Telegram Group Search
ሲጨንቅና በግራ መጋባት ውስጥ ሲኮን ሁሉም አማራጮች ትክክለኛ መፍትሄ ነው የሚመስሉት!

በበጎ አምሹ
"ሰው : ማለት?"
"ሰው : ሆኖ : የኖረ : ሰው : ነው!"

"የተወለደ : ሁሉ : ሰው : አይደለም!"
"ሰው : ለመሆን : ሰው : ሆኖ : መኖር : ያስፈልጋል!"

"ሰው : ለሰው : ተስፋው : ነው!"
"ሰው : የሰው : ሃብት : ነው!"

ከራስ ጋር ካደረኩት ንግግር የተቀነጨበ🙄
በበጎ ዋሉልኝ😍
መሮጥ : የት : ይቀራል! ከሁሉ : የሚቀድመው : መንገድ : መምረጥ : መንገድ : መጥረግ : እንጂ!

ባልታወቀና : ባልተጠረገ : መንገድ : መጓዝ : አንድ : ናቸው። ሁለቱም : መነሻ : እንጂ : መድረሻ : የላቸውም።

የጉዞ: ወጉ : መሄዱ : ላይ አይደለም። የሚኬድበትን : መንገድ : ማወቁ : ላይ : እንጂ!

በበጎ ዋሉ😍
ቀኔን በቀን አጠቀስኩት
ቀን እጄ ላይ ፈሰሰ ላስኩት
ጣቴ ጨቀየ መቆሸሽ ጨነቀው
የንጋት ገበታን መጉረስ አቃተው

የቀን ጥፍሬ አደገ
የቀኔን ዕድፌን አከከ
አለቅ አለ አልፀዳ አልፎከት
ለቀኑ ዕድፈት የቀን እጅ አለበት

እኮ እንዴት?
እኮ እንዴት?

በአቆሻሼ ቀን ልፅዳ?
የቀኔን ቂም በቀን ልርሳ?

የመርዝ ብልቃት ቢታጠብ
አምነው ውሃ ይጠጡበታል?
ለሞት የዳሮትን
ነፍሶትን አምነው ይሰጡታል?

እኮ እንዴት?

እኮ እንዴት በምን አቅም
የሳቄን ቀን በእንባ ላክም?

በአንዳንድ ቀን
የእንባ ቁስል በሳቅ አይደርቅም
ምክንያቱም!
ለሁሉም ቀን ቀን የለውም አቅም!
እስቲ በየ ፌስቡክ ገፆቻችሁ፣ በየቴሌግራም ቻናላችሁ ለጥፉልኝና የማይመለስ ውለታ ዋሉልኝ

ደውለው ይዘዙኝ የፈለጉትን መጽሐፍ ያሉበት ድረስ አደርሳለሁ።
አድማስ😍

በበጎ ዋሉልኝ🙏
ምጥ ቆንጅዬ ልጅ ለመታቀፍ የጉዞ ድልድይ ነው። ከተስፋ ጋር ለመወዳጀት የሃሳብም የድርጊት መንደርደር ነው።

ምጥ የመኖርን ጉጉት ያዘለ ስቃይ ነው።

ይከው አዲስ ቀን። ይኸው የምጥ ቀን። ይኸው ንጋት።

በቀን ንጋት ውስጥ እኛ ካንቀላፋን ምን ዋጋ አለው?
ከቀኑ እኩል እናምጥ። ከቀኑ እኩል እንንጋ።

በበጎ ዋሉልኝ😍
ይህ ወቅት ልዩነቶቻችንን ለአፍታም ቢሆን ሸሸት አድርገን በአንድ የምንሰለፍበት ጊዜ ነው። በመጎሻሸም ድል አይመጣም። በመወቃቀስ ድል አይገኝም። ለመተቻቸት፣ ለመወነጃጀል መቆምያ ያስፈልጋል። የምንቆመውም የምንኖረውም በኢትዮጵያ ነው። ሃገር ህልውናዋን እያጣች ጣት መጠቋቆም መወቃቀስ ምንድነው? ከሁሉ በፊት ሃገር ትቁም!

አድዋ ላይ ነጭን ድል ያደረግነው የውስጥ ሽኩቻዎች ሳይኖሩ ቀርተው አይደለም። በየቦታው የርስ በርስ ግጭቶች ነበሩ። የጋራ ጠላት ሲመጣ ግን ሁሉን ትተው በአንድ ቆሙ። በአንድነት ድል ነሱ! እስከዛሬ ድረስ አድዋ እያልን የምንኮራበትን፣ በነጭ ፊት የምናቀረቅርበትን ሳይሆን በክብር ቀና የምንልበትን የድል ቀን ጽፈውልን አለፉ።

ታሪክ ራሱን ይደግማል!

ከየቦታው ጦር ወደኛ እየተሰበቀ ነው። እንዴት ነው ይህን ጦር ልንጋፈጠው የምንችለው? እንዴት ነው ኢትዮጵያን እንድትቆምና የአርብ ስቃይዋን በትንሳኤዋ ልናፈካው የምንችለው? በመወቃቀስ? ጣት በመጠቋቆም? በፌዝ?

ሁሉም ልክ የሆነ ጊዜ አለው። ሁሉም በጊዜው ይጠየቅበታል። ከሁሉ በፊት ግን የሃገር ህልውና ይቀድማል!

ወደሞት እየሄድክ ስለውርስ፣ ስለገንዘብ አታነሳም። እግርህ እየተቆረጠ ስለጫማ አታስብም። ጫማ ለማድረግ እግርህ እንዳይጎዳ ከእንቅፋቶች መከላከል አለብህ! ወደድክም ጠላህም ያለሃገር መቆምያም መኖርያም የለህም!

በአንድ ሆነው መኖርያ ሃገራችንን፣ የክብር ጌጣችንን፣ ኢትዮጵያችንን ሊያጠፏት ሲመጡ በአንድ ሆነን እንመክታቸው። በመጎሻሸም ድል አይመጣም። በመወቃቀስ ድል አይገኝም።

እኛ ያለ ኢትዮጵያ ምንም ነን። ሁሉ ነገራችን የተሰፋው፣ ማንነታችንን የተሳሰረው ከኢትዮጵያ ጋር ነው። ስንቱን የጊዜ ማዕበል ተሻግራ መጥታ እኛ ጋር ስትደርስ አትፈርስም!

እኛ ኢትዮጵያዊያን ነን!
💚💛❤️

መላኩ ደምሴ!
Audio
🗣መላኩ ደምሴ

ቅንብር ናቲ
@gelana_gela
ማለዳዬ
ደህና አደራችሁ?

እስቲ "ገላና ገላ" የግጥም መጽሐፌን ያነበባችሁ የተሰማችሁን ስሜት ፃፉልኝ። በማለዳው ስሜታችሁን ጀባ በሉኝ። ስታነቡ የተሰማችሁን ስሜት! (ነቀፋም ወደሳም...)

በበጎ ዋሉ😍
ሳቂ እስቃለሁ
(መላኩ ደምሴ)

የንጋት ጥርስሽን
የሁለለት ኪዳን
የጀንበር ወጋግራን ብርሃንሽን ስትለቂ
ምርኩዝ ሰንበሌጤን
በፈገግታሽ ሰብረሽ
ዓለት ልታደርጊኝ (እድፍ) ልቤን ስትፍቂ

ሽሽ የሚል የሞት ቃል
ምላሴን ቆልፎ
ከነፍሴ ተኳርፎ ስጋዬን ሲደቃ
ትላንትሽን ገልጦ
እምነት ከከበበው
ከዘላለም ጎጆሽ ያንቀላፋው ኑረት ንጋትሽ ላይ ነቃ!

ምክንያቱም ስቀሻል

ድምቅ ካለው ሳቅሽ
የትኛው ስብራት
የቱስ የሞት ቃል ነው ደፍሮ ሚጋፈጠው?
ምንነትሽን ረስቶ
ብናኝ የሃዘን ጦር
ደጅሽ ላይ ኮልኩሎ ንጋትሽን ሚደፍረው?

ሳቂ

ስትስቂ

ቀኑን ቀን ሊያደርገው
በፈገግታሽ ፍንጣቂ
እንባውን ሊገፈው በእምነትሽ ታግዞ
ትላንትን እንዳይጥል
በዛሬ መሰላል
ሰገነት ላይ ወጣ ከጀንበርሽ ማሳ በሳቅሽ ሳቅ ይዞ!

ሳቂ!

በሳቄ ውስጥ ዛሬ ላይ ነገስኩ
ነገዬም ሲበራ አየሁ!
በእንባዬ ውስጥ ዛሬን ዘነጋሁ
ነገን ረሳሁ!

እንባና ሳቅ ፈተነኝ
ጉዞዬ ላይ አንገዳገደኝ!

ቆሜ አሰብኩ
አሰላሰልኩ

እርስ በርስ
ፊት ለፊት አጋፈጥኳቸው
እንዲከራከሩ
እንዲወያዩ
እንዲደባደቡ
እንዲሸናነፉ
የቀን እድል ሰጠኋቸው።

ደስታ ፊት ሃዘን አቅም አጣ
እንባ ሸሸ
ሳቅ ቀረበኝ
ፈገግ ስል ንጋት ከበበኝ!

ስቄ ዋልኩኝ
ስቄ ነጋሁ!

ዋሉማ😍
መ ና ፈ ቅ

ት ላ ን ት ን ነ በ ር ን!
እንለያይ ባልሺኝ ማግስት አዳሬን ሙሉ ሲያቃዠኝ አደረ።  ይሄ ቅዠት ትቶኝ ነበር። ባለሺኝ ሰዓት ሰላማዊ እንቅልፍ ተኝቼ ነበር ንጋትን በተስፋ የምቀበላት። አሁን ግን የመንጋትን ሚስጥር ማን ይነግረኛል? የወፎቹን ዜማ ማን ያሰማኛል?

ሄድሽ እንደ ድንገት። ሄድሽ እንደ ቀላል! ፍቅርን ጥለሽ! መውደድን ጥለሽ ሄድሽ! እንደ ቀልድ! በድንገት!

ካረፈበት የህይወት የገላ ከማረፍያ  ከፍራሹ ላይ ንጋት ቀስቅሶት ብድግ ሲል አይኑን መግለጥ ባይችል? ማየት ባይችል? ይሄን ስሜት ታውቂ ይሆን?

Melaku
ሌላ ግጥም ሌላ ሕይወት follow እያደረጋቹ ጋይስ😍
2024/04/28 08:29:47
Back to Top
HTML Embed Code: