#የሰሙነ_ሕማማት_ሰኞ

#መርገመ_በለስ የተፈጸመበት ዕለት ነው

ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሆሣዕና ዕለት ቢታንያ አድሮ በማግሥቱም ከቢታኒያ ሲመጡ ተራበ፡፡ (ማር.11፤11-12) ቅጠል ያላት በለስ ከሩቅ አይቶ ወደ በለሲቱ ቀረበ፤ ነገር ግን ከቅጠል በቀር አንዳች ፍሬ አላገኘባትም፡፡ ከአሁን ጀምሮ ማንም ከአንቺ ፍሬ አይብላ ብሎ ረገማት። በለስ የተባለች ቤተ እስራኤል ናት፤ ፍሬ የተባለች ሃይማኖትና ምግባር ናት፤ ከእስራኤል ፍቅርን፤ ሃይማኖትን፤ ምግባርን ፈለገ አላገኘም፤ እስራኤል (ሕዝበ እግዚአብሔር) መባልን እንጂ፤ ደግ ሰው አይገኝብሽ ብሎ ረገማት፤ በመርገሙ ምክንያት እርሱ ከለያቸው በስተቀር ደግ ሰው ጠፋባት፡፡

በለስ ኦሪት ናት፤ ኦሪትን በዚህ ዓለም ሰፍና ቢያገኛት ኦሪትና ነቢያትን ልሽር አልመጣሁም ልፈጽም እንጂ በማለት ፈጸማት፤ ሕገ ኦሪትን ከመፈጸም በቀር በእርሷ ድኅነት አላደረገባትምና፤ ፍሬ በአንቺ አይሁን አላት፤ ደኅነት በአንቺ አይደረግብሽ ብሏታልና እንደመድረቅ ፈጥና አለፈች፡፡

በለስ ኃጢአት ናት፤ የበለስ ቅጠል ሰፊ እንደሆነች ሁሉ ኃጢአት በዚህ ዓለም ሰፍታ ሰፍና አገኛት፡፡ በለስ ሲበሉት ይጣፍጣል፤ ቆይቶ ግን ይመራል፤ ኃጢአትም ሲሰሩት ደስ ደስ ያሰኛል፤ ኋላ ግን ያሳዝናል፤ ወደ እርሷም ሄዶ ማለትም ከኃጥአን ጋር ዋለ፤ ኃጥእ ከመባል በቀር በአንደበቱ ሐሰት፤ በሰውነቱ ክፋት እንዳልተገኘበት ለማመልከት ፍሬ አላገኘባትም አለ፤ በአንቺ ፍሬ አይገኝ የሚለውም፤ በኃጢአት ፍዳ ተይዞ የሚቀር አይኑር ለማለት ነው፤ ስትረገም ፈጥና መድረቋም፣ በአዳም ምክንያት ያገኘችን ዕዳ በደል በእርሱ ካሣነት እንደጠፋችልን ለመግለጽ ነው፡፡

#አንጽሆተ_ቤተ_መቅደስ የተፈጸመበት ዕለት ነው፦

ጌታችን በለስን ከረገማት በኋላ ወደ ቤተ መቅደስ ሄደ፤ ቤተ መቅደስ፣ ቤተ ጸሎት፣ ቤተ መሥዋዕት መሆኑ ቀርቶ ቤተ ምስያጥ (የንግድ ቤት) ሆኖ ቢያገኘው ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች፤ እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋችኋት ብሎ የሚሸጡበትን ሁሉ ገለበጠባቸው፤ ገርፎም አስወጣቸው፤ ይህም የሚያሳየው ማደሪያው ቤቱ የነበርን የአዳም ልጆች ኃጢአት ሰፍኖብን ስንኖር ቢያገኘን ኃጢአታችንን ሁሉ እንዳራቀልን የሚገልጽ ነው፡፡

በዚህ በሰሙነ ሕማማት ካህናትና ምእመናን በቤተክርስቲያን ተገኝተው ወዛቸው ጠብ እስኪል ድረስ በነግህ፤ በሠለስተ፣ በስድስቱ ሰዓት፤ በተሰዓቱ ሰዓትና በሠርክ መላልሰው ሲሰግዱና ሲጸልዩ ይሰነብታሉ፤ በተለይም ካህናት በማንኛውም አገልግሎት ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ፤ ምክንያቱም የደረሰብን መከራ ኀዘኑን እና 5ሺ ከ5መቶ ዘመን የሰው ልጅ በጨለማ ይኖር እንደነበረ ለማዘከር ነው፡፡

@beteafework       @beteafework
@beteafework       @beteafework
@beteafework       @beteafework
#በግብረ_ሕማማት_ውስጥ_የሚገኙ_እንግዳ_ቃላት_እና_ትርጉማቸው

በግብረ ሕማማት ውስጥ ወደ ግእዝም ሆነ በኋላ ወደ አማርኛ ሳይተረጎሙ የተቀመጡ የዕብራይስጥ፣ የቅብጥ እና የግሪክ ቃላት ይገኛሉ፡፡ የእነዚህ ቃላት ትርጉም የሚከተለው ነው፡፡

#ኪርያላይሶን
ቃሉ የግሪክ ሲሆን አጠራሩ "ኪርዬ ኤሌይሶን" ነው፡፡ "ኪርያ" ማለት "እግዝእትነ" ማለት ሲሆን "ኪርዬ" ማለት ደግሞ "እግዚኦ" ማለት ነው፡፡ ሲጠራም "ኪርዬ ኤሌይሶን" መባል አለበት፡፡ ትርጉሙ "አቤቱ ማረን" ማለት ነው፡፡ "ኪርያላይሶን" የምንለው በተለምዶ ነው፡፡ ይኼውም ኪርዬ ከሚለው "ዬ" ኤላይሶን ከሚለው ደግሞ "ኤ" በመሳሳባቸው በአማርኛ "ያ" ን ፈጥረው ነው፡፡

#ናይናን
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ "መሐረነ፣ ማረን" ማለት ነው፡፡

#እብኖዲ
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙ "አምላክ" ማለት ነው፡፡ "እብኖዲ ናይናን" ሲልም "አምላክ ሆይ ማረን" ማለቱ ነው።

#ታኦስ
የግሪክ ቃል ሲሆን ትርጉሙ "ጌታ፣ አምላክ" ማለት ነው፡፡ "ታኦስ ናይናን" ማለትም "ጌታ ሆይ ማረን" ማለት ነው፡፡

#ማስያስ
የዕብራይስጥ ቃል ሲሆነ ትርጉሙ "መሲሕ" ማለት ነው፡፡ "ማስያስ ናይናን" ሲልም "መሲሕ ሆይ ማረን" ማለት ነው

#ትስቡጣ
"ዴስፓታ" ከሚለው የግሪክ ቃል የመጣ ሲሆን ትርጉሙም ደግ ገዥ ማለት ነው።

#አምነስቲቲ_ሙኪርያ_አንቲ_ፋሲልያሱ
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም "ተዘከረነ እግዚኦ በውስተ መንግሥትከ- አቤቱ በመንግሥትህ አስበኝ" ማለት ነው፡፡

#አምንስቲቲ_ሙዓግያ_አንቲ_ፋሲልያሱ
የቅብጥ ቃል ሲሆን "ተዘከረነ ኦ ቅዱስ በውስተ መንግሥትከ ቅዱስ ሆይ በመንግሥትህ አስበን" ማለት ነው፡፡

#አምንስቲቲ_ሙዳሱጣ_አንቲ_ፋሲልያሱ
የቅብጥ ቃል ሲሆን ትርጉሙም "ተዘከረነ እግዚአ ኩሉ በውስተ መንግሥትከ የሁሉ የበላይ የሆንክ ሆይ በመንግሥትህ አስበን" ማለት ነው፡፡

@beteafework       @beteafework
@beteafework       @beteafework
@beteafework       @beteafework
#የሰሙነ_ሕማማት_ማክሰኞ

#የጥያቄ_ቀን_ይባላል

ሰኞ ባደረገው አንጽሖተ ቤተመቅደስ ምክንያት፣ ሹመትን ወይም ሥልጣንን ለሰው ልጅ የሰጠ ጌታችን፣ ስለ ሥልጣኑ በጸሐፍት ፈሪሳውያን ተጠይቋልና፤ የጥያቄ ቀን ይባላል፡፡

ጥያቄውም ከምድራውያን ነገሥታት፣ ከሌዋውያን ካህናት ያይደለህ ትምህርት ማስተማር፣ ተዓምራት ማድረግ፣ ገበያ መፍታትን፣ በማን ሥልጣን ታደርጋለህ? ይህንንስ ሥልጣን ማን ሰጠህ? የሚል ነበር፡፡ /ማቴ. 21፥23-27፣ ማር. 11፥ 7-35፣ ሉቃ.21፥23-27፣ ማር.11፥27-33፣ ሉቃ. 20፥1-8/፤ እርሱም ሲመልስ፤ «እኔም አንድ ነገር እጠይቃችኋለሁ፣ እናንተም ብትነግሩኝ በማን ሥልጣን እነዚህን እዳደርግ እነግራችኋለሁ፡፡ የዮሐንስ ጥምቀት ከወዴት ነበረ፣ ከሰማይ ነውን? ወይስ ከሰዉ? በእግዚአብሔር ፈቃድ፣ ወይስ በሰው ፈቃድ?» አላቸው፡፡ እነርሱም ከሰማይ ብንል ለምን አልተቀበላችሁትም ይለናል፤ ከሰው ብንል ሕዝቡ ሁሉ ዮሐንስን እንደ አባት ያከብሩታል፣ እንደ መምህርነቱ ይፈሩታልና ሕዝቡን እንፈራለን፤ ተባብለው ከወዴት እንደሆነ አናውቅም ብለው መለሱለት፡፡ እርሱም እኔም በማን ሥልጣን እነዚህን እንደማደርግ አልነግራችሁም አላቸው» ይህንንም መጠየቃቸው እርሱ የሚያደርጋቸውን ሁሉ በራሱ ሥልጣን እንዲያደርግ አጥተዉት አልነበረም፣ ልቡናቸው በክፋትና በጥርጥር ስለተሞላ እንጂ፡፡

#የትምህርት_ቀንም_ይባላል፡-

በማቴ. 21፥28፣ ማቴ. 25፥46፣ ማር.12፥2፣ ማር.13፥37፣ ሉቃ. 20፥9፣ ሉቃ. 21፥38 የሚገኙት ትምህርቶች ሁሉም የማክሰኞ ትምህርት ይባላሉ፡፡ በዚህ ዕለት በቤተ መቅደስ ረጅም ትምህርት ስላስተማረ፣ የትምህርት ቀን ይባላል፡፡ ክርስቲያን የሆነ ሁሉ ከሥጋዊ ነገር ርቆ በዚህ ሰሞን የሃይማኖት ትምህርት ሲማር ሲጠይቅ መሰንበቱም መጽሐፋዊ ሥርዓት ነው፡፡
@beteafework
ዐቢይ ጦም ሊጠናቀቅ ሲል የተሰጠ ምዕዳን

እነሆ የተቀደሰውን ወርኃ ጦም ወደ ማጠናቀቅ ተቃርበናል፤ የጦሙን ጉዞ ወደ ማገባደድ ደርሰናል፤ እግዚአብሔር ረድቶንም ወደ ወደቡ ልንደርስ ተጠግተናል፡፡

ነገር ግን እንዲህ በመኾኑ ልል ዘሊላን ልንኾን አይገባንም፤ ይህን ምክንያት አድርገን ከከዚህ በፊቱ ላይ ትጋታችንንና ንቃታችንን እጅጉን እንጨምር እንጂ፡፡

የመርከብ አለቆች ብዙ ባሕረኞችንና ዕቃ ጭነው ረጅም የባሕር ላይ ጉዞ ካደረጉ በኋላ ወደ ወደቡ ሊደርሱ ሲሉ መርከባቸው ከዓለት ጋር እንዳትጋጭና ድካማቸውን ኹሉ ከንቱ ላለማድረግ ከፍ ያለ ጥንቃቄ ያደርጋሉ፡፡ ሯጮችም እንደዚሁ ወደ መጨረሻው መስመር ሊቃረቡ ሲሉ ኃይላቸውን ኹሉ አሟጥጠው ተጠቅመው ሽልማቱን ለመውሰድ ይጥራሉ፡፡ ትግለኞችም ምንም እንኳን ስፍር ቊጥር የሌለው ቡጢ ቢደርስባቸውም፣ ምንም እንኳን ብዙ ጊዜ ተመትተው ቢወድቁም ሽል ማቱን ይወስዱ ዘንድ የመጨረሻውን ዙር ትግል እጅግ ከፍ ባለ ጉልበ ት ይታገላሉ፡፡

ስለዚህ የመርከብ አለቆች፣ ሯጮችና ትግለኞች ድል ወደ ማድረግ ሲቃረቡ እጅግ ከፍ ያለ ትጋትና ጥንቃቄ ኃይልም እንደሚጠቀሙ፥ እኛም ወደ ታላቁ ሳምንት ደርሰናልና እግዚአብሔር ስለረዳን እያመሰገንን ጸሎታችንን፣ ተአምኖ ኃጢአታችንን፣ በጎ ምግባራችንን፣ ምጽዋ ታችንን፣ ከሌሎች ሰዎች ጋር ያለን መስተጋብራችንን፣ ራስን የመግዛት ጠባያችንን፣ እንደዚሁም ይህን የመሰለው ሌላው ምግባራችንን ከፍ ባለ ትጋትና ጥንቃቄ ልንፈጽም ይገባናል፡፡ እነዚህን በጎ በጎ ነገሮችን ወደ ጌታ ቀን (ወደ በዓለ ትንሣኤ) የምንደርስ ከኾነ ከጌታችን ዘንድ ባለሟልነትን እናገኛለን፤ ከማዕዱ ዘንድ መሳተፍ ይቻለናል፡፡ 

(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ አምስቱ የንስሐ መንገዶች፣ ገጽ 148)


    @beteafework  @beteafework 
#የሰሙነ_ሕማማት_ረቡዕ

#ምክረ_አይሁድ_ይባላል
ምክንያቱም የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ እንደሚገባቸው ምክር ያጠናቀቁበት ቀን ነውና፡፡ በዚህ ምክራቸው ላይ በጣም ትልቅ ጭንቀት ነበር፡፡ ምክንያቱም ወቅቱ የፋሲካ በዓላቸውን የሚያከብሩበት ቀን የተቃረበ በመሆኑ ብዙው ሕዝብም በጌታችን ትምህርት የተማረኩ ተአምራቱንም የሚያደንቁ ስለ ነበር ሁከት እንዳይፈጠር ነው፡፡ በዚህ ጭንቀት ሳሉ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ በመካከላቸው በመገኘት የምክራቸው ተባባሪ ሆኖ ጭንቀታቸውን አስወግዶላቸዋል፡፡ (ማቴ. 26÷1-14፣ ማር. 14÷1-2፣ ሉቃ. 22÷1-6) የሐዲስ ኪዳን ካህናትና ምእመናን በዚሁ ዕለት በቤተ ክርስቲያን ተሰብስበው መላ ሰውነታቸውን ለእግዚአብሔር አስገዝተው የሞት ፍርዱን በማሰብና በማልቀስ ሐዋርያት ከጌታችን መያዝ በኋላ በኀዘን በፍርሐት እንደነበሩ እያሰቡ መጻሕፍትን በማንበብ በጾም በጸሎትና በስግደት ተወስነው ይቆዩና ከአሥራ ሁለት ሰዓት በኋላ ወደ ቤታቸው ይሄዳሉ፡፡

#የመልካም_መዓዛ_ቀንም_ይባላል
ምክንያቱም ጌታችን በዚህ ዕለት በቤተ ስምዖን ዘለምጽ ተቀምጦ ሳለ መላ ሕይወቷን ለዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ እፍረት (ባለሽቱዋ ማርያም) "ከእንግዲህ ወዲህ በኃጢአት ተበላሽቶ ይኖር የነበረውን ሕይወቴን እንደዚህ መልካም ሽቱ የሚያጣፍጥ ኃጢአትን ይቅር የሚል አምላክ መጣ" ስትል ዋጋው እጅግ በጣም ውድ የሆነ ከሦስት መቶ ዲናር በላይ የሚያወጣ በአልባስጥሮስ ብልቃጥ የተሞላ ሽቱ ይዛ በመሔድ በጠጉሩ (በራሱ) ላይ በማርከፍከፍ ስለቀባችው ረቡዕ የመዓዛ ቀን ይባላል፡፡

#የእንባ_ቀንም_ይባላል
ማርያም እንተ እፍረት በጌታችን እግር ላይ ተደፍታ መላ ኃጢአቷን ይቅር እንዲላት በእንባዋ እግሩን አጥባዋለችና በጠጉሯም በእንባዋ ያጠበችውን እግሩን አብሳዋለችና። (ማቴ. 26÷6-13፣ ማር. 14÷9፣ ዮሐ. 12÷8) ኃጢአትን በማሰብ ማልቀስና ራስን የተወደደ መሥዋዕት አድርጎ ለእግዚአብሔር ማቅረብን ከምታስተምረን ማርያም እንተ እፍረት እንባን ለንስሐ ሕይወት ልንጠቀምበት ይገባል፡፡


@beteafework       @beteafework
@beteafework       @beteafework
@beteafework       @beteafework
#በእንተ_ጸሎት_ሐሙስ
"ተራሮችን በኃይሉ የሚያስታጥቃቸው ለማገልገል ማበሻ ጨርቅ ታጠቀ፡፡ የባሕርን ውኃ እንደ አቁማዳ የሚሰበስበው በቀላያትም መዝገቦች የሚሾማቸው ርሱ ከወዳጁ ከአልዓዛር ቤት የውኃ ማድጋ አንሥቶ እግሮችን ለማጠብ ያገለግልባት ዘንድ ወደ  ኩስኩስት አፈሰሰ፡፡ እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን በሚታጠቡበት ገንዘብ የናስ ኩስኩስት ሠርቶ በደብተራ ኦሪት ደጃፍ እንዲያኖራት ሙሴን ያዘዘው ውኃውን በኩስኩስት ሞልቶ የደቀ መዛሙርቱን እግር ሊያጥብ ዠመረ፡፡ የተረከዞቻቸውንም እድፍ በታጠቀው ማበሻ ጨርቅ አሸ፡፡"  (አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ)

"በወገቡ የታጠቀውን ማድረቂያ አይተው መላእክት አደነቁ፤ ስሙ ከፀሓይና ከጨረቃ በፊት የነበረ ርሱ አገልጋይ ኾነ፤ ሕያው ጌታን ሱራፌል ያመሰግኑታል፤ ቦታውን ግን አያውቁም፤ ሱራፌልን የፈጠረ ርሱ በራት ጊዜ ወገቡን ዘርፍ ባለው ዝናር ታጠቀ፤ እንዳያቃጥል በመፍራት የማይታይ እሳት ለሐዋርያት አገልጋይ ኾኖ አብነት ይኾናቸው ዘንድ የትሕትና ሥራን የሚሠራበትን ውሃ በኩስኩስት ቀዳ የደቀ መዛሙርቱን አለቃ ጴጥሮስንም እግሩን ሊያጥበው ጠራው"
(ሃይማኖተ አበው ዘያዕቆብ ዘሥሩግ)

@beteafework       @beteafework
@beteafework       @beteafework
"ሁሉን የያዘውን ያዙት፤ ሁሉን የሚገዛውን አሠሩት፤ የህያውን አምላክ ልጅ አሠሩት፤ በቁጣ ጎተቱት፤ በፍቅር ተከተላቸው። በሚሸልተው ፊት እንደማይናገር እንደ የዋህ በግ በኋላቸው እየተከተለ ወሰዱት፤ ሊቃነ መላእክት በመፍራት እና በመንቀጥቀጥ ከፊቱ የሚቆሙለትን በአደባባይ አቆሙት፤

ኃጢአትን ይቅር የሚለውን ኃጥእ አሉት፥ በመኳንንት የሚፈርደውንም በእርሱ ፈረዱበት፤ ለሱራፌል ዘውድ የሚያቀዳጃቸውን የሾህ ዘውድ አቀዳጁት፤ ለኪሩቤል የገርማ ልብስ የሚያለብሳቸውን ለመዘበት ቀይ ግምጃ አለበሱት፤ ኪሩቤል በእሳት ክንፍ ተሸፍነው በፊቱ የሚሰወሩለትን እርሱን ክፉ ባሪያ አሥሮ ፊቱን ጸፋው፤ የመላእክት ሠራዊት በፍጹም መደንገጥ የሚሰግዱለት እየዘበቱበት በፊቱ ተንበረከኩ፡፡

ይህን ያህል ትህትና እንደምን ያለ ትህትና ነው? ይህን ያህል ትእግስት እንደምን ያለ ትእግስት ነው? ይህን ያህል ዝምታ እንደምን ያለ ዝምታ ነው? ይህን ያህል ቸርነት እንደምን ያለ ቸርነት ነው? ኃያል ወልድን ፍቅር ከዙፋኑ ሳበው እስከ ሞትም አደረሰው በደል የሌለበትን እንደበደለኛ ሰቀሉት፡፡ ህይወትን የሠራውን ከበደለኞች ጋር ቆጠሩት፤ አዳምን የሠሩ እጆች በመስቀል ቀኖዎት ተቸነከሩ፤  ወዮ በገነት የተመላለሱ እግሮች በመስቀል ተቸነከሩ፡፡

ወዮ በአዳም ፊት የህይወት እስትንፋስን እፍ ያለ አፍ ከሃሞት ጋር የተቀላቀለ የኮመጠጠ መፃፃን ጠጣ፤... ወዮ የወልድን መከራውን የሚናገር ምን አፍ ነው? ምን ከንፈር ነው? ምንስ አንደበት ነው? የፍቁሩ የጌታ ህማማት በተነገረ ጊዜ ልብ ይለያል፤ ህሊናም ይመታል፤ ነፍስም ትንቀጠቀጣለች፤ ሥጋም ይደክማል የማይሞተው ሞተ፤ ሞትን ይሽረው ዘንድ ሞተ፤ ሙታንን ያድናቸው ዘንድ ሞተ። የምትወዱት ሰዎች ፈጽሞ አልቅሱለት፡፡"

/ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ/
#የማርያም_ሐዘን - ዓርብ ዘጠኝ ሰዓት የሚነበብ

ልመናዋ፡ ክብሯ፡ ለዘላለሙ፡ ከእኛ ጋር ይኑርና፡ አንድ፡ አምላክ፡ በሆነ በአብ በወልድ፡ በመንፈስ፡ ቅዱስ፡ ስም አምኖ የብህንሳ፡ ኤጲስቆጶስ፡ አባ ሕርያቆስ ድንግል፡ ማርያም፡ እመቤታችን ስላለቀሰችው፡ ልቅሶ፡ በዛሬው፡ ቀን የደረሰው ይህ ነው፤ አሜን።

ወደ ዮሐንስ ቤትም በደረሰች ጊዜ አልዘገየችም። ወደ ቀራንዮ፡ ተመልሳ፡ ልትሄድ፡ የተወዳጅ፡ ልጅዋን፡ የመከራውን፡ ፍጸሜ፡ ታይ፡ ዘንድ፡ ቸኰለች፡ እንጂ።

በመስቀል፡ ላይ፡ ነፍሱን፡ በፈቃዱ፡ ሰጥቶ፡ ዝም፡ በአለ፡ ጊዜ፣ በምድር፡ ላይ፡ ስለሆነው፡ ንውጽውጽታና፡ በሰማይም፡ ስለተደረጉ፡ አስደናቂ፡ ተአምራቶች፡ ሀገሪቱ፡ ሁሉ፡ ተሸበረች። ድንግል፡ እመቤታችንም፡ ምድር፡ ስትናወጽ፡ ጨለማ፡ በምድር፡ ሁሉ፡ ስትሰለጥን፡ አይታ፡ እነሆ፡ እነዚህ፡ ተአምራቶች፡ የልጄ፡ የሞቱ፡ ምልክቶች፡ ናቸው፡ ብላ፡ ጮኸች።

እንዲህ፡ ስትልም፡ ዳግመኛ፡ ዮሐንስ፡ ደርሶ፡ እያለቀሰ፡ ከእርሷ፡ ዘንድ፡ ቆመ።

ድንግል፡ እመቤታችንም፡ ዮሐንስ፡ ሆይ፡ በመስቀል፡ ላይ፡ ልጄ፡ በእውነት፡ ሞተን፡ አለችው። እርሱም፡ ራሱን፡ ዝቅ፡ አድርጎ፡ እናቴ፡ ሆይ፡ አዎን፡ ሞተ፡ አላት። ፮፤ ከዚህም፡ በኋላ፡ ታላቅ፡ ልቅሶ፡ ሆነ። በዚያችም፡ ሰዓት፡ ድንግል እመቤታችንን፡ ፍጹም፡ ጩኸትና፡ ልቅሶ፡ ጸናባት፤ በመረረ፡ ልቅሶም፡ እየጮኸች፡ ልጄ፡ ሆይ ከዚህ፡ ካገኘህ፡ የሞት፡ ፃዕር፡ የተነሣ፡ ግፌን የሚመለከትልኝ፡ ሹም፡ ወይም፡ በሐዘን፡ የተሰበረውን፡ ልቤን፡ አይቶ፡ በማስተዋል፡ የሚፈርድልኝ፡ ዳኛ፡ አላገኘሁም፡ አለች።

መኰንን፡ ሆይ፡ እንደ፡ ሕጉ፡ የምትፈርድስ፡ ቢሆን፡ ኖሮ፡ ንጉሥ፡ ልጄን፡ እንደራበው፡ እንደጠማው፡ የአይሁድ፡ ወገኖች፡ ባልሰቀሉትም፡ ነበር።

አንተም፡ ሊቀ፡ ካህናት፡ በዕውነት፡ ፈራጅ፡ ብትሆን፡ ባርያ፡ በጌታው፡ ፈንታ፡ መሞት፡ በተገባው፡ ነበር። በበርባን፡ ፈንታ፤

ሹም፡ ሆይ፡ በቅን፡ የምትፈርድ፡ ብትሆን፡ ልጄን፡ ባልሰቀልከውም፡ ነበር። አንተም፡ ሊቀ፡ ካህናት፡ በዕውነት፡ የምትፈርድ፡ ብትሆን፡ ከልጄ፡ ይልቅ፡ ይሁዳ፡ ለሞት፡ የተገባው፡ በሆነ፡ ነበር። ሹም፡ ሆይ፡ ፍርድን፡ የምታውቅ፡ ቢሆን፡ ልጄን፡ ሥጋውን፡ አራቁተህ፡ መስቀል፡ ባልተገባህም፡ ነበር።

ሊቀ፡ ካህናት፡ ሆይ በቅን፡ የምትፈርድ ብትሆን፡ ወንበዴውን፡ አድነህ፡ ጻድቁን ባልገደልከውም፡ ነበር።

ዳኛ፡ ሆይ፡ መልካም፡ ፍርድን፡ የምታውቅ ብትሆን፡ ኑሮ፡ ጦሮች፡ በላይህ ላይ ሲያንዣብቡ፡ ጽኑዕ፡ የሆነውን፡ ባልገደልከውም ነበር።

አንተም፡ ሊቀ፡ ካህናት፡ በቅን፡ የምትፈርድ ብትሆን፡ የጌታህን፡ ፊት፡ ባፈርክ ነበር። እኔ፡ ስለጦርነት፡ ሰልፍ፡ ስሰማ፡ የንጉሥ፡ ልጅ፡ በጦርነቱ፡ ውስጥ፡ የተያዘ፡ እንደሆን፡ እንዳይሞት፡ ስለእርሱ፡ እጅግ፡ በርትተው፡ እየተዋጉ፡ ወደ፡ አባቱ፡ በፍጹም፡ ጌትነትና፡ ክብር፡ እስከ፡ አደረሱት፡ ድረስ፡ ይጠብቁታል ።

ሊቀ፡ ካህናት፡ ሆይ፡ ለምን፡ እንዲህ፡ ሆነ፡ በጠየቅኸው፡ ጊዜ፡ ዕውነቱን፡ አስረዳህ፣ ግን፡ በአንተ፡ ዘንድ፡ የተጠላ፡ ሆነ፡ ሐሰትን፡ ወደድክ፤ እምነትህንም፡ በሐሰቱ፡ ላይ፡ አጸናህ፤ እንግዲህ፡ ከእውነተኛው፡ ከእርሱ፡ በቀር፡ ማንን፡ ትጠይቃለህ። በፊትህ፡ የቆመው፡ እርሱ፡ እውነተኛ፡ እንደሆነ፡ አታውቅምን፡ እርሱም፡ በዕውነት፡ ሕይወት፡ ነው።

ንጽሕት፡ ድንግል፡ ሆይ፡ በኢየሩሳሌም፡ ከተማ፡ በዚች፡ ትውልድ፡ መካከል የሆነውን፡ ታላቅ፡ ግፍ፡ እዪ፣ እነሆ፡ ከእነርሱ በሚበልጠው፡ ላይ፡ ተሰብስበው፡ ስም ለሞት ፍርድ፡ ሰጥተውታልና።

ከዚህ፡ ሁሉ፡ በኋላ፡ ክርስቶስ፡ በመስቀል ላይ፡ እንደሆነ፡ ነበር፣ የመቶ፡ አለቃውን በዕውነት፡ ይህ፡ ሰው፡ የእግዚአብሔር ልጅ ነው፡ ብሎ፡ አመነ፤ እሊህ፡ ተአምራቶቹ በሁሉ፡ ዘንድ፡ ታመኑ። ፳፣ በዕንጨት፡ መስቀል፡ ላይ፡ ሳለ ምዕመናን ሁሉ፡ በአንድነት፡ አለቀሱለት።

ስለጌታ፡ ስቅለት፡ ከሄሮድስ፡ ዘንድ ወደ መጣው፡ የመቶ፡ አለቃ፡ ጲላጦስ ልኮ አስመጥቶ፡ ወደ፡ ቤቱ፡ አስገብቶ፡ ወንድሜ ሆይ፡ ይህን፡ ጸድቅ፡ ሰው፡ አይሁድና ሄሮድስ ያደረጉትን፡ አየህን? ይህ፡ ሁሉ ተአምራት በምድር፡ እስኪሆን፡ ድረስ፡ በግፍ ሰቀሉት።

ወንድሜ፡ ሆይ፡ በእውነት፡ እነግርሃለሁ፤ እነዚህ፡ ከፋቶች፡ ሁሉ፡ የተፈጸሙት፡ በሄሮድስ፡ ምክር፡ እንጂ፡ በእኔ፡ ፈቃድ፡ አይደለም፤ እኔ፡ እንዳይሞት፡ ልተወው፡ ወደድኩ፤ ነገር፡ ግን፡ ሄሮድስ፡ በዚህ፡ ደስ፡ እንደማይለው፡ ባየሁ፡ ጊዜ፡ ይሰቅሉት፡ ዘንድ፡ ለአይሁድ፡ ሰጠኋቸው፡ እንጂ።

ተመልከት፡ አሁን፡ ለእግዚአብሔር፡ ስለ፡ ሰቀልነው፡ ልጄ፡ ምን፡ ብድርን፡ እንከፍላዋለን፡ አለው፣ የመቶ፡ አለቃውና፡ ባለጦሩ፡ ከጲላጦስ፡ ጋር፡ ደሙ፡ በሄሮድስና፡ በካህናት፡ አለቆች፡ ላይ፡ ነው፣ እያሉ፡ መራራ፡ ልቅሶ፡ አለቀሱ።

በዚያን፡ ጊዜ፡ ጲላጦስ፡ ልኮ፡ የካህናት፡ አለቆች፡ ቀያፋና፡ ሐናን፡ ወደ፡ ጉባዔው አስጠርቶ፡ እናንተ፡ በግፍ፡ ደምን፡ የምትጠጡ፡ ተኵላዎችና፡ ቀበሮዎች፡ በዕንጨት፡ መስቀል፡ ላይ፡ ወደ፡ ሞተው፡ የናዝሬት፡ ሰው፡ አሁን፡ ተመልከቱ፣ ደሙም፡ በእናንተና፡ በልጆቻችሁ፡ ላይ፡ ይሁን፡ አላቸው።

እነርሱግን፡ ደስ፡ በመሰኘት፡ እያፌዙ፡ ደረታቸውን፡ እየደቁ ፊታቸውንም፡ እየነጩ፡ እስከ፡ ሽህ፡ ትውልድ፡ በእኛና፡ በልጆቻችን፡ ላይ፡ ይሁን፡ ኣሉ። እነርሱም፡ እንደ፡ ሕጋችን፡ ፈጽመናል፡ ስለምን፡ እንፈራለን? እንደነግጣለን፡ አሉት። ጲላጦስም፡ የሐሰት፡ ሕግ፡ ፈጸማችሁ፡ እንጂ፡ ይህ፡ ሕግ አይደለም፡ ኣለ፤ አንተም፡ ሊቀ፡ ካህናት፡ የተባልከው፡ እነሆ፡ ልብሶችሁ፡ ተቀደዋል።

ሕጉም፡ ሊቀ፡ ካህናቱ፡ ልብሶቹን፡ በቀደደ፡ ጊዜ፡ ከክህነት፡ አገልግሎት፡ ይከልከል፡ ይላል። ቀያፋም፡ እኔ፡ ልብሴን፡ የቀደድኩት፡ እርሱ፡ በእግዚአብሔርና፡ በሕጋችን፡ ላይ፡ የስድብ፡ ቃል፡ ስለ፡ ተናገረ፡ ነው፡ ብሎ፡ መለሰለት። ጲላጦስ፡ እንግዲህ፡ በሊቀ፡ ካህናት፡ ሥርዓት፡ ወደ፡ መቅደስ፡ ኣንተ፡ እንድትገባ አልፈቅድልህም፡ እንደ፡ ሕግ፡ አፍራሽ፡ እንጂ ።

አንተ፡ ወደ፡ መቅደስ፡ እንደገባህ ሌላው ቢነግረኝ፡ ቸብቸቦህን፡ ከአንተ ላይ እቆጣለሁ፡ አለው። ቀያፋም፡ ከአንተ፡ በፊት፡ ብዙ ጊዜ አልፎአል፤ ብዙዎችም፡ ሹማምንት የሚቀድሙህ፡ አሉ፤ እስከ፡ ዛሬ፡ የካህናት አለቆችን፡ ወደ፡ መቅደስ መግባትን፡ የከለከላቸው፡ አለን፡ ብሎ፡ መለሰለት። ይህንም፡ ያለ፡ የሄሮድስን፡ ሥልጣን በመተማመን፡ ነበር፤ ጲላጦስም፡ ይህን፡ ሁሉ ተአምር፡ ስታይ፡ ከሕዝቡ፡ ሁሉ፡ ጋር፡ አሁንም፡ ልብህ፡ አያምንምን፡ አለው።

ሊቀ፡ ካህናት፡ የተባለ፡ ቀያፋም፡ አንተስ፡ በዚች፡ አገር፡ አዲስ፡ ተክል፡ ነህ፣ ይህ፡ ምልክት፡ የሆነበትን፡ ነገርና፡ የተደረገውን፡ ኣታውቅም። ይህ፡ ይቅርታ፡ የሚደረግበት፡ የመጋቢት ወር፡ ፀሐይና፡ ጨረቃ፡ ዑደታቸውን፡ ፈጽመው፡ ተራክቦ፡ የሚያደርጉበት፡ ሲሆን፡ በዚሁ፡ ወር፡ መሠርያኖች፡ ጨረቃን፡ እንደ፡ ደም፡ የሚሆንበትን፡ ያደርጋሉ፤ የፀሐይንም፡ ብርሃን፡ በሥራይ፡ ኃይል፡ ይስባሉ።

የአግዓዝያንን፡ ተግባር፡ ይመረምራሉ፤ የሥንዴውን፡ የወይንንና፡ የዘይትን፡ ፍሬዎች፡ በማዘጋጀት፡ ይህን፡ የመሰለውን፡ ቀያፋ፣ በሐሰት፡ ይናገር ነበር።

ጲላጦስም፡ ከወንበሩ፡ ላይ፡ ተነሥቶ፡ አንተ እርሱን፡ ከመጥላትህ፡ የተነሣ፡ በዓለም ሁሉ፡ ላይ፡ መዐትን፡ ልታመጣ፡ ትወዳለህ ብሎ፡ ከቆዳ፡ በተሠራ፡ በደረቅ፡ በትር ደበደበው፤ ጽሕሙንም፡ ነጨው።
የመቶ፡ አለቃውና፡ ባለጦሩ ከሕይወት ይልቅ፡ ሞት፡ ይገባሃል፤ እያሉ፡ ያንን ሊቀ ካህናት፡ ይዘልፉት፡ ነበር። በአንድነት፡ ከዘለፉትም፡ በኋላ ወደ ቤተ መቅደስ፡ ይዘውት፡ ሄዱ፤ ወደ ንጉሥም ይወስዱት፡ ዘንድ፡ ተስማሙ።

የድንግል፡ ማርያም፡ በረከት የተወዳጅ ልጅዋም፡ ምሕረት፡ ከእኛ፡ ጋራ፡ ለዘላለም ይደርብን፤ አሜን።

(#ግብረ_ሕማማት)
#ቆዳ_ለሐመረ_ብርሃን

በአዲስ አበባና አካባቢው የምትገኙ ኦርቶዶክሳውያን ሁሉ በረከት አያምልጣችሁ። እንደዋዛ የምትጥሉትን የፍየሎችና የበጎች ቆዳ ለሐመረ ብርሃን በመስጠት የታሪክ ባለቤት መሆን የምትችሉበት መንገድ ተመቻችቶላችኋል ስለዚህ በየሚቀርባችሁ ቦታ ወስዳችሁ በመስጠት ጥሩ ምንጭ ኢትዮጵያን በጥራት አስቀጥሉ።
የእንስሳቱ ቆዳ ከዚህ በታች የምትመለከቱትን ብራና ሁነው ይጠብቋችኋል።

የፍየል እና የበግ ቆዳ ለሐመረ ብርሃን
የትንሣኤ ዕለት ሚያዝያ 27

📍 ፒያሳ አሮጌው ፖስታ ቤት
📍መካኒሳ ቅዱስ ሚካኤል
📍 አየር ጤና ኪዳነ ምሕረት
📍 ሰአሊተ ምሕረት
📍 ቃሊቲ ቅዱስ ገብርኤል

ለበለጠ መረጃ፦ 0966767676 | 0944240000 | 0909444400 ይደውሉ።
#ቀዳም_ሥዑር (የተሻረች ቅዳሜ)

የዐቢይ ጾም የመጨረሻዋ ቅዳሜ ብዙ ስያሜዎች አሏት፦

#ቀዳም_ሥዑር፡-
በዚች ዕለች ከድሮው በተለየ መልኩ የጌታችንን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትውል የተሻረችው ቅዳሜ ትባላለች፡፡ የማትጾመዋ ቅዳሜ ስለምትጾም ስዑር /የተሻረች/ ተብላለች በዓል መሻርን አይመለከትም በቀዳም ሥዑር ሌሊት ሥርዓቱ የሚጀመረው በመኀልየ ሰሎሞን ምንባብ ነው፡፡ ማኀሌቱም እዝሉ እየተቃኘ እየተመጠነ፣ እየተዘመመ እየተመረገደ እየተጸፋ ያድራል፡፡ ጥዋት አቡን መዋሥዕት ውዳሴ ማርያም ዜማ ተደርሶ ወለመልአከ ሕይወትሰ ሰቀልዎ በሚለው ሰላም ይጠናቀቃል፡፡በዚህ ዕለት ልብሰ ተክህኖ የለበሱ ካህናትና ዲያቆናት ቄጤማ ተሸክመው ቃጭል ሲያቃጨሉ መታየታቸው ዕለተ ትንሣኤውን ለሚናፍቅ ምእመን ትልቅ ብስራት ነው፡፡

#ለምለም_ቅዳሜ፡-
ካህናቱ ለምእመናን ለምለም ቀጤማ የሚያድሉበት ዕለት ስለሆነ በዚህ ተሰይሟል፡፡ ቀጤማውንም ምእመናን እስከ ትንሣኤ ሌሊት በራሳቸው ላይ ያስሩታል፡፡ በቀዳም ስዑር ቀሳውስቱና ዲያቆናቱ ቃጭል /ቃለዓዋዲ/ እየመቱ ገብረ ሰላመ በመስቀሉ ትንሣኤሁ አግሃደ የሚለውን ያሬዳዊ ዜማ በመዘመር፤ ጌታ በመስቀሉ ሰላምን እንደሰጠን እና ትንሣኤውንም እንደገለጠልን በማብሰር፤ ቄጤማውን ለምእመናን ይሰጣሉ፡፡ ምእመናኑም በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት የሚውል ገጸ በረከት ያቀርባሉ፡፡ ቄጤማውንም በራሳቸው ያስራሉ፡፡ ይህም አይሁድ ጌታችንን እያሰቃዩ ሊሰቅሉት ባሉ ጊዜ የእሾህ አክሊል ጭንቅላቱ ላይ ያሠሩበትን ድርጊት የሚያስታውስ ነው፡፡

(የቀጤማው አመጣጥና ምስጢርም ከአባታችን ከኖኅ ታሪክ ጋር የተያያዘ ነው፡፡ ምድር በማየ አይኅ /በጥፋት ውኃ/ በጠፋችበት ወቅት የኖኅ ታማኝ መልእክተኛ ርግብ የውኃውን መጉደል ያበሰረችው ቀጤማ ይዛ በመግባት ነው፡፡ ዛሬም ለሐዲስ ኪዳን ክርስቲያኖች የኃጢአት ውኃ ጐደለ፣ የኃጢአት ውኃ ጠፋ በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ነጻነት ተሰበከ ታወጀ በማለት ካህናት ቄጠማ ይዘው ምእመናንን ያበሥሩበታል፡፡)

#ቅዱስ_ቅዳሜ፡-
ቅዱስ ቅዳሜ መባሉ ቅዱስ የሆነ እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ፍጥረታትን አከናውኖ ከፈጠረ በኋላ በዚህ ቀን ከሥራው ሁሉ ያረፈበት ነው፡፡ በዘመነ ሐዲስ ደግሞ የማዳን ሥራውን ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው በመቃብር ሲያርፍ፣ በነፍሱ ሲዖልን በርብሮ ባዶዋን አስቀርቷታል፡፡ በዚያ ለነበሩት ነፍሳትም የዘለዓለም ዕረፍትን ያወረሰበት ዕለት ስለሆነ ከሌሎቹ ዕለታት የተለየ ዕለት ለማለት ቅዱስ ቅዳሜ ተብሏል፡፡

(ስምዐ ተዋሕዶ የስምዐ ጽድቅ ልዩ እትም ዘሰሙነ ሕማማት ሚያዝያ 2004 ዓም)

@beteafework       @beteafework
@beteafework       @beteafework
@beteafework       @beteafework
እግዚአብሔርን የሚያምንና የሚወድ ቢኖር፥ እርሱ በዚህ አንፀባራቂና የደስታ በዓል ደስ ይበለው፡፡ ብልህ አገልጋይ ቢኖር፥ እርሱ ወደ ጌታው ሐሴት ገብቶ ዕልል ይበል፡፡

በጾም የደከመ ቢኖር፥ አሁን ደመወዙን ይቀበል፡፡ በመጀመሪያው ሰዓት ወደ አምላኩ የቀረበ ቢኖር፥ ዛሬ ሽልማቱን ይውሰድ፡፡  በሦስተኛው ሰዓት የመጣ ቢኖር፥ እርሱ በዓሉን በምስጋና ያክብር፡፡ በስድስተኛው ሰዓት የደረሰ ቢኖር፥ አይጎድልበትምና አይጠራጠር፡፡ እስከ ዘጠነኛ ሰዓት የዘገየ ቢኖር፥ ሳይጠራጠር ይቅረብ፡፡ እስከ ዐሥራ አንደኛዋ ሰዓት የዘገየ ቢኖር፥ ስለ መዘግየቱ አይደንግጥ፡፡ ጌታ ቸር ነውና፤ በመጨረሻ የመጣውንም እንደ መጀመሪያው አድርጐ ይቀበሏልና፡፡ በዐሥራ አንደኛው ሰዓት ለመጣው ከመጀመሪያው ሰዓት አንሥቶ ሲደክም ከነበረው ጋራ እኩል ይሰጧልና፡፡

መጨረሻ ለመጣው ጌታ ምሕረቱን ይለግሰዋል፤ መጀመሪያ ለመጣውም ያስብለታል፡፡ ለአንደኛው ይሰጠዋል፤ ለሌላኛውም ጸጋውን ያድለዋል፡፡ ለአንደኛው መልካም ምግባሩን ይቀበልለታል፡፡ ለሌላኛውም መልካም ፍቃዱን ይቀበልለታል፡፡ ለአንዱ ምግባሩን ያከብርለታል፤ ለሌላኛውም በቅን ልቡና የሚያደርገውን ጥረት ያደንቅለታል፡፡ ስለዚህ ኹላችሁም ወደ ጌታችሁ ደስታ ግቡ፡፡

ፊተኞች ኋለኞችም ሆይ! እኩል ደመወዛችሁን ተቀበሉ፡፡ ባለጸጐች ድኾችም ሆይ! በአንድነት ዘምሩ፡፡ እናንተ ብርቱዎች ደካሞችም ሆይ! በዓሉን አክብሩት፡፡ እናንተ የጾማችሁ መጾም ያልቻላችሁም ሆይ! ዛሬ ላይ ደስ ይበላችሁ፡፡

መሠዊያው ሙሉ ነውና ኹሉም በማዕዱ ደስ ይበለው፡፡ ፍሪዳው የሰባ ነውና አንድ ሰው ስንኳ እንደ ተራበ እንዳይሔድ፡፡ ኹላችንም የእምነት በዓሉን እንካፈል፤ ከቸርነቱና ከፍቅሩ ሀብትም እንቋደስ፡፡

ማንም ስለ ድኽነቱ አይዘን፥ ኵላዊቷ መንግሥት ተገልጣለችና፡፡ ማንም በኃጢአቱ አያንባ፥ ከመቃብሩ የይቅርታ ብርሃን ተንቦግቧልና፡፡ ማንም ሞትን አይፍራ፥ የመድኃኒታችን ሞት ከዚህ ነጻ አውጥቶናልና፡፡ ለእርስዋ  በመታዘዝም ጌታ አጥፍቷታልና፡፡ በሞቱ ሞትን ገደለው፡፡ ወደ ሲዖል በመውረድ ሲዖልን በዘበዘው፡፡

ኢሳይያስም አሰምቶ እንደ ተናገረ ሲዖል ከጌታችን ጋር ፊት ለፊት ተገናኘች፤ መረራትም! ከንቱ አድርጓታልና መረራት! ሸንግሏታልና መረራት! ሽሯታልና መረራት!
ነፍሳትን ይዛ እንዳታስቀር አስሯታልና መረራት!
[መቃብር የዕሩቅ ብእሲ] ሥጋ አገኘሁ ብላ ዋጠችው፤  ስትውጠው ግን እግዚአብሔር ኾኖ አገኘችው - መረራትም!

ሞት ሆይ! መውጊያህ ወዴት አለ? ሲዖል፥ መቃብርም ሆይ! ድል መንሣትህ ይዞም ማስቀረትህ ወዴት አለ?
ክርስቶስ ተነሣ፤ ሞት ሆይ፥ አንተም ጠፋህ!
ክርስቶስ ተነሣ፣ አጋንንትም አዘኑ!
ክርስቶስ ተነሣ፤ መላእክትም ሐሴት አደረጉ!
ክርስቶስ ተነሣ፤ የሰው ሕይወትም ነጻ ወጣች!
ክርስቶስ ተነሣ፤ መቃብርም ባዶ ኾነች!
ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሥቶ ለአንቀላፉት ኹሉ በኵር ኾኖላቸዋልና፡፡

(#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ)
ሞት ሆይ! መውጊያህ ወዴት አለ? ሲዖል፥ መቃብርም ሆይ! ድል መንሣትህ ይዞም ማስቀረትህ ወዴት አለ?
ክርስቶስ ተነሣ፤ ሞት ሆይ፥ አንተም ጠፋህ!
ክርስቶስ ተነሣ፣ አጋንንትም አዘኑ!
ክርስቶስ ተነሣ፤ መላእክትም ሐሴት አደረጉ!
ክርስቶስ ተነሣ፤ የሰው ሕይወትም ነጻ ወጣች!
ክርስቶስ ተነሣ፤ መቃብርም ባዶ ኾነች!
ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሥቶ ለአንቀላፉት ኹሉ በኵር ኾኖላቸዋልና፡፡

(#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ)
"ከሙታን ተነሥቶ ሲኦልን ረግጦ በሞቱ ሞትን ደመሰሰው” (መጽሐፈ ኪዳን)

እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሰን!

@beteafework       @beteafework
ከትንሳኤ እሁድ በኋላ ያሉ ዕለታት ስያሜ፡-

#ሰኞ
#ማዕዶት_ይባላል፡- ማዕዶት ማለት መሻገር፣ ማለፍ ማለት ነው፡፡ በዚህ ዕለት በፋሲካችን በክርስቶስ ትንሣኤ ከድቅድቅ ጨለማ ወደ ሚደነቅ ብርሃን፣ ከሞት ወደ ሕይወት፣ ከሲኦል ወደ ገነት፣ ከሃሳር ወደ ክብር መሻገራችንን እናስባለን፡፡

#ማክሰኞ
#ቶማስ_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቶማስ ጌታን አይቶ ማመኑ፤ ጌታዬና አምላኬ ብሎ መመስከሩ ይዘከራል፡፡ ዮሐ. 20፡27-29

#ረቡዕ
#አልአዛር_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ትንሣኤና ሕይወት የሆነው ጌታ ኢየሱስ አልአዛርን ከሞት እንዳስነሳው እናስባለን፡፡ ክርስቶስ የሞትን ስልጣን የሻረ የሕይወት ራስ፤ የመቃብርን ሥርዓት ያጠፋ ትንሣኤ፡ በድልም ያረገ ንጉሥ መሆኑን እንመሰክራለን፡፡

#ሐሙስ
#አዳም_ሐሙስ_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ለአዳም የተሰጠው ተስፋ እና የተገባለት ኪዳን እንደተፈጸመ አዳምና ልጆቹ ነጻ እንደወጣን እናስባለን፡፡

#አርብ
#ቅድስት+ቤተክርስቲያን_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቤተክርስቲያን በክርስቶስ ሞትና ትንሣኤ ስለመመስረቷ ይሰበካል፡፡ ክርስቶስ ስለ እርሷ ራሱን አሳልፎ ሰጥቶ ቤዛ ሆኖ በደሙ አንጽቶ በትንሣኤው ድል ሰጥቶ እንዳከበራት ይነገራል፡፡ ቤተክርስቲያን ስንል ሕንፃውን ሳይሆን አማኞችን ነው፤ ክርስቶስ ለሕንፃ አልሞተምና፡፡

#ቅዳሜ
ቅዱሳት_አንስት_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ቅዱሳት አንስት የክርስቶስን አካል ሽቶ ለመቀባት ጨለማ አቋርጠው ወደ መቃብር መምጣታቸውና ትንሣኤውንም ቀድመው ማየታቸው ይሰበካል፡፡

#እሁድ
#ዳግም_ትንሳኤ_ይባላል፡- በዚህ ዕለት ክርስቶስ ለሦስተኛ ጊዜ ለደቀመዛሙርቱ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይሰበካል፡፡
"የብርሃናት ንጉሥ ብርሃን ኢየሱስ ክርስቶስን ለመውለድ ዛሬ የብርሃን እናት ቅድስት ድንግል ማርያም በእውነት ተወለደች። ከሊባኖስ ተራሮች ርግብ ጸዐዳ ተወለደች፤ በሔዋን ምክንያት የተዘጋው የሕይወት መንገድ ይከፈትልን ዘንድ የሕይወት እናት ዛሬ ተወለደች፡፡ የዓለም ብርሃን ኢየሱስ ክርስቶስን ከእርሷ ይወለድ ዘንድ እመብርሃን ዛሬ ተወለደች፡፡

ኢያቄምና ሐና ዳግሚት ሰማይ ተብላ የተጠራችውን ድንግልን ወለዱ፤ እውነተኛው ፀሐይ ኢየሱስ ክርስቶስ ከእርሷ ይወለድ ዘንድ እመ ፀሐይ (የፀሐይ እናት) ቅድስት ድንግል ዛሬ ተወለደች፤ ብርሃንን ለማስገኘት መወለድ መታደል ነው፤ ከሰው ልጆችም መካከል መመረጥ ዕፁብ ድንቅ ነው፤ የመድኃኔዓለም እናት ለመሆን መወለድ ሰማያዊ ፀጋ ነው።

በእውነት እመብርሃን ቅድስት ድንግል ማርያም የእግዚአብሔር ስጦታ ናት። ንጽሕተ ንጹሐን ቅድስተ ቅዱሳን እመብርሃን ዛሬ ተወልዳልናለችና ደስ ይበለን እልልም እንበል።"

የአለሙን ሁሉ መድኃኒት ለወለደች ለብርሃናት ጌታ እናት በቀራንዮ በመስቀሉ ስር እናት ትሆነን ዘንድ ለተሠጠችን ለመመኪያችን ዘውድ ለተወዳጇ ለቅድስተ ቅዱሳን እናታችን ልደት በዓል እንኳን አደረሰን

(Orthodox and Bible fb page)
#ልደታ_ለማርያም (#ግንቦት_1)

በግንቦት አንድ በዚህችም ቀን አምላክን የወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ተወለደች እርሷም ለሰው ሁሉ ወገን ድኀነት የሆነባት ናት። ከወንዶች ወገን የከበረ አባቷም ስሙ ኢያቄም ከሴቶች ወገን የከበረች ሚስቱ ሐና ይባላሉ። ሁለቱም ልጅ በማጣት ሲያዝኑ ኖሩ በዚያ ወራት የመካኖችን መብዓ ካህናቱ አይቅበሉም ነበርና።

እነርሱም ከሰው የሚደርስባቸውን ሽሙጥና ኅዘናቸውን ያርቅላቸው ዘንድ በቀንና በሌሊት ወደ እግዚአብሔር ፈጽሞ ይማልዱ ነበር። ሰውን የሚወድ እግዚአብሔርም ከዘራቸው ለዓለሙ ሁሉ መድኃኒት ይሆን ዘንድ መልካም የሆነ ኀሳባቸውን ተመለከተ።

ክቡር እያቄምም አርባ ቀን እስኪፈጸም በተራራ ውስጥ ቁሞ ሲጸልይ ከእግዚአብሔር የታዘዘ መልአክ ተገለጸለትና ለዓለሙ ሁሉ ድኀነት የሚደረግባት ዘር እንደሚሰጠው አበሠረው።

በፍጹም ልብ አምኖ ከተራራው ወረደ ለተመሰገነች ሚስቱ ለሐናም ከእግዚአብሔር መልአክ የሰማውን ያንን ራእይ ነገራት ቃሉ እውነት እንደሆነ እርሷም አመነች ልዑል እግዚአብሔርንም አመሰገኑት።

የተመሰገነች ቅድስት ሐናም ከእርሷ የሚወለደውን በዘመኑ ሁሉ ለቤተ እግዚአብሔር አገልጋይ ታደርገው ዘንድ ለእግዚአብሔር ስለትን ተሳለች። ከዚህም በኋላ ይቺን የከበረች ሕፃን ፀንሳ ወለደች ስሟንም ማርያም ብላ ሰየመቻት ትርጓሜውም እመቤት ነው ደግሞም ሀብትና ስጦታ ማለት ነው።

በእውነት የዓለሙ ሁሉ እመቤት ናት ሁላችን በእርሷ ሰማያዊ ሀብት ልጅነትን ያገኘንባት። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን የሥጋና የነፍስ መድኃኒት የሆነች እርሷን እናቱን ለሰጠን በረከቷም ከሁላችን የክርስቲያን ወገኖች ጋራ ለዘላለሙ ይኑር አሜን።

(#ስንክሳር_ዘወርኀ_ግንቦት)
አንድ ደቂቃ ወስደው ያንብቡት ድንቅ ምክር ነው
(ለሌሎች ያጋሩት)

በሠርጉ ዋዜማ እናት ወንድ ልጇን ምን አለችው?

የኔ ልጅ አሁን አንተ ትልቅ ሰው ነህ። ነገ ሌላ እናት ታገኛለህ አዲስ ሰው ምግብህን ያበስላል ምስጢርህን ይካፋላል እኔ ከእንግዲህ ይህንን አላደርግም አዲሷን እናትህን ውደዳት። እሰከመጨረሻው በእጆቿ ላይ ከመተኛትህ በፊት ምክሬን ልስጥህ!

አንድ ቀን ከአባትህ ጋር እየተነጋገርን ነበር በጣም በስሜት ሆነን እንጯጯህ ነበር በቁጣ ስሜት ውስጥ ሆነን ሳላ እኔ በድንገት አንተ የማትረባ ስለው በጣም ተሸማቀቀ ወደ እኔ እየተመለከተ እንዴት እንደሱ ትያለሽ ? ሲለኝ ቀበል አድርጌ አዎ አንተ የማትረባ ሞኝ እብድ ብዬ ያለ የሌለውን የስድብ ናዳ አወረድኩበት ታድያ እሱ ምን እንዳደረገ ታውቃለህ? እሲቲ ገምት? ሊደበድበኝ ይችል ነበር ግን እጆቹን ሳያነሳ ምንም ሳይለኝ መዝግያውን አላትሞ ወጥቶ ሄደ።

ልጄ አባትህ ቢመታኝና ፊቴን ቢያበላሸው አንተ ዛሬ በተበላሸው ፊቴ ታዝንብኝና ታፍርብኝ ነበር እሱንም እንደ አባት አትቆጥረውም ሁሌ ታዝንበት ነበር የምትኮራበት አባት አይሆንህም ነበር።

ልጄ ሚስትህን እንዳትመታት! ብትሰድብህም ብታዋርድህም ከአጠገቧ ለግዜው ዞር በል ኋላ ላይ ነገሮች ይስተካከላሉ። እንግዲህ ሚስትህ ስታበሳጭህ ይህንን የእኔን ታሪክ አስታውስ!

ካቋረጥኩበት ልቀጥል...... ልክ ብቻየን ትቶኝ እንደሄደ ስለሰደብኩት በጣም ፀፀተኝ .. ታድያ የተጣላን ቀን ምሽት አንድ አልጋ ላይ አብረን አደርን በሚቀጥለው ቀን ማድረግ የሚገባኝን ሁሉ አድርጌ ይቅርታ ጠየኩት እርሱም ተቀበለኝ .. ታድያ የዛን ቀን ምን አደረኩ መሰለህ የሚወደውን ምግብ አዘጋጅቼ ስሰጠው ደስ እያለው በላ ካዛ ቀን በኋላ ከአፌ ክፉ ቃል አልወጣኝም ለእሱ ያለኝ ክብር እስር እጥፍ እየጨመረ መጣ።

አንድ በጣም አስፈላጊ ነገር ማድርግ ያለብህ ነገር አለ። ሚስትህን። በደንብ አድምጣት ጋሻና መከታ ሁናት በጭንቅ ግዜ ከጎኗሁን ጓደኞችህ ቢጠሉዋትም ያንተ ንግስት እንደሆነች አሳያቸው ታውቃለህ አጎትህ አይወደኝም ነበር አባትህ ግን ስለኔ ያለውን አሳምኖት ሓሳቡን አስለውጦት እኔን ይደግፈኝ ነበር።

ልጄ.. . አንድ ቀን አባትህ 3 ሰዎች ወደ ቤት ጋብዟቸው ነበር አንደኛው የስራ አለቃው ሲሆን ሁለቱ ጓደኞቹ ነበሩ ምግብ አብስዬ ሁሉን አሟልቼ ካቀረብኩ በኋላ አንድ ነገር ረሳሁ ጨው አልጨመርኩም ነበር በጣም አፈርኩኝ አባትህ ወድያው ምግቡን እንደቀመሰ ወደኔ ተመልክቶ ወደ እነሱ ዞር አለና በጤና እክል ምክንያት ከወር በፊት ምግብ ውስጥ ጨው እንዳትጨምር አዝዣት ነበር ብሎ ሲስቅ ሁሉም ሳቁና እባክሽ ጨው ስጭን ብለው ሁሉም እንደፍላጎቱ ጨምረው ተመገቡ።

እንግዶችም በሄዱ ግዜ ተንበርክኮ ጌታ ሆይ ስለዋሸው ይቅር በለኝ አለ።

ሚስትህ ልክ እንደ ህፃን ናት አንዳንዴ ምን ማለት ወይም ማድረግ እንዳለባት አታውቅ ይሆናል ነገር ግን ተነስተህ ስለ እሷ ስትል ተናገርላት።

ልጄ.. . ስለ ግብረስጋ ግኑኝነት ልንገርህ.. .ወሲብ ጥሩ ነገር ነው።ሚስትህ በወሲብ የምትደሰተው ካንተ በላይ ከሆነ አይግረምህ። ታውቃለህ አንዳንድ ቀን እኔን በጣም ያስፈልገኛል እሱ ግን እስከዚህም ይሆናል ሌላ ግዜ ደግሞ እሱን በጣም ያስፈልገዋል እኔ ግን እስከዚህ እሆናለው... አንድ ማውቅ ያለብህ ነገር እራስ ወዳድ አትሁን አንደኛው ሌላኛውን መረዳት አለበት።

አስቸጋሪ ግዜያት ይመጣል አባትህን ለመደገፍ ስል ሁለት ቦታ ስራ እሰራ ነበር  ታድያ አንድ ቀን ምሽት በጣም ደክሞኝ ወደ መኝታ ክፍል ሳመራ እሱ በጣም ተነቃቅቶ ጠበቀኝ ግን አልተቃወምኩም ቢደክመኝም ፍላጎት እንዳለው ሰው ሆንኩለት ነገር ግን እንደጠበቀው ስላልሆንኩለት ፊቴን አይቶ በመረዳት ምን ሆነሻል? አለኝ ምንም አልኩት ከዚያ ስለተረዳኝ እቅፍ አድርጎ የመኝታ ታሪኮችን/bed time story/ እየነገረኝ እንቅልፍ ወሰደኝ ... ወሲብ የሁለት ሰው የእዕምሮና የአካል ዝግጁነት ይጠይቃል። አንዳንዴ ሚስትህን በደንብ ተመልከታትና ተረዳት።

ልጄ.. .ከሚስትህ ጋር የትም መሄድ ልማድ አድርገው ከስራህ ውጭ ሰትሆን ከሚስትህ ጋር አሳልፍ አንድ ሰው ከሚስትህ ውጭ ብቻህን ቤቱ እንድትመጣ ከጋበዘህ ተጠንቀቅ ብልህ ሁን።

እኔን እንደምትወደኝ ችግሮችህን እንደምትነግረኝ አውቃለው አሁን ግን ይህ ሁኔታ ተቀይሮአል። ከነገ በኋላ ሚስትህ ሁሉንም ነገር ማወቅ አለባት። ከእሷ ጋር ስትጋጭ ወድያው ወደኔ አትሩጥ ለአንድ ወይም ለሁለት ቀን ታገሳት ከዚያ ነገሩ ጋብ ሲል ተነጋገሩ ፀልዩበት ስለ እሷ ለሌላ ሰው ለማንም አትናገር ።

በመጨረሻም በየወሩ ከሚስትህ ጋር እየመጣችው ጠይቁኝ ጥሩ ትዳር እንደሚኖርህ ተስፋ አደርጋለው አንተ ምርጥ ልጄ ነህ እግዚአብሔር ይባርክህ ወደ ፈጣሪ ፀልይ ሁሌም የእርሱን እርዳታ እሻ!!!

#Anani Moti
Like, Comment, Share.Lot's of thanks.

@beteafework         @beteafework
@beteafework         @beteafework
@beteafework         @beteafework
2024/05/17 10:28:08
Back to Top
HTML Embed Code: