tg-me.com/yenetube/54503
Last Update:
የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር በይፋዊ የ X ገፁ ላይ በትግርኛ ካሰራጨው በቀጥታ ተተርጉሞ የተወሰደ ነው።
"ኢትዮጵያ ካላት ጂኦ-ፖለቲካዊ እና ስልታዊ ጠቀሜታ፣ የህዝብ ብዛት እና ተፅዕኖ የተነሳ በአፍሪካ ቀንድ ጠቃሚ ሀገር መሆኗ ጥርጥር የለውም።
እስካሁን ኢትዮጵያ የምትመራው ከአፄ ምኒልክ ጀምሮ በአምስተኛው መንግሥት ነው።
ይሁን እንጂ በተለይ በብልጽግና ፓርቲ አገዛዝ ሥር ከወደቀች በኋላ ታይቶ በማይታወቅ ትርምስ ውስጥ ገብታለች።
ስለሆነም የኢትዮጵያ ዜጎች የሀገራቸው ሉዓላዊነት ሲደፈርስ እና አንድነታቸው መደፍረሱ በእጅጉ ያሳስባቸዋል።
በአሁኑ ወቅት የችግሩ ብቸኛ መፍትሄ ሁከት ነው ብለው በማመን በትጥቅ ትግል የሚካፈሉ ወገኖች በሁሉም የኢትዮጵያ ክፍሎች አሉ።
ከ2020-2022 ከባድ ጦርነት በኋላ ኢትዮጵያዊነቱ ወደ ኋላ የቀረ የትግራይ ህዝብ የኢትዮጵያ አካል በመሆንም ሆነ በሌላ መንገድ ሰላምና ደህንነትን ይናፍቃል።
በአማራ ክልል ህዝቡ በመንግስታቸው ላይ እምነት አጥቶ ሰብአዊ መብቱንና ሀገራዊ ክብሩን ማስከበር ብቸኛ አማራጭ አድርጎታል፣የኦሮሚያ ብልፅግና ፓርቲም ከጥይት ድምጽ አልወጣም።
የብልፅግና መንግስት በዋና ከተማው (በአዲስ አበባ) ብቻ ተወስኖ በህገ መንግስቱ ስም እየዘፈነ ያሉትን ችግሮች ችላ ማለትን የመረጠ ይመስላል።
እንደውም በኢትዮጵያ ያለውን የፖለቲካ እና የጸጥታ ሁኔታ ለመፍታት ብስለትና ብቃት ያለው አይመስልም። ኢትዮጵያውያን በመንግስታቸው ጅልነት እንዲህ ያለ ያልተረጋጋ አካባቢ መጋፈጣቸው በእውነት ያሳዝናል። በኢትዮጵያ ያለው የፖለቲካ እና የጸጥታ ሁኔታ በተፈጥሮው ለዜጎቿ ብቻ ሳይሆን ለመላው የአፍሪካ ህዝብ እና ከዚያ እስከ የኢትዮጵያ ዳር ድንበር ድረስ አሳሳቢ ነው።
በአራት መንግስታት (በምኒልክ፣ በሃይለስላሴ፣ በደርግ እና በኢህአዴግ) ሉዓላዊነቷን እና አንድነቷን ያስጠበቀችው የኢትዮጵያ ጂኦፖለቲካል ቅርፅ አሁን ላይ ያለው ሁኔታ ብዙዎችን ያሳስባቸዋል" ይላል።
የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስቴር ኢትዮጵያን በተመለከተ ተመሳሳይ ትንተና እንደሚያቀርብ እና ቀጣይነት እንዳለው ገልጿል።
መንግሥት ሰሞኑን ኤርትራ እያራመደችሁ ያለውን ተከታታይ ዘለፉን በተመለከተ ምላሽ ከመስጠት ተቆጥቧል።
@Yenetube @Fikerassefa
BY YeneTube
Warning: Undefined variable $i in /var/www/tg-me/post.php on line 283
Share with your friend now:
tg-me.com/yenetube/54503