Telegram Group Search
ፕሮግራሙ ተሰርዟል
================
(ተስፋ ያደረግነውም ቀርቷል!)
||
የፕሮግራሙ አዘጋጆች ቀድመው መጨረስ የነበረባቸውን ህጋዊ አካሄዶች ቀድመው ባለመጨረሳቸው መከልከል ለሚፈልጉ አካላት መንገዱን ስላመቻቹት፤ በነገው ዕለት በአዲስ አበባ ስቴዲዬም ይካሄዳል ተብሎ ተጠብቆ የነበረው በሃገራችን የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ የቁርኣን ውድድር ተሰርዟል። ቀጣይ አቅጣጫዎችን የፕሮግራሙ አዘጋጆችና የሚመለከታቸው አካላት የሚያሳውቁን ይሆናል።



አንዳንድ ጊዜ ትልቅ የሚባሉ ሰዎች በሁሉ ነገር እኛው በሚል ብሂል በትልቅ ህዝብ ውክልና ሽፋን የህፃን ሥራ እየሠሩ ተዋርደው ያዋርዳሉ።


የሚያሳዝኑኝ ከክፍለ ሃገር ድረስ ትምህርታቸውን፣ ሥራቸውንና የግል ጉዳያቸውን ጥለው የመጡ እህትና ወንድሞች ናቸው።

አብሽር! ለኸይር ነው። በሁሉም ነገር አላህ ይክሳችኋል። አደራ! እንዳትበሳጩ! ለበጎ ነው በሉና እለፉት!



ከዚያ ውጭ በዚህ ጉዳይ ወደ መንግስት አፍን ማንጓጠጥ አልደግፍም። በርግጥ ስህተቱ ከኛው ሰዎች ቢሆንም ለግሞ ነው እንጂ ማስተካከል ይችል ነበር። ጭራሽ ደግሞ ህግና ደንቡ በትክክል ሳይፈጸም የሚካሄዱ ፕሮግራሞች እንደሚበዙባት ሃገር ይሄን ክፍተት ማከም ይቻል ነበር። ይሄን ክፍተት ካገኘና እንደ ምክንያት ካቀረበ ግን መብቱ ነው። ማንም ሊወቅሰው አይገባም። መንግስት የሚወቀሰው የሚጠይቀውን ህጋዊ አግባብ አጠናቀህ ሰበቡን ሁሉ ካደረስክ በኋላ እምቢ ሲልህ ነው።
https://www.tg-me.com/¶በላጭ ሕዝቦች¶/com.theamazingquran
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ይህን ኹጥባ ሳንለቅ ማሳደር አልቻልንም!
--------------
ፕሮፌሰር ሸይኽ ከማል አልጀዛኢሪ ዛሬ የቁርአን ውድድሩ ላይ ስለ ሀበሻ ምድር ያደረጉት ኹጥባ እጅግ ድንቅ ነበር! ሀቂቃ ለመናገር ታሪካዊ ኹጥባ ነበር!! ስለ ሀበሻ በሌሎች አንደበት እንዲህ መስማት ያስደስታል!

እነሆ እናነተም ትመለከቱትና ታጣጥሙት ዘንድ ለቀነዋል!!!

خطبة الشيخ البروفيسور كمال الجزائري في حفل المسابقة لحفظ القرأن الكريم شارك فيها الحفاظ من دول متنوعة في العالم
تم القاؤه في نادي اديس ابابا في الدولة اثيوبيا يونيو 13 عام 2022
الحمد لله الذي بنعمته تتم الصالحات
𒊹︎︎︎አጫጭርና ጠቃሚ መልዕክቶች ለማግኘት ይቀላቀሉን☟︎︎︎ ☟︎︎︎
𑁍𑁍𑁍𑁍𑁍𑁍𑁍𑁍𑁍𑁍𑁍𑁍
❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀❀
☀️ሁዳ መልቲሚዲያ

ቴሌግራም 👇
www.tg-me.com/huda4eth

ፌስቡክ👇
fb.com/huda4eth

ዩትዩብ👇
http://www.youtube.com/c/HudaMultimedia
ሁሌ ውስጣችንን ቢዚ የሚያደርገን ምንድን ነው?

እውነት በውስጣችን ሌላን የዱኒያ ጉዳይ እንደምናስበው ያክል አላህን እናወሳልን?

የዱኒያ ጉዳይ አሳስቡ እንደሚያስጨንቀን ሁሉ የቀብራችን የነገ አኼራችን ጉዳይ ያስጨንቀናልን?

ኢማሙ ኢብኑልቀይም ረሒመሁሏህ እንድህ ይላሉ

«(ከጌታህ ጋር) በመለያየት የወረደብህን አደጋና (ከጌታህ) የጋረደህን የውረደት ሂጃብ(ግርዶ) ማወቅ ከፈለግክ: ቀልብህ ለማን ባሪያ፣ አካልህ ለማን አገልጋይ እንደሆነ ተመልከት ውስጥህ በምን ጉዳይ ቢዚ እንደሆነ የመተኛ ቦታህን የያዝክ (ለመተኛት በጎንህ ጋደም ባልክ) ጊዜ ቀልብህ የት እንደሚያድር ከእንቅልፍህ ስነቃ ቀልብህ ወደየት እንደሚበር ተመልከት? ያ(እንድህ ውስጥህ ቢዚ የሆነለት ነገር) ነው (በትክክል) አምላክህ።
የቂያማ እለት ሁሉም (በዱኒያ ላይ) ሲያመልክ የነበረውን ይከተል መባልን በሰማህ ጊዜ (ይህ ውስጥህን እንድህ ቢዚ ያደረገው ነገር) የሆነውም ቢሆን ከእርሱ ጋር አብረኽ ትሄዳለህ። [መዳሪጅ ሳሊኪን (3/308)]

ሐቂቃ ይህ በጣም ያስደነግጣል የሁሌ ጭንቀታችን ሀሳባችን የነገ አኼራ ወይንስ እች ርካሿ ዱኒያ? ሁላችንም ቆም ብለን እራሳችንን እንፈትሽ?
_
قال الإمام ابن القيم رحمه الله

إِذَا أَرَدْتَ أَنْ تَعْرِفَ مَا حَلَّ بِكَ مِنْ بَلَاءِ الِانْفِصَالِ، وَذُلِّ الْحِجَابِ، فَانْظُرْ لِمَنِ اسْتَعْبَدَ قَلْبَكَ، وَاسْتَخْدَمَ جَوَارِحَكَ، وَبِمَنْ شَغَلَ سِرَّكَ، وَأَيْنَ يَبِيتُ قَلْبُكَ إِذَا أَخَذْتَ مَضْجَعَكَ؟ وَإِلَى أَيْنَ يَطِيرُ إِذَا اسْتَيْقَظْتَ مِنْ مَنَامِكَ؟ فَذَلِكَ هُوَ مَعْبُودُكَ وَإِلَهُكَ، فَإِذَا سَمِعْتَ النِّدَاءَ يَوْمَ الْقِيَامَةِ: لِيَنْطَلِقَ كُلُّ وَاحِدٍ مَعَ مَنْ كَانَ يَعْبُدُهُ، انْطَلَقْتَ مَعَهُ كَائِنًا مَنْ كَانَ. [مدارج السالكين (٣/ ٣٠٨)]
Forwarded from ሰአድ ኢብኑ አቢወቃስ የኪታብ ተማሪዎች
የተክቢራ ጊዜው በሁለት ይከፈላል
1)በጊዜ ያልተገደበ ወይንም ልቅ የሆነ(unlimited)
2)በጊዜ የተገደበ ወይንም መደበኛ የሆነ

1)ልቅ የሆነው ከመጀመሪያው የዙልሂጃ ቀን ጀምሮ እስከ 13ኛው ቀን ማገባደጃ አስር ወቅት መጨረሻ ድረስ በተመቸው ሰዓት ተክቢራ ማለት ይችላል።

2)መደበኛው እና የተገደበው የተክቢራ አይነት ከዓረፋ (ሚፆምበት)ቀን ፈጅር ጀምሮ እስከ 13ው ቀን አስር ሰላት ድረስ ነው።
የተገደበ ስንል በየሰላቱ መጨረሻ ብቻ ስለሚል ነው።ይህም ከሙስሊሞች ጋር በጀምዓ ለሰገደ ብቻ የሚሆን ነው ብለው ያስቀምጣሉ።
ተክቢራ አይነቶች አሉት።
ከነሱ ውሰጥ ዑለማዎቹ የመረጡት ሃዲስ ላይ ሰነዱ ጠንካራ የሆነውን ሁለት ጊዜ ተክቢራ ያለበትን ነው።
"الله أكبر الله أكبر لا إله إلا الله الله أكبر الله أكبر الله ولله الحمد "

በያለንበት ቦታ እና ጊዜ ማብዛቱ በጣም የተወደደ ተግባር ነው።ሰሃባዎችኝ ያደርጉት ነበር።ልክ እንነ አቡ ሁረይራ እና ኢብን ዑመር ወደ ሱቅ በሚወጡበት ጊዜ ድምፃቸውን ከፍ እያደረጉ ተክቢራቸውን ይሉ ነበር።
Forwarded from ሰአድ ኢብኑ አቢወቃስ የኪታብ ተማሪዎች
ነገ ከመግሪብ በኋላ
አንድ ሴት ልጅ የሆንን ወንድ ለትዳር ከወደደችው ፣ለእሷ የሚመጥናት ከሆነ ራሷን አቅርባ አግባኝ ማለት ትችላለች።
በሌላም ሰው እንዳገባት ማሳወምቅ ትችላለች።

ሸይኽ ሷሊህ አል ፈውዛን ናቸው
👇ድምፁን ከታች ጀባ
ሳይደክሙና ሳይሰለቹ ረበና.. ረበና... ረበና... ያሉ ምላሶች፣ ምላሽን ማግኘታቸው አይቀሬ ነው!
አላህ የማይሰለች ምላስ፣ የማይደክም ልብ ይስጠን❤️🤍
Forwarded from ሰአድ ኢብኑ አቢወቃስ የኪታብ ተማሪዎች
ደስ የምትባል ታሪክ ናት 👇👇

አውሮፓ ውስጥ የሚገኝ ዩኒቨርስቲ...

አዳራሹ በተማሪዎች እና ጥሪ በተደረገላቸው ምሁራን እንግዶች ጥቅጥቅ ብሎ ሞልቷል። የዩኒቨርስቲው ፕሬዝዳንት አጠር ያለ ንግግር ካደረገ በኋላ የሀገሪቱን ሊቀ-ጳጳስ ወደ መድረክ ጋብዞ ወረደ።

ጳጳሱ ረዘም ያለ ሰዐት ንግግር አደረገ'ና፦ «ከመድረክ ከመውረዴ በፊት እዚህ አዳራሽ ውስጥ የምትገኙ የእስልምና ሀይማኖት ተከታዮችን 2 ጥያቄ መጠየቅ እፈልጋለሁ።»

አዳራሹ ውስጥ ፀጥታ ሰፈነ፤ ሁሉም ከመድረክ የሚሰነዘረውን ጥያቄ ለማደመጥ ትኩረቱን ከመድረኩ ላይ አደረገ።

ከአደራሹ ውስጥ የሚገኙ ውስን ቁጥር ያላቸው ሙስሊም ተማሪዎችም ከጳጳሱ ለሚሰነዘረው ጥያቄ መልስ ለመስጠት ራሳቸውን አዘጋጁ።

ጳጳሱ ጥያቄውን ጀመረ፦
«እናንተ ሙስሊሞች 'ሙሀመድ በአንድ ሌሊት ቅፅበት ውስጥ ከመካ እስከ እየሩሳሌም ከእየሩሳሌም እስከ ሰማየ-ሰማያት ሄዶ መጥቷል' ብላችሁ ታምናላችሁ። ይህ እንዴት ይሆናል?»

ከተማሪዎቹ መሀል አንድ ወጣት ብድግ አለ። ለተሰነዘረለት ጥያቄ ማሰላሰያ እንኳን ሳያሻው መልሱን ወደ መድረኩ ሰደደ፦«አንተ ከቤትህ ቁጭ ብለህ በምታዳምጣት የሬድዮ ሞገድ የአሜሪካንን ድምፅ ትሰማለህ፤ ሲያሻህ የአውስትራልያን ጣብያ ቀይረህ ታዳምጣለህ።

የሰው ልጅ በሰራው ሞገድ ቤትህ ቁጭ ብለህ በቅፅበት ውስጥ የአለምን አፅናፍ ካዳረስክ የሰውን ልጅ የፈጠረው ጌታ በአንድ ሌሊት ሙሀመድን ቢያንሸራሽረው ምን ይደንቃል...?»

አዳራሹ ለረጅም ደቂቃዎች በጭብጨባ ደመቀ...። ጳጳሱ ወጣቱን አድንቆት ወደ ቀጣዩ ጥያቄ ተሸጋገረ፦

«እስላሞች 'ነፍስን ሁሉ በመግደል ስራ ላይ የተሰማራ አንድ መልዓክ ነው' ትላላችሁ።

ለምሳሌ፦ በመቶዎች የሚቆጠሩ የባህር መንገደኞች በሜድትራንያን ውቅያኖስ ላይ ሰጥመው ቢሞቱ እና በተመሳሳይ ሰዐት ህንድ ውቅያኖስ ላይም በርካታ የመርከብ ተጓዦች ቢሞቱ እንዴት ነው የሞት መልአክ በዝያ ቅፅበት ሁለቱም የአለም አፅናፍ ጋ ሊደርስ የሚችለው...?»

አዳራሹ ውስጥ የተሰበሰበው ህዝብ የሙስሊሞቹን መልስ ሊያዳምጥ አዳራሹ ላይ ፀጥታን አሰፈኑ፤ ያ ልጅ ዳግም ብድግ አለ፦

«በዚህ በምንኖርባት ሰፊ ከተማ ውስጥ ስንት የመብራት አምፖሎች ይገኛሉ...? ብዙ ናቸው። ያን ሁሉ አምፖሎች አንድ የመብራት ሀይል ሰራተኛ ቢሮው ቁጭ ብሎ በአንድ ሴኮንድ ማጥፋት አይችልም...?»

ጳጳሱ፦ «ይችላል...»
ወጣቱ፦ «ታድያ የመብራት ሀይል ሰራተኛ በቅፅበት ውስጥ ያን ሁሉ አምፖሎችን ማጥፋት ከቻለ፤ የአላህ ሰራተኛ ነፍሶችን በቅፅበት ማጥፋት እንዴት ይሳነዋል..!!!»
Forwarded from 𝓜𝓸𝓱𝓪𝓶𝓶𝓮𝓭
አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ

እርሶ ከቁርዓን ጋር ይተዋወቃሉ? የቂርዓቶ ደረጃንስ ማሻሻል ይፈልጋሉ?እነሆ የምስራች በመላው አለም ለምትገኙ ለቁርዐንና ለሀዲስ ትምህረት ፈላጊዎች በሙሉ አልበራሒን ኦንላይን ቁርአን የቦታ ርቀት ሳይገድባቹ ቁርዐንን ባላቹህበት ቦታ አስተካክሎ ለመቅራት ልዩ የኦንላይን ቁርዐን ፕሮግራም አዘጋጅቷል።በተጨማሪም ለርሶና ለልጆችዎ በመልካም ልዩ ትምህርት (ዓቂዳ፣አኽላቅ፣አዝካር፣ ሲራ እና ሀዲስ) የትም መሄድ ሳይጠበቅባቸው በኦንላይን የዘመኑን ቴክኖሎጂዎች በመጠቀም ትምህረት ለመስጠት ዝግጅቱን አጠናቋል።  ፈጥነው ይመዝገቡ


እርሶ እኛ ጋር ሲቀሩ ከወጪ ቀሪ የሚገኘው ትርፍ ሙሉ ለሙሉ ኢስላማዊ ስራዎችን ብቻ በመስራት ላይ ላለው አልበራሒን ጀመዓ የሚውል መሆኑ  በደስታ እንገልፃለን!ኒያ ካሎት የኸይር ስራ ተቋዳሽም  ኖት

ስልክ ቁጥር +251967936098
በኢንቦክስ👇👇
@Ba_Alewi

ግሩፑን ይቀላቀሉ👇👇👇
https://www.tg-me.com/+5c5NKMc7F75hNDQ0
አሰላሙ አለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱሁ


ልዩ የረመዷን መቀበያና የዳዕዋ መዝጊያ እንዲሁም የገቢ ማሰባሰብያ ፕሮግራም በሀሰንና ሁሰይን መስጂድ መሰናዳቱን ስናበስርዎ በታላቅ ደስታ ነው።በእለቱም የተለያዩ ዝግጅቶች ከመኖራቸውም ጋር ከምንጊዜውም በተለየ ፍቅርና አንድነታችንን አጠናክረን የረመዷንን ወር ከኛ ጋር በጋራ እንድንቀበል እንጋብዞታለን።ረመዷን የ11 ወር ጉዟችንን የሚያደስ የደከሙ ነፍሶቻችንን ወደ ከፍታ የሚያወጣ ህይወት የቸረችን ልዩ መሰላል ነው። በወንጀል ባህር የቀዘፉ ነፍሶቻችን ከስጥመት የሚያድን የአላህ ችሮታ ነው።የረመዷን ምሽት አዲሷ ጠረቃ ከመወለዷ በፊት አስቀድመን እንድንቀበላት በሀሰንና ሁሰይን መስጂድ ሀሙስ ከመግሪብ በኋላ ፕሮግራም የኢስቲቅባለ ረመዷን ፕሮግራም አዘጋጅተን እንጠብቆታለን!


መጋቢት 7 የፊታችን ሀሙስ ከመግሪብ በኋላ
ተጋባዥ እንግዶች
ኡስታዝ ኑሩ ቱርኪና
ኡስታዝ አብዱልቃድር(የሁዳ መስጂድ ኢማም)



መቅረትም ሆነ ማርፈድ ያስቆጫል!ለሴት እህቶቻችንም ቦታ ያዘጋጀን መሆኑን በደስታ እንገልፃለን!

አዘጋጅ አልበራሂን ኢስላማዊ ማህበር
የሚያሳዝነው አብዛኞቻችን በዲን ተከልለን መበሻሸቅን ስራችን አድርገን ይዘነዋል።የሆነ ጥፋት ስናይ አጥፊውን አካል በተገቢው መልኩ ከመምከር ይልቅ ማሽሟጠጥና ማጣጣል መተረብ ብሎም እስከመሳደብም የምንደረስ አንዳንድ ሰዎች አለን አላህ ይዘንልን ምን አይነት ካልኩሌሽን ይባል ይሆን ይሄ?! ሌላው በወንጀሉ እንዳይጠየቅ እንደምንቆረቆር እያሳየን እኛ እራሳችን ተከትለን በመሳደብና በመዛለፍ የወንጀል ባለቤት እንሆናለን።ለምሳሌ ቢድዓን ስናወግ በመውሊድ ሰሞንና የሸዋል ኢድን ብለው አንዳንድ ወንድሞቻችን የሚያከብሩት ተግባሩ ልክ እንዳልሆነ ስናስታውስ አብዛኞቻችን የምናሳየው ምግባር በጥፋታቸው ላይ እንዲቀጥሉና ችክ እንዲሉ የሚያረግ እንጂ የሙስሊም ወንድሞቻችንን መመራት የሚያመጣ ሲሆን አይስተዋልም።አብዛኞቻችን ዲን ላይ ጥፋትን ስናይ ማረማችን እጅግ ተወዳጅነቱ እንዳለ ሆኖ የምናርምበትን መንገድ ግን መለስ ብለን ማየት ይኖርብናል ወላሁ አዕለም።
Forwarded from Has
አረፋህ ሊመን አረፈህ!

ነገ ቤት የማፅጃ ወይ መጋረጃ የማውረጃ ቀን አይደለም። የኢድ ሸመታም ሆነ የመዝናኛ እንዲሁ!

ነገ አላህ የሰማይ ባለሟሎች ላይ በአረፋ ሰዎች የሚኩራራበት፤ የሰው ልጆች ከእሳት በገፍ ነፃ የሚባሉበት ከሁሉ በላይ ዱአዎች በሙሉ ተቀባይነት የሚያገኙበት እለት ነው።

ለይለቱል ቀድር ባትታወቅ የውሙ አረፋ ትታወቃለች። በለይለቱል ቀድር መላእክት ቢወርዱ በአረፋ አላህ (እሱን በሚመጥን አወራረድ) የሚወርድበት ነው!

ነገ አላህ በጊዜ ፀጋ ላጣቀማችሁ አንድ to do list ላካፍላችሁ

ጠዋት

ከፈጅር በፊት ከለይሉ ጥቂቱን መስገድ፣ ስሁር መመገብ እና ኢስቲግፋር ማብዛት!

ከሰላት በኋላ ቀጥታ ተክቢራ መጀመር ከዛም ፀሀይ እስክትወጣ ቁርአን፣ተህሊል፣ተህሚድ በአጠቃላይ በዚክር ማሳለፍ(አዝካረ ሰባህ ሳይረሳ)

ፀሀይ ስትወጣ የፀሃይ መውጣትን ሰላት እዛው ከመስገጃችን ሳንነሳ በመከወን ከረሱሉ (ሰ.ዐ.ወ) ጋር ሀጅ የማድረግን ምንዳ እንዲጎናጸፍ

ለቀን ኢባዳ ያግዘናል ብለን ካሰብን መጠነኛ እኝቅልፍ እንተኛ። ስንነሳ በትንሹ 4 ረክኣ ሰላተ ዱሃ እንስገድ!

ከሰአት

ከዝሁር ሰላት በኋላ ቁርዐናችንን እንቀራለን። የአረፋ ኹጥባ(ከመስጂደ ነሚራህ የሚተላለፈውን) መልእክት በጥብቅ መከታተል

ልባችንን ሊያረጥብ የሚችል መፅሐፍ ወይም ቪድዮ እየተመለከትን እራሳችንን እናርጥብ!

ከአስር በጥሎ እንዲሁ በቁርአን እና በዚክር መግሪብ 1 ሰአት አቅራቢያ እስኪቀረው ማሰለፍ!

የእለቱ ወሳኝ ሰአት ይህ ነው።

የተሰበረ የሚጠገንበት፤ የታመመ የሚፈወስበት፤ ተስፋ የቆረጠ ተስፋው ነፍስ ሚዘራበት ድንቅ ሰአት!

ዱኣ!!! ዱኣ ብቻ!

በዚህ ቀን ከእሳት ነፃ አለመባል ኪሳራ ነው። ምኞት ኖሮን ምኞታችንን ሳናሳካ መቅረት ቂልነት ነው!

ነገ አላህ አልመረጥንም እና እየተመለከታቸው ከሚኮፈስባቸው ጌታቸውን ለማላቅ በነጭ ተውበው ከአረህማን ድግስ ከሚታደሙት አልሆንም!

"አረፋ ተራራ ላይ መቆም ያልቻለ
አላህ ያሳወቀው ድንበር ላይ ይቁም

ሙዝደሊፋ ላይ ማደር ያልቻለ
በአላህ ትእዛዝ ላይ ይደር...ያቀርበዋልና!

ሚና ላይ እርዱን መከወን ያልቻለ
ምኞቱን ይረድ! ከፍ ይላልና።

ወደ ቤቱ በርቀት ምክንያት መድረስ ያልቻለ ከደም ስሩ ቅርብ ወደ ሆነው የቤቱ ጌታ ይከጅል!" ኢብኑ ረጀብ

እርቅ ይበጀናል!

Huzeyfa Sultan
አካዉንታቹን ታደጉ !!!!!

ከላይ በመጀመሪያ ፎቶ የምትመለከቱት የ200 ብር ኖት ፎቶ የያዘ እና ቻናሉን ሰብስክራይብ አድርጉ የሚለዉ ሚሴጅ ከተላከላቹ በምንም አይነት መልኩ እ ን ዳ ት ሞ ክ ሩ !!!!

በመጀመሪያ ወደ chrome ይወስዳቹና የቴሌግራም አካዉንታቹን login አስደርጓቹ የ login code ያስልክና ኮዱን ስታስገቡ በቃ ተበላቹ!!!! አካዉንታቹ ሀክ ይደረግና ያንኑ የዉሸት ሚሴጅ ስልካቹ ዉስጥ ወዳሉት ግሩፕ ቻናልና አካዉንቶች በሙሉ ይበትናል ስልካቹ ከቁጥጥራቹ ዉጪ ይሆናል !!!!

ነገር ግን ተበልታችሁ ከሆነ በሁለተኛ ላይ በለጠፍኩት ፎቶ መሠረት ወደ setting ትገቡና Device ወደሚለዉ ገብታቹ ፎቶ ላይ ያከበብኩበትን ተጭናቹ በአፋጣኝ Terminate አርጉት አለበለዚያ አካዉንታቹ በአጭበርባሪዎች እጅ ይዘልቃል!!!!!

በተረፈ ሌሎችንም ለማስጠንቀቅ ይሄን መልዕክት ሼር አርጉ የበኩሌን ተወጥቻለሁ።
ኡስታዝ ኑሩ ቱርኪ
https://vm.tiktok.com/ZM23JsgnW/
2024/04/29 12:14:28
Back to Top
HTML Embed Code: