Telegram Group Search
በዚህ ሲዝን ለማንችስተር ሲቲ ኬቨን ደብሩይን እና ኤርሊንግ ሃላንድ ፦

ደ ብሩይን ፦

21 ጨዋታዎች
6 ጎሎች
16 አሲስት

ኤስሊንግ ሃላንድ፡

40 ጨዋታዎች
32 ጎሎች
6 አሲስቶች

ልዩ 👏🏽🔥

SHARE @MULESPORT
ክርስቲያን ሮሜሮ በዚህ የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የውድድር ዘመን 5 ጎሎችን ማስቆጠር ችሏል።

ይህ ቁጥር የሚከተሉት አጥቂዎች ካስቆጠሩት የጎል ብዛት ይበልጣል፦

ጋብሬል ጄሱስ ፡ 4 ጎሎች
ሚሃይሎ ሙድሪክ ፡ 4 ጎሎች
ፓብሎ ሳራቢያ ፡ 4 ጎሎች
ማዱኬ ፡ 4 ጎሎች
አንቶኒ : 1 ጎል

SHARE @MULESPORT
የሳዑዲ ፕሮፌሽናል ሊግ ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ሚካኤል ኢማናሎ ኬቨን ደብሩይንን ከማንቸስተር ሲቲ ለማስወጣት እየሰሩት ሲሆን በሰኔ ወር 33 አመቱ የሚሞላው ቤልጄማዊው ተጫዋች የሳውዲዎችን ሀሳብ እስካሁን እንዳልተቃወመ ተገልጿል።

ዘ አትሌቲክስ

SHARE @MULESPORT
ሊቨርፑሎች በክረምቱ የዝውውር መስኮት የመሀል ተከላካዮችን መመልከት ጀምረዋል ቡድኑን ለማጠናከር ቅድሚያ ከሚሰጣቸው ቦታዎች አንዱ ነው።

በመጪዎቹ ሳምንታት ውስጥ ከአርኔ ስሎት ጋር ለመወያየት አማራጮችን እና ዝርዝርን በተመለከተ የውስጥ ድርድር በመካሄድ ላይ ነው።

- Fabrizio Romano

SHARE @MULESPORT
ሊቨርፑል ሞሃመድ ሳላህ እንደሚቆይ ይጠብቃሉ እና ከእሱ ጋር ቢያንስ አንድ ተጨማሪ የውድድር አመት እቅድ አውጥተዋል። በተጫዋቹ በኩል መልቀቅ የመፈለግ ምልክት የለም። ሳላህ በሚቀጥለው የውድድር ዘመን በሊቨርፑል ለመቆየት አቅዷል።

ዴቪድ ኦሬንስታይን

SHARE @MULESPORT
ቲያጎ ሲልቫ ቼልሲን ይለቃል !

ቲያጎ ሲልቫ በዚህ ሲዝን መጨረሻ እና ከ4 አመታት በኋላ ቼልሲን እንደሚለቅ አስታውቋል።

የ39 አመቱ ተከላካይ ቲያጎ ሲልቫ በ2020 ቼልሲን የተቀላቀለ ሲሆን ከዚህ ቡድን ጋር እንደ አውሮፓ ሻምፒዮንስ ያሉ ጠቃሚ ዋንጫዎችን ማንሳት ችሏል።

ቲያጎ ሲልቫ UEFA ሱፐር ካፕ እና የአለም ክለብ ዋንጫንም ማሳካት ችሏል።

ሲልቫ ለቼልሲ 151 ጨዋታዎችን የተጫወተ ሲሆን 9 ጎሎችን እና 3 አሲስቶችን ማድረግ ችሏል።

ፍሉሚንሴ የዚህ ልምድ ያለው ተከላካይ ቀጣይ መድረሻ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

SHARE @MULESPORT
አዲሱ የሊቨርፑል ስፖርቲንግ ዳይሬክተር ሪቻርድ ሂዩዝ የመሀመድ ሳላህ ፣ ቨርጂል ቫንዳይክ እና ትሬንት አሌክሳንደር አርኖልድ የኮንትራት ሁኔታን ያስተናግዳል። የሶስቱም ተጫዋቾች ውል በ2025 ያበቃል።

ዴቪድ ኦሬንስታይን

SHARE @MULESPORT
"ቼልሲ ለእኔ ትልቅ ትርጉም አለው"

በውድድር አመቱ መጨረሻ ቼልሲን እንደሚለቅ ያሳወቀው ቲያጎ ሲልቫ የስንብት ንግግር አድርጓል።

"ቼልሲ ለእኔ ትልቅ ትርጉም አለው እኔ እዚህ የመጣሁት ለአንድ አመት ብቻ ለመቆየት በማሰብ ነበር ግን እዚህ አራት አመት ሆኖኛል ፤ ለእኔ ብቻ ሳይሆን ለቤተሰቤም ጭምር።"

"ልጆቼ ለቼልሲ ይጫወታሉ ስለዚህ የቼልሲ ቤተሰብ አባል መሆን ትልቅ ኩራት ነው ፤ በተለይ ልጆቼ እዚህ ስላሉ። ብዙ ተጫዋቾች ሊሳተፉበት በሚፈልጉበት በዚህ አሸናፊ ክለብ ውስጥ ህይወታቸውን እንደሚቀጥሉ ተስፋ አደርጋለሁ። "

"ይመስለኛል በአራት አመታት ውስጥ ሁል ጊዜ ያለኝን ሁሉንም ነገር እሰጥ ነበር ፤ ግን በሚያሳዝን ሁኔታ ሁሉም ነገር መጀመሪያ ፣ መሀከል እና መጨረሻ አለው።"

"ይህ ማለት ግን ይህ በአጠቃላይ መጨረሻ ነው ማለት አይደለም ፤ በቅርብ ጊዜ ውስጥ በሌላ ሚና መመለስ እንድችል በሩ ክፍት እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ።"

"ግን ይሄ ሊገለጽ የማይችል ፍቅር ነው። እና አመሰግናለሁ ብቻ ነው የምለው"ሲል ቲያጎ ሲልቫ ተናግሯል።

SHARE @MULESPORT
ሞሃመድ ሳላህ በሊቨርፑል እንደሚቆይ ይጠበቃል። ውሉን ለማደስ ድርድር በቅርቡ ይጀመራል።

- ፖል ጆይስ

SHARE @MULESPORT
Forwarded from Post Bot
ሄኒከን የተለያዩ አጓጊ የሆኑ ሽልማቶችን አዘጋጅቶ በየሳምንቱ እጅ ከስጦታ ይሎታል።
እርስዎሰ ባለ እድል ለመሆን ምን ይጠብቃሉ?
ይምጡ ሊንኩን በመከተል ይቀላቀሉ የቀረቡ ጥያቄዎችን በመመለስ ሰጦታዎችን የግልዎ ያድርጉ።

@HNKQuizBot

መልካም እድል!
ሙሌ SPORT
Photo
"ሪያል ማድሪድን አሸንፈን ወደ ዌምብሌይ መሄድ እንፈልጋለን።

ጀርመናዊው የባየር ሙኒክ አሰልጣኝ ቶማስ ቱሄል ነገ በአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ግማሽ ፍፃሜ መርሀ ግብር ከሪያል ማድሪድ ጋር ከሚያደርጉት ጨዋታ በፊት በጋዜጣዊ መግለጫ ስለጨዋታው ንግግር አድርጓል።

የአልያንዝ አሬና ድባብ?፦ "ፍጹም ፍፁም የሆነ ድባብ እንፈልጋለን። ከአርሰናል ጋር የነበረው ድባብም ጥሩ ነበር ነገም የተሻለ ሊሆን ይገባል። በተለይ አካሄዱ ከባድ በሚሆንበት ጊዜ የተመልካቾችን ድጋፍ እንፈልጋለን።"

"ጫናዎችን መቋቋም ያለብንን ደረጃዎች ለማለፍ ከፍተኛ ድጋፍ እንፈልጋለን። ከታዳሚው ጋር በመሆን ታላቅ ድባብ መፍጠር አለብን።"

"ይህ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ እንደ ፍፃሜው ነው። የእኔ አቀራረብ እንደ ፍጻሜ ወደ ሜዳ መሄድ ነው። አሁንም የመልሱ ጨዋታ ቀርቷል በሚል አስተሳሰብ አንጫወትም። ይህንን ጨዋታ ለየብቻ ማጤን እንፈልጋለን።"

"ወደ ዌምብሌይ ደርሰን ሻምፒዮናውን ማሸነፍ እንፈልጋለን። እኛ ዝግጁ ነን እናም ብዙ በራስ መተማመን አለን። አርሰናልን ያሸነፍንበት ጨዋታ አስፈላጊ ነበር። አሁን ቀጣዩ እርምጃ ሪያል ማድሪድ ላይ ነው። ይህን በማለፍ ወደ ዌምብሌይ መድረስ እንፈልጋለን። በነገው ጨዋታ ላይ አተኩረን ጥሩ ዝግጅት ማድረግ አለብን።"

"ሪያል ማድሪድ ሁለት ጊዜ ከቼልሲ እና ከዚያ በፊት ከፓሪስ ሴንት ዠርሜን እና ዶርትሙንድ ጋር ገጥሞኛል። ከቼልሲ ጋር ካለፈው ጨዋታ ጋር ሲወዳደር በጣም የሚታየው ልዩነት የካሪም ቤንዜማ አለመኖር ነው። በወቅቱ የሪያል ማድሪድ ዋና ማዕከል ነበር።"

"ባየርን ከ ሪያል ማድሪድ በእርግጠኝነት ሁላችንም በጉጉት የምንጠብቀው ትልቅ እና የተከበረ ጨዋታ ነው። ይህ በቻምፒየንስ ሊግ የግማሽ ፍፃሜ ውድድር ነው። ብዙ ደስታ አለ።"

ጁድ ቤሊንግሃም? "ጁድ ድንቅ እድገት ያደረገ ድንቅ ተጫዋች ነው። እዚህ ደረጃ ላይ መድረስ የምትችለው በታላቅ ባህሪ ብቻ ነው። በሪያል ማድሪድ የሚጫወት ማንኛውም ሰው በዚህ ማሊያ ጫና እና ክብደት ይጫወታል። ቤሊንግሃም ቁልፍ ተጫዋች ነው። እሱን ለመያዝ መፍትሄዎችን ለማግኘት እየሞከርን ነው።"

የካርሎ አንቸሎቲ ጉዳይ?፦ "ካርሎ በተጫዋችነት እና በአሰልጣኝነት ለእግር ኳሱ ያደረገው ነገር አስደናቂ ነው። ሌጀንድ ነው። ግን አሁንም በጣም ጨዋ እና ትሑት ነው። ይህ ድንቅ ነው። ሌላ የሊግ ዋንጫ ለማሸነፍ ከጫፍ ደርሷል እና በቻምፒየንስ ሊግ ግማሽ ፍፃሜ ላይ ይገኛል።"

ነገ ግባሪ ሪያል ማድሪድ ላይ ጎል የሚያስቆጥር ይመስልካል?"አዎ ይሆናል. እንዴት እንደሆነ አላውቅም ግን እርግጠኛ ነኝ ያስቆጥራል"ሲል ቱሄል ተናግሯል።

SHARE @MULESPORT
"ሁለት ትልልቅ ክለቦች ይገናኛሉ"

ጀርመናዊዉ የባየር ሙኒኩ ኮከብ ጆሽዋ ኪሚች ነገ ከሪያል ማድሪድ ጋር በሜዳቸው ስለሚያደርጉት ወሳኝ ጨዋታ በጋዜጣዊ መግለጫ ንግግር አድርጓል።

"ሁለት ትልልቅ ክለቦች ይገናኛሉ። ሪያል ማድሪድ በጣም ልምድ ያለው እና ከፍተኛ ጥራት ያለው ቡድን ነው። ከሊፕዚግ እና ከሲቲ ጋር በተደረጉት ጨዋታዎች ብልጫ አልነበራቸውም ነገርግን በጥንካሬያቸው እና በጥራት ስለሚያምኑ ማለፍ ችለዋል። እኛ በጠንካራ ጎኖቻችንም ማመን አለብን።"

በዌምብሌይ ወደ ፍጻሜው ለማለፍ ያለው ተነሳሽነት? ፦ "የ2020 ፍፃሜው ያለ ተመልካች ነበር ስለዚህ በዚህ ጊዜ ከደጋፊዎች ጋር ልናጣጥመው እንፈልጋለን።"

"በግማሽ ፍፃሜው ላይ ነን እና ወደ ፍፃሜው ለመድረስ ትልቅ እድል አለን። ትኩረታችን በነገው ጨዋታ ላይ ሲሆን የመልሱን ጨዋታ በጥሩ ሁኔታ ለመቀበል ጥሩ ውጤት ማምጣት እንፈልጋለን።"

ከሪያል ማድሪድ ጋር ጨዋታ?፦ "በእርግጠኝነት የተለመደ ጨዋታ አይሆንም። የቻምፒየንስ ሊግ የግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ ሁሌም ልዩ ነው ፣በተለይም ትልቅ ክለብ ከሆነው ሪያል ማድሪድ ጋር።"

"በእግር ኳስ የሚደሰት ማንኛውም ሰው በባየር እና ሪያል ማድሪድ መካከል የሚደረገውን የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታ መመልከት ይፈልጋል።"

"ለመዘጋጀት ብዙ ጊዜ አልነበረንም። የሪያል ጥንካሬዎች ኳስን በማቀበል ላይ ናቸው። ጥሩ መከላከል አስፈላጊ ነው ነገርግን አሁንም በፍርሃት መጫወት የለብንም ደፋር እና የኳስ ቁጥጥር ሊኖረን ይገባል።"

ካርሎ አንቸሎቲ?፦ "አንቸሎቲ አሁንም በሪያል ማድሪድ በጣም ስኬታማ ነው። በነበረበት ቦታ ከሞላ ጎደል ስኬታማ ሲሆን ቻምፒዮንስ ሊግን ብዙ ጊዜ አሸንፏል"ሲል ጆሽዋ ኪሚች ተናግሯል።

SHARE @MULESPORT
የሪያል ማድሪዱ አሰልጣኝ ካርሎ አንቸሎቲ የላሊጋው የወሩ ምርጥ አሰልጣኝ ተብለው ተመርጠዋል።

SHARE @MULESPORT
የኤሲ ሚላኑ ግብ ጠባቂ ማይክ ሜይጋን ከባድ ጉዳት አጋጥሞታል እናም ከሜዳ የሚርቅበት ጊዜ በቅርቡ ይታወቃል።

SHARE @MULESPORT
አርዳ ጉለር ስለ ደስታ አገላለፁ ተጠይቆ ፦

"የጎል ደስታዬ አገላለጽ በአላህ ላይ ያለኝን እምነት ያሳያል።"

SHARE @MULESPORT
"በ ሻምፒዮንስ ሊጉ ሁሉም ጨዋታዎች በጣም ከባድ ናቸው"

የራያል ማድሪዱ አማካይ ፌዴሪኮ ቫልቨርዴ ነገ ከባየር ሙኒክ ጋር ስለሚያደርጉት ጨዋታ በጋዜጣዊ መግለጫ ንግግር አድርጓል።

"በ ሻምፒዮንስ ሊጉ ሁሉም ጨዋታዎች በጣም ከባድ ናቸው። ሁሉንም ተጋጣሚዎች እናከብራለን በተለይም ባየር ሙኒክን እናከብራለን። በታሪክም በዚህ ውድድር በጣም ጠንካራ ቡድን ናቸው። ማን ሲቲን ባከበርንበት መንገድ እነሱንም እናከብራቸዋለን።"

"ከማን ሲቲ ጋር በነበረው ጨዋታ ፔናልቲ ለመምታት ዝግጁ አልነበርኩም ፤ ደክሞኝ ነበር አንዳንዴ ኢጎህን ወደ ጎን ትተህ ታማኝ መሆን አለብህ ወደ መኝታ ስሄድ ተፀፅቼ ነበር ፤ እንደገና በዚህ ሁኔታ ውስጥ ላለመግባት ጠንክሬ እሰራለሁ።"

"ከቶኒ ክሩስ ጋር መጫወት እወዳለሁ ፤ በጣም ጥሩ ግንኙነት አለን ፤ እንደ እሱ ካለ ተጫዋች ብዙ የምንማረው ነገር አለ።"

"ስለ ሃሪ ኬን? "በአለም ላይ ምርጡ ተከላካይ መስመር አለን ለተከላካዮቻችን ያለንን አድናቆት ማሳየት አለብን።"

"ማን ሲቲን ከውድድሩ ለማሰናበት ጥሩ ስራ ሰርተናል። እድለኛ ስለሆንክ ብቻ እንደዚህ አይነት ቡድኖችን አታሸንፍም።"

"በጣም በትልቅ በራስ መተማመን ይዘን ወደ ባየርኑ ጨዋታ እንሄዳለን ፤ በራሳችን እናምናለን"

" ካርሎ አንቸሎቲ በጣም ረድቶኛል ፤ እሱ የቡድናችን ቁልፍ አካል ሆኖ ቆይቷል። እያንዳንዱን ተጫዋች እንዴት ማሻሻል እንደሚችል ብዙ ሃሳቦችን ይዟል። በሱ በጣም አምናለሁ።"

"ለሪያል ማድሪድ መጫወት በጣም ቆንጆ ነገር ነው ፣ አንድ የእግር ኳስ ተጫዋች ሊያጋጥመው የሚችለው እጅግ የሚያምረው እድል ይሄ ነው"ሲል ፌዴሪኮ ቫልቨርዴ ተናግሯል።

SHARE @MULESPORT
"ባየር ሙኒክ ድንቅ ቡድን ነው"

ጣሊያናዊዉ የሪያል ማድሪድ አሰልጣኝ ካርሎ አንቾሎቲ ከባየር ሙኒክ ጋር ስለሚያደርጉት ጨዋታ ንግግር አድርጓል።

በ2014 ባየርንን ስለ ማሸነፋቸው? "ያ በጣም ጥሩ ታሪክ ነበር ነገር ግን ነገ ሌላ ጨዋታ ነው ጠንካራ ተጋጣሚ እየገጠመን ነው።"

"እዚህ በመሆናችን በጣም ደስተኞች ነን ፤ በዚህ የፕሬስ ክፍል ውስጥ ያሉትን ጨምሮ ብዙ ሰዎች እዚህ እንደምንሆን ያላሰቡ አሉ።"

"ወደ ፍፃሜው ስለማለፍ? "በራሳችን እናምናለን የማሸነፍ ብቃት እንዳለን እናውቃለን ግን ባየርንን ማክበር አለብን። ምርጥ የውድድር ዘመን አላሳለፉም ግን አሁንም አደገኛ ናቸው።"

"ባየርን ድንቅ ቡድን ነው በፕሪሚየር ሊጉ አናት ላይ ከሚገኘው እና በዚህ ሲዝን በጣም ጠንካራ ከሚባለው አርሰናል ጋር በሚገርም ሁኔታ ጥሩ እንቅስቃሴ አድርገዋል።"

"ሪያል ማድሪድን በቻምፒየንስ ሊጉ ላይ በፍፁም አቅልለህ ማየት የለብህም።"

አንቾሎቲ ስለ ሙኒክ ቆይታው? "እዚያ ብዙ አስደሳች ትዝታዎች አሉኝ። ጀርመንኛ ቋንቋ ሙሉ በሙሉ ረስቻለሁ ግን ሙኒክ ለመኖር የምትችልባት ድንቋ ከተማ ነች። ጀርመንኛን በደንብ ባለመማሬ ግን ተፀፅቻለሁ።"

"የባየር ሙኒኩን ጨዋታ እንዴት እንደምንጫወት በጣም ግልፅ የሆነ ሀሳብ አለኝ። ስልታችንን አጥብቀን የጨዋታ እቅዳችንን እንደታቀደው መፈፀም አለብን።"

"የአሰልጣኝ ሚና ሁሌም በጣም አስፈላጊ ነው ነገር ግን ሁሉም አሰልጣኝ ተጫዋቾቹ ቁልፍ መሆናቸውን ይረዳል።"

"ቱሄል ምርጥ አሰልጣኝ ነው። የሚገርም የታክቲክ ደረጃ ያለው ፣ ታላቅ ፕሮፌሽናል ነው። ለእሱ ትልቅ ክብር አለኝ"ሲል አንቾሎቲ ተናግሯል።

SHARE @MULESPORT
የሳውዲ ቡድኖች በዚህ ክረምት 5-6 ተጨማሪ ግዢዎችን ማድረግ ይፈልጋሉ፣ ለእነዚህ ግብይቶች ወደ 2 ቢሊዮን ፓውንድ ተመድቧል።

- ቤን ጃኮብስ

SHARE @MULESPORT
ዴቪድ ኦሬንስታይን እንደገለፀው ማንቸስተር ዩናይትድ ማርከስ ራሽፎርድን አይሸጥም ልዩ ጥያቄ ካልመጣ በስተቀር የእንግሊዙ ክለብ ተጫዋቹን ጥሩ አቋሙን መልሶ እንዲያገኝ መርዳት ይፈልጋል።

SHARE @MULESPORT
2024/04/30 01:10:25
Back to Top
HTML Embed Code: