"ያሳዝናል! ነገሩ የተወሰኑ ቀናት ይሆንና ያልፋል ብዬ አስቤ ነበር። ግን ህይወቴ ሆነ።" ዱስቶቪስኪ
አንዳንዴ… ብዙም የማንኖርባቸውና መሻገሪያችን የሚመስሉን ነገሮች ራሳቸው መዳረሻችንም ይሆናሉ። ድንገት የተፈጠሩ ናቸው እንልና ዝንተዓለሙን እነርሱ ውስጥ እንኖራለን። ለተወሰኑ ቀናት አስበን እንጀምራቸውና የህይወታችን ክፍል ሆነው ይቆያሉ። የጓደኝነት ህይወት፣ የስራ ዓይነትና ወይም ለሆነ ችግር መፍትሄ ያደረጋችሁትን አስቡ። ብዙዎች ለሆኑ ቀናት መታለፍ የተጀመሩ ናቸው፣ አሁን ግን ህይወት ሆነዋል።
@Fuad kheyredin
@Qteloch
፨ Join ፨
@qteloch

"ውብ ቃላቶችን አትመኑ። እውነቱን ከክስተቶች አንደበት ውሰዱ።" ነጂብ መህፉዝ
አንዳንዶቹ ሲያደንቁህ ከሰማይና ከጨረቃ ውበት ጋር ያመሳስሉሃል፣ ውዴታቸውን ሲገልፁልህ ደግሞ ላንተ መስዋዕት እስከመሆን ያዘልቁሃል። ያ ሁሉ የቃል ውዳሴና ውዴታ በፈታኝ ተግባር ውስጥ ግን ኦና ይሆናል። ሁሌም ከጎንህ እንደሆኑ ቢነግሩህም ሲፈልጉህ እንጂ በቁም ነገር ስትፈልጋቸው አታገኛቸውም። ክስተቶች እውነትን ይገልጣሉ። በቃላት የተከሸኑ ውዴታዎችም በአንድ ወቅት በተግባር ይፈተናሉ።
@qteloch
፨Join it፨

Forwarded from Fuad kheyredin
ከወደዱ…
(ፉአድ ኸይረዲን)
ጨረቃን ናፋቂ አይሸሽም ጨለማን
ብርሃን ፈላጊ፣
ትቀልጣለች ብሎ አይተዋትም ሻማን።
ወዳጅ የተባለ…ውበት ተመልክቶ፣
እሾሁን አይፈራም ፅጌሬዳን ሽቶ።
የተሸነፍክ እንደው
ለሀሳብ እምነቷ ለፀባይዋም ጭምር
ስለቁንጅናዋም ባድናቆትህ ዘምር
ምሉዕ ነገር …
በሰውኛ አዳራሽ
አይገኝም ጭራሽ!
@qelemmrko
(ፉአድ ኸይረዲን)
ጨረቃን ናፋቂ አይሸሽም ጨለማን
ብርሃን ፈላጊ፣
ትቀልጣለች ብሎ አይተዋትም ሻማን።
ወዳጅ የተባለ…ውበት ተመልክቶ፣
እሾሁን አይፈራም ፅጌሬዳን ሽቶ።
የተሸነፍክ እንደው
ለሀሳብ እምነቷ ለፀባይዋም ጭምር
ስለቁንጅናዋም ባድናቆትህ ዘምር
ምሉዕ ነገር …
በሰውኛ አዳራሽ
አይገኝም ጭራሽ!
@qelemmrko
Forwarded from Fuad kheyredin (Fuad Kheyredin)
የምትሰራውን ስራ ፅድቅ እንደሆነ ለማብራራት አትሞክር። እነርሱ የማያምፁ የሰባተኛው ሰማይ መልዓክት አይደሉም፣ ከእግሮቻቸው ስርም ገነት የለም። መስራት ያለብህን ብቻ ስራ… በልብህ ሚዛን፣ በእምነትህ መለኪያ!
@qelemmrko
@qelemmrko
@qelemmrko
@qelemmrko
Forwarded from Fuad kheyredin (Fuad Kheyredin)
ተፈጥሮ ሆኖ
ብገረምብሽ ባደንቅ መልክሽን
አስተውላለሁ
"ምግባር" የሚሉት የሰው ልክሽን።
ይቻለኛል ወይ?
አንቺን ደፍቼ መልክሽን መዝገን
አይሻልም ወይ?
ከማይፈርስ ውበት ሄዶ መወገን።
የሚያኖረን ምግባር
እርሱን ማመስገን
በርሱ መመስገን።

በፍቅር ውዱዕ
ናፍቆት ሲያቆመው ከስግደቱ በር
"ምን ቸግሮት ነው" የሚልም ነበር
አወይ ሰው መሆን…
አወይ መወጠር
እንዲህ መጠርጠር።
ያንዳንዱ ባሪያ ከፈጣሪው ጋር የያዘው ፍቅር
በችግር እንጂ ለማይመጣ ሰው ያሰኛል "ይቅር"።
"ምን ቸግሮት ነው?"

አንዳንዴ የሚያስፈልግህ ዣንጥላ የሚሰጥህ ሰው ሳይሆን አብሮህ የሚበሰብስ ሰው ነው… ስሜትን የመጋራት ሜዳ ከመስጠት ሜዳ ይበልጣል።
@Fuadkheyr
@Fuadkheyr
Forwarded from Fuad kheyredin (Fuad Kheyredin)
ዝንተዓለሙን ምርጥ የሆነ ሰው አይገኝም። በባህሪው ምሉዕ የሚባል ፍጡርም የለም። እዚህ… የሚሞላ ክፍት ቦታና የሚታከም ህመም አለ። እዚያ ደግሞ… የሚደበቅ ነውርና የሚሰረዝ ጥፋት አለ… አብሮ ለመኖር ስንል። መተራረም እንደሚያስተካክለን ሁሉ… መተላለፍም ፍቅራችንን ያቆየዋል… ሳይበዛ።
@Fuadkheyr
@Fuadkheyr
Forwarded from Fuad kheyredin (Fuad Kheyredin)
የሰው ልጅ በከባዱ የሚፈተነው… መሻቱን በተቃረኑ የአላህ ውሳኔዎች ውስጥ ነው። ሳይፈልጋቸው እንዲሆን በሚገደድባቸው ሁኔታዎች ውስጥ በከባዱ ይፈተናል። ውስጡ ይንቀጠቀጣል። ከልቡ ጋር ትግል ገጥሞ ለማረጋጋት ይሞክራል። ግን ግን… የምር የሆነ ኢማን እዚህ ቦታ ነው ያለው… የአላህን መሻት ወዶ መቀበል ጋር!!
@Fuadkheyr
@fuadkheyr
@Fuadkheyr
@fuadkheyr