላይ ጠባቂ ያለባት እንጅ ሌላ አይደለችም"*፡፡ إِن كُلُّ نَفْسٍ لَّمَّا عَلَيْهَا حَافِظٌ
6፥61 እርሱም ከባሮቹ በላይ ሲኾን ሁሉን አሸናፊ ነው፥ በእናንተም ላይ ጠባቂዎችን ይልካል፡፡ وَهُوَ الْقَاهِرُ فَوْقَ عِبَادِهِ ۖ وَيُرْسِلُ عَلَيْكُمْ حَفَظَةً

መላእክት ጠባቂ የተባሉበት አሏህ ጠባቂ በተባለበት ሒሣብ እና ቀመር በፍጹም እንዳልሆነ እሙን እና ቅቡል ነው። ምክንያቱም “መልአክ” مَلْأَك የሚለው ቃል “ለአከ” لَأَكَ ማለትም “ላከ” ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ተላላኪ” ማለት ነው፥ የመለክ ብዙ ቁጥር ደግሞ “መላኢክ” مَلَائِك‎ ወይም “መላኢካህ” مَلَائِكَة‎ ነው። እነዚህ የአሏህ መላእክት የተለያየ የሥራ ድርሻ ተሰቷቸው ይጠብቃሉ፦
72፥8 ‹እኛም ሰማይን ለመድረስ ፈለግን፡፡ ብርቱ ጠባቂዎችን እና ችቦዎችንም ተሞልታ አገኘናት፡፡ وَأَنَّا لَمَسْنَا السَّمَاءَ فَوَجَدْنَاهَا مُلِئَتْ حَرَسًا شَدِيدًا وَشُهُبًا
72፥27 ከመልክተኛ ለወደደው ቢኾን እንጅ ለሌላ አይገልጽም፡፡ እርሱም ከስተፊቱም ከስተኋላውም ጠባቂዎችን ያደርግለታል፡፡ إِلَّا مَنِ ارْتَضَىٰ مِن رَّسُولٍ فَإِنَّهُ يَسْلُكُ مِن بَيْنِ يَدَيْهِ وَمِنْ خَلْفِهِ رَصَدًا
ስለዚህ አሏህ "ጠባቂ" የተባለው በራሱ የተብቃቃ እና የባሕርይ ገንዘቡ"ontological term" ሲሆን መላእክት "ጠባቂዎች" የተባሉት የጸጋ እና የሹመት ጉዳይ"functional term" ነው። አንድ ስም ተመሳሳይ ቃል ቢኖረው እንኳን ተመሳሳይ አሳብ እና ትርጉም እንደሌለው ዕሙር እና ስሙር ነው፥ የአንድን ቃል አማራጭ ትርጉም የሚወስነው ቃሉ የሚገኝበት ዐረፍተ ነገር ወይም ዐውድ እንደ ሆነ እሙን ነው። መታየት ያለበት ቃሉ ሳይሆን ቃሉ የወከለው አሳብ፣ የአንቀጹን ምህዋር፣ አውታርና ምህዳር እንደሆነ ቅቡል ነው። ይህ እንዲገባችሁ ከባይብል አንድ ናሙና እንመልከት! ፈጣሪ ብዙ ቦታ፦ "ከእኔ በቀር ሌላ አምላክ የለም" ይላል፦
ኢሳይያስ 45፥22 እናንተ የምድር ዳርቻ ሁሉ እኔ አምላክ ነኝና፥ "ከእኔም በቀር ሌላ የለም"። פְּנוּ־אֵלַ֥י וְהִוָּשְׁע֖וּ כָּל־אַפְסֵי־אָ֑רֶץ כִּ֥י אֲנִי־אֵ֖ל וְאֵ֥ין עֹֽוד
ዘዳግም 32፥39 አሁንም እኔ ብቻዬን እኔ እንደ ሆንሁ፥ "ከእኔም በቀር አምላክ እንደሌለ" እዩ!።  רְא֣וּ ׀ עַתָּ֗ה כִּ֣י אֲנִ֤י אֲנִי֙ ה֔וּא וְאֵ֥ין אֱלֹהִ֖ים עִמָּדִ֑י אֲנִ֧י אָמִ֣ית וַאֲחַיֶּ֗ה מָחַ֙צְתִּי֙ וַאֲנִ֣י אֶרְפָּ֔א וְאֵ֥ין מִיָּדִ֖י מַצִּֽיל
ኢሳይያስ 45፥5 እኔ ያህዌህ ነኝ፥ ከእኔም ሌላ ማንም የለም። "ከእኔም በቀር አምላክ የለም"። אֲנִ֤י יְהוָה֙ וְאֵ֣ין עֹ֔וד זוּלָתִ֖י אֵ֣ין אֱלֹהִ֑ים אֲאַזֶּרְךָ֖ וְלֹ֥א יְדַעְתָּֽנִי

ኢሳይያስ 45፥22 ላይ "አምላክ" ለሚለው በዕብራይስጡ የገባው ቃል "ኤል" אֵ֖ל ሲሆን "ኤሎሃ" אלוהּ ለሚለው ቃል ምጻረ-ቃል ነው፥ ዘዳግም 32፥39 እና ኢሳይያስ 45፥5 ላይ  "አምላክ" ለሚለው በዕብራይስጡ የገባው ቃል "ኤሎሂም" אלהים ሲሆን "ኤሎሃ" אלוהּ ለሚለው ቃል ብዜት ነው። ከእርሱ በቀር ኤሎሂም ከሌለ መላእክት "ኤሎሂም" אלהים ተብለዋል፦
መዝሙር 97፥7 "አማልክትም" ሁሉ ስገዱለት።  הִשְׁתַּחֲווּ־לֹ֝ו כָּל־אֱלֹהִֽים
መዝሙር 8፥5 "ከአማልክትን" እጅግ ጥቂት አሳነስኸው። וַתְּחַסְּרֵ֣הוּ מְּ֭עַט מֵאֱלֹהִ֑ים
መዝሙር 138፥1 በአማልክት" ፊት እዘምርልሃለሁ። נגד אלהים אזמרך

እነዚህ ሦስት አናቅጽ ላይ "ኤሎሂም" כֵּֽאלֹהִ֔ים የተባሉት መላክእት ስለሆኑ ግሪክ ሰፕቱጀንት እና የዕብራውያን መልእክት ጸሐፊ፦ "መላእክት" ብለው በግልጽ አስቀምጠዋል። ጥያቄአችን፦ "ያህዌህ ከእኔ ሌላ ኤሎሂም የለም" ካለ ዘንዳ በሌሎች ጥቅሶች መላእክት ለምን ኤሎሂም ተባሉ? አዎ መልሱ፦ "መላእክት "አማልክት" የተባሉት ፈጣሪ "አምላክ" በተባለበት ስሌት እና ቀመር አይደለም" ከሆነ እንግዲያውስ መላእክት ጠባቂ የተባሉበት አሏህ ጠባቂ በተባለበት ሒሣብ እና ቀመር በፍጹም አይደለም። ተግባባን? አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://www.tg-me.com/ወሒድ የንጽጽር ማኅደር/com.Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
በወሒድ ዕቅበተ ኢሥላም ማኅበር ድረ ገጽ ላይ አዲስ የተለቀቁ 👇

1) አሏህ አንድ ነው
https://www.wahidislamicapologetics.org/አሏህ-አንድ-ነው/

2) የአሏህ ፍትሓዊነት
https://www.wahidislamicapologetics.org/የአሏህ-ፍትሓዊነት/

3) የጴጥሮስ መንበር
https://www.wahidislamicapologetics.org/የጴጥሮስ-መንበር/

✍️ወሒድ ዐቃቢ ኢሥላም

🌐 ወደ ድረ ገጹ ለመግባት
http://www.wahidislamicapologetics.org
በወሒድ ዕቅበተ ኢሥላም ማኅበር ድረ ገጽ ላይ አዲስ የተለቀቁ 👇


1) ገደቢስነት
https://www.wahidislamicapologetics.org/ገደቢስነት/

2) የኤፍራጥስ ወንዝ
https://www.wahidislamicapologetics.org/የኤፍራጥስ-ወንዝ/

3) ሙሥሊም
https://www.wahidislamicapologetics.org/ሙሥሊም/

🌐 ወደ ድረ ገጹ ለመግባት
http://www.wahidislamicapologetics.org
ባወቀ ኖሮ

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

8፥23 በውስጣቸውም ደግ መኖሩን አሏህ ባወቀ ኖሮ ባሰማቸው ነበር፡፡ ባሰማቸውም ኖሮ እነርሱ እውነትን የተው ኾነው በሸሹ ነበር፡፡ وَلَوْ عَلِمَ اللَّهُ فِيهِمْ خَيْرًا لَّأَسْمَعَهُمْ ۖ وَلَوْ أَسْمَعَهُمْ لَتَوَلَّوا وَّهُم مُّعْرِضُونَ

ኢሥላም እንደ ትቢያ በኖ እንደ ጢስ ተኖ እንዲጠፋላቸው የሚፈልጉ ሚሽነሪዎች እውነትን የመሸጥ እና የመሸቀጥ አባዜ የተጠናወታቸው ሰዎች እንጂ መስማት እና መስማማት ሞታቸው ነው። እነዚህ ባተሎ እና ዘባተሎ ሙግት የሚሟገቱ ተላላ እና ጽሉል ሰዎች "አሏህ ሁሉን ዐዋቂ አይደለም" ብለው ይህንን ጥቅስ ይጠቅሳሉ፦
8፥23 በውስጣቸውም ደግ መኖሩን አሏህ ባወቀ ኖሮ ባሰማቸው ነበር፡፡ ባሰማቸውም ኖሮ እነርሱ እውነትን የተው ኾነው በሸሹ ነበር፡፡ وَلَوْ عَلِمَ اللَّهُ فِيهِمْ خَيْرًا لَّأَسْمَعَهُمْ ۖ وَلَوْ أَسْمَعَهُمْ لَتَوَلَّوا وَّهُم مُّعْرِضُونَ

"በውስጣቸውም ደግ መኖሩን አሏህ ባወቀ ኖሮ" ማለት "አሏህ የሚያውቀው በውስጣቸው ክፉ መኖሩን ነው" ወይም "አሏህ የሚያውቀው በውስጣቸው ደግ አለመኖሩን ነው" ማለት ነው፥ ሙፈሢሮች ያስቀመጡልን "አሏህ ያላሰማቸው በውስጣቸውም ደግ አለመኖሩን ስለሚያውቅ ነው" በማለት ነው። "ለው" لَوْ የሚለው ሐርፉሽ ሸርጥ የመጣው በውስጣቸው ደግ አለመኖሩን ለማሳየት የገባ አጽንዖታዊ እና አንክሮታዊ ቃል ነው። ለምሳሌ፦ አንድ ነገርን አለመኖሩን ለማሳየት አጽንዖታዊ እና አንክሮታዊ ቃል መግባት በባይብልም የተለመደ ነው፦
ኢሳይያስ 44፥8 ከእኔ ሌላ አምላክ አለን? አምባ የለም፥ ማንንም አላውቅም። הֲיֵ֤שׁ אֱלֹ֙והַּ֙ מִבַּלְעָדַ֔י וְאֵ֥ין צ֖וּר בַּל־יָדָֽעְתִּי׃

"ማንንም አላውቅም" የሚለው ኃይለ ቃል ይሰመርበት! "ያዳአቲ" יָדָֽעְתִּי የሚለው ቃል "ያዳ" יָדַע ማለትም "አወቀ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "አውቃለው" ማለት ነው፥ "በል" בַּל־ የሚለው አፍራሽ ቃል ሲሆን "በል ያዳአቲ" בַּל־ יָדָֽעְתִּי ማለት "አላውቅም" ማለት ነው። "ማንንም አላውቅም" ሲል "ሁሉን ዐዋቂ" ከሚል ማንነቱ ጋር ይጋጫል? ወይስ "ማንንም አላውቅም" ሲል "አምልኮ የሚገባው አምላክ ከእኔ ውጪ የለም" ለማለት ፈልጎ ነው? አዎ! "አላውቅም" ሲል "የለም" ለማለት ከሆነ እንግዲያውስ አሏህ የሚያውቀው በውስጣቸው ክፉ መኖሩን ስለሆነ "ደግ በውስጣቸው የለም" ማለት ነው። ሌላ ምሳሌ፦
ሆሴዕ 8፥4 ለራሳቸው ነገሥታትን አነገሡ፥ ከእኔም ዘንድ አይደለም። አለቆችንም አደረጉ፥ እኔም አላወቅሁም። ለጥፋታቸውም ከብራቸውና ከወርቃቸው፤ ጣዖታትን ለራሳቸው አደረጉ። הֵ֤ם הִמְלִיכוּ֙ וְלֹ֣א מִמֶּ֔נִּי הֵשִׂ֖ירוּ וְלֹ֣א יָדָ֑עְתִּי כַּסְפָּ֣ם וּזְהָבָ֗ם עָשׂ֤וּ לָהֶם֙ עֲצַבִּ֔ים לְמַ֖עַן יִכָּרֵֽת׃

እስራኤላውያን ለራሳቸው አለቆች ሲያደርጉ ያህዌህ ስለማያውቅ "እኔም አላወቅሁም" ብሏል። "አላወቅሁም" ለሚለው የገባው ቃል "ቨሎ ያዳአቲ" וְלֹ֣א יָדָֽעְתִּי ሲሆን እርሱ ሳያውቅ እንዴት አንድ ድርጊት ይከናወናል? ሰካራም ሰው በስካር ውስጥ እያለ ሲጎስሙት ስለማይታወቀው የገባው ቃል በተመሳሳይ "በል ያዳአቲ" בַּל־ יָדָֽעְתִּי ነው፦
ምሳሌ 23፥35 መቱኝ፥ ያውም አልተሰማኝም፤
ጐሰሙኝ፥ "አላወቅሁምም"። መቼ እነሣለሁ? ደግሞ ጨምሬ እሻታለሁ ትላለህ። הִכּ֥וּנִי בַל־חָלִיתִי֮ הֲלָמ֗וּנִי בַּל־יָ֫דָ֥עְתִּי מָתַ֥י אָקִ֑יץ אֹ֝וסִ֗יף אֲבַקְשֶׁ֥נּוּ עֹֽוד׃

እንዲህ ዓይን ያስፈጠጠ እና ጥርስ ያገጠጠ ሐቅ ሲመጣ ሞንሟና እና ሸሞንሟና ከመሆን ይልቅ ተረጋግቶ የራስን መጽሐፍ መፈተሽ ይገባል! አየክ ጥቂት ኩርማ መረዳት በጥሪኝ እና በእፍኝ ቀድቶ እና ዘግኖ ማቅረብ ዕቅበተ ኢሥላም ላይ ለሚሠራ ሰው ኢምነት ነው። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://www.tg-me.com/ወሒድ የንጽጽር ማኅደር/com.Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
በወሒድ ዕቅበተ ኢሥላም ማኅበር ድረ ገጽ ላይ አዲስ የተለቀቁ 👇


1) የባሕርይ እናት
https://www.wahidislamicapologetics.org/የባሕርይ-እናት/

2)ታላቁ ገደል/

https://www.wahidislamicapologetics.org/ታላቁ-ገደል/

3) ተዋዱዕ

https://www.wahidislamicapologetics.org/ተዋዱዕ/

🌐 ወደ ድረ ገጹ ለመግባት
http://www.wahidislamicapologetics.org
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ለስዕል አትሰግዱምን?

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

41፥37 ሌሊትና ቀንም ፀሐይና ጨረቃም ከምልክቶቹ ናቸው፡፡ ለፀሐይና ለጨረቃ “አትስገዱ”፡፡ ለእዚያም ለፈጠራቸው ለአሏህ “ስገዱ” ፡፡ እርሱን ብቻ “የምታመልኩ” እንደ ኾናችሁ ”ለሌላ አትስገዱ”፡፡ وَمِنْ آيَاتِهِ اللَّيْلُ وَالنَّهَارُ وَالشَّمْسُ وَالْقَمَرُ ۚ لَا تَسْجُدُوا لِلشَّمْسِ وَلَا لِلْقَمَرِ وَاسْجُدُوا لِلَّهِ الَّذِي خَلَقَهُنَّ إِن كُنتُمْ إِيَّاهُ تَعْبُدُون

በግሪክ "ኢኮን" εἰκών በዕብራይስጥ “ኤሊል” אֱלִיל ማለት "ስዕል"image" ማለት ሲሆን በሰሌዳ ላይ በቀለም፣ በጠመኔ፣ በእርሳስ አለዚያም በሌላ ነገር ተስርቶ በዓይን በማየት የሚገነዘቡት የአንድ ማንነት ወይም ምንነት ምስል ነው። አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ በመጽሐፈ ሰዋሰው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ላይ ሥዕልን እንዲህ ይገልጹታል፦
ኪዳነ ወልድ ክፍሌ፤ መጽሐፈ ሰዋሰው ወግሥ ወመዝገበ ቃላት 673
"ስዕል ማለት በቁም መልክ፣ የመልክ ጥላ፣ ንድፍ፣ አምሳል፣ ንድፍ በውኃ፣ በመጽሔት፣ በጥልፍ፣ በስፌት ወይም በቀለም በወረቀት ገዝፎ ተጽፎ ከደብር፣ ከእብን፣ ከእጽ፣ ከማዕድን ታንጦ፣ ተቀርጦ፣ ተሸልሞ፣ አጊጦ የሚታይ የሚዳሰስ ነገር ነው፡፡"

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ በአንድ ትምህርቱ ላይ ዓይኑን በጨው አጥቦ "እኛ ለስዕል አንሰግድም" ብሎ ሽምጥጥ አርጎ ክዷል፥ በተግባር ለስዕል እየሰገዱ እና በትምህርታቸው ውስጥ ለስዕል መሰገድ እንዳለበት እያስተማሩ "አሞኛችሁ ዘንድ ዓይናችሁን ጨፍኑ"በማለት ተከታዩን ያሞኛል፦
ተአምረ ማርያም የዘወትር መቅድም ቁጥር 35-36 ገጽ 7
ግዕዙ፦
"ወቅድመ ስዕላ ስግዱ! ዘኢሰገደ ላቲ ይደምስስ እምቅዋሙ ወኢይትዐወቅ ዝግረ ስሙ። ወይበሉ መላእክተ ሰማይ ኲሎሙ አሜን"።

ትርጉም፦
"በስዕሏ ፊት ስገዱ! ለሥዕሏ ያልሰገደ ግን ከቆመበት ቦታ ይጥፋ! ስም አጠራሩ አይታወቅ። በሰማይ ያሉ መላእክትም ይደረግ ይሁን ይበሉ"።

"በስዕሏ ፊት ስገዱ! ለሥዕሏ ያልሰገደ ግን ከቆመበት ቦታ ይጥፋ" የሚል እያለ "እኛ ለስዕል አንሰግድም" ብሎ ማቄሉን እዛው የማያነቡትን ያቂል! በኦርቶዶክስ መምህራን "እኛ ለስዕል አንሰግድም" የሚል እንዲህ ዓይነት ለውጥ እንዴት ሊመጣ ቻለ? ሲባል መልሱ የሙሴ አምላክ ለሙሴ፦ "የተቀረጸም ምስል ወይም ሐውልት አታቁሙ፤ ትሰግዱለትም ዘንድ በምድራችሁ ላይ የተቀረጸ ድንጋይ አታኑሩ፣ የማናቸውንም ምሳሌ፥ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ፣ አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውምም” ብሎ አዞልታ፤ እንደውም መዝሙረኛው፦ "ለተቀረጸ ምስል የሚሰግዱ ሁሉ ይፈሩ" ስለሚል ነው፦
ዘሌዋውያን 26፥1 እኔ ያህዌህ አምላካችሁ ነኝና ለእናንተ ”ጣዖት አታድርጉ፥ የተቀረጸም ምስል ወይም ሐውልት አታቁሙ”፤ ትሰግዱለትም ዘንድ በምድራችሁ ላይ የተቀረጸ ድንጋይ አታኑሩ።
ዘጸአት 20፥4 በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር ”የማናቸውንም ምሳሌ፥ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ፤ አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውምም”*፤
መዝሙር 97፥7 ”ለተቀረጸ ምስል የሚሰግዱ ሁሉ፥ በጣዖቶቻቸውም የሚመኩ ይፈሩ፤ መላእክቱ ሁሉ ስገዱለት።

ሰው ለሠራው የእጅ ሥራ እንዴት ይሰገዳል? በኦርቶዶክስ፣ በካቶሊክ እና በአንግሊካን ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ለስዕል የጸጋ ስግደት ይሰገዳል፤ ልብ አድርግ የጸጋ ስግደት ስገዱ የሚል ትእዛዝ የለም። በተቃራኒው ለተቀረጸ ምስል "አትስገድላቸው" የሚል ትእዛዝ ቢኖር እንጂ። ይህንን አስፈሪ ወንጀል እያየ ወደ ክርስትና የሚገባ ሰው ቂል ካልሆነ ወይም በጥቅማ ጥቅም አሊያም በተቃራኒ ፆታ ፍቅር መነደፍ ካልሆነ በስተቀር አይሞክረውም። ይህንን ፍርድ እያወቀ ወደ ኢሥላም የማይመጣ በእሳት የሚጫወት ነው፦
41፥37 ሌሊትና ቀንም ፀሐይና ጨረቃም ከምልክቶቹ ናቸው፡፡ ለፀሐይና ለጨረቃ “አትስገዱ”፡፡ ለእዚያም ለፈጠራቸው ለአሏህ “ስገዱ” ፡፡ እርሱን ብቻ “የምታመልኩ” እንደ ኾናችሁ ”ለሌላ አትስገዱ”፡፡ وَمِنْ آيَاتِهِ اللَّيْلُ وَالنَّهَارُ وَالشَّمْسُ وَالْقَمَرُ ۚ لَا تَسْجُدُوا لِلشَّمْسِ وَلَا لِلْقَمَرِ وَاسْجُدُوا لِلَّهِ الَّذِي خَلَقَهُنَّ إِن كُنتُمْ إِيَّاهُ تَعْبُدُون

" እርሱን ብቻ የምታመልኩ እንደ ኾናችሁ ለሌላ አትስገዱ" የሚለው ኃይለ ቃል ይሰመርበት! በኢሥላም ፈጣሪ ከሆነው ከአንዱ አምላክ ከአሏህ ውጪ የሚሰገድለት ማንነት ሆነ ምንነት የለም። ስዕል የሰው እጅ ሥራ ነው፤ ለዚህ ግዑዝ ነገር የምትሰግዱ ካላችሁ ጊዜው ሳይረፍድ ወደ አሏህ በንስሓ ተመለሱ! ከአሏህ በቀር የምትጠሯቸው ሊረዷችሁ አይችሉም፤ እራሳቸውንም አይረዱምና፦
7፥197 እነዚያም ከእርሱ በቀር የምትጠሯቸው ሊረዷችሁ አይችሉም፤ እራሳቸውንም አይረዱም። وَٱلَّذِينَ تَدْعُونَ مِن دُونِهِۦ لَا يَسْتَطِيعُونَ نَصْرَكُمْ وَلَآ أَنفُسَهُمْ يَنصُرُونَ

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://www.tg-me.com/ወሒድ የንጽጽር ማኅደር/com.Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የሃይማኖት ንጽጽር ኮርስ

በወሒድ ዕቅበተ ኢሥላም ማኅበር"Wahid islamic apologetics society" 13ኛ ዙር የሙቃረናህ ደርሥ!

"ሙቃረናህ" مُقَارَنَة የሚለው ቃል "ቃረነ" قَارَنَ ማለትም "አነጻጸረ" ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "ንጽጽር" ማለት ነው፥ ሙቃረናህ የሃይማኖት ንጽጽር"Comparative Religion" ሲሆን በዱኑል ኢሥላም እና እና በክርስትና መካከል ያለው የሥነ መለኮት አንድነት እና ልዩነት እየተነጻጸረ የሚቀርብበት ጥናት ነው። ደርሡ (ትምህርቱ) የሚፈጀው 7 ወር ኢንሻሏህ ሲሆን ሁለት ተርም አለው።

፨ የመጀመሪያው ተርም ዐጽመ አሳብ በፈጣሪ እሳቦት ላይ የሚያውጠነጥነው፦
1.በነገረ ሥላሴ ጥናት"Triadogy"
2.በነገረ ክርስቶስ ጥናት"Christology"
3.በነገረ ማርያም ጥናት"Mariology"
4. በነገረ መላእክት ጥናት"angelology"
5. በነገረ ምስል ጥናት"Iconlogy" ላይ ነው።

፨ የሁለተኛው ተርም ዐጽመ-አሳብ በቅዱሳን መጽሐፍት ላይ የሚያውጠነጥነው፦
1.በአህሉል ኪታብ"People of the Book"
2.በመጽሐፍት"scriptures"
3. በመጽሐፍ አጠባበቅ"preservation"
4.በመጽሐፍት ልኬት"Standardization"
5. በባይብል ግጭት"Contradiction"
6. በኦሪት"Torah"
7. በወንጌል"Gospel" ላይ ነው።

አባሪ ኮርሶች፦
1. ዐቂዳህ"creed"
2. ሥነ ምግባር"ethics"
3. ሥነ አመክንዮ"logic"
4. ሥነ ልቦና"psychology"
5. ሥነ ቋንቋ"linguistics" ናቸው።

ለመመዝገብ ከታች የተዘረዘሩት አድሚናት በውስጥ ያናግሩ!
እኅት ጀሙቲ፦ http://www.tg-me.com/myprophet34
ወንድም አቡ ኑዓይም፦https://www.tg-me.com/arhmanu
እኅት ሰላም፦ http://www.tg-me.com/SeuweSe
አኅት ዘሃራ፦ https://www.tg-me.com/Zhara_mustefa
እኅት አበባ፦ http://www.tg-me.com/selemtewa

ቦታ ሳይያዝ ይመዝገቡ! መልካም የትምህርት ጊዜ ይሁንልዎ!
ወጀዛኩሙላህ ኸይራ!
የኒቂያ ጉባኤ

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

112፥3 «አልወለደም አልተወለደምም»፡፡ لَمْ يَلِدْ وَلَمْ يُولَدْ

ጥንት ላይ የነበሩ ነቢያት እንዲሁ ኢየሱስ እና ሐዋርያት አሓዳዊያን"Unitarian" የነበሩ ሲሆን ከሐዋርያት ኅልፈት በኃላ የተነሱ የቤተክርስቲያን አበው ደግሞ በሂደት "ክልዔታውያን"Binitarian" ነበሩ። ከክልዔታውያን አበው መካከል ጠርጡሊያኖስ"Tertullian" ስለ ወልድ ሲናገር እንዲህ ይለናል፦
"አብ አጠቃላይ ባሕርይ ነው፥ ነገር ግን ወልድ የአጠቃላዩ መገኘት እና ክፍል ነው"
(Against Praxeas (Tertullian), Chapter 9).

አንድ ሰው ሰውነቱ ከራሱ ጋር ኖሮ ኖሮ ልክ ሲወልድ አባት እንደሚባለው አንድ አምላክ አምላክነቱ ከራሱ ጋር ኖሮ ኖሮ ልክ ሲወልድ አብ ተባለ የሚል ትምህርት ያስተማረው ጠርጡሊያኖስ ዘካርቴጅ ነው፦
"ምክንያቱም አምላክ እንዲሁ አብ ነው፥ እንዲሁ ደግሞ እርሱ ፈራጅ ነው። ሁልጊዜም አምላክ በሆነው መሠረት ላይ ብቻ እርሱ ግን ሁልጊዜ አብ እና ፈራጅ አልነበረም፥ ከወልድ በፊት አብ ሊሆን አይችልም፤ እንዲሁ ከኃጢአት በፊት ፈራጅ ሊሆን አይችልም። ነገር ግን በእርሱ ዘንድ ኃጢአት ባልነበረበት እና እንዲሁ ወልድ ባልነበረበት ወቅት ጊዜ ነበር፥ የመጀመሪያው ጌታ ፈራጅ ሆኖ እና የኃለኛ አብ ሆኖ መመሥረት ነበር። በዚህ መንገድ እርሱ ጌታ ሊሆን ከነበረባቸው ነገሮች በፊት ጌታ አልነበረም፥ ነገር ግን እርሱ ግን ወደፊት በሆነ ጊዜ ብቻ ጌታ ሊሆን ነበር። ልክ እንደዚሁ እርሱ በወልድ አብ እንደ ሆነ በኃጢአትም ፈራጅ ሆነ።
Against Hermogenes (Tertullian) chapter 3

ተመልከቱ! አብ ያለ አባትነት ከፍጥረት በፊት ወልድን እስከሚወልድበት ጊዜ ብቻውን በአምላክነት ነበር የሚለው እሳቤ የጠርጡሊያኖስ እሳቤ ነው፦
"ከፍጥረት በፊት እስከ ወልድ ውልደት ነበረ፥ ከሁሉ ነገር በፊት አምላክ ብቻውን ነበረ"።
Against Praxeas (Tertullian) Chapter 5.

በዚህ ወቅት የትርጓሜ ትምህርት ቤት"School of Thought" በእስክንድሪያ እና በአንጾኪያ ነበር፥ የእስክንድሪያን ትምህርት ቤት በአፍላጦን"Plato" ፍልስፍና ሰርጎገብ መሠረት ያረገ ሲሆን የአንጾኪያው ትምህርት ቤት ደግሞ በአሪስጣጣሊስ"Aristotle" ፍልስፍና መሠረት ያረገ ነው። በእስክንድሪያ ትምህርት ቤት ይማር የነበረው አትናቴዎስ ዘእስክንድሪያ "ከአምላክ አምላክ ተወለደ" የሚል አቋም ሲኖረው በአንጾኪያ ትምህርት ቤት ይማር የነበረው አርዮስ ዘሊቢያ "ከአምላክ አምላክ ተፈጠረ" የሚል አቋም ነበረው፥ አርዮስ ዘሊቢያ ስለ አቋሙ እንዲህ ይለናል፦
"አብ ወልድን ከወለደው የተወለደው መጀመሪያ ነበረው፥ ከዚህም ክስተት የተነሳ ልጁ ያልነበረበት ጊዜ እንደ ነበረ ግልጥ ነው። ስለዚህም እርሱ [ወልድ] ምንነቱ ካለመኖር እንደ ነበረው ነው"።
(Socrates of Constantinople, Church History, Book I, Ch. 5.)

በሁለቱ ውዝግብ የመጀመሪያው ዓለም ዓቀፍ ሲኖዶስ በኒቂያ ተካሄደ፥ "ሲኖዶስ" σύνοδος ማለት "ጉባኤ" "ስብሰባ"council" ማለት ነው። ኒቂያ፣ ቆስጠንጢኒያ፣ ኤፌሶን እና ኬልቄዶን በጥንት ጊዜ ቱርክ ውስጥ የሚገኙ ከተሞች ናቸው። በ325 ድኅረ ልደት በንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ሊቀ መንበርነት የኒቂያ ጉባኤ ላይ 318 ኤጲጵ ቆጶሳት ከመላው ዓለም ተሰብስበው "ሆሙኡሲዮስ" እና "ሆሞኡሲዮስ" የሚባሉ ክርክሮችን ለመታደም መጡ፥ "ሆሙኡሲዮስ" ὅμοιοιούσιος የአርዮስ አቋም ሲሆን "ሆሞኡሲዮስ" ὁμόιοιούσιος ደግሞ የአትናቴዎስ አቋም ነው።
"ኡሲያ" οὐσία የሚለው ቃል "ኤይሚ" εἰμί ማለትም "ነኝ" ከሚል አያያዥ ግሥ የተገኘ ሲሆን "ህላዌ" "ሃልዎት" "ኑባሬ" የሚል ትርጉም አለው፥ "ሆሙስ" ὅμοιος ማለት "የተለያየ" ማለት ሲሆን "ሆሞስ" ὁμός ማለት ደግሞ "ተመሳሳይ" ማለት ነው።

፨አርዮስ፦ "ወልድ ፍጡር ነው፥ አንዱ አምላክ አብ እና ኢየሱስ "ሆሙኡሲዮስ" ὅμοιοιούσιος ማለትም "የተለያየ ህላዌ" እንጂ ተመሳሳይ አይደለም" በማለት ኢየሱስ "ሆሙኡሲዮን ቶ ፓትሪ" ὅμοούσιον τῷ Πατρί ማለት "ከአብ ጋር የተለያየ ህላዌ ነው" የሚል አቋም ነበረው።
፨አትናቴዎስ፦ "ወልድ ፍጡር አይደለም፥ አንዱ አምላክ አብ እና ኢየሱስ "ሆሞኡሲዮስ" ὁμόιοιούσιος ማለትም "ተመሳሳይ ህላዌ" እንጂ የተለያየ አይደለም" በማለት ኢየሱስ "ሆሞኡሲዮን ቶ ፓትሪ" ὁμόούσιον τῷ Πατρί ማለት "ከአብ ጋር ተመሳሳይ ህላዌ ነው" የሚል አቋም ነበረው።
ጉባኤው የማታ ማታ ኢየሱስ "ቴዎን ኤክ ቴዉ" Θεὸν ἐκ Θεοῦ ማለትም "ከአምላክ የተገኘ አምላክ ነው" በማለት አጸደቀ፥ "አምላክ አምላክን አህሎ እና መስሎ፣ ከባሕርይ ባሕርይ ወስዶ፣ ከአካል አካል ወስዶ ተወለደ" በማለት "ሆ ቴዎስ ሆ ሁዎስ" Ο Θεός ο γιος ማለትም "እግዚአብሔር ወልድ"God the Son" የሚል የአቋም መግለጫ ተሰጠ።

ከዚህ ጉባኤ ተነስተን ጥያቄ እናጭራለን፦
፨በኒቂያ ጉባኤ ድንጋጌ ላይ አምላክ አምላክን ከወለደ ሁለት አምላክ አይሆንም?
፨አምላክ አምላክን አስገኘ የሚለው ትምህርት ሕሊናስ ይቀበለዋልን?
፨ማስገኘት መንስኤ መገኘት ውጤት ከሆነ መቀዳደም ስላለ ጅማሮ እና መነሾ ያለው አምላክ ምን ዓይነት አምላክ ነው?

ይህ የነገረ ክርስቶስ"Christology" ውዝግብ ጠመዝማዛ መንገዱ የጀመረው ከዚህ ጉባኤ ጀምሮ ነው። አንብሮስ ዘሚለን "አብ የወልድ ኑባሬ ምንጭ እና ሥር ነው"ይለናል፦
"አብ የወልድ ኑባሬ ምንጭ እና ሥር ነው"
Exposition of the Christian Faith (Ambrose) > Book IV(4) Chapter 10 Number 133

አብ አስገኚ ወልድ ግኝት ከሆነ በመስኤ እና በውጤት በመካከላቸው መቀዳደም አለ፥ ዛሬ ላይ ዐበይት ክርስቲያኖች፦ "ወልድ ከአብ ባሕርይ ባሕርይን ወስዶ፣ ከአካሉ አካልን ወስዶ እና አብን አህሎና መስሎ ከእርሱ ወጣ፣ ተወለደ፣ ተገኘ" በማለት አሏህን ወላዲ መሢሑን ተወላዲ በማድረግ ለአሏህ ቁራጭን አደረጉለት፦
43፥15 ከባሮቹም ለእርሱ ቁራጭን ልጅ አደረጉለት፡፡ ሰው በእርግጥ ግልጽ ከሓዲ ነው፡፡ وَجَعَلُوا لَهُ مِنْ عِبَادِهِ جُزْءًا ۚ إِنَّ الْإِنسَانَ لَكَفُورٌ مُّبِينٌ

ከአንዱ አምላህ ባሕርይ ባሕርይን ወስዶ፣ ከአካሉ አካልን ወስዶ፣ እርሱን አህሎና መስሎ ከእርሱ ወጣ፣ ተወለደ፣ ተገኘ ማለት የአምላክን አንድነት ክፉኛ የሚያናጋ ትምህርት ነው። በዚህ ውዝግብ ጊዜ አምላካችን አሏህ እነዚያን «አሏህ ልጅን ወልዷል» ያሉትን ሊያስጠነቅቅበት ቁርኣንን አወረደው፦
18፥4 እነዚያንም «አሏህ ልጅን ወልዷል» ያሉትን ሊያስጠነቅቅበት አወረደው፡፡ وَيُنذِرَ الَّذِينَ قَالُوا اتَّخَذَ اللَّهُ وَلَدًا

አምላካችን አሏህ አንድ ነው፥ እርሱ የሁሉ መጠጊያ ነው። አምላክ ከወለደ ይባዛል፥ ከተወለደ በአጭር ቁመት በጠባብ ደረት ይወሰናል፣ ያድጋል፣ ይሞታል። አሏህ ግን አንድ ነውና አልወለደም አልተወለደምም፦
112፥1 በል «እርሱ አላህ አንድ ነው፡፡ قُلْ هُوَ اللَّهُ أَحَدٌ
112፥2 «አሏህ የሁሉ መጠጊያ ነው»፡፡ اللَّهُ الصَّمَدُ
112፥3 «አልወለደም አልተወለደምም»፡፡ لَمْ يَلِدْ وَلَمْ يُولَدْ

አሏህ መውለድ መወለድ የሚባል ባሕርይ ስለሌለው ብጤ፣ አምሳያ፣ ተፎካካሪ፣ እኩያ፣ ወደር፣ እኩያ አንድም የለውም፦
114፥4 «ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም»። وَلَمْ يَكُن لَّهُ كُفُوًا أَحَدٌ

"ኩፉው" كُفُو ማለት "ወደር" "እኩያ" "አቻ" "ብጤ" "አምሳያ" "ተፎካካሪ" "ባላንጣ" ማለት ሲሆን እርሱ የሚተካከለው አቻ እና እኩያ እንዲሁ የሚመሳሰለው አምሳያ እና ቢጤ ከሌለው «አሏህ ወለደ» ያሉት እነርሱ በእርግጥ ውሸታሞች ናቸው፦
37፥152 «አሏህ ወለደ» አሉ፥ እነርሱም በእርግጥ ውሸታሞች ናቸው፡፡ وَلَدَ اللَّهُ وَإِنَّهُمْ لَكَاذِبُونَ

ክርስቲያኖች ሆይ! ከዚህ ውስብስብ ትምህርት ወጥታችሁ በአንድነት ላይ ሁለትነት፣ መከፋፈል፣ መባዛት የሌለበትን አንዱን አምላክ አሏህን በብቸኝነት እንድታመልኩት ጥሪያችን ነው። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://www.tg-me.com/ወሒድ የንጽጽር ማኅደር/com.Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
የቆስጠንጢኒያ ጉባኤ

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

5፥75 የመርየም ልጅ አል መሢሕ ከበፊቱ መልእክተኞች በእርግጥ ያለፉ የኾነ መልእክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ مَّا الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ إِلَّا رَسُولٌ قَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِهِ الرُّسُلُ

ቆስጠንጢኖስ ከአባቱ ከንጉሥ ቊንስጣ እና ከእናቱ ከንግሥት እሌኒ 272 ድኅረ ልደት ተወልዶ በ306 ድኅረ ልደት የምዕራቡ የሮም ግዛት ንጉሠ ነገሥት ሆነ፥ በ313 ድኅረ ልደት ለክርስትና ሃይማኖት ዕውቅና የሰጠ ሲሆን በ 325 ደግሞ የኒቂያ ጉባኤ ሊቀ መንበር በመሆን መራ።
ቆስጠንጢኖስ የፀሐይ አምልኮ አምላኪ ስለነበር እሑድን የፀሐይ ቀን"sun day" በማድረግ ሰንበትን ከሰባተኛው ቀን ወደ መጀመርያው ቀን አሸጋገረ፥ ይህ ንጉሠ ነገሥት መስቀልን የጦር ሠራዊቱ ዓርማ አድርጎ ይጠቀምበት ጀመር።
ቆስጠንጢኖስ ክርስትናን የተቀበለው ቀደም ሲል ቢሆንም የተጠመቀው ግን ሊሞት ገደማ ነው፥ እርሱ ቱርክ የምትገኘውን ከተማ በ 330 ድኅረ ልደት "ቆስጠንጢኒያ" በማለት ከቆረቆረ በኃላ በ 337 ድኅረ ልደት ሞቷል።

ከቆስጠንጢኖስ ሞት በኃላ በ381 ድኅረ ልደት በንጉሥ ቀዳማይ ቴዎዶስዮስ ሊቀ መንበርነት የቆስጠንጢኒያ ጉባኤ ላይ 150 ኤጲጵ ቆጶሳት ከመላው ዓለም ተሰብስበው የሎዶቂያው ኤጲስ ቆጶስ አቡሊናርዮስ እና የቆስጠንጢኒያ ኤጲስ ቆጶስ መቅደንዮስ ያነሱትን ሙግት ለመታደም መጡ።
፨አቡሊናርዮስ፦ "ኢየሱስ ሥጋ እንጂ ነፍስ የለውም፥ በነፍስ ፋንታ መለኮት ተተክቷል። አብ እና ወልድ በውጫዊ ግብር"outward function" ወይም በምጣኔ ግብር"economic function" ይለያያሉ፥ አብ ላኪ ወልድ ተላኪ በመሆን የተለያየ የሥራ ድርሻ አላቸው" በማለት ሙግቱን አቀረበ።
፨መቅደንዮስ፦ "መንፈስ ቅዱስ የአምላክ እስትንፋስ እና ኃይል እንጂ እራሱን የቻለ አካል እና አምላክ አይደለም" በማለት ሙግቱን አቀረበ።

ጉባኤው "ኢየሱስ እራሱ የቻለ የሰው ነፍስ አለው" በማለት እና "አብ እና ወልድ በውጫዊ ግብር አንድ ግብር እና ፈቃድ አላቸው" በማለት አቡሊናርዮስን አወገዙት። እንዲሁ፦ "መንፈስ ቅዱስ እራሱ የቻለ አካል እና አምላክ ነው" በማለት መቅደንዮስን አወገዙት።
"መንፈስ ቅዱስ "ሆ ቴዎስ ሆ ኑማ ቶ ሐጊዎን" Ο Θεός ο Πνεῦμα τὸ Ἅγιον ማለትም "እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ"God the Holy Spirit" በማለት አጸደቁ፥ በተጨማሪም ኢየሱስን፦ "ቶን ኤክ ቶዩ ፓትሮስ ጌኒቴንታ ፕሮ ፓንቶን ቶን ኣይኦኖን τὸν ἐκ τοῦ Πατρὸς γεννηθέντα πρὸ πάντων τῶν αἰώνων ማለትም "ከአብ ከዘመናት በፊት የተወለደ" ወይም በአገራችን "ዓለም ሳይፈጠር እና ዘመን ሳይቆጠ ከአብ ያለ እናት ተወለደ" በማለት የአቋም መግለጫ ተሰጠ።

ከዚህ ጉባኤ ተነስተን ጥያቄ እናጭራለን፦
፨በቆስጠንጢኒያ ጉባኤ አንድ መለኮት የአብ ገንዘብ ሲሆን ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ ከእርሱ ይጋራሉ ማለት ወልድ እና መንፈስ ቅዱስ ከአብ ውጪ ከሆኑ ሌላ መለኮት አይሰኙምን?
፨አንዱ አምላክስ አምላክነትን ከእርሱ ሌላ ያጋራልን? ፨በውጫዊ ግብር አብ እና ወልድ የየራሳቸው የሥራ ድርሻ ከሌላቸው እና በውጫዊ ግብር አንድ ግብር ካላቸው ወልድ ሲላክ አብም ተልኳልን? ወልድ ሲወለድ አብ ተወልዷልን?
፨እንደ እናንተ ትምህርት በብሉይ ወልድ መልአክ እየሆነ ሲላክ ወይም መንፈስ ቅዱስ ሲላክ አብም ተልኳልን?
፨ዓለም ሳይፈጠር የተወለደው የአብ ልጅ ለማርያም የባሕርይ ልጇን ነውን? ከእርሷ ተገኝቷልን?
የማርያም ልጅ ፍጡሩ ለአብ የባሕርይ ልጁ ነውን? ያ ፍጡር ከአብ ተገኝቷልን?

የ 325 የኒቂያ ጉባኤ "ኢየሱስ ከአምላክ የተገኘ አምላክ ነው" የሚለው ትምህርት አቡሊናርዮስ፦ "ኢየሱስ ሥጋ እንጂ ነፍስ የለውም፥ በነፍስ ፋንታ መለኮት ተተክቷል" የሚለውን ውሳኔ ገፋፍቶታል። "ኢየሱስ ሙሉ ሰው ነው" የሚለው ደግሞ ንስጥሮስ ላይ ተጽዕኖ አርጎበታል፥ በኤፌሶን ጉባኤ ኢንሻላህ እናያዋለን። የመርየም ልጅ አልመሢሕ ከበፊቱ መልእክተኞች በእርግጥ ያለፉ የኾነ መልእክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፦
5፥75 የመርየም ልጅ አል መሢሕ ከበፊቱ መልእክተኞች በእርግጥ ያለፉ የኾነ መልእክተኛ እንጅ ሌላ አይደለም፡፡ مَّا الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ إِلَّا رَسُولٌ قَدْ خَلَتْ مِن قَبْلِهِ الرُّسُلُ

ክርስቲያኖች ሆይ! ከዚህ ውስብስብ ትምህርት ወጥታችሁ በአንድነት ላይ ሁለትነት፣ መከፋፈል፣ መባዛት የሌለበትን አንዱን አምላክ አሏህን በብቸኝነት እንድታመልኩት ጥሪያችን ነው። አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://www.tg-me.com/ወሒድ የንጽጽር ማኅደር/com.Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም
በሽታ ከሰው ወደ ሰው እንደሚጋባ ሁሉ ጤንነትም ከሰው ወደ ሰው ይጋባል። ጤናማ አስተሳሰብ ካላቸው ሰዎች ጋር መዋል ጤናማ አስተሳሰብ እንድንይዝ ያረገናል። ሰው የአስተሳሰብ እና የድርጊት ውጤት ነው።

የአስተሳሰብ ውጤት
ሰው ለራሱ እራሱ የሚሰጠው እና የሚነገረው ነገር ያ ማንነቱ ነው። ወሒድ ማለት ወሒድ ለወሒድ የነገረው ነገር ነው። ለራሴ እችላለው፣ እሞክራለው፣ እጎብዛለው ብዬ ካልኩት እችላለው፣ እሞክራለው፣ እጎብዛለው፥ በተቃራኒው ለራሴ አትችልም፣ አረባም፣ ደካማ ነኝ ካልኩት እራሴ የማይችል፣ የማይረባ እና ደካማ እሆናለው።

የድርጊት ውጤት
ሰው አስተዳደጉ እና አዋዋሉ በሕየወቱ ላይ አውንታዊ ሆነ አሉታዊ ተጽእኖ ማድረግ ይችላል። ልጆቻችንን በጥሩ አስተዳደግ ማሳደግ እና አዋዋላቸውን ማሳመር አለብን! ይህ ትውልድን የመቅረጽ መርሓ ግብር ለትውልድ የሚሆን መደላድል ነው።

ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://www.tg-me.com/ወሒድ የንጽጽር ማኅደር/com.Wahidcom
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አሥ ሠላም ዐለይኩም ያ ጀመዓህ!

ወሒድ ዕቅበተ ኢሥላም ማኅበር ይህንን የሃይማኖት ንጽጽር መተግበሪያ"application" ለሕዝበ ሙሥሊሙ አዘጋጅቷል። በገጠር አውታረ መረብ"network" የሌላቸው እና በከተማ የአውታረ መረብ ችግር ያለባቸው ያለ አውታረ መረብ ይህንን መተግበሪያ በማውረድ መጠቀም ይችላሉ። አውርደው በውስጡ ያለውን ርእሰ ጉዳይ እንዴት መጠቀም እንዳለብዎ እዚህ ላይ የተቀመጠውን ቪድዮ ይመልከቱ!
ሁላችንም በፓስት፣ በኮሜት፣ በራሳችሁ የጊዜ መስመር"timeline" ሼር በማድረግ የአጅሩ ተካፋይ መሆን ይችላሉ።
ወጀዛኩሙላህ ኸይራ!
Check out "Wahid Islamic Apologetics"
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.hexlabs.wahid.islamicapologetics
2024/06/18 05:27:42
Back to Top
HTML Embed Code: