የእኔ ታሪክ(ምዕራፍ -2)

ክፍል 7

ቪቪያን ይሄንን በጭራሽ እንደማልፈቅድልሽ ታውቂያለሽ ጊቢ ወደውስጥ ሕዝቅኤል ጮኸባት። አባ.... አይኖቿን አቁለጨለጨችበት። ቪ የእኔ ታሪክ አንቺ ላይ ሲደገም ቁጭ ብየ የማይሽ ይመስልሻል ልጄ? ያንን ሁሉ ታሪክ ነግሬሽ እንዴት እንደዚህ .....? ሕዝቅኤል በሃዘን ውስጥ ሆኖ ይናገራታል። ቪቪያን ቅስሟ ተሰበረ ግንኮ ......እወደዋለሁ
ሌላ ጓደኛ ስለሌለሽ ነው ወደሽው አይደለም ልጄ እመኝኝ አባዬ ልቤንኮ አንተ ስላልከኝ የምተወው ነገር አይደለም ምን ላድርገው ። እኔስ ብሆን ያንተን ታሪክ ከሰማሁ በኋላ ማስቆም ምችለው ነገር ቢሆን ኖሮ አቆመው ነበርኮ። እባክህ ተረዳኝ አልችልም አባ.......እንባዋን ማውረድ ጀመረች። ሕዝቅኤልን እንደ ወትሮው እንባዋ ሊያስደነግጠው አልቻለም። ነገውኑ ከዚህ ልጅ ጋር ካልተለያየሽ በህይወት አታገኝኝም ከእኔ እና ከእሱ ትመርጫለሽ....? ጨርሻለሁ ጊቢ ወደውስጥ......ቪቪያን የምትሰማውን ቃል ማመን አቃታት አባቷ እንደዚህ አይነት ጠንካራ ቃላትን ሲሰነዝርባት የመጀመሪያዋ ነው። ከድንጋጤዋ ብዛት አፏን ብቻ ከፍታ ደርቃ ቆመች። ጊቢ ቪቪያን!!!!


እያለቀሰች ወደ ክፍሏ ገብታ አልጋዋን በእንባዋ ማራሷን ቀጠለች። ሕዝቅኤልም እሷ ከገባች በኋላ የተናገራት ለራሷ ቢሆንም ሀዘኗን እያሰበ ውስጡ ቆሰለ።

አሌፍ ለ ቪቪያን ከ ሕዝቅኤል ባታደርሰውም ከማንም በላይ የምታፈቅረው ሰው ነው። ከእርሱ መራቅን ብዙ ጊዜ አስባለች ። ለ ሕዝቅኤል ከመንገሯም በፊት ደጋግማ ሞክራው አልተሳካላትም።

ሳምንታት አለፉ የነ ሕዝቅኤል ቤት ፀጥታ ብቻ ከሆነ ሰነባብቷል። ቪቪያን ከክፍሏ አትወጣም። እንደው ድንገት ብትወጣ እንኳን ራሷን ጠርዛ በለቅሶ ብዛት ቀልተው የጎደጎዱ አይኖቿን ሰብራ ማንንም ሳታናግር ምትፈልገውን እቃ ይዛ ወደ ክፍሏ ትመለሳለች። ሕዝቅኤልም ፀጉሯን የሚያሻሻት ፣ግንባሯን ሳይስማት የማይውለውን ልጁን ካናገራት ሳምንታት አለፉት።እሱም ከመፅሀፍቶቹ ጋ ካልሆነ ማንም ጋ ማውራት አቁሟል።
ይሔን ያክል ተዘጋግተው እንዲቆዩ የተመቻቸው ደሞ የቪቪያን እናት የታመመች እናቷን ለመጠየቅ ወደ ሌላ ሃገር መሄዷ ነበር።

አንድ ቀን ግን ሕዝቅኤል የቤት አጋዣቸውን ጠርቶ ቪቪያን እንድትጠራለት ነገራት። ከዚህ በላይ እሷን ፊት ነስቶ መቆየት አልተቻለውም።ብዙ ከራሱ ጋር ከታገለ በኋላ የፈለገችውን እንድታደርግ ሊተዋት ወሰነ። ለዛም ነበር ያስጠራት.......


ቪቪያን ራሷን ለማጥፋት ብዙ ጊዜ አስባለች። ነገር ግን ያንን ባደረገች ማግስት ሕዝቅኤልም እንደሚከተላት ታውቃለች። ብዙ ጊዜ የመኖሩ ምክኒያት እንደሆነች ስለሚነግራት ደፍራ ይሄንን ለማድረግ አትችልም እሷም ከአባቷ እና ከአሌፍ ለመምረጥ እየተሰቃየች ነው ።


ኳኳኳ ....ቪ... ዝም..... ልጅቷ አሁንም ታንኳኳለች ቪቪያን.......ክፈችው እንጅ..... ተይኝ እባክሽ ተኝቻለሁ። በተዳከመ እና በተሰላቸ ድምፅ መለሰች። ክፈችው አባባ እየጠራሽ ነው።.....ቪቪያን ከአልጋዋ ተስፈንጥራ ተነሳችየታለ አለቻት በደስታ በሩን እየከፈተች .....ልጅቷ በሁኔታዋ ግራ እየተጋባች በ..በረንዳ ላይ..ነ ሳታስጨርሳት እየሮጠች ወደ አባቷ ሔደች።


አጠገቡ ስደርስ ሩጫዋን ቀስ አደረገችውና በቀስታ ተራመደች አ... አቤት አባ አለችው ጀርባውን ሰጥቷት እንደቆመ ነይ ወደዚህ አላት ፊቱን ሳያዞር ተጠጋች...ተጠጋች አልቻለችም ጀርባውን ጥምጥም አድርጋ አቅፋ እንባዋን ማፍሰስ ጀመረች።


ይቀጥላል .......

@nibab_lehiwot
የእኔ ታሪክ(ምዕራፍ- 2)

ክፍል 8

ሕዝቅኤል እና ቪቪያን የናፍቆታቸውን ከተቃቀፉ እና ከተላቀሱ በኋላ ተቀምጠው መወያየት ጀመሩ። ሕዝቅኤልም ምንም እንኳን ውስጡ ባያምንበትም የፈለግሽውን አድርጊ እኔ ፈቅጄልሻለሁ ብቻ ግን ተጠንቀቂ የማይሆን ነገር እንዳታደርጊ ልትመከሪ የሚገባ አይነት ልጅ እንዳልሆንሽ አውቃለሁ ግን በእድሜ ከአንቺ ስለምበልጥ ስለ ህይወት ከአንቺ የተሻለ አውቃለሁ። ያየሁትን ሁሉ ነግሬሻለሁ አሁን እንደምታስቢው ቀላል እንደማይሆን እወቂው ግን አንዴ ሜዳ ውስጥ እስከገባሽ ድረስ ማሸነፍ እንጅ ወደ ኋላ ማፈግፈግ የለብሽም መንገድሽን ያሳምርልሽ ልጄ። ቪቪያን ቅስም የሚሰብር ንግግሩ ውስጧን አሳመማት ምን ያክል ቢወዳት እንደሆነ ይሄንን እያደረገ ያለው ከምን ጊዜውም በላይ ዛሬ ወለል ብሎ ታያት። ምንም ሳትለው እጁን ብቻ ስማው ወደውስጥ ገባች።


እንደ እውነቱ ከሆነ አሌፍን ምንም ያክል ብትወደውም ግንኙነት ለመጀመር ግን መጀመሪያ የአባቷ ፈቃደኝነት እንደሚያስፈልጋት ነግራው መልሷን እየጠበቀ ነበር። ቪቪያን ግን ለ አባቷ አሌፍ ፍቅረኛዋ እንደሆነ አድርጋ ነበር የነገረችው። ይሔንንም ያደረገችው ሆን ብላ ነበር።


ወደክፍሏ እንደገባች በደስታ እየፈነጠዘች ለ አሌፍ ደወለች። ሄሎ ቪ....አላት ዝምተኛው አሌፍ አባዬኮ እሽ አለ አለችው ሰላም እንኳን ሳትለው። አሌፍ ግን እንዳሰበችው ያን ያክል ደስተኛ አልሆነም። አይ ደስ ይላል ሰሞኑን እንገናኝና እናወራለን ሰላም ሁኝ ብሏት ስልጉን ዘጋው። ቪቪያን ግራ ገባት እውነት ግን አሌፍን መምረጤ ትክክለኛ ውሳኔ ነው ? ስትል ለራሷ አጉረመረመች።



አሌፍ ሻይ እየጠጣ ነበር ቀድሞ የጠበቃት። እንደደረሰች ሰላም ብላው ተቀመጠች። ደህና ነህ አይደል አለችው ፈገግ እያለች። አወ ቪ አሁን ጊዜ የለኝም ስሚኝ አብረን መሆን አንችልም ይሔንን ልነግርሽ ነው የመጣሁት በጣም ይቅርታ ቪቪያን።

ለምን ????

አለችው ግራ በተጋባ አስተያየት እያየችው።


የሰማሁት ታሪክ ስላለ ሕይወት እኛ እንዳሰብነው ቀላል ስለማይሆን.....

ጥሩ ጓደኞች እንሆናለን ደህና ሁኝ ብሎ ግንባሯን ስሟት ተነስቶ ወጣ።

ቪቪያን በፀጥታ ወደ ቤቷ ተራመደች ሀዘኗ ፊቷ ላይ በግልጽ ቢታይም ግን ላለማልቀስ ከራሷ ጋ እየታገለች ነው። በሩን ከፍታ ስትገባ እንደተለመደው ሕዝቅኤል በረንዳ ላይ ተቀምጦ መፅሐፉን እያነበበ ነበር። አባ የመጨረሻ ጥያቄ ላስቸግርህ እባክህ አለችው ከይኖቿ ሊወጡ የሚያቆጠቁጡ እንባወቿን ወደ ውስጥ ለመመለስ እየታገለች።


ምንድን ነው ልጄ ግራ ገባው።

ወንድሜን ፈልጌ ላግኘው ወደዚያች ሀገር ላከኝ።

ቪቪያን ሕዝቅኤል ፍጥጥ ብሎ ጠራት።

አባየ ካልሆነ እሞታለሁ በቃ ወንድሜ ያስፈለሰገኛል። እንባወቿ ሕጓን ጥሰው ወደታች ተውረገረጉ......



ምን ሆነሻል???
ሕዝቅኤል ደነገጠ።

ይቀጥላል...........
@nibab_lehiwot
የእኔ ታሪክ ምዕራፍ -2

ክፍል ዘጠኝ

የሕዝቅኤል ሚስት ኤልሳ ወደ ቤቷ ስትመለስ ብቻዋን አልነበረም ከ አንድ ትልቅ እንግዳ ጋ ነበር ። በተለይ ሕዝቅኤልን በጣም ሊያስደነግጥ ከሚችል እንግዳ ጋ......... ከዛ በፊት ቪቪያን እና ሕዝቅኤል ስለወንድሟ ጉዳይ ተነጋግረው ጨርሰዋል። አብረው ሊሄዱ ወስነው ጉዳዩን ዘግተውታል።



ሕዝቅኤል ወደቤት ሲገባ ኤልሳን መጥታ ስላገኛት የናፍቆቱን ካቀፋት በኋላ ቤት ውስጥ ሌላ እንግዳ እንዳለ ተመለከተ። ፊቷን ሲያየው ድንገት ልቡ ድንግጥ አለ። የሚያውቀው ግን የረሳው ፊት.......የት ነበር ማውቃት ..... ብቻ ግን ፈራት ሴትዮዋ ከተቀመጠችበት እየተነሳች ፈገግ አለች ጭራሽ ስትስቅ ደነገጠ ማን ነች??? አለ ለራሱ የሚያውቃት የልጅነት ጓደኛው ሜሮን ነች። እሷን በመርሳቱ ራሱን ታዘበው ሜሪ አላት በማመን እና ባለማመን ውስጥ ሆኖ ሕዝቄ አለችው ፈገግታዋ ከፊቷ ሳይጠፋ.....ለ ረጅም ደቂቃወች ተቃቀፉ ከብዙ አመታት በኋላ ....... ሕዝቅኤል የልጅነቱን ሕይወት አስታወሰ እንደአዲስ የሆነ መሰለው ። ተቀምጠው ትንሽ ካወሩ በኋላ ኤልሳ እንዴት እንዳገኘቻት ነገረችው። (የሔደችው የእውነትም እናቷን አሟት ሳይሆን ሜሮን እና ጓደኞቿን ፍለጋ ነበር በጅምር የቀረውን የሕዝቅኤልን ታሪክ ለመጨረስ........


ሜሮን ካቆመበት ትቀጥለዋለች። ከዛ በኋላ ግን ምን ተፈጠረ ደህና ሆንሽ? ማቲስ ተገኘ? አብርሽስ ደህና ነው? ልጆችስ ወለድሽ? ሕዝቅኤል የጥያቄ መዓት አወረደባት።


ያኔ ልጄን ካጣሁ በኋላ ለብዙ ሳምንታት መንቃት አልቻልኩም ነበር ። ነገር ግን በህልሜ ይሁን በእውኔ ባላውቅም አንድ ሰው እየመጣ እጄን እየያዘ ያለቅስ ነበር። ይቅርታ አድርጊልኝ ሲል ይሰማኛል። ሜሮን ንቂ እባክሽ ተይ እንደዚህ አታድርጊ ይለኛል። ባለቤቴ እንዳልሆነ ግልፅ ነበር።



አንድ ቀን ግን እንዲህ አለ ሜሪ ዛሬ አይንሽን ገልጠሽ ልነግርሽ ያልቻልኩትን ይዤው የምኖረውን ሕመሜን እነግርሻለሁ። እኔ ቤት ውስጥ ምንም ያልጎደለብኝ ልጅ ነኝ ። ግን ፍቅር ጎድሎብኝ ነበር። በጓደኛቼ ተሰድቤያለሁ፣ ተንቄያለሁ፣ በቤተሰቦቼ ተፈጥሮ ምክኒያት የሰወች ማላገጫ ሆኛለሁ። ልጅነቴን እንደ ልጅ አላደግኩም ሲያሾፉብኝ፣ ከልጆች ጋ በተጣላሁ ቁጥር የእግረ አጭር ልጅ እያሉ ሲያሳምሙኝ፣ አባትህኮ እግሩ አንካሳ ነው ሲሉኝ ህመሜን ዋጥ አድርጌው ኖሬያለሁ። ወንድ ልጅ አያለቅስም ሲሉ ታውቂያለሻ ማንም እንዳያየኝ እየተደበቅኩ ደም እንባ አፍስሻለሁ። ያኔ ግን ማንም ዞር ብሎ አላየኝም ቤተሰቦቼም ቢሆኑ ......ልጅ ነበርኩ ፍቅር ያስፈልገኝ ነበር። ግን አጣሁት በእነሱ አልፈርድም ምክኒያቱም ሳዝን አይተውኝ አያውቁማ.....በቃ ራሴን በሙዚቃ ውስጥ ሸፈንኩት። ማንም እንደማይወደኝ ደመደምኩ እኔም ራሴ ራሴን ጠላሁት ። የነበረኝ አማራጭ ራሴን ከሰወች ማራቅ እና ከፍ ከፍ አድርጎ መታየት ነበር። ግን እውነታው እንደ እኔ ራሱን ዝቅ አድርጎ የሚያይ አለመኖሩ ነው።



በተቀየርኩ ሰዓት መጣሽ ከራስሽም በላይ ትወጅኝ ነበር ። ምን ነበር ያኔ ልጅነቴ ሳይበረዝ ወደ እኔ ብትመጭ የምወደውን ማንነቴን ሳላጣው ባገኝሽ። ግን እድለ ቢስ ነኝ። እኔ ያላገኘሁትን ፍቅር ለ አንቺ ከየት አምጥቼ ልስጥሽ? የፈለግኩት ከቤተሰቦቼ፣ ከጓደኞቼ ፣ ከማህበረሰቡ ያጣሁትን ፍቅር አንቺ ጋ ማግኘት ነበር። ሁልጊዜ እንድትንከባከቢኝ፣ እስከ ፍፃሜ ድረስ ምንም ባደርግሽ እንዳትተይኝ፣ ከእኔ ውጭ ሌላ ሰው ጋ መኖር እንዳትችይ.......ብቻ በጣም ብዙ ነገር ከአንቺ ፈለግኩኝ በምላሹ ግን እኔ ለአንቺ ምንም መስጠት አልፈልግም።ምክኒያቱም ፍቅር ለ እኔ ሽንፈት ነው። ተሸናፊ መሆን ደግሞ አልፈልግም አንዴ ራሴን ከፍ አድርጌ ሰቅየዋለሁ።ለዛም ነው እንደማፈቅርሽ ለ አንቺ እንደተሸነፍኩ አውጥቼ መናገር የማልችለው እና ፍቅሬን ደብቄ መኖርን የመረጥኩት።




አንቺ ግን ግልፅ ነበርሽ።እብድ ነህ በይኝ አወ እብድ ነኝ ያ ጥሩ የነበረ ነገር ግን ማህበረሰቡ ያሳበደው እብድ......ብቻ ሁሉም አለፈ አንቺም ትተሽኝ ሔድሽ እንደምትመለሽ በሙሉ ልቤ አምኜ እጠብቅሽ ነበር። ግን አግብተሽ ተመለስሽ.....እኔኮ ራስ ወዳድ ነኝ ጭራሽ ከባልሽ ተፋቺ እና እኔ ጋ ሁኚ አልኩሽ። አሁን ሁሉንም ተይው ዛሬ እንደተሸነፍኩ ልመንልሽ በሙሉ ልቤ ከማንም በላይ አፈቅርሻለሁ ሜሪ ይሔው ተነሽ ስሚኝ እኔ ጉረኛው ማቲያስ በጣም አፈቅርሻለሁ!!!!! ማቲ ሲያለቅስ የሲቃ ድምፁን ለመጀመሪያ ጊዜ ሰማሁት ግን አይኖቼ መገለጥ አልቻሉም እንባዬ ብቻ ፈሰሰ ማቲ እንደነቃሁ ገባው መሰለኝ ግንባሬን ስሞኝ ተሰወረ። ወዲያው ዶክተሮቹ ተከታትለው ገቡ።.........


ይቀጥላል...........
@nibab_lehiwot
አገኘሁት.......😄


ስፈልገው ከእኔ ሸሽቷል፣
ስገሰግስ ጥሎኝ ሮጧል፣

ልደርስበት ያ ያልቻልኩት፣
ትቼው ሁሉን ስል ወደፊት፣
መንገዴ ላይ አገኘሁት፣
ምን ያደርጋል ተለያይቷል መስመራችን፣
ለየቅል ነው መንገዳችን፣
ብናውቀውም ትላንታችን፣
ነገን ማየት ነው ዛሬያችን፣
ከፊት ለፊት በአይን ተያይተን፣
ከሐሳቤ ጋ ተላለፍን!!!😁😌


bee
የእኔ ታሪክ ምዕራፍ 2

ክፍል -10

እሽ ቀጥይ ከዛስ ሕዝቅኤል በጣም ለማወቅ ጓጓ። ከዛማ ስለሱ ሰምቼ ጋር አላውቅም። ግን ምናልባት ጥሩ ቦታ ይሆናል ያለው ከእኛ መራቁ ጥሩ ነው ።ግን አላመንኩሽም ሜሪ አንቺስ ታዲያ ከዛ በኋላ ወለድሽ.....እኔማ አንድ ወንድና አንዲት ቆንጆ ሴት ልጆች አሉኝ። ከባለቤቴ ጋር ወደ አሜሪካ ተመለስን ጥሩ ህይወት እየኖርን ነው። ግን ማቲ ትዝ አይልሽም ሕዝቅኤል ፈገግ አለ። ሜሮንም እንደ መሽኮርመም እያደረጋት እውነት ሕዝቄ አንድ ቀን ከሀሳቤ ወጥቶ አያውቅም በህልሜ እንኳን ሳላየው ያደርኩባቸው ቀናት በጣት የሚቆጠሩ ናቸው።
አብርሽስ.....ሰላምስ......ግን ታስታውሱኝ ነበር? ወይስ ከነመፈጠሬ ረስታችሁኛል??? ሜሮን ስለቤተሰቡ ድጋሚ አንስታ ቁስሉን መቀስቀስ ስላልፈለገች ወሬውን በአጭሩ ለመግታት ስትል ሁል ጊዜ ሕዝቄ በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ብቻ ግን ተወው እኛም ያልተነገረ ብዙ መከራን አሳልፈናል። ማለፉ መልካም ነው ትላለች እማዬ። አንተስ ወለድክ አለችው ቀና ብላ እያየችው። አወ አንዲት ቆንጆ ሴት ልጅ አለችኝ አላት ፈገግ ብሎ ድንገት ግን ከ ራቢያ የወለደው ልጅ በአእምሮው መጣ እና አንድ ወንድ ልጅም አለኝ ምናልባት ራቢያ ከነገረችሽ።


አወ ነግራኝ ነበረ። ግን ለምን ዝም አልክ እሱምኮ አባት ያስፈልገዋል። አይ ሜሪ እኔ ለ እሱ አባት ለመሆን የምገባ ሰው አይደለሁም። ራቢያም አትፈልግም ተይው አባቱን አባቴ እያለ ይኑር አላት እዝን ብሎ። በዚህ ቅፅበት አንድ ሰው በር አንኳኩቶ ገባ። ሜሮን ስታየው ደርቃ ቀረች።


ሰላም ዋላችሁ አባባ ቪቪያንን ፈልጌ ነበር። አለ አንገቱን በሀፍረት እንደሰበረ።ሕዝቅኤል ቪቪያንን ስላሳዘናት በአሌፍ ቢያዝንበትም። የመለያየት ሀሳቡ ከሱ ስለመጣ ግን ብዙ ቂም አልያዘበትም።

" ሰ....ሰሚር " አለችው እየተወዛገበች። ሕዝቅኤል ሰሚር የሚለውን ስም ሲሰማ ልቡ ራደ።እንዴ የምን ሰሚር ነው አሌፍ ነው እንጅ.....አላት እየተወዛገበ ወይዘሮ ሜሪ እዚህ ምን ትሰሪያለሽ ? አንተ ራሱ እዚህ ምን ትሰራለህ? ወይ ጉድ ሁለቱም እየተፋጠጡ ነው። ሕዝቅኤል ሁለቱንም አስቀምጧቸው የት እንደሚተዋወቁ ሜሮንን ጠየቃት። የእናቱ ጓደኛ እንደሆነች አጭር መልስ ነገረችው።እናንተስ የት ተዋወቃችሁ አለችው። እየተገረመች የቪቪያን ጓደኛ ነው አላት ፈገግ ብሎ.........ወይ ጉድ ብላ ዝም አለች። አሌፍ እሷን ትቶ ሕዝቅኤልን አባባ ላናግርወት ፈልጌ ነበር ቀን መርጠው ቢነግሩኝ ? በትህትና ጠየቀው። ሕዝቅኤል የአሌፍን ስብዕና ከሁሉም በላይ በጣም ይወድለታል። ምናልባት እምነታቸው ባይለያይ ኖሮ ቪቪያንን ከሱ ውጭ ሌላ አታገቢም ብሎ በከለከላት ነበር። ብቸኛ ጭንቀቱ የ እምነት ልዩነት ነው።



ነገ ከሰዓት አለው አሌፍም ስራ ስላለኝ ልሂድ ብሎ ተሰናብቷቸው ወጣ።

ሕዝቄ ግን ይሔንን ልጅ ከዚህ በፊት አታውቀውም?

ሜሪ ደሞ ብዙ አመት ነውኮ ከ ቪቫ ጋር እንደልጄ ነው የማየው።


አይ አይ ሌላ ቦታ.....

አታወዛግቢኝ የት????



ይቀጥላል ..............
@nibab_lehiwot
"እወድሀለው" ብላኝ በረጅሙ ተነፈሰች.... አተነፋፈሷ ዜማ ነበረው ዘወትር ሊሰሙት እንደሚናፍቁት አይነት አንዳንዴ ምን የሙዚቃ  መሳርያ ትወዳለህ ሲሉኝ የእሷ ትንፋሽ ማለት ይቃጣኛል...እነዛ እቧይ የሚያክሉ እይኖቿን አይኔ ላይ ተክላ "ዝም አልክ እኮ እ...." ስትለኝ "እኔም" ብዬ አንገቴን ደፋው ከዛች እለት ጀምሮ "እኔም" ተተርጉሟ ሌላ መልክ ያዘች የመውደዴ ጥግ ተለካበት.. ተመዘነበት ወደቅሁ ..አንዳንዴ በዚች ቃል ተረግሜ ነው የፍቅር አድባር የሸሸኝ እላለሁ

🖌121
የእኔ ታሪክ ምዕራፍ 2

ክፍል-11

እናቱን እና አባቱን አታውቃቸውም?

ምነው ሜሪ ችግር አለ እንዴ?

ሕዝቄ የጠየቅኩህን ብቻ መልስ..........

እሽ ሁለቱም እዚህ አገር አይደሉም እሱ በስኮላርሽፕ ነው እዚህ ቪቪያን የምትማርበት ዩኒቨርሲቲ የመጣው እሱ ማስተርሱን እሷ ደግሞ ዲግሪዋን ስታጠና ተዋወቁ። በጣም መልካም ልጅ ነው። ከምነግርሽ በላይ ለ እናቱ ትልቅ ፍቅር አለው እንደ ህፃን ልጅ ነው በየሰዓቱ የምትደውልለት። አሌፍ ይሄ ነው በአጭሩ። ወይ አሌፍ ስሙ እንዴት እንደወጣለት ነግሮሃል ያው ማለቴ ይሄን ያክል ቅርርብ ካላችሁ? ሜሪ እያናደድሽኝ ነው የመጨረሻ ይሔንን እመልስልሻለሁ የምታውቂውን ሁሉ ትነግሪኛለሽ ጨርሻለሁ። ሕዝቅኤል ትንሽም ቢሆን ተቆጣ እና ወደ መልሱ ገባ። አሌፍ የአባቱም ስም ነው ግን አባቱ ስሙ እንዲጠፋ ስላልፈለገ ልጁንም ራሱን አሌፍ አለው። ይሔንን ነው የማውቀው አሁን የአንቺን እውነት ቀጥይ ምንም እንዳትደብቂኝ.....


በሩ ተንኳኩቶ ቪቪያን ገባች። ሜሮን ራሷ ስታያት በውበቷ ተገረመች። እንዴት ቆንጆ ነች ሕዝቄ አለች አንዴ ወደ እሷ አንዴ ወደ ሕዝቅኤል እየተመለከተች። አባ አለች ቪቪያን ብዙ አመት ተራርቆ እንደተገኘ ሰው አንገቱ ላይ እየተጠመጠመችበት።

እንግዳ አለን ቪ ተዋወቂያት ሜሪ ትባላለች አላት። ቪቪያን አፏን ያዘች ሜሪ??? ሜሪ የልጅነት ጓደኛክ??? እሷ ነች አባ አለች አይኗን በብርሃን እየተሞላ ። አው አላት ፈገግ እያለ። እሷም ላይ ሔዳ ተጠመጠመችባት። የኔ ቆንጆ ደሞ ስታምሪ አለቻት እሷም አገላብጣ እየሳመቻት። ደሞ ስለእኔ እንዴት አወቅሽ አለቻት ድንቅ እያላት። አባ በደምብ ነግሮኛል ደሞ አባየ እንዳለኝ በጣም ቆንጆ ነሽ ....

ወይኔ ሕዝቄ ምን አይነት ጣፋጭ ልጅ ነው የወለድከው ትላለች በስስት እየተመለከተቻት። ሜሮን ቪቪያን ከልቧ ወደደቻት። በቃ አክስቴ አንቺ እና አባ አውሩ እኔ ማሚን ላግዛት ብላ ጉንጯን ስማት ሔደች። ሜሮን ቃላቶች አጠራት ታድለህ ህዝቄ ....... አወ ልጄ በረከት ነች።በይ አሁን ነገሬን አታስረሽኝ ወደ ጀመርነው ጨዋታችን እንመለስ....


ሜሮን ሕዝቅኤል በቀላሉ እንደማይተዋት ስላወቀች አጠር አድርጋ ልትነግረው ወሰነች።
እሽ በ አጭሩ ይሔ አሌፍ ያልከው ልጅ ስሙ ሰሚር ነው እናቱ ደግሞ የሁለታችንም ጓደኛ ራቢያ ነች። ኡህህህህህ ሜሮን በረጅሙ ተነፈሰች።

ምንንን?!!!!

ሕዝቅኤል ራሱን ሊስት ተንገዳገደ።


ይቀጥላል.......

Join us @nibab_lehiwot
የእኔ ታሪክ (ምዕራፍ 2)

ክፍል -12

ሕዝቅኤልን አረጋግታ ካስቀመጠችው በኋላ ሜሮን ታሪኩን መናገር ጀመረች። አሌፍ ብሎ ስሙን ያስቀየረው አባቱ ነው።ምክኒያቱም ከሌሎቹ ልጆቹ አስበልጦ በሚባል ደረጃ በጣም ይወደው ነበር። ከልጆቹ አንዱ ኡስታዝ እንዲሆን ይመኝ ስለነበረ ሰሚር ደሞ እንደሚፈልገው አይነት ብሩህ አእምሮ ስላለው ገና በልጅነቱ ነው ቁራን መቅራት የጀመረው ፍጥነቱ ሼሆቹኝ ሳይቀር አስደንቋቸው ነበር። ያም ሆነ ይህ ግን አሌፍም ይሁን ሰሚር የአንተ ልጅ ነው። በህይወቴ እንደዚህ አይነት የነገሮች ግጥጥም አይቼ አላውቅም ።ሕዝቅኤል መንቀጥቀጥ ጀመረ።ሜ....ሜሮን አ ልገባሽም ቪ..ቪቪያን እና አሌፍኮ.... ተናግሮ ሳይጨርስ ራሱን ስቶ ወደቀ። ሜሮን ጮኸች....ቪቪያን........አንተ ሕዝቅኤል ....ቪ ቶሎ ድረሱ እያለች ማልቀስ ጀመረች። ቪቪያን እና እናቷ ጩኸቱን ወደሰሙበት ሮጡ ሕዝቅኤል ተዘርሮ ወድቋል። አባዬ......ቪቪያን ጮኸች....እናቷ ይባሱኑ ስታየው ደርቃ ቀረች ። ሜሮን ለአምቡላንስ ደውላ ሕዝቅኤልን ወደ ሆስፒታል ወሰዱት ።




የሜሮን ወንዱ ልጇም ያለችበትን ነግራው ወደ ሆስፒታል እየመጣ ነው። ድንገት የሆስፒታሉ በር ላይ ሰማያዊ አይኖች ያሏት ፀጉሯ በጀርባዋ የወረደ ልጅ እንባዋን እንደጎርፍ እያወረደች ተመለከታት። ሲያያት አንጀቱን በላችው.....አድርጎት የማያውቀውን አጠገቧ ተቀመጠ። ግን ምን ማድረግ እንዳለበት ስላላወቀ ዝም ብሎ ያያት ጀመር። ለትንሽ ደቂቃ ትኩር ብሎ ሲያያት ከቆየ በኋላ ለምንድን ነው ምታለቅሽው አላት ቃላቱን በመከራ እያወጣ። ልጅቷ ጭራሽ አጠገቧ ሰው እንደተቀመጠ አላስተዋለችም ነበርና ደነገጠች። እንባዋን እየጠራረገች አይ ምንም አለች(የጠረገችው እንባዋ ወዲያው እየሞላ) ። ይኸውልሽ ምን እንደሆንሽ አላውቅም ግን ያለምክንያት እንደማታለቅሽ አውቃለሁ ። ምንም ይሁን ምን ግን ጠንካራ መሆን አለብሽ ። የምታስታምሚው ሰው የአንቺ ጥንካሬ ያስፈልገዋል። ከመድሃኒት በላይ የሰውን ልጅ የሚያድነው ተስፋ እና ብሩህ ፊት ነው እሽ....ስለዚህ ሁለተኛ እንዳታለቅሽ .....ልጅቷ ፈገግ አለች አወ ልክ እንደሱ ብሏት እሱም ፈገግ እያለ ትቷት ወደውስጥ ገባ።



እማዬ አላት ወዳለችበት እየሮጠ። ሜሮን ተቀምጣ እያለቀሰች ነበር። ምንድን ነው እናቴ አጎቴ ምን ሆነ አላት እያቀፋት። ደህና ነው ልጄ ና ቁጭ በል እዚህ አለችው አጠገባ ያለ መቀመጫ እየጠቆመችው። ኤልሳ በጣም ደንግጣ ስለነበረ እንዲያረጋጋት ወደሷ ላከችው። እሱም የሜሮን ልጅ እንደሆነ ተዋውቋት አጠገቧ ከተቀመጠ በኋላ ከልብ በሆኑ ቃላቶቹ አረጋግቷት ተመለሰ። ሜሮን ሁሌም እሱን ስታይ የሚያስታውሳት አንድ ሰው አለ። ሙሉ በሙሉ በእሱ እምነት አላት። ኤልሳም ሜሪ ልጅሽን ፈጣሪ ይባርከው አለቻት ፈገግ እያለች። ቅድም ውጭ ያያት ልጅ ራሷን አረጋግታ ከውጭ ስትገባ ተመለከታት። ምክሬ ሰራ ማለት ነው አለ ከልቡ ደስ እያለው።

እማዬ አለች ቪቪያን አባቷ ወደተኛበት ክፍል እየተመለከተች። ነይ እዚህ አባትሽ ደህና ነው ይልቅ ሰው ላስተዋውቅሽ አለቻት ። ቪቪያን ዞር ስትል የምታውቀውን ልጅ አየችው። እሱም አያት ያውቃታል...... ተዋወቁ የ ሜሪ ልጅ ነው አለቻት። ቪቪያን ለሰላምታ እጇን ዘረጋችለት። ማቲያስ አላት እጇን እየጨበጠ ቪቪያን አለችው እሷም ፈገግ ብላ። (የማቲያስ እና የሜሮንን ታሪክ ከአባቷ በደምብ ስለምታውቅ በስሙ ገረማት)።


አንቺ አልቃሻ አላት ቀስ ብሎ ቪቪያን እንደማፈር ብላ ወደ ክፍሉ ዞረች።


አሌፍም የሕዝቅኤልን መታመም ሰምቶ
ሊጠይው ወደ ሆስፒታል ሲገባ ቪቪያን እና ማቲያስ እያወሩ ተመለከታቸው።


ይቀጥላል............

@nibab_lehiwot
እኔ ብቻ ነኝ ግን በዚህ ህይወት ደስተኛ ያልሆንኩት ???🤔

@nibab_lehiwot
የእኔ ታሪክ ምዕራፍ-2)

ክፍል- 12

አሌፍ በተረጋጋ መንፈስ በቀስታ እየ ተራመደ ወደእነ ቪቪያን ቀረበ። ቪቪያን ስታየው ልቧ ክፍል አለ። ሮጣ ሔዳ ተጠምጥማበት የአባቷን ህመም አብሮ ቢያስታምማት፣ ፀጉሯን እያሻሸ አይዞሽ አባባ ደህና ይሆናሉ ቢላት በወደደች ነበር። ግን አትችልም አሌፍ ራሱ አብረን መሆን አንችልም ብሎ ግንኙነታቸውን አቋርጦታል። ስለዚህ እንደምንም ራሷን አረጋግታ ተቀመጠች። አሌፍም ቪ ምን ሆነው ነው አባባ አላት ማቲያስን ከነመፈጠሩ ረስቶ። ራሱን ስቶ ነው ብላ ዝም አለች። ስብር ባለ ፊት አይዞሽ ፈጣሪ ይጠብቀዋል ብሏት ወደ ኤልሳ ሔደ። እሷንም እንዲሁ ካፅናናት እና ከሜሮንም ጋ ትንሽ ካወሩ በኋላ ሜሮን ማቲያስን ጠርታ አስተዋወቀችው። ግን የራቢያ ልጅ እንደሆነ ለማንም አልተናገረችም።


ከ 5 ሰዓታት ጥበቃ በኋላ ሕዝቅኤል ነቃ። ቪቪያን እና ኤልሳ ለመግባት በጣም ቢፈልጉም ቀድሞ ማግኘት የፈለገው ግን አሌፍን ነበር። አሌፍ ደግሞ ወጥቶ ከሄደ ቆይቷል። ስልክም ሲደውሉ ሊያነሳ ስላልቻለ ቪቪያን እና ማቲያስን ስራ ቦታው ጋ ሔደው እንዲያመጡት ሜሮን ላከቻቸው። በጉዟቸው ላይ ስለ ቤተሰቦቻቸው በጣም ብዙ አወሩ። ቪቪያን በሜሮን ተደነቀች ። ልክ ሕዝቅኤል ለ እርሷ እየነገረ እንዳሳደጋት ሜሮንም ለማቲ እንደዛ ሙሉ ታሪኳን እየነገረች እንዳሳደገችው ተረዳች። በጣም የሚገጣጠሙ አይነት ሰወች ሆነዋል። አባዬ ግን አሌፍን ይሔንን ያክል ለምን እንደፈለገው አልገባኝም አለች ወደ ማቲያስ እየተመለከተች(በጣም ቅልል ብሏት ነው የምታወራው) አትጨነቂ ምናልባት በጣም አስፈላጊ ስለሆነባቸው ይሆናል ይልቅ እንድናገኘው ፀልይ ........


ወደ አሌፍ ቢሮ ሲገቡ ማቲያስ እንደፈራው አላገኙትም የስራ ባልደረቦቹን ሲጠይቁ ቢሮ ብዙም ሳይቆይ እንደወጣ ነገሯቸው። ቪቪያን እሱን ሳትይዝ ላትመለስ ለራሷ ቃል ገብታለች ። ና ማቲ የት እንደሚገኝ አውቃለሁ ብላው ተያይዘው ወጡ።


ሕዝቅኤል ሜሮን እና ኤልሳን በደከመ ድምፅ እያናገራቸው ነው። ኤልሲ አ...አሌፍ...ልጄ... ነው ነገሮች ከመበላሸታቸው በፊት ....እባክሽ...አስቁሚያቸው......ይላታል ድምፁ ቁርጥ...ቁርጥ እያለ ነው ከመቼውም በላይ ውስጡ ሲደክም ይሰማዋል ለሞት ዳር ዳር እያለ እንደሆነ ባይናገረውም ታውቆታል። ኤልሳ የሰማችው ነገር በጣም ቢያስደነግጣትም ለእሷ ሕዝቅኤልን ከማጣት በላይ የሚያስፈራት ነገር የለም። እንዳይሞት በጣም ፈርታለች። ዝም በል ሕዝቄ እኔ ሁሉንም ነገር አስተካክለዋለሁ.....ስታወራ ይደክምሃል....አለች እየተርበተበተች። ለእሱ ያላት ፍቅር ሁሌም ቃላት ስለሚያሳጣው ከትዕዛዟ መተላለፍ አይፈልግም ቢያንስ በዚህ ልካሳት ይላል ሁልጊዜ ዛሬም እሽ ብሏት አሌፍ እስኪመጣ ዝም አለ።..
.





ቪቪያን እንደገመተችው አሌፍን ብቻውን ቁጭ ብሎ ሲያስብ አገኘችው ከማቲያስ ተለይታ ወደ ፊት ተራመደች ከጀርባው እንደቆመች የሽቶዋ መዓዛ ነገረው ፊቱን ሳያዞር ቪ ይቅርታ በጣም ልብሽን እንደሰበርኩት አውቃለሁ ግን ጠልቼሽ ሳይሆን ነገሮች ከመበላሸታቸው በፊት ማስቆም ፈልጌ ነው። እናቴን አማከርኳት በጭራሽ እንደዚህ አይነት ነገር እንዳላስብ አድርጋ አሳመነችኝ። የአንቺም አባት ተመሳሳይ ነገርን ነገረሽ ያለ እነሱ ፈቃድ የተመሰረተ ህይወት ደግሞ ሊሰምር እንደማይችል ደመደምኩ። ግን አቃተኝ አባባንም ላናግራቸው እቤት መጥቼ ቀጠሮ አስይዧቸው ነበር። ለምን እንደሆነ ታውቂያለሽ ቪ አንቺን መተው እንደማልችል ልነግራቸው እና በክብር አንቺን እንዲሰጡኝ ልጠይቃቸው ነበር ......ቪቪያን ዝም ብላ እንባዋን ማፍሰስ ጀመረች።ቪ አላት ፊቱን ወደሷ አዙሮ እየተንበረከከ። ሁሉንም ነገር እንተወው ፍቅር ከ ሀይማኖት፣ ከሀገር፣ ከአለም፣ ከሁሉም ነገር ይበልጣል አንቺም በ ሀይማኖትሽ እኔም በ ሀይማኖቴ መኖር እንችላለን ዋናው መሃላችን ያለው ፍቅር ነው። ልጆችንም ቢሆን በፍላጎታቸው እንዲወስኑ እንተዋቸዋለን ። በአንቺም በ እኔም እምነት ፍቅር ከሁሉም እንደሚበልጥ የሚያስተምር አምላክ ነው ያለን። ወንድ እና ሴት ብንሆን፣ ሙስሊም እና ክርስቲያን ብንሆን፣ ፍቅር ግን ያስተሳስረናል።

ማቲ ተገርሞ ይመለከታቸዋል። ቪ የ አባትሽን ታሪክ እንዳትደግሚው እፈራለሁ አለ በውስጡ።

የቪቪያን እንባ ፈስሶ የሚያልቅ አይመስልምተነስ አሌፍ አባባ አንተን ብቻ ነው ማናገር የፈለገው አለች እንደ ጅረት የሚንቆረቆረውን እንባ ለማስቆም በግድ እየታገለች።

አሌፍ እንደተንበረከከ እጇን አጥብቆ ያዛት።ቪ መጀመሪያ እሽ በይኝ አብረን እንሁን እባክሽ ወደ ፍቅር አለማችን ይዤሽ ልጥፋ የራሳችንን ሕይወት ከዛሬ ጀምሮ ሀ ብለን እንደ አዲስ እንጀምር.............

ቪቪያን ደነገጠች የልብ ምቷ ፈጠነ።


ይቀጥላል........

@nibab_lehiwot
እኔ እና አንተ.......

በዘመን በቅለን ከአንድ ውሃ ፈልቀን፣
በአንዲት ጨረቃ በፀሀይ ምለን፣
እንዳንለያይ ቃል የተጋባን፣
ዘመን ያፈራን አንድ አይነት ነበርን ፤


እኔ እና አንተ

እንደ ውቅያኖስ ሰፍተን የጠለቅን፣
እንደ ክዋክብት ከእልፍ የበዛን፣
እንደ አሸዋ ከቁጥር የላቅን፣
በአንድ ወቅት የነበርን አበቦች ነበርን፣

እኔ እና አንተ

በመኖራችን የተኗኗርን፣
በደስታችን ሀሴት ያደረግን፣
የተለያየን አንድ አይነት ነበርን፣


እኔ እና አንተ

የአለምን ውበት ጠልቀን የቀመስን፣
የነፍስ እስትንፋስ አብረን እፍ ያልን ፣
ከእውነት ጋራ በክንፍ የበረርን፣
ዘመን ያፈራን ውብ ፍሬ ነበርን።

ግን

እኔ እና አንተ አንድ አይነት እንጅ አንድ ስላልሆንን፣
ተሰበረና እህል ውሃችን፣
ደፈረሰብን ባንድ ያፈለቀን ንፁህ ውሃችን፣
ብርሀን ነፈገች ያማማለችን ውብ ጨረቃችን፣
ጥልቁ አሰመጠን ውቅያኖሳችን፤
ድንገት ጠፉብን ክዋክብቶቻችን፣
ጠወለጉብን አበቦቻችን፣
መደሰታችን ለሀዘን ሆነብን፣
ተለያየና እህል ውሃችን፣

ተበታተንን አንድ አይነት እንጅ አንድ ስላልሆንን ።
😉

bee
የእኔ ታሪክ ምዕራፍ -2

ክፍል -12

ቪ እባክሽ እሽ በይኝ .....አትወጅኝም እንዴ አሌፍ እንደተንበረከከ መለመኑን ቀጥሏል። ቪቪያን በእሽ እና እምቢ ውስጥ ግራ ገብቷት ቆማለች። በአባቷ እና በአሌፍ መሃል .....ድንገት አብራው መሆን እንደምትችል የነገራት ትዝ አላት........ እና ልትናገር ከንፈሮቿን ማንቀሳቀስ ስትጀምር ....እ....ማቲ መጥቶ አቋረጣቸው። ቪቪ አባባ አሌፍ ካልመጣ አላወራም ብሏል በጣም እየደከመ ነው እባክሽ እንፍጠን ስለምታወሩት ነገር በኋላ አውሩ አላት ፍጥን ፍጥን እያለ። አሌፍ ተነስ እንሂድ አለችው ከተንበረከከበት እጁን ጎትታ እያስነሳችው። (አሌፍ በዛ ቅፅበት ማቲያስን ጠላው።) ሶስቱም ተያይዘው ወደ ሆስፒታል ጉዞ ጀመሩ።






ሆስፒታል ሲደርሱ አሌፍ ብቻ ወደውስጥ ገብቶ ሌሎቹ ውጭ ጠበቁት። አባባ ደህና ኖት አለ የፊቱ መገርጣት እያስደነገጠው። ደ......ደህና ነኝ ልጄ... ለ ...ምን ነበር ልታናግረኝ የፈለግከው? ኧረ እሱ ቀስ ብሎ ይደርሳል መጀመሪያ ጤና ይበልጣልኮ
ልጄ ለሽማግሌ ነገ የሚባል ጊዜ የለውም አሁን ን...ገረኝ የሕዝቅኤል ድምፅ ቁርጥ ቁርጥ ይላል።
እ ስለ ቪቪያን እና ስለ እኔ ላናግርክ ነበር ። ብዙ አሳሳቢ አይደለም ቀስ ብሎ ይደርሳል አለ አንገቱን እያቀረቀረ። እምምምም እስኪ ለ እናትህ ደውልና አገናኘኝ አለ ሕዝቅኤል ውስጡ እየተጨነቀ። አሌፍ የሕዝቅኤል ሁኔታ ግራ ቢያጋባውም መጥፎ ነገር እንደማያደርግ በሙሉ ልቡ ስለሚያምነው እና ከምንም በላይ ስለሚያከብረው እሽ ብሎ ያዘዘውን አደረገ። ራቢያ አሶስት ጥሪ በኋላ ስልኩን አነሳችው ።እማየ አላት እንደሁሌው ሰሚሬ እንዴት ዋልክ ልጄ ዛሬ ሳናወራ ዋልንኮ ደህና ነህ አለች በስስት አነጋገር። ደህና ነኝ እማ ትንሽ ስላልተመቸኝ ነው የ ቪቪያን አባት ሊያናግርሽ ይፈልጋል አዋሪው ብሎ ስልኩን ሰጣው። ራቢያ ሰውየውን ባታውቀውም ደነገጠች እሷም የቪቪያንን እና የ ልጇን አንድ ላይ መሆን አጥብቀው ከሚቃወሙት ውስጥ ናት። ሰውየው ምን ሊለኝ ይሆን አለች በውስጧ። ሰ...ሰላም ለ አንቺ....አለ ሕዝቅኤል የልብ ምቱ እየፈጠነ። ራቢያ በቁሟ ደረቀች። ሔሎ ሔሎ...ራ .....ሊጨርሰው አለና መልሶ ዋጠው። ሕዝቄ......በህይወት አለህ? እንባ ተናነቃት..... እንደምንም ራሷን እየታገለች.....አንተ ነህ ሕዝቄ.....እውነት አንተ ነህ? አወ እኔ ነኝ ደህና እንደሆንሽ ተስፋ አደርጋለሁ። "ልጆቻችንም ሊጋቡ ነው እንኳን ደስ አለሽ ወይዘሮ ራቢያ" ቅስሙ ስብር ብሎ ነበር ይሄንን የተናገራት ምን ለማለት እንደፈለገ በደምብ ገብቷታል። የእርሷም ውስጥ ስብር አለ .... ምናለ ያኔ ባስተዋውቀው ኖሮ ወይ ራቢያ በቃ ችግር አያጣሽም አይደል ወይ ጣጣ ቻው አቶ ሕዝቅኤል ብላ ስልኩን ዘጋች።



ለስንት አመታት ሙሉ ድምፁን ያጠፋው ሕዝቅኤልን ከብዙ ጊዜ ጥበቃ እና ሀዘን በኋላ እንደሞተ ደምድማ ሀዘኗን አምና ተቀብላው ነበር። ድንገት ግን ሕዝቅኤል መጣ ያውም የሴት ልጅ አባት ሆኖ ለዛውም ደሞ ልጆቻቸው ጭራሽ ሊጋቡ ነው። ራቢያ ራሷን መቆጣጠር አቅቷት ወንበሩን ተደግፋ ማልቀስ ጀመረች። ለምን ? ለምን ይሄ ሁሉ.......


ትተዋወቃላችሁ እንዴ አለ አሌፍ ንግግራቸው ገርሞት .....አወ አሁን አወቅኳት ልጆች እያለን አንድ ላይ ነበር የተማርነው በጣም ጎበዝ ነበረች ይገርምሃል አለው። አሌፍ ግን ደስ የማይል ስሜት ተሰማው እናቱ ከዚህ በላይ ትልቅ ደረጃ መድረስ የምትችል ጠንካራ ሴት እንደሆነች ያውቃል......ባትወልድ ኖሮ!!!!


ሕዝቅኤል ሊሞት እንደሆነ እየተሰማው ስለሆነ ምንም ጊዜ ማጥፋት አልፈለገም።ከዚህ በኋላ ዝም በማለት የማሳልፈው ጊዜ የለኝም አለ በውስጡ።

አሌፍ አባትህ ግን ስለ አንተ ምንም ነገር ነግሮህ አያውቅም?

አልገባኝም ምን አይነት ነገር አለ ግራ እየተጋባ .....

ታሪካቸውን አባትህ እና እናትህ እንዴት እንደተገናኙ አንተ እንዴት እንደ ተወለድክ ?

አይ አባቴ ለዛ ጊዜ አልነበረውም ባይሆን እናቴ ግን ነግራኛለች። አለ...

እንዴት ነበር የተወለድከው?



ይቀጥላል............
@nibab_lehiwot
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ጌታ ምን ላድርግልህ ቢለኝ ልቤን አሳይልኝ ነበር የምለው ልቤ ውስጥ ብገልጠው ያመኛል ብዬ የሸሸግኩት እልፍ ደብዳቤ ነበረ

ጌታዬ ሌላ ምን ላድርግልህ ቢለኝ ተንበርክኬ እሷን ስለሰጠኸኝ አመሰግናለሁ ያልኩትን የምስጋና ፀሎት አሳይልኝ እለው ነበር

አሁንም ሌላ ምን ላድርግልህ ቢለኝ እሷ ያልነበረች ግዜ አረማመዴን እና ልቤ ውስጥ የተንከላወሰውን ሃሳብ አሳይልኝ እለው ነበር

      እሱ ግን ምን ላደርግልህ ብሎ አይጠይቀኝም ...እኔ አድርግልኝ ብዬ ልጠይቀው ሳሰፈስፍ ስጣደፍ

ልጃቸው ሊሞትባቸው አኑርልኝ የሚሉ ፀላይ፣ ልጄ ሳያድግ አትግደለኝ የሚል አባት ፀሎት ፣ ፍትህ የሚሹ ብዚ ነብሶች ፣ ርሃብ ጠፍሮ ይዟቸው አንድ ጉርሻ ብትቸረኝ የሚሉትን
እውነታቸውን በገነዘብ የተቀሙ እልፍ ደካሞችንአምላክን በተማፅኖ የሚኖሩትን  ሰዎች ወረፋ  አስቀድማቸዋለሁ 

የኔ ጥያቄ ቅንጦት ይሆን? እላለሁ

ምን አልባት ልባችን ላይ ያለው መሻት ቢመዘን እኩል ይሆን?  ይሆናል ማን ያውቃል ?
የኔ ጥያቄ ከሌላው ጋር ሲስተያይ ቅንጦት ይመስለኛል ብዬ አስብና መሻቴን ገታለሁ🙃

Miraዥ
የእኔ ታሪክ (ምዕራፍ-2)

ክፍል-14

አወ እኔ ነኝ የራቢያ የድሮ ፍቅረኛ የአንተም አባት .....

ማለት አልገባኝም አባባ በሽታው ነው ወይስ በትክክል ጤነኛ ኖት ? አሌፍ ግራ ገብቶታል...የሚይዝ የሚጨብጠውን አጣ ....በዛ ሰዓት ውሸቱን እንደሆነ ማመን ብቻ ነበር የፈለገው ወደ ራቢያ በድጋሚ ደወለ...... ራቢያ ፈራችው የሆነ ነገር እንደተፈጠረ ልቧ ነግሯታል .......ልጄ.. አለች ፈራ ተባ እያለች

እማዬ አባቴ ማን ነው ???? ቀጥተኛ መልስ ነው ምፈልገው ምንም እንዳታስተባብይ....ቶሎ በይ.....ራቢያ በቁሟ ራደች። እ...ቆይ አንዴ..... እሱ......እማዬ ዝም በይ!!!! አሌፍ በህይወቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ጮኸባት። አባቴ አቶ ሕዝቅኤል ነው አይደለ??? መልሽልኝ እንጅ አወ ወይም አይደለም በይኝ ወላሒ ለአዚም ካልሆነ ደግመሽ አይኔን አታይው!! የአሌፍ ጩኸት ሕዝቅኤልን ራሱ በትንሹ አስፈራው። ራቢያ አማራጭ ስላልነበራት "አወ" አለች። ረጋ ባለ ድምፅ አሌፍ የሚያደርገውን አጣ.....እማየ አሁንስ አንቺን መቋቋም በቃኝ!! አልቻልኩም ስልኩን ጆሮዋ ላይ ዘግቶ የወንድ ልጅ እንባ መታየት የለበትም የሚለውን አባባል እዛው ሻረው። ሕዝቅኤል ለማፅናናት እጁን ሰደደ። እንዳትነካኝ!!! እሱም ላይ ጮኸ እኔ አንድ አባት ብቻ ነው ያለኝ እሱም ሞቷል በቃ!! ማናችሁንም አልፈልግም አላምናችሁም ሁላችሁም ውሸታሞች ናችሁ.....አሌፍ ብሶቱን አንድ ላይ ዘረገፈው



ቪቪያን ሲጯጯሁ በመስኮት በኩል ስታያቸው ስለነበረ በሩን ከፍታው ገባች። አሌፍ እያለቀሰ ነበር....ምንድን ነው አሌፍ አለች አንዴ አባቷን አንዴ እሱን እየተመለከተች።
ሕዝቅኤል በደከመ ድምፁ ሊያፅናናው ቢሞክርም አሌፍ ጭራሽ መረጋጋት እየተሳነው መጣ ። ቪቪያን ወደሱ ስትጠጋ እንዳትነኪኝ እህቴ እያለ ሳቅ እና ለቅሶ ባዘለ ድምፅ ጮኸ!!!


ምንድን ነው አባዬ ራቢያ አፈጠጠችበት። በቃችሁ ዝም በሉ!!! ሕዝቅኤልም የቁጣ ጩኸቱን ለቀቀው ።(ሜሮን እና ኤልሳ ከውጭ ዶክተሮች እንዳይመጡ እየተጠባበቁ ነው። ማቲያስ ደግሞ ያልታወቀ ስልክ ተደውሎለት ሊያናግር እንደወጣ አልተመለሰም)

በሕዝቅኤል ቁጣ ክፍሉ ፀጥ አለ ያሁሉ ጩኸት በአንድ ጊዜ ጠፋ። ተቀመጡ ሁለታችሁም .....ቪቪያን እና አሌፍ የታዘዙትን አደረጉ። አንቺ ዝም በይ ምንም ድምፅ አልፈልግም። አንተ ደሞ ሙሉ ታሪክህን ስማና የምታደርገውን ታደርጋለህ....ትልቅ ሰው ነህ ከምንም ነገር ከልክየ አላድንህም። ከቁጣው የተነሳ ብቻ ሳይሆን ሊናገር ያሰበውን ነገር ቀድሞ የታወቃት ይመስል የቪቪያን እጆች መንቀጥቀጥ ጀምረዋል።


ሕዝቅኤል ለቪቪያን የነገራትን ሙሉ ታሪክ ለ አሌፍ አንድ በአንድ ነገረው። አወ በንግግሩ ቪቪያን አሌፍ ወንድሟ እንደሆነ አወቀች። ልቧ ስብርብር አለ፣ ክንፏን እንደተመታች ወፍ እዛው ባለችበት ተልፈሰፈሰች። እንደዛ ልታገኘው ስትጓጓለት የነበረችው ወንድሟ፣ እንደዛ አቅፎ እንደ ታናሽ እህቱ ፀጉሯን እንዲነካካት የምትመኘው ሰው የምታፈቅረው አሌፍ ነው። ገና ዛሬ ወንድሜ ባይሆንስ ለዘለዓለም ሳላገኘው ብቀር ብላ ተመኘች።


አሌፍ ሙሉ ታሪኩን ከሰማ በኋላ ምን አደረግን? ቆይ በምን ጥፋታችን ነው እንደዚህ የምታሰቃዩን? ምን አይነት ህይወት ነው የሰጣችሁን?? እህቴን እንዳፈቅር ኧረ ጭራሽ ባላውቅማ አግብቻት እንድኖር? ለምን???አሌፍ ከልቡ አምርሮ ሕዝቅኤልን መናገር ጀመረ።


ሕዝቅኤል እስኪጨርስ ዝም አለው። ቪቪያን ተናገሪ እንጅ ለምን ዝም ትያለሽ እያለ በእጁ ይገፋፋታል።ፈርተሽ ነው? የአሌፍ እንባ እንደ ጎርፍ ይወርዳል። ቪቪያን ግን ደንዝዛለች አትናገርም፣ አታለቅስም፣ ፀጥ ፍዝዝ፣ ብቻ።



ለ እኛስ ቀላል ነው? ብለህ ታስባለህ ኧ እስኪ ራቢያን ተመልከታት። ለ አንተ ብላ አይደለም በጊዜው የማትወደውን ሰው ያገባችው? ኧ አንተን ማስወጣት እና በሰላም ከቤተሰቧ ጋር መኖር አቅቷት ይመስልሃል? መልስልኝ?? አየህ ከክብሯ ፣ ከቤተሰቧ፣ ከማህበረሰቡ አንተን ስላስበለጠች እንጅ እንደ አንድ ተራ ሰው በ 2 እና 3 ሺ ብር አሽቀንጥራ ጥላህ እስካሁን ህልሟን አሳክታ እየኖረች ነበር። ይሄን እንዴት ማሰብ ያቅትሃል ስቃይዋ አይታይህም? ላንተ ስትል የተሸከመችው መከራ አይታይህም ወይ? ልታዝንላት ነበርኮ የሚገባው ....ምን ልትል እንዳሰብክ ይገባኛል" እኔ ፈልጌ አልመጣሁም" ልትል ነው አይደለ እንግዲያውስ እኔም ልንገርህ እኛም ፈልገን አልነበረም ያመጣንህ ድንገት ሳናስበው በተሰራ የአንድ ቀን ስህተት ነበር። ራቢያኮ አንተን ለመግደል ብዙ ምክኒያቶች ነበሯት። ጭራሽ እንደተፈጠርክ ለ እኔ ሳትነግረኝ ብቻዋን ስቃዩን ተሸከመችው። ለ አንተ ብቻ ሳይሆን እንደነገርኩህ ለ እኔም ታስብ ነበር። እስኪ አንድ ቀን በአንተ መወለድ ስታማርር ሰምተሃት ታውቃለህ? ወደኋላ ጎተትከኝ ብላህ ታውቃለች?? ሳትፈለግ የመጣህ ስህተት ....ብላህ ታውቃለች ወይ ንገረኝ?



አሌፍ አንገቱን ደፍቶ ፀጥ አለ።(ራቢያ ለ 50ኛ ጊዜ እየደወለች ነው።)
ታዲያ እኔስ አላሳዝንም ይሄ ሁሉ ሚስጥር ተደብቆብኝ ኖርኩ። ጭራሽ እህቴን አፈቀርኳት ከዛ ድንገት መጥታችሁ እህትህ ነች አላችሁኝ። ከዛስ....ቆይ አግብቻትስ ቢሆን...


ለሱ ነውኮ ፈጣሪን አመስግን የምልህ ቢያንስ የእኛን ታሪክ አልደገማችሁም። ለበጎ ነው ያገናኛችሁ ብለህ ተቀበል። አሌፍ ልጄ ከልጅነትህ ጀምሮ ባውቅህ እና ብንከባከብህ ምንኛ ደስ ባለኝ ነበር።ግን አልተፈቀደልንም ምን ማድረግ እንችል ነበር ሁላችንም የራሳችን ሕመም አለብን።


ይሔንን ሁሉ ለአሌፍ ሲያወራ ቪቪያንን ረስቷት ነበር። ወደሷ ዞሮ እርግብ ነይ ወደዚህ አላት ደመነፍሷን ሔዳ ታቀፈችው።

አሌፍም ተነስቶ ሔዶ ታቀፈው። ሕዝቅኤል በጣም ደነገጠ፣ ደስታም ተጨመረበት። እንደዚህ ይፈጠራል ብሎ በጭራስ አስቦት አያውቅም ነበር። ሁለቱን ልጆቹን በቀኝ እና በግራው አቅፎ የደስታ እንባን አነባ። ከብዙ አመታት በኋላ የተጣላውን ፈጣሪውን ቀና ብሎ በእንባ አይኑ አመሰገነው። ልጆቼ እርስ በርስ ተጠባበቁ። አለ በየተራ ግንባራቸውን እየሳመ።ከዚያም አይኖቹንም ሸፈነ። ያቀፏቸው እጆች ከትከሻቸው ሲንሸራተቱ ቪቪያን እና አሌፍ ቀና አሉ።

ይቀጥል ይሆናል........
@nibab_lehiwot
"ሀይቅ ዳር ተሰብስበው እንቁራሪቶች አብዝተው ስለጮኹ ሀይቁ የ እንቁራሪቶች ነው ማለት አይደለም፤ለ ክብራቸው ሲሉ ዝም ያሉ ብዙ ዓሳዎች ሀይቁ ውስጥ አሉ!"

ሎሬት ፀጋዬ ገ/መድሕን
መስራት እየቻልክ አትገምት ያለው ማን ነበር?🤔
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
አንድ ቀን ግን..........ሁሉም ነገር ፀጥ እንደሚል አውቃለሁ ትንፋሼን ጨምሮ!

✍️ me
በጣም ከምወዳቸው ነገሮች ይልቅ የምጠላቸው ነገሮች ብዙ ጊዜ አእምሮዬ ውስጥ ይመላለሳሉ።

@nibab_lehiwot
2025/05/12 19:08:40
Back to Top
HTML Embed Code: