Telegram Group & Telegram Channel
በወንጀል የተገኘ ንብረት ህጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣው አዋጅ ከፍርድ ቤት ፍቃድ ውጪ የሚደረግ ምርመራን እንደማይፈቅድ የፍትህ ሚኒስቴር ተናገረ፡፡

የፍትህ ሚኒስቴር ይህን የተናገረው ባለፈው ሰኔ 10 ቀን በህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ባጸደቀው በወንጀል የተገኘ ንብረት ሕጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ተሻሽሎ የቀረበውን አዋጅ ይዘት በተመለከተ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ነው፡፡መስሪያቤቱ አዋጁን አንዳንዶች የተረዱበት መንገድ ልክ አይደለም ብሏል፡፡

ስለ አዋጁ ማሻሽያ፣ ይዘት እና ምንነት ማብራርያ የሰጡት የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን አማረ ኢትዮጵያ በወንጀል ድርጊት የተገኘ ንብረትን ህጋዊ አስመስሎ ማቅረብ እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመርዳት ወንጀልን ለመቆጣጠር ተቋም ያቋቋመችው በ2002 ዓ.ም ነው ብለዋል፡፡በዚህም የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት መቋቋሙን የተናገሩት ዋና ዳይሬክተሩ ተልዕኮው ደግሞ ሀገራችን የአለም አቀፍ የፋይናንስ ድርጊት ግብረሃይል የሚባለው ምከረሃሳብን መተግበር ከሚጠበቅባቸው ከ200 በላይ ሀገራት አንዷ በመሆኗ ነው ሲሉ አስረድተዋል፡፡

የፋይናንስ ድርጊት ግብረሃይል 40 ቀጥታ አባል አገራት አሉት፡፡ እንዲሁም ደግሞ ዘጠኝ ቀጠናዊ አባል ሀገሮች አሉ ተብሏል። ከአፍሪካም ሶስት የምስራቅ እና ደቡቡን የሚያካትተው 21 አባል ሀገሮችን የያዘው የምስራቅ እና ደቡብ አፍሪካን የያዘው ኢስተርን ነደ ሶውዘርን አፍሪካ አንቲ ላውንድሪ ግሩፕ (eastern and southern africa anti money laundry group) ይባላል፡፡ ኢትዮጵያም ከ21 አባል ሀገራት አንዱ ናት ሲሉ ተናግረዋል፡፡

እነዚህ አባል ሀገራት የፋይናንስ ድርጊት ግብረሃይል ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመርዳት ወንጀልን ለመከላከል የሚያስችሉ 40 ምክረ ሃሳቦችን ይተገብራሉ፤ በየአምስት ዓመቱም የእርስ በእርስ ግምገማ ያካሂዳሉ ያሉት አቶ ሙሉቀን ሶስተኛውም ገምገማ በመጪው ዓመት ይካሄዳል ብለዋል፡፡እነዚህን ምከረ ሃሳቦች ተግበባራዊ ከምናደርግባቸው ህጎች አንዱ ባለፈው የተሸሻለው በወንጀል የተገኘ ንብረት ሕጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳት ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣው አዋጅ ነው ሲሉ በመግለጫቸው ጠቁመዋል፡፡

የተሸሻለው አዋጅ ኢትዮጵያ ለ12 ዓመታ ስተገለገልበት መቆየቷን ያስረዱት ዳይሬክተሩ የተሸሻለበት ምክንያት ደግሞ አለም አቀፉ የፋይናንስ ድርጊት ግብረሃይል ምክረሃ ሰቦቹን እያሻሻለ በመሄዱ ነው ብለዋል፡፡በዚህም የተሸሻሉ ምከረ ሃሳቦች ስላሉ እነሱን ሊመልስ የሚችል ህግ በማስፈለጉ እና ግብረ ሃይሉም ወንጀሎች እየተለዋወጡ ስለመጡ ሀገራት እነሱን ለመከላከል የሚመጥን የህግ ማዕቀፍ እንዲኖራቸው ስለሚያዝ ነዉ ብለዋል፡፡

የቀድሞው አዋጅ አመንጪ ወንጀሎችን በዝርዝር አያስቀምጥም ይህም አንዱ የአዋጁ ችግር ነበር ብለዋል የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙለቀን አማረ፡፡ በፍትህ ሚኒስቴር የህግ ጥናት እና ማርቀቅ ዳይሬክተር ጀነራል  አቶ አዲስ ጌትነት በበኩላቸው አዲሱ አዋጅ ከመደበኛ የወንጀል መርመራ ሂደት የወጣ መንገድን የሚከተል እንደሆነ ሰው ሊረዳው ይገባል ብለዋል፡፡

አዲሱ አዋጅ ልክ በመደበኛው የምርመራ ሂደት እንደሚደረገው ተጠርጣሪዎችን በፍርድ ቤት መያዣ መያዝ ፣ሰነዶችን ማሰባሰብ፣ ምስከሮችን መስማት እና መሰል ሂደቶችን አይከተልም ያሉት አቶ አዲስ ወስብስብ የሆኑ ወንጀሎችን ከመሰረቱ ለመለየት የሚስችል የምርመራ ሂደትን የሚከተል ነው ብለዋል፡፡

ለምሳሌም መርማሪው አካል ወንጀለኞችን መስሎ ተቀላቅሎ ወይንም አብሮ በመስራት፣ ተባባሪ መስሎ አብሮ ውሎ በማደር፣ ሲሸጡ ገዢ መስሎ፣ ሲገዙ ሻጭ መስሎ ሊሆን ይችላል ሲሉ በፍትህ ሚኒስቴር የህግ ጥናት እና ማርቀቅ ዳይሬክተር ጀነራል አቶ አዲስ ጌትነት ተናግረዋል፡፡

ምርመራውን የሚየካሂደው አካል ምረመራ ማድረግ የሚችለው የፍርድ ቤት ተዕዛዝ ካገኘ ብቻ ነው ያለው የፍትህ ሚኒስቴር እንደሚባለው አዋጁ ተጠርጣሪን አስሮ እያሰቃዩ አይመረምርም ይህም ፍጹም ስህተት ነው ብሏል፡፡

በወንጀል የተገኘ ንብረት ሕጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ መርዳትን የሚመረምር ሰው፤ በምርመራ ወቅት ከአቅሙ በላይ በሆነ ምክንያት ከግድያ ውጪ የትኛውንም ዓይነት ወንጀል ቢፈጽም ተጠያቂ የማያደርግ አዋጅ ከሰሞኑ መፅደቁ ይታወሳል፡፡ይህም መርማሪዎችን ወንጀል እንዲፈፅሙ በር ይከፍታል በሚል ከምክር ቤት ትችት ሲቀርብበት ነበር።

Via Sheger
@YeneTube @FkkerAssefa

tg-me.com/yenetube/54773
Create:
Last Update:

BY YeneTube

Warning: Undefined variable $i in /var/www/tg-me/post.php on line 283

Share with your friend now:
tg-me.com/yenetube/54773

View MORE
Open in Telegram

YeneTube Telegram | DID YOU KNOW?

Date: |

Telegram has exploded as a hub for cybercriminals looking to buy, sell and share stolen data and hacking tools, new research shows, as the messaging app emerges as an alternative to the dark web.An investigation by cyber intelligence group Cyberint, together with the Financial Times, found a ballooning network of hackers sharing data leaks on the popular messaging platform, sometimes in channels with tens of thousands of subscribers, lured by its ease of use and light-touch moderation.

What is Telegram Possible Future Strategies?

Cryptoassets enthusiasts use this application for their trade activities, and they may make donations for this cause.If somehow Telegram do run out of money to sustain themselves they will probably introduce some features that will not hinder the rudimentary principle of Telegram but provide users with enhanced and enriched experience. This could be similar to features where characters can be customized in a game which directly do not affect the in-game strategies but add to the experience.

YeneTube from us

Telegram YeneTube
FROM USA