ለካ ከሆነ ቀን ሳምንት ወር አመት በኋላ እኔ የኔ አልነበርኩም ሁሉ ነገሬን ሌላ እኔ ያልኩት ውስጥ አኑሬው ነበር ታዲያ አሁን ምን ይብጀኝ
ንጋቴም ምሽቴም የኔ ባልኩት ውስጥ ሆነና እሱን ሳጣ እሆነው ጠፋኝ ያ ሰአት እስኪያልፍ ምን ልሁን ከእለትም ሠአት መርጦ አንድ ሁነት መፈለግ ሽታ ጠረን ድምፅ ምስል ወደኔ ገዝፎ ይመጣል እሆነው ይጠፋኛል ማለዳ ከወፍ ቀድሜ እነቃለሁ እራሴን አብሰለስላለሁ ሰአት አያለሁ በቃ ቀኑ ይውልና ቀትር ማብቂያ ላይ ሌለ ግዙፍ የመፈለግ ህመም መቶ ነፍሴ ላይ ይቀበቀባል አለኝ የምለው ሁሉ በአንድ ምስል የተሞላ ነው ለካ ቤቴ ጊዜዬ ቦታዎቼ የማልፍበቸው ጎዳኖች የጎዳናው እጥፋት ውስጥ የታጠፈ እምነት ይዞ ያጮልቁብኛል የጎዳና ዳር ያኔ በደስታ ያዜምኳቸውን ሙዚቃዎች እያንቧረቁ ይጠዘጥዙኛል የት ልሂድ የት ልከለል ሁሉን ሸሸሁ ቤቴን ዘጋሁ ከሁሉም ልቆ ቤቴ ውስጥ ገነነ ከመቀመጫው ላይ ከጠረጴዛው ላይ ከአልጋው ከትራሱ ላይ ከመብያ መጠጫው ላይ .....
ሌት 06:49

ሠብልዬን
ለትንሳኤ የሚባቃ አኗኗር የለኝም ይህን አውቃለሁ ይቅር በለኝ ብዬ አልለማመጥህም ይቅር ማለት ሳልችል ምህረትህን አልጠብቅ አንተም ደና ሁን እኔም ደና አልሆንም
እንዴት ነው ተረትህ ?
ደሃ ድህነቱን ይረሳ ዘንድ ወይን ይጠጣ
የወይን ዋጋ ሠማይ ወጣ
እና በቃ ድህነታችንን አንርሳ ?
ወይ አበሳ !
ይታይልን ዳግም ለግዜር አመልክቱ
ወይን ተወዶብናል ፍረድልን በሉ

ሠብልዬን
በየ ህይወት ሽንቁራችን ለሠዎች መከራን አፈሰስን ደስታና ሃሴት በከበበን ጊዜ ያ መከራችንን ያፈሰስንበትን ሽንቁር ደፈንን ! በቃ ሠው መሆን ይህ ነው ? ሠው ነኝ እያሉ ደሞ ሠውነትን እያራከሡ ፅንፍ ወደሌለው ወደራስ ውስጥ ዝቅጠት መውረድ ከዛ የሠውነት የዝቅጠት ማጥ እየጨለፉ ተስፍና እምነትን እውነትና ቃልን የጨለማ ግርፍ መግረፍ ..ልንሠማ የማንወደውን ካወራን የምናረገውን ካልገራን ቀና ማለታችን የሚሠማን ሌሎችን አስጎንብሰን ደፍጥጠን ከሆነ እስከምን ? የምንችለው ይህን ብቻ ነው ?ሲያሻን ብቻ የግዜር አምሳል ገፁ ነኝ ብሎ መፎከር እለት እለት በዲያቢሎስ ገፅ ምድር ላይ መፍሰስ እንደው ለቧልቱ እግዜርን መጥቀስ በቁም ነገሩ በሴጣን መገለጥ .... የኔ እምነት ሴጣን ይሉት ነገር የለም !!!!!!! ምኞትና ምክንያታችን ነው ዲያቢሎስ አርጎ የቀረፀን ። ሴጣን ይሉት የለም ምኞት መፈለጋችን ምክንያት አለመርካታችን ነው ከሰው መሆን የነጠለን
ሴጣን የለም ሰው ነው ሴጣን!!
መግቢያ :- መምጣት
የሚመስለንን ልንጨዋወት የቀጠሮ ካርዳችንን ሠደድንላችሁ
ስትመጡ እጅ ከምን ነውና ተፅፎ የተቀመጠ ግጥም ካላችሁ ያዝ አርጋችሁ እማወጋችሁም አለ ካላችሁን በጄ ማንጎርጎርም ካሻችሁ ምን ገዶን ጎሮሯችሁን ጠረግ አርጋችሁ ከች ...የጋራ መድረክ ነው የደገስነውና ሽር ብለን እንገናኝ
ቸር ይግጠመን....
እንደው በፈጣሪ ይህንን ቻናል ሰፕስክራይብ አድርጉ፡፡ ክበሩልኝ፡፡ ውለታችሁ አለበኝ፡፡
endalegeta multimedia እንዳለጌታ መልቲሚድያ
https://youtube.com/@endalegetamultimedia?si=hEO0egZkKPtR1mv0
የዘንድሮውን አድዋ እንደ ጥምቀት ልንደግስ ወደናልና ልትቀላቀሉን የፈቀዳችሁ በዚህ ቤተሰብ ሁኑን
https://www.tg-me.com/adwaadewa
አንዳንዴ እምኖረው እውነት አይመስለኝም
የምር የምሬን ባንኜ መንቃት እመኛለሁ ቅዘት የሆነ ህይወት ውስጥ መች እንደሰመጥኩ አላውቅም

ድንገት ጩህ ጩህ ይለኛል እበድ እበድ
እብደት ነፃነት ነው እንዴ


ደጋግሜ የኮምፒውተርሬን ዲሌት የሚለውን በተን ደጋግሜ እጫናለሁ ውስጤን ጥፋትፋት ቢያረግልኝ እየተመኘሁ

ለሠው ግን ያስፈልግ ነበር እኮ shift + Delete

ይሄንንም ከእድሜዬ ላይ ቀንሶ አያፍርም እኮ ሞት ይመጣ ይሆናል

ማነው የኔን መኖር እቁብ የበላ የተበላ መኖር እና እድሜ ላይ እንዳይሆን የምገፈግፈው
የበአል ለት የማይመለከታችሁነሰ መመልከት ለበቃችሁ እነሆ በረከት ብለናል
2024/06/19 17:11:58
Back to Top
HTML Embed Code: