Telegram Group Search
"በኔ ላይ አንድ ሰለዋት ያወረደ አላህ በእሱ ላይ 10 ሰለዋት ያወርድለታል" (ረሱል ﷺ)

اللهم صل وسلم وبارك على سيدنا محمد وعلى آله عدد حروف القرآن حرفًا حرفًا، وعدد كل حرف ألفًا ألفًا، وعدد صفوف الملائكة صفًا صفًا، وعدد كل صف ألفًا ألفًا، وعدد الرمال ذرة ذرة، وعدد ما أحاط به علمك، وجرى به قلمك، ونفذ به حكمك في برك وبحرك، وسائر خلقك

ዉብ ጁመአ ይሁንልን 😍
@ONLYFORTRUTHERSJ
ًًً﷽
Selam Aleykum 😘😘😘dena aderachulgn Jumma ❤️❤️❤️


﴿ إِنَّ اللَّهَ وَمَلائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ يَا
أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا ﴾

‏_قال صلى الله عليه وسلم:
‏"أكثروا الصلاة عليّ يوم الجمعة وليلة الجمعة"
‏"فإن صلاتكم معروضة عليّ"
🥺 አልፋና ከሪማ ❤️😭

ክፍል አንድ .1⃣
( ፀሀፊ ጃቢር ሙስጠፋ)

የገዘፈው ሁኔ ከመቸው ረገደ
አንቺን አንቺን ሲል በሀሴት ነደደ 😭

ከዋክብት ብቅ ሳይሉ ጨረቃ ቀደመች ቀኑን ሙሉ ሀይሏን ዝቅ እያረገች እየጨመረች ስትንበለበል የነበረችዋም ፀሀይም ሰማዩ ላይ ሌላ ምህዋር በመተካት ተሰለበች ታችኛዋ ምድር ላይ ያለሁት እኔ ግን ቢመሽም ቢነጋ ሂወቴ ይቀጥላል 😊😊

በተፍጥሮየ ከየዋህነት ባህሪ ፍፁም የራቅኩ ነኝ ራሴን ከሁሉም በላይ በመውደዴ የብዙወችን ጥላቻ ባተርፍም ለማንም ግድ አለመስጠቴ ኩራት ሚሉትን ባህሪ እንዲለጥፉብኝ አስገድዷቸዋል 😐 ከማንም የውጭ ሰው ጋር የሳቅም የጨዋታም ምሳሌ አይደለሁም ጭምት ማይፈታ ሰው እንጂ
ምናልባት በሂወቴ ቅርብ ከሆኑ ሰወች ጋር እንጂ ፍፁም ሌሎች ጋር ቀረቤታ የለኝም !!

የሳምንቱ የመጀመሪያ እለት ላይ ነኝ በእሁዱ የእረፍት ቀን ገና በማለዳው ፀሀይ እንኳን በቅጡ ሳትወጣ በሩ እየተንጋጋ ሰሚር የሚል ድምፅ ይሰማል ልክ በሩን ሲከፍቱት ይህ ቀውስ የሆነ ልጅ ነው የሰው ልጅ እንዴት በዚህ መልኩ አእምሮውን እስኪስት እብድ ብሎም ኬር ይሆናል ሲፈጥረው ለሰው አትጨነቅ የልብህን ስራ ብሎታል በዛ ላይ ምንገድ ላይ እየጮሀ ሲያወራ ሽምቅቅ ያረገናል ከጉሮሮ በታች ማያስቅ ቀልዱን እየቀለደ ለብቻው ይስቃል ማሜ እና አብዱ ለሞራሉ ቢስቁም እኔ እንኳን ጥርሴ ሊከፈት ፊቴ ላይ (ምንድነው ሚጃጃለው) አይነት ስሜት ይነበባል አይ ማሂር

ቶሎ በሩ እንደተከፈተለት ገባና ግቢ ፀጉሬን እየታጠብኩ እያለ ሰሚር ሰሚር 😳 ዛሬ የአብዱ አክስት ብር ልካለች ቶሎ ለባብስና ፈታ ስንል እንውላለን እየጠበቁን ነው አለኝ ☺️
ሳምንቱ የተመታ ሳምንት ስለነበ ነው መሰለኝ በጣም ደስ አለኝ ምንም ሳልመልስለት ክፍሌ ገባሁ ልለባብስ ስዘገጃጅ እንደድንገት አባየ ( ጋሽ አህመድ )ሰሚር የት ልትሄድ ነው አለኝ ?

እኔም ማሂ ጋር መሆኔን ነገርኩት አባየ ሲበዛ ጠርጣራ እና የተረጋጋ ሰው ነው በኢስላሚክ ተርቢያ ልጆችን ለማሳደግ ሁሌም ይጥራል ነገር ግን እንደአዋዋልህ እንጂ እንደምትመከረው አይደለም መቼስ🤷‍♂
ልክ ለባብሼ እንወጣሁ ያየሁትን ማመን ከበደኝ ማሜ ቪትዝ መኪና ይዞ
አብዱ ጋቢና ነበረ ዛሬማ ልዩ ቀን ነው ብየ እየሮጥኩ ገባሁ አንተ ቀውስ ከየት አባህ አመጣህ ስለው ማሂሩ ፈጥኖ ትናንት ተከራይቷት ነው አለኝ እና ትንሽ ሁላችንም ዝም ካልን በኋላ አንድ ላይ ጋቢና ወዳለው አብዱ ዞርን ከዛም ማሜ የዛሬው ሙሽራችን አብዱ ነው አክስቱ ብል ልካለች አለ ስንት አስገባች ስለው አብዱን ትከሻውን እየመታሁ ብሩን ሳይነግረኝ ሰሚርየ ዛሬ በአል ነው በቃ አለኝ

ውይ ሳልነግራችሁ ስሜ ሰሚር አህመድ ይባላል ሰሙ እያሉ ሲጠሩኝ ያመኛል🙄 ምክኒያቱም ሰሚራንም ሲያቆላምጧት ሰሙ ነው 😏 ማሜ አብዱ ማሂሬ ፉአድ የሌለ ሚጃለሱኝ ጓደኟች ናቸው ፉአድ እንኳ ድሬ ዩኒቨርስቲ ሂዷል አሁን እሱ የለም
ለማንኛውም በማሜ ጊዜያዊ መኪና መሄድ እንደጀመርን ማሂ ከተፍ ብሎ የቪትሷን ብሉትዝ አገናኘው እና የሆነ በደንብ ማይሰማ እንጉርጉሮ ከፍቶ እናሽቅ እያለ ጭንቅላቱን ማወዛወዝ ጀመረ እኔና አብዱ ወዲያውኑ ጮህንና አቦ አታላዝንብን ቀይረው አልነው ማሂሬ የሀድራ ሰው ነች አረንጓዴ ልብስ ለብሳ ማበድ ነው ስራዋ ከኛ ውስጥ የዲን አዋቂው አብዱ ነው ከሱ ጋር ሁሌ ይከራከራሉ ይጨቃጨቃሉ እኔ ብዙም አይገባኝም ብቻ ሁሌም ክርክራቸው ሚያልቀው በማሂር አንተ የነቢ ፍቅር ገና መች ገባህ በሚል ትችቱ ነው
እንደምንም በማላዘኑ አሳምኖት ድቤ እንኳን በሌለው እንጉርጉሮ እያዛጋን ደረስን ማሜ እንኳን ኤርፎኑን ሰክቶ ለራሱ የፈረንጅ ዘፈን ይሰማል እሱ ምን ግድ ሰጠው 🙄
የት እንደምንሄድ ሳይነግሩኝ የሆነ ቦታ ላይ ወረድን ምን የመሰለ ቦታ ገባን ውስጡ ሜዳ ነው ስክሪን ተገጥሞ ፊልም ሚያይ አለ ሚዝናናም አለ ድንቅ ቦታ ነው እዛ ቀኑን ሙሉ ስንዝናና ቆይተን አምሽተን ተመለስን እንደተመለስኩ ጫማየን አውልቄ ለጥ ነው ያልኩት

ማይነጋ የለምና ለሊቱ ተሰውሮ በንጋቱ ተቀሰቀስኩ ልክ ከእንቅክፌ ስነቃ ፊትለፊቴ አባየ ቀጥ ብሏል ትናንት ለምን አመሸህ? ሚል ጥያቄ ሰነዘረ ዛሬ ፈጅር ለምን አልመጣህምም አለኝ ? እኔም በቴ ልስገድ ብየ ነው ብየ ዋሸሁት ሰላት ላይ ያለኝ አቋም ቀጥ ያለ ባይሆንም ፈጅር ከፋዘር ጋር ሁሌ ነው ምወጣው ፈዘዝ እንዳልኩ ልብሴን ቀያይሬ ወደ ትምርትቤት አቀናሁ ክላሰ ውስጥ ኮስታራ ነኝ አረ ሂወቴ መኮሳተር በሉት ከጓደኞቼ ፊት ካልሆነ ለማንም ፈገግ እንኳን አልልም ወንዶቹ በዚ ባህሪየ ቀና ብለው አያዩኝም ሴቶቹ ብዙወቹ እንደምመቻቸው እና ወንድ ማለት እንደኔ እንደሆነ ይገልፃሉ በፍፁም ዞር ብየ አይቻቸውም አላውቅም ለቤታችን ብቸኛ ልጅ ስለሆንኩ ብዙም የእህትነት የወንድም ትርጉም አልገነዘብም ድርቅ ያለ ልቦና መገለጫየም ነበር መልኬ ጠየም ብሎ ፀጉሬ የበዛ ብዙም ያልደረቀ ሉጫም ያልሆነ ሚያምር ፀጉር ከደስ ደስ መልክ ጋር ተሰጦኛል ከክፍላችን ልጆች አረ ከትምርትቤቱ የወንዳወንድ መገለጫ የውበት ምሳሌ ነኝ ግን እኔ ብዙም ለዚ ግድ አይሰጠኝም🤷‍♂ የሰው ልጅ ብዙ ሚያዝናናው ነገር አያስደስተኝም

ዛሬ መክሰስ አብዱ ልጋብዛቹህ ብሎ ቤቱ ሂደናል ልክ ቤቱ እንደገባን ትንሿ ኢልሃን ማሜ እና ማሂር ላይ ተጠመጠመች እኔ ላይ ብዙም የደስታ ስሜት አላሳየቺም ትንሽ ቅናት ቢጤ ፈጠረብኝ ግን ወዲያውን ረሳሁት ኢልሃን የአብዱ ብቸኛ እህቱ ናት በጣም ደስምትል ተግባቢ ምላሳም ህፃን ልጅ ናት እነ አብዱ ከእናታቸው ጋር ነው ሚኖሩት ያው እናታቸው በንግድ ታስተዳድራቸዋለች ከመካከላኛ ትንሽ ዝቅ ያለ ኑሮ ይኖራሉ ፍቅራቸው ደስ ይላል አብዱ እኛጋ አይማርም ኢስላማዊ መድረሳ ሚሉት የሆነ ሀይማኖታዊ ቦታ ነው ሚማረው እዛ ትምርትቤታቸው ሁሉም ይወደዋል ጎበዝ ተማሪም ነው የዲን እውቀት ላይ ጎበዝ ነው ብር ዘመዶቹ ይልካሉ ማሜም ማሂም በሆነ ምንገድ ብር ያገኛሉ እኔ ግን ብዙም አይደለሁም ድንገት ግን ወደቤት ስመለስ ስራ ምሰራበትን ምንገድ ቤት ላማክር አሰብኩ ምክኒያቱም በገንዘብ እጥረት በጣም ብዙ ነገር ሚስ እያረኩ ስለሆነ

በዛሬው እለት ምሽት ሁሌ አእምሮየ ላይ ያለ ጥያቄ ለአባየ ልጠይቀው ወስኜ ነበር ምንም ብፈራው ምላሹ ምን ቢሆን መች ስራ መጀመር እንዳለብኝ ልነግረው ወሰንኩ አባየ ጋር ማታ ራት እየበላን አባየ አልኩት በለዘበ ድምፅ ወየ ልጄ አለኝ አባየ ስራ መስራት እፈልጋለሁ አልኩት

ቀጥታ እሱም አፍጦ ካየኝ በኋላ ለምን አለኝ ትንሽ ግራ አጋባኝ ድንግጥ ብየ አረ ለምንም ብየ ክፍሌ ገባሁ
ትንሽ ክፍሌ ውስጥ ማሰብ እንደጀመርኩ በሩ ተንኳኳ አባየ በመቆጣቴ መጦ ነው ብየ ስከፍት አሚ ናት እናቴ ከሁሉ በላይ ትረዳኛች ለኔ መሸፈን እንጂ ፈፅሞ ጫና አታበዛብኝም አትቆጣኝምም ጭምር ትከሻየን እያሸች እንዴት ይህን ጥያቄ አነሳህ ሰሚሬ አለቺኝ
ከዛም በመገረም
የራሴ የሂወት ምእራፍ እና ጎዳና የለኝምን ? እኔስ ወደፊት ሂወትን መኖር ገንዘብ ማግኘት አያምረኝም አልኳት ከዛም ትምርት ሳጨርስ ምን አይነት ችኩልነት ነው ከየት አመጣሀው አለቺኝ እኔም እየሰራሁም መማር እንደምችል ያለሁበት ሁኔታ ብር ሚያስፈልገኝ ዋና ሰአት ላይ እንደሆንኩ ነገርኳት ትምርቱም ላይ ሁላችሁም ፍላጎት እንደሌላችሁ አውቃለሁ አልኳት ከዛም መጀመሪያ ስራ ለመስራት ከሰው ጋር መግባባት አለብህ ብላኝ ሄደች ይቺ ቃሏ ለሊቱን ስትረብሸኝ አደረች ራሴን ዝቅ ማድረግ ሚመስሉኝ
ባህሪያቶች ዋጋ

እንዳያስከፍሉኝ ሰጋሁ ይህን የኮሌጅ ክላስ ጨርሼ ወደ ትምርት አለም መመለስ አልፈልግም በአጎቴ ግዳጅ እና ክፍያም ነው ምማረው ሲጀመረም ሂወቴን በተማርኩበት ለማስመር አላደረኩትም ይህንም ያውቃሉ ለትምርት ትኩረት ካልሰጡ ልስራ ብል ምን ይላሉ ብየ ነበር ጥያቄውን ያነሳሁት ??

የቀጣዩን ቀናቶች ክላስ አልገባሁም ማሜ ስራ ቦታ ሂጄ ነበር ማሜ አሪፍ ይሰራል ግን ብር አያገኝም 😂 እዚ ግባ ማትባል ጉራንጉር የፕላስቲክ መሸጫ ሱቅ አለችው ኪሳራዋ ይበዛል 🤷‍♂

አብዱም እዛው ሱቅ ነበረ ለካ ከዛ ወዲያውኑ ሰሚሬ መጣህ እንዴ ብሎ ሰላም ካለኝ በኋላ ሰምተሃላ እኛጋ የመድረሳች ሃላፊ ቤቱ ጠርቶኛል ከናንተ ጋር ነው ምንሄደው አለኝ እኔም ደሞ ለምግብ እሽ አልኩት
በነገው እለት ከማሂ ጋር ነበር
መድረሳቸውን የገባሁት ልክ እንደገባሁ ያማረ መስተንግዶ ጠበቀን አብዱ እንደቤቱ ሽር ጉድ ይላል ምግብ በላን ገራሚ የምግብ ፕሮግራም ነበር ☺️

እንደጨረስን እጃችንን ታጥበን ቁጭ እንዳልን ድንገት የተዘጋው ሳሎን ክፍት አለ 😳
ያማረ አቋም ከውብ መልክ አይናፋር ልጅ እቃ ይዛ መጣች መልኳ ቀልቶ አይኗ ከልቡ ያምራል ጥቁር ሂጃብ ጠምጥማ ገፅታዋ ለእይታ ይማርካል ያአላህ ምን አይነት ውበት ነው እዛው አይኔን ሳልነቅል ፍራፍሬውን ቁጭ አርጋው ተመልሳ ወጣች በሀሳብ ፀጥ እንዳልኩ ድንገት የቤቱ ባለቤት ከሪማ ሲል ሰማሁት 😟
ከዛ ድጋሚ መጣችና ስለ ቡና እጣን ምናምን አወሩ ከሪማ ላትመጣ በድጋሚ ወጣች ....

ይቀጥላል ........😊

@ONLYFORTRUTHERSJ
ወንድሜ አዋዋልህን አስተካክል ጉዋደኞችህን ምረጥ አዋዋልህ ከደካማ ተስፋ ከቆረጡ ሰዎች ጋ ከሆነ አንተም ብዙም ሳትቆይ ህይወት አስጠላችኝ ህይወት ሰለቸችኝ ማለት ትጀምራለህ ህይወትህ ሙሉ ተበለሻሽቶ መታየት ይጀምራል
ነገር ግን አዋዋልህ ከበሳሎች ህልማቸውን ለማሳካት ከሚሮጡ ሰዎች ጋ ከሆነ አዕምርህ ይለወጣል
ወዳጄ አዋዋልህ ከምታስበው በላይ ህይወትህን ይለውጠዋል
ጉዋደኛ ከ3ቱ አንዱ ነው ይለናል ኢብኑል ቀይም አላህ ይዘንለትና
1ኛው ልክ እንደ ምግብ ላንተ አስፈላጊ የሆነ ሁሌም ልተገኘው የተገባ ጉዋደኛ
2ኛው ደሞ ልክ እንደ መድሀኒት በጊዚያት ነው ምታገኘው ግን ጥቅሙ የላቀ
3ተኛው ልክ እንደ በሽታ ሁሌም ሊርቅህ የሚገባ ነው ይለናል
ወዳጄ ጉዋደኛህ የቱ ነው መድሀኒት ሚሆንህ ነው ወይስ ሁሌም ወደ ታች የሚወስድህ በሽታ እያስቀመጠብህ የሚሄደው ነው
ራስህን ጠይቅ?
ነቢዩ ሰ.ዐ.ወ እንዲህ ብለዋል (ከሽቶ ነጋዴ ጋር የዋለ ሰው በመልካም ጠረን የታወደ ይሆናል ከአንጥረኛ ጋር የዋለ ደሞ በአመድ ቡሊት ቡል ብሎ ይውላል)
መልካም ቀን
𝕚𝕤𝕝𝕒𝕞𝕚𝕔 𝕚𝕟𝕤𝕡𝕚𝕣𝕖
https://www.tg-me.com/islamicinspir
የተቀራው ቲላዋ የተራዊሁ ትርምስ የአንጀታችን መታጠፍ ለሌላ አይደለም ለጌታችን ውዴታ እንጂ እስኪወድልን እንደክማለን በዚሁ ተግባር አመቱን የቀጠለ ምነኛ ታደለ 🙏 አላህ የሰራነውን ይቀበል ስማቸውን ጠርታችሁ ዛሬ በስተመጨረሻው አፍጥር ዱአ ምታረጉለትን ሰው ኮሜንት ላይ መንሹት እሱም ያረግላችሁ ዘንዳ 🤲
🤪እብዱ ደራሲ

👌ምርጥ፣ተወዳጅ❤️ እና አጓጊ😱 ታሪክ

በቅርብ ቀን......😌
እብዱ ደራሲ
# ክፍል አንድ(1)


# አዲስ ተከታታይ ልቦለድ ተጀመረ!!


..........

ለመኖርም ለመሞትም አልታደለም በመኖር ውስጥ የሞተ፣ሞተ እየተባለ የኖረ፣ምስኪን ፍጡር ነው።የማያውቁት ሰዎች ከሩቅ ሲያዩት በፍርሀት ልባቸው ጥለው ይሮጣሉ።ከፊሉ እያዘነለት፣ከፊሉ እያዘነበት በአጠገቡ ያልፋሉ።ሁሌም ከእጁ ላይ የማትለየዋ ቡኒ ተስቢህ የማሂር መታወቂያ ነች።ሲቀመጥ ሲነሳ ሲተኛ ሲበላ ሁሌም በእጁ ላይ አለች።ሲዞር ሳንቲም ሲለቅም ይውል እና የሰፈሩ ወጣቶች በሸራ እና በማዳበሪያ የሰሩለት ቤት ውስጥ ገብቶ ይተኛል።የተቦጫጨቀ ልብሱ እላዩ ላይ ሊያልቅ ትንሽ ቀርቶታል።የማይታየው የሰውነት ክፍሉ የሚታየው ይበዛል።ያለፈ ያገደመውን ሳንቲም ይጠይቃል።ግማሹ በሀዘኔታ ግማሹ ብከለክለው ይመታኛል በሚል ፍራቻ ይሰጡታል።አንድ አንድም አለ ሂድ ከዚ!ብሎ ቀልቡን ቀፎ የሚያባርረው፡ለነገሩ ማሂር ቀልብ የለውም!ቀልብ ቢኖረውማ የተቦጫጨቀ ልብሱን በቀየረ፣መንገድ ማደሩን ትቶ ወደ ቤቱ በገባ፣ግን የት ነው ቤቱ?ከየትስ ነው የመጣው?እንደዚ ሲሆን ጠያቂ የለውም?ለምንድነው አብዛኛው ጊዜ እዚህ ሰፈር የሚኖረው?ና ልጄ ብላ የምትሰበስብ እናት ወይም የሚሰበስብ አባት የለውም።ቤተሰቦቹስ?ዘመዶቹስ?የማን ልጅ ነው?ወደ ሰፈሩ የመጣ አዲስ ነዋሪ፤ለእንግድነት የመጣ ሳይቀር የሚጠይቀው ጥያቄ ነው፤ግን መልስ የለም።ማሂር እዚህ መንደር መቶ መዋል ማደር ከጀመረ አምስት አመታትን አስቆጥሯል።አንዳንዴ ለተወሰነ ቀናት ከሰፈሩ ይጠፋል።ግን እሰይ ተገላገልን የሚለው የለም።ሁሌም አንድ ሳምንት ቆይቶ ይመጣል።የት ይሂድ?ለምን ይሂድ?የሚያውቅ የለም!የመንደሩ ሰው እንደ ጎረቤቱ ለምዶታል!ከአይናቸው ሲጠፋ ባይፈልጉትም ይጠይቃሉ።የት ሄዶ ይሁን?ብለው ይጨነቃሉ!መኪና ገጭቶት ይሆን?እብድ ነው ብለው ቀጥቅጠውት ይሆን?ማሂር እኮ ግን እብድ አይደለም!ሰው አይነካም።የጫት ሱስ የለበትም፣ሰው አያስቸግርም አይጮህም እንደ እብድም አይለፈልፍም!ትልቅ ሰው ይወዳል።እቃ ተሸክመው ካየ ተቀብሏቸው የሚፈልጉት ቦታ ያደርስላቸዋል።አሁን አሁንማ እነሱም ና እስቲ የኔ ልጅ እቺን እቃ አድርስ!እያሉ ይልኩት ጀምረዋል።እንቢ አያውቅምአንገቱን እንዳቀረቀረ የተባለበት ቦታ ያደርሳሉ።የሰፈሩ ጎረምሶች #እብዱ ደራሲ ይሉታል፤ያገኘው ላይ ይፅፋል።ለሰው የማይገባ ለሱ እረፍት የሚሰጠው አይነት ፅሁፍ!ወጣቶቹ ይወዱታል እሱም ሳንቲም እንዲሰጡት ስለሚፈልግ ሲያዙት ይታዘዛል።እነሱም እጃቸውን ለሱ ይዘረጋሉ።ደሞ ብር አይቀበልም ሳንቲም ብቻ፣ለሊት በሱ አጠገብ ያለፈ ሰው ሳንቲም ሲቆጥር ማየት የተለመደ ነገር ሆኗል።ምን እንደሚያረግለት ባያውቁም ይሰጡታል።እሱም ይሰበስባል።ህፃናት የሚጫወቱበት ቦታ ላይ አይጠፋም።አንድ ሰሞን ሲመጣ ይሮጡ ነበር።አሁን ይቀርቡት ጀምረዋል።አንዳንዴ አብሯቸው ይጫወታሉ።አብሯቸው ይስቃል በሳቁ ውስጥ ግን ሁሌም እንባ አለ።ቶሎ የማይደርቅ እንባ ሀዘን፣ስብራት እንዳዘለች የምታስታውቅ እንባ ያነባል።ተስፋ የቆረጠ ናፍቆት ያጠቃው ብቸኝነት ያጎሳቆለው ሰው የሚያፈሰውን እንባ እንደ ጎርፍ ያፈሰዋል።ማልቀስ ከጀመረ አያቆምም ግን እሱ እየሳቀ ነው ሚያለቅሰው!ሳቁ ደሞ ከጣራ በላይ ይሰማል፤ሰዎች ሲያለቅሱ ደግሞ ይስቃል፤ሰፈር ውስጥ ለቅሶ ካለ በአካባቢው አይጠፋም ሰዎች በሀዘን እንባቸውን ሲያወርዱ እሱ ግን በደስታ በሚመስል መልኩ ይስቃል፤በደስታ እንደሚቦርቅ ህፃን ይፈነድቃል እንግድነት ለመጣው ሰው አዲስ ነገር ቢሆንም መንደሩ ግን ለምዶታል ተዉት #እብድ ነው ይባላል።


ሰዎች እብድ ነው የሚሉት ማሂር ዛሬ የለም።እናቶች እንደ ህፃን የሚልኩት የህፃናቶች የጨዋታ ማድመቂያ ወጣቶቹን ሳንቲም እያለ የሚለምናቸው የፈለጉት ቦታ የሚልኩት ማሂር ዛሬ ቦታው የለም።እንደለመደው አንድ ሳምንት ቆይቶ ይመጣል።ሁሉም እየጠበቀ ነው።እሱ ግን እናት ልጇ ወቶ እንደቀረባት ልጅ ከስራ ሲመጣ ብስኩት ገዝቶ እንደሚያመጣለት አባት ደጅ ደጁን እያዩ ነው።አረ ባካቹ #እብዱ ደራሲ እኮ ከጠፋ ሳምንት አለፈው።እያሉ የወንድማቸው ያህል የሚጨነቁለት ጎረምሶች ፍለጋ ከጀመሩ ቆይተዋል።ማሂር ግን የለም.....

............ይቀጥላል..........
https://www.tg-me.com/tesefgna
Forwarded from ብዕሬ ስትደማ (crazy girl🤒)
🤪እብዱ ደራሲ

ተከታታይ ልቦለድ📖

#ክፍል ሁለት(2)

"ሲሁ ሲሀም ተነሺ እንጂ ስራ ረፍዷል፡እንደ ቀልድ ሱብሂ መስገድ ተውሽ አይደል?እሺ አሁን ብድግ በይ ውሀ ሳልገለብጥብሽ"ብላኝ ወደ ኩሽናዋ ሄደች በጠዋት እንቅልፍ ማልደራደረው እኔ ስልኬን ከአጠገቤ ሳብ አድርጌ ሰዐቱን አየሁት ምክንያቱም ኡሚ ሁሌ ሱብሂ ልትቀሰቅሰኝ ስትፈልግ ስራ ረፍዷል ነው የምትለኝ እንዴት እንደምበሳጭባት!አንዴ ከተነሳው እንቅልፍ ስለማይወስደኝ በተነሳው ሰዐት ነው መስገድ ምፈልገው እሷ ግን አትሰማኝም "ሱብሂ መስገድ ቀንሽን ሙሉ ደስተኛ እንድትሆኚ ያደርግሻል" ትለኛለች።ለኔ ደስታ የሚሰጠኝ የጠዋት እንቅልፍ መሆኑን አይገባትም ግን ላለመጨቃጨቅ ስል"እሺ"እላታለው።ኡሚ ግን እሺ ማለቴ የባሰ ያናድዳታል።"ሁሌም እሺ ብቻ እስቲ አንድ ቀን እንኳን ተግብረሽ አሳይኝ ትለኛለች"።አሁን አሁንማ ሰለቻት መሰለኝ በስራ ሰዐት ነው የምትቀሰቅሰኝ ግን ምንም ቢሆን ከ12:40 አታሳልፈኝም ነበር፤ዛሬ ግን ረፍዷል ስልኬን ሳየው1:05 ይላል።ውሀ እንደተረጨ ሰው ብርድ ልብሴን ወርውሬ"ኡሚ ግን ምን ሆና ነው?እስካሁን ያልቀሰቀሰችኝ"እየተነጫነጭኩ ሻወር ለመውሰድ ወጣው።ትላንት ስዞር ስለዋልኩ እና አምሽቼ ስለተኛው ሰውነቴ ዛል ብሏል ሻወር ስወስድ ከለቀቀኝ ብዬ ቀዝቀዝ ባለ ውሀ ሻወር ወሰድኩ ምንም ስራ የመሄድ ሙድ ሊመጣልኝ አልቻለም ግን ደግሞ ግዴታ ነው!ለሰሙ አልነገርኳትም፤ይህን እያሰብኩ ስልኬ ጠራ ሰሙ ነበረች።
"እ አንቺ ጨረሽ" አለችኝ ምን አለ ደና አደርሽ ቢቀድም አልኳት "ትላንት አብረን መስሎኝ ያመሸነው በይ ነይ ውጪ እየደረስኩ ነው"ብላ ስልኩን ዘጋችው።ምን አለ እንዳወራ እድሉን ብትሰጠኝ ኡፍፍ ብዬ ልብሴን መልበስ ጀመርኩ።"አንቺ ልጅ አረ ነይ ውጪ ሻዩ ቀዘቀዘ እኮ ምን ይሻልሻል በአላህ?ሰው አንድ ቀን እንኳን አያልፍለትም?ጓደኛዬ ምን ትለኛለች እንኳን አትይም እንዴ?አረ ተይ ሲሁ ቀልብ ግዢ ተይ"ኡሚ ምክሯን ጀመረች።ጨርሻለው እኮ ቁርስ ደሞ አልበላም፤አራበኝም አልኳት።ከክፍሌ ውስጥ ሆኜ፤አራበኝም ማለት ምን ማለት ነው?ከእንቅልፍ አይደል እንዴ የተነሳሽው?ነይ ውጪና ብይ!"ቁጣ እና ትዕዛዝ የተቀላቀለበት ድምፅ!!መልስ ልሰጣት ስል በር ተንኳኳ"ይሀው ጓደኛሽ መጣችልሽ ስትንከራፈፊ ብላኝ በር ለመክፈት ወጣች"ኡፈይ አልሀምዱሊላህ ተገላገልኩኝ"ብዬ ቦርሳዬን አንጠልጥዬ ከክፍሌ ወጣው።ጫማዬን እየፈለኩ እያለ ኡሚ መጣች ከሗላዋ ጓረቤታችን ወይዘሮ አኢሻ ተከትለዋት ገቡ።ፊታቸው ልክ አልነበረም መርዶ ነጋሪ ነበር የሚመስሉት፤ኡሚም ተረብሻለች፤አጠገቧ እንደቆምኩ ራሱ ልብ አላለችም ነበር፤"ደሞ ማን ሞተ አይ እኛ ሰፈር አዝራኤል ከገባ ካልጠራረገን አይወጣም አይደል?"እያልኩ ጫማዬን ለብሼ እንደጨረስኩ ሰሙ ደወለች"አረ አንቺ ሴትዬ ነይ ውጪ ጥዬሽ ነው ምሄደው"ብላ ስልኩን ዘጋችው።
እንደተበሳጨች ስለገባኝ ኡሚን"ደና ዋይ ብያት"ልወጣ ወደ ሳሎን ስገባ እሷም ስትወጣ በር ላይ ተጋጨን ግን ትዝም አላልኳት!"ኡሚ ደና ዋይ በቃ ልሄድ ነው"ብዬ እንደለመድኩት ግንባሯን ልስማት ስል አይኖቿ እንደጉድ እንባን አዘነቡ፤በጣም ነበር የደነገጥኩት"ኡሚ ምንድነው የሆንሽው?ማነው የሞተው!ማን ምን ሆኖ ነው!መልሷን አልጠበኩም ነበር"ምንም ምንም አይደል ልጄ ሂጂ በይ ከስራሽ ቶሎ ተመለሺ የግቢውን በር ቆልፈሽ ሱቅ አስቀምጪልኝ።ብላ ጉንጬን ሳም አድርጋኝ ከቤት ወጣች ጨራርሼ ስለነበር ተከትያት ወጣው።አይ የኔ ልጅ፣የኔ የዋህ፣አይ ማሂርዬ የሚሉ ከአንደበቷ የሚወጣ የለቅሶ ድምፅ ይሰማኛል።ጓረቤታችን እትዬ አይሻም "በልጅነቱ እንዲ መሆኑ ሳያንስ አይ የሰው ልጅ መከራ አይ ማሂር"እያሉ ከኡሚ ተከታትለው ወጡ.....ማነው ማሂር ምን ሆኖ ነው ለማወቅ በጣም ፈለኩ።


..........ይቀጥላል........



https://www.tg-me.com/tesefgna
Forwarded from ብዕሬ ስትደማ (crazy girl🤒)
🤪እብዱ ደራሲ

#ተከታታይ ልቦለድ📖


#ክፍል ሶስት(3)


ሰዐቱ አምስት ሰዐት ሆኗል ሰሙ ጠዋት ስላረፈድኩባት እንደተኮፈሰች ኮምፒውተሯ ላይ አፍጥጣለች።እኔም የማሂር ነገር ስላሳሰበኝ ቢሮ ከገባው ጀምሮ ከማንም ጋር አላወራሁም እሷንም ቢሆን እንደ ሌላ ቀኑ አልተለማመጥኳትም።ሰሙ ልምምጥ ትወዳለች፤ዛሬ ግን ምንም አላልኳትም ቁርስ አለመብላቴን ራሱ ረስቼዋለው።
ሰሙም እንደደበረኝ ገብቷታል፤አስር ጊዜ ስልክ ስደውል በቆሪጥ ታየኛለች፤አጠገቤ መታ ልታወራኝ ፈልጋለች፤ሄጄ አንዴ እንኳን ሰሙ sorry ብላት እንደምትመለስ አውቃለው፤ግን በቃ ዛሬ ሙዴ አይደለም!የማሂር ነገር አስጨንቆኛል፤ምን አለ ባልመጣ?እቤቴ ሆኜ በነበር ምን እንደተፈጠረ አውቄ ነፍሴ ትረጋጋ ነበር!
"የኡሚ ስልክ አለማንሳት ደግሞ የባሰ ጭንቀቴን ጨመረው"ማሂር ምን ሆኖ ይሆን?መኪና ገጭቶት ይሆን?ሞቶ ይሆን?ይህንን እያሰብኩ እንባዬ ፈሰሰ።ሰሙ እያየችኝ እንደሆነ እንኳን አላስተዋልኩም።
"አሀ ሲሁ እያለቀሽ እኮ ነው"ብላ ከወንበሯ ላይ ተስፈንጥራ አጠገቤ ተቀመጠች።እንባዬን ጠራርጌ"sorry ሰሙ"አልኳት።አሁን እሱን ተይውና ምን ሆነሽ ነው?ኡሚዬ ደና አይደለችም እንዴ?ከገባን ጀምሮ ልክ አልነበርሽም!"ምንም ሰሙ ዝም ብዬ ነው" "ኡፍፍ አንቺ ደግሞ ችግር አለብሽ ወይስ ሰውዬሽ ናፍቆሽ ነው?"ስትል ሳቄን ለቀቅኩት።

..................

ሰሙ የሳቄ ምንጭ፤የጭንቀቴ ማቅለያ ነች።ትውውቃችን የቅርብ ጊዜ ቢሆንም ለሚያየን የልጅነት ጓደኛሞች እንጂ የአመት ከ6ወር ትውውቅ አይመስልም።ያወኳት እዚሁ መስሪያ ቤት ልቀጠር ሲቪ ላስገባ ስመጣ ነው እሷም ልትቀጠር መሆኑ ነው።ድርጅቱ የሚፈልገው 2ሴት ብቻ ነው።እንደኛ ሊቀጠሩ የመጡት ግን ከ50 ይበልጣሉ፤ድርጅቱ የሙስሊም ስለሆነ ግማሽ ያህሉ ሙስሊም ናቸው።እኔና ሰሙ ወረፋችን ፊት እና ሗላ ስለነበር ለመግባባት አልተቸገርንም፤የት/ት ማስረጃችን የሚቀበለን ሰው 4ሰዐት ቢሆንም የሚገባው እኛ ግን ወረፋ ለመያዝ ስንል ጠዋት 1ሰዐት በቦታው ተገኝተናል።ከሰሙ ጋር ብዙ አወራን፤እዛ ቦታ ላይ የተገናኘን ሳይሆን አብረን የመጣን ነበር የምንመስለው፤ሰሙን ስላወኳት ደስ ብሎኛል፤የሚገርመው ደሞ ሁለታችንም የAccounting ተመራቂ መሆናችን እና የተማርንበት ት/ቤት መገጣጠሙ ነው ያልተዋወቅነው ሰሙ የማታ ተማሪ ስለሆነች እኔ ደሞ የቀን ተማሪ ስለሆንኩ ነበር።"እራሴ እየከፈልኩ ስለሆነ የምማረው የማታ ነበር"አለችኝ።"ዋናው መማርሽ ነው ባክሽ" አልኳት።እንደዛ እንደዛ እያልን ብዙ ነገር አወራን፤ሲበዛ ግልፅ መሆኗ አስገረመኝ፤ብዙ ጓደኞች ቢኖሩኝም አብሪያት መሆንን ተመኘው፡አሁን ወረፋችን ደርሷል፤ሁለታችንም ገብተን ወረቀታችንን አስገብተን ተያይዘን ወጣን።"ሁለታችንም አልፈን አብረን ብንሰራ ደስ ይለኛል" አለችኝ።የኔም ፍላጎት ነበርና"ኢንሻአላህ"አልኳት።ስልክ ተለዋውጠን ተለያየን።ከሰሙ ጋር ቅርርባችን በጣም ጠብቋል እቤት ትመጣለች ኡሚም ወዳታለች የት/ት ማስረጃ ያስገባንበት መስሪያ ቤት ለፈተና ስንጠራ አብረን ነበር የሄድነው ውጤቱ ግን በጣም ዘግይቷል ሁለታችንም ተስፋ ቆርጠናል፤ቢሆንም ግን አልደበረንም፤አብረን እንውላለን፤አንዳንዴ ሰሙ እኛ ቤት ታድራለች።የምትኖረው ብቻዋን ስለሆነ ወደቤቷ የምትሄደው ለአዳር ብቻ ነው።ቤተሰቦቿ እንደሞቱ እና ከአያቷ ጋር ክፍለ ሀገር እንደኖረች፤የ10ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና በአጎቷ ልጅ እገዛ አ.አ እንደመጣች እና ከሱ ጋር እንደነበር ምትኖረው፤ነገር ግን ሚስቱ ክፉ ስለነበረች የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና እንደመጣላት ስታውቅ ከሱ ጋር አጣልታ ከቤት እንዳባረረቻት ሆኖም እሱ ከሚስቱ ደብቆ እንደሚረዳት፤ስራ እንዳስጀመራት፤የቤት ኪራይ ይከፍልላት እንደነበር፤የማታ ት/ት ያስመዘገባት እሱ እንደነበር፤ከአመት በፊት ግን በልብ ህመም እንደሞተ ሁላ በመጀመሪያ ቀን ነበር የነገረችኝ።ይህንን ሁላ ስቃይ በልጅነቷ ስለተሸከመች ታሳዝነኛለች ጥንካሬዋ ብርታቷ በጣም ይገርመኛል።


አንድ ቀን እንዲ ሆነ ሰሙ እኛ ቤት ነበር ያደረችው በጠዋት ስልኬ ጠራ ሳየው ባለፈው የተፈተንበት ድርጅት ቁጥር ነው ምን አልባት ሰሙ ካላለፈች እንዳትሰማኝ ብዬ ኔቶርክ እንደተቆራረጠበት ሰው ሄለው እያልኩ ከክፍሌ ወጣው.......


.........ይቀጥላል..............


https://www.tg-me.com/tesefgna
🤪እብዱ ደራሲ

#ተከታታይ ልቦለድ📖

#ክፍል አራት(4)


እንደገመትኩት ነበር የሆነው ደውለው ፈተናውን እንዳለፍኩ እና ስራ መጀመር እንዳለብኝ ተነገረኝ።የሀዘን እና የደስታ ስሜት ነበር የተሰማኝ፤ቀስ ብዬ ለኡሚ ነገርኳት ኡሚ በጣም ትጨነቅላታለች"በቃ አትንገሪያት ይከፋታል ለሷ ካልተደውለላት ስራው ይቀራል!እኔ እናታቹ እንድትለያዩ አልፈልግም ስትለኝ ቅልል አለኝ ወደ ክፍሌ ስገባ ሰሙ ነቅታለች"ሴትዬ ተነስተሻል እንዴ?ነይ በይ ቁርስ ቀርቧል አልኳትና ወጣው ሰሙ ፊቷ ልክ አይደለም የተረበሸ ከተማ መስላለች ቁርሱንም በስርዐት እየበላች አይደለም።የሰሙ እንደዛ መሆን ስናይ የኔም የኡሚም ግምት አንድ አይነት ነበር።"ምነው ሰሙ ደና አይደለሽም እንዴ ፊትሽ ልክ አይደለም?"አለቻት።"አረ ምንም አልሆንኩም ኡሚ ማታ ስቅዥ ነበር ያደርኩት"አለቻት።እየዋሸች እንደሆነ ሁለታችንም አውቀናል።"አብሽሪ እህቴ ብዬ ሳብ አድርጌ አቀፍኳት"አንገቴ ውስጥ ተወሽቃ"እወድሻለው እሺ ምንም ይሁን ምን ካንቺ አይበልጥብኝም"ስትወኝ ሳላስበው እንባዬ ወረደ ኡሚ ብቸኛ ልጇ ስለሆንኩ እንደዚህ አይነት እህት በማግኘቴ ደስ ብሏታል።"አብሽሩ ልጆቼ እኔ እናታቹ እያለው ማንም አይለያቹም!"ብላን የበላንበትን እቃ አንስታ ወደ ኩሽና ገባች ሰሙም ሱፍራውን ጠቅለል አድርጋ ተከትላት ገባች ኡሚና ሰሙ በሹክሹክታ ሲያወሩ ይሰማኛል፤ኡሚ ለሰሙ እየነገረቻት ይሁን?ብዬ በጣም ፈርቻለው።ወሬያቸውን ጨርሰው ከኩሽና ሲወጡ ኡሚ ያለመደባትን"ሂዱ በሉ የሰሙን ቤት ፏ ፏ አድርጋቹ ኑ ብላ ላከችን"ሰሙም አይይ እኔ ለብቻዬ እሄዳለው አለች።"ከመች ጀምሮ"?አለች ኡሚ በመቆጣት ድምፅ እኔም ግራ በመጋባት ቀና ብዬ አየሗት እንደከፋት ታስታውቃለች ኡሚን በቁጣ አይነት አስተያየት ሳያት"ምን ታፈጪብኛለሽ? ተነሺ ደርሳቹ ኑ"አለችኝ።አሀሀ ሌላ ቀን የሰሙን ቤት አፅድተን እንመለስ ስንል የምን ቤት ነው?የሷ ቤት እዚህ ነው!እንደውም እቃውን ጭናቹ ኑ!ነበር የምትለን ዛሬ ምን ተገኘና?በቃ ሰሙ ፈተናውን አላለፈችም!ኡሚም ነግራታለች ለዛ ነው ሰሙም ብቻዬን እሄዳለው ያለችው ኡፍፍ ኡሚ ምን አጣደፋት ደሞ ይቀራል ብላኝ አልነበር እንዴ?ብቻ በፍርሀት ስሜት ውስጥ ሆኜ ከሰሙ ጋር ተያይዘን ወጣን።የሰሙ ቤት ከኛ ብዙም አይርቅም፤ሌላ ቀን በእግራችን ነበር የምንሄደው፤ዛሬ ግን ሁለታችንም አይደለም እየተንጓተትን በእግራችን ልንሄድ እቤት ብንቀመጥ ሁላ ደስተኞች ነበርን።ከኡሚ ጋር ላለመነታረክ ነው የወጣነው፤ምንም አላወራንም።አንዴ ብቻ ሰሙ"ሲሁ ከድርጅቱ ደወሉልሽ እንዴ?"አለችኝ።"አይ" አልደወሉም ላንቺ ደወሉልሽ እንዴ?አልኳት።"አይ" አለችኝ ብቻ እንደዛ እንደደበረን የሰሙን ቤት አፅድተን ተመለስን።

...............


ቤት ስንገባ ኡሚ ጓረቤት ሰብስባ ዳቦ ደፍታ ቤቱን በዐል አስመስላ ነበር የጠበቀችን።ገና ከበር ስንገባ በእልልታ ግቢውን አቀለጠችው እኔም ሰሙም ተያየን ለካ ሁለታችንም ፈተናውን አልፈን ኖሯል እኔም ለሷ ፈርቼ እሷም ለኔ ፈርታ ነበር ያልተነጋገርነው ምንኛ ያማረ ጓደኝነት😍 ከሳምንት በሗላ ስራችንን ጀመርን አንድ ድርጅት አንድ ቢሮ ላይ ሰሙ አንዳንዴ ቤቷ ብዙውን ጊዜ ደግሞ እኛ ቤት መኖር ጀምራለች።

...............


"ነይ በቃ ምግብ አልበላሁም እየሄድን እነግርሻለው"አልኳት እና የቢሮውን በር ዘግተን ወጣን።ወደ ምግብ ቤቱ ስንሄድ ጠዋት የሆነውን ከ"ሀ" እስከ "ፐ" ነገርኳት ሰሙ ማሂርን ሰፈር ላይ ታውቀዋለች የመጀመሪያ ሰሞን ትፈራው ነበር!ጭራሽ ከቤት መውጣት እስክትፈራ ድረስ ከጊዜ በሗላ ግን ማሂር እብድ አይደለም!ብላ ትሞግት ጀምራለች።በነገርኳት ነገር አዝናለች፤የኔ ስሜት ተጋብቶባታል፤ተፅናንታ ልታፅናናኝ ፈልጋለች፡ግን ሁለታችንም ልባችን ፈርቷል ማሂር ሞቶ ይሆን?የሁለታችንም ጥያቄ ነው!ምግቡን አዘን ቀማምሰን ተውነው፤"ምነው?ምግቡ አልጣፈጣቹም እንዴ?"የሚለው የእማማ ድምፅ ነበር ከሀሳባችን ያባነነን፡ልክ እንደተመካከረ ሰው እኩል "አረ ይጣፍጣል እማማ!"አልን ንግግራችን ለራሳችን ፈገግ አደረገን እና ሂሳብ ከፍለን ወጣን የሁለታችንም ሀሳብ ማሂር ጋር ስለነበር ምንም ማውራት አልቻልንም በሀሳብ ተጠምደን ወደ ቢሮ በዝግታ እየሄድን የኔ ስልክ ጠራ ኡሚ ነበረች............


.............ይቀጥላል...............


https://www.tg-me.com/tesefgna
🤪እብዱ ደራሲ

#ተከታታይ ልቦለድ📖

#ክፍል አምስት(5)


እኔና ሰሙ የደወለችው ኡሚ መሆኗን ስናውቅ በድንጋጤ ቆመን ቀረን መንገድ ላይ ስለሆነ ያለነው ማንሳት አልፈለኩም ኡሚ ስለ ማሂር ምንም አለች ምን መንገድ ላይ መሆኑን አልፈለኩትም ሰሙም ሀሳቤን ተጋርታለች ኡሚ ደጋግማ ብትደውልም ቢሮ እስክንገባ ላለማንሳት ወስነናል ሁለታችንም ውስጣችን በፍርሀት ተሞልቷል።
እንዴትም ብለን ቢሮ ስንደርስ የቢሮውን በር ክፍት አገኘነው ሁለታችንም በድንጋጤ እና በመሰላቸት አይነት ተያየን በቃ ሰውዬሽ መቶ ይሆናል አለችኝ።ኤጭ ባልጠፋ ቀን በዚ ሰዐት ይመጣል ምኑ ብሽቅ ነው በአላህ አልኳት የሚከተለንን የስራ ብዛት እያሰብኩ፤አለቃችን በእድሜ ብዙም አይበልጠንም ነገር ግን ነገረ ስራው ሁላ የሽማግሌ ነው መነጫነጭ ይወዳል።ሰሞኑ እቃ ለማምጣት ወደ ዱባይ ሄዶ ስለነበር ተገላግለነው ነበር ደግሞ ሳይናገር ነው የሚመጣው እሱ እዚ ቢሮ አለ ማለት ማውራት የለ መሳቅ የለ መውጣት መግባት የለ ከእኔ ጋርማ የሆነ ጂኒ አያይዞታል ሲሀም እንዲ ሆነ ሲሀም እንደዛ ሆነ ሲሀም በዚ ገባ ሲሀም በዚ ወጣ🤦‍♀በደቂቃዎች ውስጥ 50ጊዜ ነው ስሜን ሚጠራው በሱ የተነሳ ስሜን ሁላ ጠልቼዋለው አንዳንዴማ ከኔ ውጪ ሰራተኛ ያለ እስከማይመስለኝ ድረስ እበሳጫለው።ሌላ ቅርንጫፍ ቢኖረውም እሱ ግን እዚ ያዘወትራል አሁንማ ጭራሽ ከአጠገባችን ያለውን ቢሮ የራሱ ሊያደርገው እያሳደሰው ነው እሱ እዚ ቢሮ የገባ ቀን እኔ ስራ አቆማለው ስላት ሰሙ ትስቃለች ስለሚወድሽ እኮ ነው ትለኛለች ለዛም ነው ሰውዬሽ ምትለኝ እኔ ግን አሁን ከስራው እና ከአለቃችን በላይ የማሂር ነገር ነው ያሳሰበኝ ቢሮ ከገባን ቡሀላ መደወል ስለማልችል አሁን እንደውልላት አልኳት ሰሙ ምንም እንኳን የማሂር ነገር ቢያሳስባትም ኡሚን በተጣደፈ አነጋገር ማናገሩን አልወደደችውም ለምሳ መውጣቱ ስለማይቀር በዛ ሰዐት እንደውላለን ባይሆን እንዳትጨነቅ አለቃችን እንደመጣ ንገሪያት ስራ እንደሚበዛ ይገባታል ብላኝ ለኡሚ ደወልኩላት ግን ለማናገር ድፍረቱን ስላጣው ለሰሙ ሰጠሗት ሰሙ የኡሚን ድምፅ ስትሰማ ፊቷ ተቀያየረ ግን እንዳልነቃ ስለፈለገች በግድ ለመሳቅ ሞከረች ነገሩ ግራ ስለገባኝ ስልኩን ተቀብዬ ኡሚ ደና ነሽ?አልኳት።ኡሚ ድምፄን ስትሰማ እንደደነገጠች ድምጿ ያሳብቅባታል ከኡሚ ጀርባ ደግሞ ለቅሶም አይሉት ሳቅ የሚመስል ድምፅ ይሰማኛል አሁን ከቅድሙ በበለጠ ልቤ በፍርሀት ልትፈነዳ ደርሳለች ደና ነኝ ሲሁ እንዴት ዋልሽልኝ እህትሽ እኮ አለቃቹ እንደመጣ ነገረችኝ ስራ ይበዛባቹሀል በቃ ካልሆነ ቤት ቶሎ ኑ ምትወዱትን ምሳ ሰርቼ እጠብቃቹሀለው ብላ ምንም መልስ እንዳልሰጣት በሚመስል መልኩ ስልኩን ጆሮዬ ላይ ጠረቀመችብች።ይሄ የኡሚ የሁል ጊዜ ንግግር መሆኑን ባውቅም የዛሬው ግን የሀዘንና የስስት ነገር አለበት።አሁን የበለጠ ልቤ ፈርቷል ያ የተመታ ሰውዬ ባይመጣ ኖሮ ቤት እንሄድ ነበር አሁን ግን ግዴታ ነው ከሰሙ ጋር ወደ ውስጥ ገባን።ገና ከመግባታችን እሺ ማጂላኖች በስራ ሰዐት እንኳን አትቀመጡም ብሎ በነገር ለኮሰን ምን አለ አሁን ከዱባይ ነው የመጣው ሰላምታው አይቀድምም የተረገመ ሼባ ብዬ በውስጤ ተሳድቤ ወደ ቦታዬ ሄጄ ተቀመጥኩ ገና ከመቀመጣችን የስራ order ጀመረ በቃ እኔና ሰሙ የማሂርን ነገር ባንረሳውም ግን አሁን 75% የሚሆነው ሀሳባችን ስራው ላይ ሆኗል ሳናውቀው 9ሰዐት ሆኗል ለካ አረ እንስገድ አለች ሰሙ በዛውም ምሳ እንብላ አይነት መልዕክት በቃ በተራ ተራ ስገዱ ምሳ ደግሞ እኔ ነኝ ምጋብዛቹ እዚሁ አብረን እንበላለን ብሎ የኛን ፍቃድ ሳይጠይቅ ልዘዝ ብሎ ወጣ ምሳ ሰዐት ላይ ኡሚ ጋር እንደውላለን ብለን የነበረ ቢሆንም ይሄ ሰውዬ አልፈታም አለን ሁለታችንም የየራሳችንን ስድብ አወረድንበትና ለኡዱ ወጣን በተራተራ ሰገድን እና ምሳችንን በልተን ወደ ስራችን ተመለስን አሁንም ሳናውቀው 12ሰዐት ሆነ ኡሚም ደወለች በድንጋጤ ሰሙን ቀና ብዬ አየሗት አለቃችንም ስለነበር ማውራት ቢደብረኝም ስልኩን አንስቼ ወዬ ኡሚ አልኳት እናንተ ልጆች ቡናው እኮ ቀዘቀዘ አለችኝ መጣን መጣን ኡሚዬ ልንወጣ ነው አልኳት በዛውም ለሰሙ እንውጣ ለአዩብ ደግሞ ልንወጣ ነው የሚል መልዕክት እያስተላለፍኩ ስልኩን ስዘጋው በቃ ሂዱ ጠዋት በጠዋት ኑ እና ትጨርሱታላቹ አለን ማስጠንቀቂያ መሆኑ ነው።እሺ ደና እደር ብለን ተያይዘን ውልቅ አልን ሁለታችንም እቤት እስክንደርስ ቸኩለናል ምንም ባያገባንም ስለ ማሂር ማወቅ ፈልገናል ኡሚ ስለማሂር ምን ትለን ይሆን?ምን ሆኖ ይሆን.........?



..........ይቀጥላል...........



https://www.tg-me.com/tesefgna
🤪እብዱ ደራሲ

#ተከታታይ ልቦለድ📖

#ክፍል ስድስት(6)


አረማመዳችንን ላየ ቶሎ ብለህ ና ተብሎ ማስፈራሪያ የተላከ ህፃን ነው ምንመስለው ከእርምጃ በጣም በፈጠነ ከሩጫ ባልተናነሰ እርምጃ ታክሲ መያዣው ጋር ደረስን ታክሲ ሰልፉ እንደዛሬ ረዝሞብኝ አያውቅም ደሞ ለእልሁ ታክሲውም የለም የምንሰራበት ድርጅት መሀል መርካቶ እንደመሆኑ መጠን በስራ መውጫ ሰዐት ብዙ ህዝብ ነው የሚኖረው ያንን ሁላ ሀልቅ ደግሞ ሲኖ ካልጫነው በስተቀር አያልቅም።መቆም ሁላ ሰልችቶናል ተጋፍተን እንደማይሆንልን እያወቅን መጋፋትን መርጠናል ግን ምንም ሊሳካልን አልቻለም እንደውም አንድ አህያን የሚያስንቅ😒ሰውዬ እግሬን ረገጠኝ በጥፊ ብለው ሁላ ውስጤ ነበር!ደሞ ከሱም ብሶ እያየሽ አትጋፊም?አለኝ ሰሙ ሳቅ መቆጣጠር የሚባል ነገር አልፈጠረባትም ሳታስበው በሰማችው የሰውዬው ንግግር ሳቋን ለቀቀችው እና እኔን ከመሀል ጎትታ አወጣችኝ እኔ ለራሴ እግሬን አሞኛል አንቺ ትገለፍጫለሽ ብዬ ግልምጥ አደረኳት!እሷ ግን አይደለም አይዞሽ ልትለኝ ማውራት እስኪያቅታት ትንከተከታለች አሁን ከሰውዬው እርግጫ እና ስድብ የባሰ የሷ ሳቅ አበሸቀኝ።ችግር አለብሽ ወላሂ አንዴ መሳቅ ከጀመርሽ አታቆሚም እንዴ?ደሞ ምን አለ ምትስቂበትን ቦታ ለይተሽ ብታውቂ?ኡሚ እንደዛ ሆና እየጠበቀችን እዚ ታስካኪያለሽ?ገደል ግቢ ስትፈልጊ!ሰሙን ጥያት ወደ ታክሲው ሰልፍ ተመለስኩ የተናገርኳት ሁሉ በንዴትና በጭንቀት ብዛት ቢሆንም ጥፋተኛ ነች ብዬ ደምድሚያለው።።እሺ በቃ ይቅርታ!ነይ በቃ ራይድ እንጥራ እኔ ጋር ብር አለ አለችኝ በተሰበረ ድምፅ ምንም መልስ አልሰጠሗትም!ሰሙን አስከፍቻታለው ግን አሁን ላይ ማሂር ነው ሚያሳስበኝ ራይድ በ5 ደቂቃ ውስጥ ያለንበት መጣ እቤት እስክንደርስ በጣም ቸኩያለው የኔ ፍጥነት ደሞ የተለየ ነበር ሹፌሩን ቀይሬው ብነዳ ሁላ ደስተኛ ነኝ ይህን ያህል ያንገበገበኝ ግን ምንድነው?መመለስ ያልቻልኩት ጥያቄ!የትራፊክ መብራት 2ደቂቃ ሳይሆን 2ሰዐት ነበር የሆነብኝ ልጅ ጥላ የመጣች እናት ነበር የሚያደርገኝ ሰሙ ግን ተረጋግታለች ፊቷ ቢረበሽም ልቧ በጭንቀት ቢወጠርም የኔን ያህል አልቸኮለችም ዝም እንደተባባልን ሰፈር ደረስን ለምን እንደሆነ ባላውቅም ወደ ሰፈር መግቢያ ስንደርስ አውርደን አለችው ሌላቀን ቤት ካላደረሰን የምትል ልጅ በቃ ተናዳለች ወደቤቷ ልትሄድ ነው ብዬ ምንም ሳልል ወረድኩ እሷም ሂሳቧን ከፍላ ተከተለችኝ።በጣም ቀለለኝ ወደ ሰፈር ስንደርስ ሰሙ እጄን ይዛ አስቆመችኝና እህቴ በጣም እንደጨነቀሽ የማሂርን ነገር ለማየት እንደቸኮልሽ አውቃለው ግን መጀመሪያ መረጋጋት አለብሽ ኡሚን ተረብሸሽ እንዳትረብሻት አለችኝ ከኡሚ ጋር ሲያወሩ ሰሙ ፊቷ ሲቀያየር ኡሚ የኔን ድምፅ ስትሰማ የደነገጠችው ድንጋጤ አስታውሼ የሆነ ነገር እንደተፈጠረ አሳመነኝ እና ተረጋግተን ወደ ሰፈር ስንገባ ምንም አዲስ ነገር የለም ቤት ስንገባ ኡሚ ቡና አፍልታ እየጠበቀችን ነበር ሱፍራ ላይ ሰሙ የምትወደው የስጋ ጥብስ በአንድ ሰሀን እኔ የምወደው ሩዝ አድርጋ ነበር የጠበቀችን የማየውን ማመን አልቻልኩም ኡሚን የጠበኳት አዝና ምናምን ነበር ግን ከጠበቅነው በተቃራኒ ነበር ያገኘነው እኔና ሰሙ ተያየን የኡሚ ነገር ሁለታችንንም ግራ አጋብቶናል ግቡ እንጂ ምን ይገትራቿል፤እናንተን ስጠብቅ ቡናውን እኮ ቀቀልኩት😁አለችን ሁለታችንም ሳቅ ብለን ሰላም ብለናት እጃችንን ታጥበን ገባን ሰሙም እኔም ግራ ቢገባንም ምግባችንን መብላት ጀመርን ኡሚ ማሂርን ከነመፈጠሩ የረሳችው ትመላለች እኔና ሰሙ ግን ማሂርን ማሰብ አላቆምንም ኡሚንም መጠየቅ ፈርተናል ምን አልባት ማሂር እኛ እንደገመትነው ቢሆን እና ኡሚ እሱን ለመርሳት ቢሆንስ እንዲ እያረገች ያለችው?ኡሚ ቀኑን ሙሉ የሰራችውን እየነገረችን ነበር ግን አንዴም የማሂርን ስም አላነሳችም በጣም ግራ ገብቶኛል አሁን ልጠይቃት ወስኛለው እኔ ምልሽ ኡሚዬ ወዬ አለችኝ በጣም እየፈራሁም ቢሆን ማሂር እንዴት ሆነ?አልኳት የፈራሁት አልቀረም ኡሚ እንባዎን አወረደችው😳 ሰሙ እና እኔ ድንጋጤ አደነዘዘን በተቀመጥንበት ደርቀን ቀረን ተነስተን እንኳን ኡሚን ማባበል አልደፈርንም...........



..........ይቀጥላል..........

https://www.tg-me.com/tesefgna
🤪እብዱ ደራሲ

#ተከታታይ ልቦለድ📖

#ክፍል ሰባት(7)


ትረፊ ያላት ነፍስ አሉ ጋሽ አህመድ ብቻ አልሀምዱሊላህ ተርፏል ባይባልም አልሞተም።የመኪና አደጋ ነበር የደረሰበት ነገር ግን ሹፌሩ አላህ የመረቀው ወጣት ስለሆነ ትቶት አልሄደም እሱ ወድያው ሀኪም ቤት ባይወስደው ኖሮ አይተርፍም ነበር ብቻ አልሀምዱሊላህ ብላ እንባዋን ጠራረገች።እሺ አሁንስ እንዴት ነው ሰሙ ነበረች የጠየቀችው ዶክተሮቹ ሰው የማይገባበት ክፍል አስተኝተውት ማንም አላየውም እነዚ እነማናቸው እዛ ታች የሚቀመጡት ጎረምሶች?እነ ኡስማን ነው ኡሚ?አልኳት አዎ!እነሱም ካላየነው አናምንም ብለው ቢበጠብጡም የባሰ ከሀኪም ቤቱ ተባረሩ አለችን።ሰሙ እና እኔ በረጅሙ ተንፍሰን እኩል አልሀምዱሊላህ አልን በጣም ተጨንቀን እንደነበር የገባት ኡሚ ልጆቼ ለሰው ልጅ መጨነቅ እኮ የኢማን ግማሽ ነው አለችን ኡሚ ሁሌም እኛን ለማስፈራት ሆነ ለማስደሰት በራሷ ሀዲስ እንደምትፈጥር ስለምናውቅ ሳቃችንን ለቀቅነው"ምን ያስገለፍጣቿል"አይ ኡሚዬ ሀዲሶችሽን በዝተውብን እኮ ነው ብለን ተሳሳቅን።ሰው አረ እንኳን ተረፈ እኛኮ በጣም ተጨንቀን ነበር የሲሁ ደግሞ ይባስ ስትል ኡሚ ቀበል አድርጋ አንቺ ከመች ጀምሮ ነው እንደዚ አስተዋይ የሆንሽው እ አለችኝ ሾርኒ መሆኑ ነው።አይ ኡሚዬ ወላሂ ለኔም ግራ የገባኝ እሱ አይደል ከልክ በላይ ነውኮ የተጨነኩት ኡፍ ዋናው እንኳን አልሞተ ደሞ ማን ያውቃል አላህም የኔን ጭንቀት አይቶ ይሆናል ያተረፈው አልኩ በማልገጥም በጉራም አይነት ነገር እሺ የኔ ወልይ ሰላቱን በስርዐቱ በሰገድሽው ወገኛ አለች ኡሚ።ኡሚ ስለ ሰላት ከተነሳ በዛውም የምክር አገልግሎት እንደምትጀምር ስለማውቅ እሷ ከጀመረች ደግሞ አቶ ሰሚራም እንደምትከተላት ስለገባኝ በሉ ደክሞኛል ልረፍ ብዬ ተነሳው🚶‍♀🚶‍♀እሺ ሸይጧንሽ ተነሳ አለችኝ ኡሚ ሁሌም እንደዚ ስለማደርግ ለምዳዋለች ሰሙም በቃ ልሂድ ስትል መለስ አልኩ የምን መሄድ ነው ወላሂ እዚ ነው ምታድሪው በጠዋት ተነስተን ማሂርን ጠይቀን ነው ስራ ምንገባው አልኳት ኡሚም እንድትሄድ ስላልፈለገች አዎ ብላ ሰሙን አሳመነቻትና አደረች።

...................
ቀናት ቀናትን እየተኩ ማሂር ሀኪም ቤት ከተኛ 15ቀን ሆኖታል ዶክተሮቹ ከ1ሳምንት ቡሀላ እንደሚወጣ ነግረውናል የሰፈሩ ሰው እኛ ስላለን ነው መሰለኝ ብዙም አይመጡም እነ ኡስማን ወደ ሀኪም ቤት መግባት ስለተከለከሉ እኛን ነው ሚጠይቁት መድሀኒት ምናምን ሲያስፈልገው ገዝተው ያመጡልናል ለነገሩ ማሂርንም የገጨው ሰውዬ ኡሚ እንዳለችው ጥሩ ሰው ነበር እሱ ነበር ሚያድርለት ሁሌም አውፉ በለኝ እያለ የማሂርን እጅ ይዞ ያለቅሳል ማሂር የግራ እግሩ ስለተጎዳ በዊልቸር ይሂድ እንጂ ሙሉ ለሙሉ በሚባል መልኩ ደና ነው።ኡሚም ምግብ እየሰራች እሱን መካደም የዘወትር ልማዷ አድርጋዋለች እኔና ሰሙም ወይ ስራ ስንወጣ ወይም ስንመለስ እንጠይቀዋለን መንገዳችን ስለሆነ በቀን አንዴ ሳናየው አንውልም እሱም ደስተኛ ነው አእምሮውም ቢሆን ወደራሱ ተመልሷል ኡሚንም እማ እያለ መጥራት ጀምሯል እሷም ቢሆን አላሳፈረችውም የእናት ያህል ትንከባከበዋለች።ነገር ግን ለሁላችንም ጥያቄ የሆነብን እና ለመናገርም የፈራነው ነገር ቢኖር ማሂር ከሀኪም ቤት ከወጣ ቡሀላ እዛ ማዳበሪያ ውስጥ ነው ሚመለሰው ወይስ ምንድነው ሚሆነው ዶክተሮቹ ደሞ ቢይንስ መድሀኒት እስኪጨርስ እንክብካቤ እንደሚያስፈልገው ለአእምሮ ህመሙ ምክንያት ብቸኝነት ሰው ማጣት እና ጭንቀት እንደሆነ ነግረውናል መጀመሪያ አካባቢ ማሂርን የገጨው ሰውዬ እንደሚወስደው አስበን ነበር እሱ ግን ለኡሚ እዚ ሀገር እንደማይኖር እና ለመዝናናት እንዲመጣ ከ15ቀን ቡሀላ ወደ አሜሪካ እንደሚመለስ ነጎሯታል ኡሚም በሰዐቱ እሺ አታስብ እንዳለችው እና የሚያስፈልገውን ነገር ለማድረግ እና በአላህ ስም አደራ እንዳላት ነግራናለች ነገር ግን ጊዜው ሲደርስ ኡሚ ግራ ተጋብታለች ጓረቤቶቿም ቢሆኑ በሀሳቧ አልተስማሙም እንዴት ማታቂውን ለዚያውም እብድ ወደ ቤትሽ ታስገቢያለሽ እያሉ ይወተውቷት ጀምረዋል።ሰዒድም ወደ ሀገሩ ሂዷል ማሂር ከሀኪም ቤት ሊወጣ 3ቀን ብቻ ቀርቶታል።ማን ያኖረው ይሆን?ማን ጋር ያርፍ ይሆን?መልስ የታጣለት ጥያቄ.............



............ይቀጥላል...........

https://www.tg-me.com/tesefgna
🤪እብዱ ደራሲ

#ተከታታይ ልቦለድ📖

#ክፍል ስምንት(8)


ቀኑ ጁምዐ ነው ማሂር ከሀኪም ቤት የሚወጣበት ቀን በመሆኑ በጠዋት መነሳት አለብን ስራ እንደማንገባ ለአለቃችን ነግረነዋል እሮብ ለት ከኡሚ ጋር አውርተን ማሂር እስኪሻለው እኛ ቤት እንዲሆን ከዛ በሗላ ደግሞ ሰሙ እኛ ቤት መታ እሱ እሷ ቤት ሊኖር ተስማምተናል።ኡሚ በጠዋት ጉድ ጉድ ማለት ጀምራለች ማሂር ሳይሆን ሙሽራ ሚመጣባት ነበር የምትመስለው መነሳታችንን እንኳን ልብ አላለችም ደና አደርሽ ኡሚ አልኳት ውይ ተነስታቿል እንዴ?በሉ ቶሎ ቁርሳቹን ብሉና ማሂር ጋ ሂዱለት ደግሞ እንዳይከፋው አለችኝ አሀ ኡሚ ደሞ ገና 8ሰዐት እኮ ነው ይወጣል የተባለው አይደል ሰሙ?የተናገርኩትን ለማረጋገጥ፦አንገቷን በአውንታ ነቀነቀችልኝ አይይ ቢሆንም ልጄ የሀኪም ቤት ጣጣ አያልቅም እሱን እስክትጨርሱ 10ሰዐትም በመጣቹ

................
ሰዐቱ 7:30 ሆኗል ማሂር ጋር ከገባን አራት ሰዐት አለፈን ሰሙ እንደገባን አንቺ ማሂር ጋር ቁጭ በይ እኔ መጨረስ ያለብንን ነገር ልጨርስ አለችኝ በሀሳቧ ተስማምቼ እኔ ማሂር ጋር ቁጭ ብያለው ሰሙም አልተመለሰችም ወረፋው በጣም ብዙ ነው ብቆይ እንኟኳን እንዳታስቡ ማሂርን አዳብሪው የሚል መልዕክት ከሰዐታት በፊት ስለላከችልኝ አልተጨነኩም ሰዒድ ወጪውን ሙሉ ልኮልን ስለነበር ብር አልተቸገርንም ከገባው ጀምሮ ከማሂር ጋር ብዙም አላወራንም።ሊወጣ 30ደቂቃ ቀርቶታል ሰሙ እስካሁን አልመጣችም ኡሚ እንዳለችው እስከ10 መቆየታችን ነው በቃ መቀመጡ በጣም ሰልችቶኛል ስልኬም ቻርጅ ስለዘጋ ሰሙን ማግኘት አልቻልኩም የት ይሆን ያለችው ወጥቼ አልፈልጋት ነገር የሀኪም ቤቱ በር ብዙ ነው ደሞ እሷ ስትመጣ እኔ ስሄድ ብንሸዋወድስ?ይህን እያሰላሰልኩ ሲሁ የሚል ድምፅ ከሀሳቤ አባነነኝ ማሂር ነበር የጠራኝ ወዬ አልኩት አጠራሩ አስደንግጦኝ እናንተ ቤት እንደማርፍ ኡሚ ነግራኛለች ግን ቤት ከመግባታችን በፊት ወደራሴ ቤት መሄድ እፈልጋለው እቤቴ? አልኩት በመደናገጥ አይነት ማሂር አጠያየቄ ስለገባው ፈገግ ብሎ እሺ ማዳበሪያዬ ጋር ከመልሱ ይልቅ ፈገግታው አስደንግጦኛል ሌላ ቀን አይደርስም?አሁን ይሁንልኝ በአላህ አጠያየቁ የህፃን ልጅ ነበር የሚመስለው እሺ እንደፈለክ ግን አንተ ከመኪና መውረድ ስለማትችል ምትፈልገውን ትነግረኛለህ እኔ አመጣልሀለው አልኩት፤በሀሳቤ መስማማት አልፈለገም ግን ደሞ ከመኪና ለመውረድ ግድ ሰው እንደሚያስፈልገው ያውቃል አይሆንም ቢል እኛን ማስቸገር ነው እሺ በቃ ወረቀቶች ናቸው ታመጪልኛለሽ ግን ሲሁ ልመንሽ?አለኝ ጥያቄው ያስደነግጣል እንደደበረው ስለገባኝ እኔ ምለው የሀገር ጉዳይ ነው እንዴ?ብዬ ቀለድኩበት ፈገግ ብሎ ዝም አለ የማሂር ዝምታ ያስፈራል!!መጣው ሰሙን ልፈልጋት ብዬ ወጣው አወጣጤ እንዳልኩት ሰሙን ለመፈለግ ሳይሆን የማሂር ዝምታ አስፈርቶኝ ነው ወጥቼ ኮሪደሩ ላይ ቆምኩኝ ሳይታወቀኝ በሀሳብ ጭልጥ ብያለው የማሂር እርጋታ የዝምታው ማስፈራት እና ማዳበሪያ ውስጥ ስላለው ወረቀት........
ሲሁ የሚል ድምፅ ከሀሳቤ አባነነኝ እህ አልኳት የት ሄድሽ ደሞ ማሂርን ጥለሽው ወጣሽ እ ልፈልግሽ እኮ ነው ሰሙ የሆነ ነገር እንደሆንኩ ገብቷታል አትዋሺ ሲሁ ማሂር ምን ብሎሽ ነው አለችኝ ስለነገረኝ ነገር ነገርኳት እና ምን ችግር አለው በራይድ ስለሆነ ምንሄደው እዛው ጋር ስንደርስ እናወርደዋለን አለችኝ እሺ በቃ እንዳልሽ ጨረሽ አሁን እሂድ አልኳት አይ ቆይ ትንሽ ይቀረኛል ሰዒድ ደውሎ ማሂርን አገናኚኝ ስላለኝ ነው የመጣሁት ብላኝ ወደ ውስጥ ገባች ተከትያት ገባው ሰሙ ማሂርን ከሰዒድ ጋር አገናኝታው በቃ አውርተው ሲጨርሱ ስልኬን ተጠቀሚበት እንዳይደብርሽ እኔ ልጨራርስ ብላኝ ሄደች ማሂር ከሰዒድ ጋር 30ደቂቃ አወራ እንደዚ ለረጅም ለደቂቃ ሲያወራ ለመጀመሪያ ጊዜ አየሁት ንግግራቸው በተመስጦ ነበር ስሰማ የነበረው አይደለም 30ደቂቃ ያወራ አይመስልም እርግት ብሎ ነበር ሚያወራው እሺ ወአለይከሰላም ሰያ እናወራለን በቃ ብሎ ስልኩን ዘግቶ አቀበለኝ ሰሙ ስልክ ላይ ባፈጥም ስለ ማሂር ማሰብ ግን አላቆምኩም ነበር ላወራው ብፈልግም ግን ምን እንደማወራው ግራ ገብቶኛል እሱም አያወራ እኔም አላወራ በዝምታ ተውጠን ሁለታችንም በሀሳብ ነጉደናል ሲሁ ግን ልመንሽ?የሚለው የማሂር ጥያቄ ምንም ከጭንቅላቴ ሊወጣ አልቻለም፤ሰሙ 12:30 ሲሆን መጣች ራይድ ደውለን ጠርተን ማሂርን በዊልቸር እየገፋው ሰሙ ቀድማ ቦታውን ነግራው ስለነበር የማሂር ሸራ ጋር አቆምን ማሂር እየሆነ ባለው ነገር ግራ ተጋብቷል እሱ የገመተው ወደቤት እየሄድን እንደነበረ ነው ይሀው እንውረድ እና ምትፈልገውን ነገር ውሰድ አለችው ሰሙ ማሂር ፊቱ በደስታ ተሞላ በሹፌሩ እገዛ ዊልቸሩን እየገፋ ወደናፈቀው ቤቱ ማዳበሪያው ውስጥ ገባ የሚፈልገው ነገሬ ካለ እንድታግዢው ተከተይው አለችኝ እኔ ግን ሲሁ ልመንሽ ያለኝ ነገር ስላለ አይ ሰሙ አጋዥ ቢፈልግ ይጠራን ነበር እዚሁ እንጠብቀው አልኳት መኪና ውስጥ ተቀመጥን 30ደቂቃ ሆኖናል።ማሂር እስካሁን አልመጣም ልቤ በጣም ተጨንቋል ሹፌሩም ተቆጣ መልስ አልሰጠሁትም ተነሺ እስቲ ሲሁ እይው በአላህ አለችኝ ሰሙ እግሯ ላይ ያስቀመጠችው ነገር ስለነበር ለመነሳት አልተመቻትም እሺ ቆይ ትንሽ 10ደቂቃ እንየው እና እሄዳለው አልኳት መልስ አልሰጠችኝም 10ደቂቃው አልፎ 15ደቂቃ ጠበቅነው እሺ አሁንስ አለች ሰሙ አሁን ግን ከሷ ይበልጥ ማሂር ለምን ቆየ የሚለው ነገር እኔንም አሳሰበኝ 10ደቂቃ እንዳለፈው ባውቅም ሂጂ እስኪሉኝ ነበር የጠበኩት እሺ መጣው በቃ ብዬ ከመኪና ወረድኩ የምኔ መጣው ነው ይዘሽው ነይ እንጂ ኡሚኮ እየጠበቀችን ነው አለችኝ ትዛዝ መሆኑ ነው እሺ እሺ እመጣለው ብዬ ወደ ማሂር ማዳበሪያ ሄድኩ።የማሂር ማዳበሪያ ጋር ስደርስ ያገኘሁት ግን ያልጠበኩት ነበር...........


..........ይቀጥላል...........


https://www.tg-me.com/tesefgna
2024/04/28 08:55:31
Back to Top
HTML Embed Code: