Telegram Group Search
ብሒላተ አበው ወእመት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ pinned «የበኩረ መዘምራን ኪነ ጥበብ የዩቲዩብ ቻናል ነው ተብለናል ። የቀደሙት መዝሙራት በነበሩበት ቅጂ ቀርበዋል። ከመዝሙራቱ ጥዑምነት ባለፈ በረከትና ለታላቁ ትሑት አገልጋይ ወንድማችን ፍቅራችንን መግለጫ ይሆነናልና Subscribe እናድርግ። https://youtu.be/3ZflOHprp5g?si=IYnd3rs1MnlpfKfX»
የልብን ከሰይጣን።
.
ቀደምት አበው እና እማት የሰይጣንን ማንነት በሚገባ ከማወቃቸው የተነሣ ሰይጣንን መዋጋት እና ማሸነፍ ብቻ ሳይሆን ሰይጣንን ራሱን ያታልሉት ነበር። ይህም መንፈሳዊ ብቃታቸው እና ዕውቀታቸው የቱን ያህል ይደርስ እንደነበረ ከሚመሰክሩት ነገሮች አንዱ ነው። የትምህርተ-ኅቡዓት መተርጉማን «ሰይጣን የተነገረውን እንጂ የታሰበውን አያውቀውም» ይላሉ። ሰይጣን የሚችለው በሰው ልቡና የታሰበውን መገመት ብቻ ነው። በሰው ልቡና የተመላለሰውን ማወቅ ስለማይችል ሰዎች የልባቸውን ሁሉ እንዲናገሩ ይገፋፋቸዋል። ሔዋንን ስለዕጸበለስ ያንን ሁሉ የጠየቃት ለማወቅ ወይንም ለመረዳት ፈልጎ ሳይሆን ሥላሴ በሔዋን ልቡና የጻፉትን ነገር ማወቅ ስላልቻለ ነው። ሔዋን ስትናገር ግን ሃሳቡን ዐወቀ። ዐውቆም ዝም አላለም፤ ጠልፎ የሚጥልበትን ወጥመድ አዘጋጀ። እናቶቻችን ወደ ቅዱሳት መካናት ለመሳለም ሲሄዱ «ላሊበላ፣ አኩስም፣ ግሼን ልሄድ ነው» አይሉም ነበር። «እንጨት ልሰብር፣ ውኃ ልቀዳ፣ ዘመድ ልጠይቅ» እያሉ ነበር የሚጓዙት። ይህም ሰይጣን በልቡናቸው ያለውን ተረድቶ ዕንቅፋት እንዳያመጣባቸው ነው። ይህንን የሰይጣን ስንፍና ከሚያውቁ አበው መካከል አባ ሉቃ እና አባ ታድራ ያደረጉትን ከመጽሐፈ-መነኰሳት አንዱ የሆነው መጽሐፈ-ፊልክስዮስ ክፍል ፬ ተስእሎ ፶፮ ገጽ 91 ላይ እንዲህ ይነግረናል።
በአንድ ገዳም ውስጥ አባ ታድራ እና አባ ሉቃ የሚባሉ መነኰሳት ነበሩ። “እንጸናለን” ብለው የመጡ ብዙ መነኰሳትን ሰይጣን ከበኣታቸው ሲያስወጣቸው ተመለከቱና እንዲሁ ውስጥ ለውስጥ ተግባቡ። «በቀጣዩ ክረምት ከበኣታችን ወጥተን በበረሃ ለብቻችን እንጋደላለን፤ በዚያም ሰይጣንን ድል እናደርገዋለን» ተባባሉ። ሰይጣንም እውነት መስሎት እነርሱን ከበኣታቸው ለማውጣት የሚያደርገውን ፈተና ተወው። በበረሃም ይጠብቃቸው ጀመር። ክረምት በደረሰ ጊዜም «አሁንማ በክረምት እንዴት እንሄዳለን፤ በጋ ሲወጣ በረሃ ወርደን ሰይጣንን እንቀጠቅጠዋለን፣ እስከዚያ ዝም ብለን እንቀመጥ» ተባባሉ። ሰይጣንም እውነት መስሎት ፈተናውን ሁሉ ትቶ በጋ እስኪደርስ ጠበቃቸው። በጋም በደረሰ ጊዜ «ወደ በረሃ እንሄዳለን ተባብለን’ኮ ሰነፍን፣ ምን ይሻላል? በቃ በክረምት እንሄዳለን» ተባባሉ።
እንዲህ እያሉ ሰይጣንን ሃምሳ ስድስት ዓመት ዘበቱበት። በዚህም የተነሣ የመልክአ-ሥላሴ ደራሲ እንዲህ የሚል አርኬ ደረሰላቸው:
ሰላም ለአክናፊክሙ እሳታውያን አክናፍ፤
እለበማእከል ሀለዉ ወእለሀለዉ በጽንፍ፤
አለብወኒ ሥላሴ ቀትለ-መስተጋድል መጽሐፍ፤
ከመ-ወትረ ይትዋሥአኒ ትምይንተ-ሉቃ ትሩፍ፤
ወጉሕሉተ-ታድራ ምስሌየ ይዛዋዕ በአፍ።
በጎ ነገሮችን ከሰው ተማክሮ መሥራት መልካም ነው። ነገር ግን ቆራጥነትን የሚጠይቁ፣ ፈተናም የሚበዛባቸውን መልካም ነገሮችን ከመሥራት በፊት ማውራት ግን በራስ ፈቃድ መከራ መጋበዝ ነው። አበው እንዳሉት ሰይጣን የተነገረውን እንጂ የታሰበውን አያውቅም። ስለዚህም ስለምናስበው ነገር ሁሉ በየአጋጣሚው እንድናወራ ያደርገናል። ሥራን አንደበት ከሚገልጠው ራሱ ሥራው ራሱን ቢገልጥ እንዴት የተሻለ ነው? ብዙ እያወሩ ጥቂት ከመሥራት፣ ምንም ሳያወሩ ብዙ መሥራት እንዴት መልካም ነው? “ሙያ በልብ ነው” ይላል የሀገሬ ሰው። በየትዳሩ፣ በየማኅበሩ፣ በየጉባኤው፣ በየአጥቢያው ፈተና ከሚበዛባቸው ምክንያቶች አንዱ ይኼ ሊሆንስ ከቻለ? ሁሉንም ነገር ለሰይጣን ስለምንነግረው። ባል እና ሚስት ተያይተው ብቻ የሚግባቡባቸውን መንገዶች ገንዘብ ማድረግ አለባቸው። የምናስበውን ሁሉ አናውራ። በልቡናችን ተቀምጦ በተግባር ብቻ መገለጥ ያለበትን እንለይ።
ኮሚቴ ሲበዛ፣ ስብሰባ ሲበዛ፣ ውይይት ሲበዛ፣ ሰው ሲበዛ ብዙ ጊዜ መንፈሳዊ ሥራ መስራት ከባድ ይሆናል፤ መሰናክሉም ይበዛል። አንዳንድ ጊዜ ከተሰብሳቢዎቹ ጋር አጅሬም አብሮ ሳይሰበሰብ አይቀርም። ሴት የበዛበት ወጥ እና ወሬ የበዛበት መንፈሳዊ ሥራ ሁለቱም ይበላሻሉ። እስኪ ከወሬ ተግባር ይቅደም። የነአባ ታድራን እና የነአባ ሉቃን ነገር ባንረሳው መልካም ነው።

ስማችሁ የለም" ከተሰኘው መጽኃፍ የተወሰደ
༻༺✟"ክብሩ በአንቺ ላይ ይታያል"✟༺
. ༻༺✟ኢሳ.60፥2 ✟༻༺
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን!

በቅድምያ እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላምና በጤና አደረሳችሁ
አደረሰን!

እንደ ሚታወቀው ግንቦት ሃያ አንድ ቀን በዚች ዕለት አምላክን የወለደች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በደብረ ምጥማቅ በስሟ በተሠራች ቤተ ክርስቲያን ጉልላት ላይ በብርሃን መርከብ ተቀምጣ፤ በልጅዋ የመለኮት ብርሃን ተጎናፅፋ፤
የመላእክት ሠራዊት
የመላእክት አለቆች በየማዕረጋቸው ክንፋቸውን ዘርግተው በዙሪያዋ ቆመው ፊቷ በግልጥ ስለመታየቱ የክርስቲያን ወገኖች ሁሉ ታላቅ በዓልን ያደርጋሉ ።

ግልፅ በሆነ አማርኛ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የእግዚአብሔር የክብሩ መገለጫ ናት።

ስለዚህ እንዲህ ነው ብሎ ለማስረዳት እንኳ በሚያስቸግር መልኩ የእግዚአብሔር ክብሩ በእርሷ ላይ ተገለጠ።

እርሷ በብልሃተኛ እጅ ያልተሠራች ከብርሃን የተገኘው ራሱ የአብ ብርሃን በእርሷ ላይ አድሮ በአምላክነቱ ለዓለም ሁሉ ያበራባት የወርቅ መቅረዝ ምሳሌ ናት።

በእርሷ ላይ ክብሩን ገልጦ
ጨለማን ከሰዎች ላይ ያራቀውና
"እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፤
በብርሃኔ እመኑ፤
ብርሃን ሳለላችሁ ተመላለሱ"
ብሎ በሚያድን ቃሉ ያዳነን ደግሞ እርሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

ድንግል ማርያም እንደ መስታወት ናት።
መስታወት በራሱ በተፈጥሮው ብርሃን የለውም።
የፀሐይ ብርሃን ሲበራበት ግን የሁሉም ሰው ዓይን ሊቋቋመው በማይችል መልኩ መስታወቱ በሩቅ ያንፀባርቃል።

እመቤታችን ድንግል ማርያምም ከሐና እና ከኢያቄም የተወለደች የሰው ዘር ናት።

ነግር ግን ፀሐየ ጽድቅ ክርስቶስ ብርሃኑን በእርሷ ላይ ስለ አበራባት
ንጽሕናዋ፣
ቅድስናዋ፣
ድንግልናዋ፣
እናትነቷ ሁሉ ዓለም አቀፋዊ ነፀብራቅ ሆነ።

እርሱ ክብሩን ስለገለጠባት
የእርሷ ክብሯ ገነነ።

እርሱ ስለ ወደዳት
እርሷ በትውልድ ሁሉ ዘንድ ተወደደች።

እርሱ ከፍ ከፍ ስለ አደረጋት
የእርሷ ከፍታ ከከፍታዎች ሁሉ በላይ ሆነ።

በደብረ ምጥማቅ ከተማ ላይ የተገለጠውም እውነት ይኸው ነበር።

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምን በቤተ ክርስቲያን ጉልላት ላይ የልጅ ዓይን ወደ እናቷ ትኩር ብላ እንደምትመለከት ያመኑትም ያላመኑትም ብርሃንን ለብሳ ብርሃንን ተጎናጽፋ አምስት ቀን ሙሉ ተሰልፈው ሲያይዋት ሰነበቱ።

"ሰላም ለእለ ርእዩኪ ከመ ዐይነ ወለት ኀበ እማ፤ መዋዕል ሐምስ እስከ ይትፌጸማ፤
ማርያም ንግሥት ውስተ ደብረ ምጥማቅ ከተማ፤ ብፁዓት አዕይንት ዘነጸራኪ በግርማ፤
ወብፁዓት አእጋር ቅድሜኪ ዘቆማ።"
እንዳለ አርኬ።

ሰማያውያን መላእክት ከብበዋት ብርሃን ለብሳ ብርሃን ተጎናፅፋ በሚያስደንቅ ግርማ ሆና ትልቁም ትንሹም ወንዱም ሴቱም አምስት ቀን ሙሉ በዚያው ሥፍራ ላይ ድንኳን ተክለው አጎበር ጥለው በግልጥ እየተመለከቷት በዓል ሲያደርጉ ሰነበቱ።

ዛሬ ግን ጉዳዩ ከደብረ ምጥማቅም አልፎ በመላው ዓለም በዓሉ በደማቅ ሁኔታ ሲከበር ይኖራል።

የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ጉዳይ ይህን ያህል እንዲህ በክርስቲያኖች ሕይወት ውስጥ ሥር ሰድዶ ትልቅ ትኩረት ሊያገኝ የቻለው ደግሞ ኢሳይያስ በነገረን መልኩ እግዚአብሔር ክብሩን በእርሷ ላይ ስለ ገለጠ ነው።

ወዳጄ እግዚአብሔር እንዲህ ክብሩን ሲገልጥብህና አንተም የክብሩ መገለጫ ስትሆን ለዓለም ሁሉ መነጋገርያ አጀንዳ ትሆናለህ።

እግዚአብሔር ከፍ ሲያደርግህ ቀና ብሎ አንተን ለማየት የማይጓጓ ፍጥረት የለም።

እግዚአብሔር ስምህን ሲባርከው የስምህ መዓዛ ከልበኔ፣ ቁስጥ እና ሰንበልት ከሚባሉት ሽቱዎች በላይ ዓለምን ሁሉ የሚያውድ ግሩም የሆነ መዓዛ ይኖረዋል።

እኛም ዛሬ በምስጋና ማማ ላይ ሆነን፦
"ሰላም ሰላም ለዝክረ ስምኪ ሐዋዝ፣
እምነ ከልበኔ ወቀስጥ ወእምነ ሰንበልት ምዑዝ፣..."
እያልን የድንግል ማርያምን ስም በክብር የምናነሳበት ትልቁ ምሥጢር ይኸው ነው።

ድንግል ማርያምን ሁል ጊዜ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት የሚላት ብርቱ የሆነ እርሱ እግዚአብሔር በእርሷ ላይ ታላቅ ሥራን አድርጎአልና ነው።
እርሷ ራሷ "እስመ ገብረ ሊተ ኃይለ ዓቢያተ" እንዳለች።
ሉቃ.1፥49

ይህ እግዚአብሔር በእርሷ ላይ ያደረገው ታላቁ ሥራም ክብሩን በእርሷ ላይ የገለጠበቱ ረቂቅ ምሥጢር ነው።

ስለዚህ እግዚአብሔር ክብሩን የገለጠባትን ድንግል ማርያምን እግዚአብሔር ባከበራት ክብር ስናከብራት እንኖራለን።

የክብር ባለቤት የሆነውን እግዚአብሔርን ደግሞ ለዘለዓለም እናመልካለን።

አሜን!!!

╭✥✥✥✥✥✥✥✥✥╮
✥┈┈••●◉✞◉●••┈••✥
. አባ ኒቆዲሞስ (ጳጳስ)
. 21/09/2016 ዓ.ም
. ከሕይወት ተራራ ላይ
✥┈┈••●◉✞◉●••┈┈✥
╰✥✥✥✥✥✥✥✥✥╯
"አርእይኒ ገጸ ዚአኪ ማርያም ምእረ፤ ዘኢይሰምዖ ካልዕ እንግርኪ ነገረ"
"ማርያም ሆይ፣ ለሌላው የማልነግረውን ነገር እነግርሽ ዘንድ አንድ ጊዜ ፊትሽን አሳይኝ"

መልክአ ማርያም

እንኳን ለበዓለ ደብረ ምጥማቅ በሰላም አደረሳችሁ!
የክርስቲያናዊ ጋብቻ መገለጫዎች

አንድነት ፦
ቤተክርስትያን የምታስተምረው የጋብቻ ትምህርት አንድ ወንድ ለአንድ ሴት የሚባለውን ነው በመጀመሪያ እግዚአብሔር ያዘጋጅው አንድ አዳምን ለአዲት ሄዋን ነውና። በሥርዓተ ተክሊል እና በቅዱስ ቁርባን ሁለት የነበሩት ተጋቢዎች በክርስቶስ አንድ ይሆናሉ ስለዚህም ወደ ፊትም አንድ እንጂ ሁለት አይባሉም። ስው አባትና እናቱን ይተዋል ከሚስቱም ጋር ይተባበራል ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ (ኤፌ 5፥21)

ዘላቂነት ፦
ጋብቻ ሁለቱ ጥንዶች ያለ መለያየት እስከ እድሜያቸው ፍጻሜ በአንድነት የሚቆዩበት ሕይወት ነው። ምናልባት ሊለያዩባቸው የሚችሉበት ምክንያቶች ይኖራሉ ከነዚህም ውስጥ:-
* አንዱ ዝሙት ነው ይህም የመለያያ ምክንያት የሚሆነው የቅዱስ ጋብቻ ቅድስና ስለሚያሳድፈው ነው። ነገር ግን ኃጥያቱን የሠራው ወገን ንስሃ ከገባ እና ይቅር ከተባባሉ አብረው እንዲቀጥሉ ቤተክርስትያን ታስተምራለች ።
ሁለተኛው ፍቺ ሊፈፀም የሚችልበት ምክንያት ከሁለት አንዳቸው እምነታቸውን (ሃይማኖታቸውን) የለወጡ ከሆነ ወይም አለመመሳሰል (ልዩነት) ሲኖር ነው።
*
ሦስተኛው ጋብቻ የሚፈርስበት ምክንያት ባል ወይም ሚስት ከሁለት አንዳቸው በሞት ሲለዩ ነው።

ፍሬ ማፍራት ፦
በመንፈስ ቅዱስ ረዳትነት በቅዱስ ጋብቻ ሕይወታቸውን የሚመሩ ጥንዶች በርካታ ፍሬዎችን ያፈራሉ። ፍሬዎቻቸውም ፍቅር፣ በጎነት፣ የቤተክርስትያን አገልግሎት እንዲሁም ልጆች ናቸው።

ማጠቃለያ ፦የጋብቻ ሕይወት ጥንዶች በንፅህናና በቅድስና ሆነው በጋራ መንፈሳዊ ሕይወታቸውን በመምራት ክርስትያናዊ ተጋድሎ እየፈፀሙ ራሳቸውን ለመንግስተ እግዚአብሔር የሚያዘጋጁበት ሕይወት ነው። በተጨማሪም እግዚአብሔርን የሚያገለግሉ ሃገርን የሚጠቅሙ ልጆችን ወልደው በአግባቡ በማሳደግ በስርዓት የሚያንፁበት ሕይወት ነው።
ስለዚህ ከጋብቻ በፊት ይህንን ኃላፊነት ለመወጣት በቂ ስነ ልቦናዊና መንፈሳዊ ዝግጅትና ምክር ያስፈልጋልና ወደ አባቶች ቀርበን ልንማርና ልምድ ልንወስድ ያስፈልገናል።

(afa-የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ፍሬ page ላይ የተወሰደ)
“ክርስቲያን” ተብለህ መጠራትህ ዋስትና አይኾንህም፤ ዋስትና የሚኾንህ …

በመንገድ ዳር ላይ ዘርን የሚዘሩ ሰዎች ምንም የሚያገኙት ጥቅም እንደ ሌለ ኹሉ፥ እኛም ለልጅነታችን የሚገባ’ ምግባር ከሌለን ክርስቲያኖች ተብለን ከመጠራት የምናገኘው በቁዔት የለም፡፡ ይህ እንዴት ይኾናል የምትለኝ ከኾነም የጌታችን ወንድም የተባለው ያዕቆብን ምስክር አድርጌ እነግርሃለሁ፡፡ እርሱ፡- “ሥራ የሌለው እምነት ቢኖር በራሱ የሞተ ነው” ብሎአልና (ያዕ.2፡17)፡፡ ስለዚህ ለእኛ (ለክርስቲያኖች) ምግባር መያዝ ግዴታ ነው፡፡ ምግባር ከሌለን ግን “ክርስቲያን” የሚለው ስም ለእኛ የሚፈይደው ምንም ነገር የለም፡፡ በዚህ ተደነቅህን? እንኪያስ ንገረኝ ! በዓውደ ውጊያ የማይሳተፍ፣ ለሚመግበው ንጉሥም የማይዋጋ ከኾነ አንድ ወታደር ወታደር ተብሎ ቢጠራ ምን ጥቅም አለው? ለንጉሡ ክብር የማይዋጋ ከኾነስ ወታደር ተብሎ ባይጠራ ይሻለዋል፡፡ ይህ ሰው በንጉሡ የሚመገብ ኾኖ እያለ፥ ነገር ግን ንጉሡ በጠላቱ ላይ ድል እንዲያደርግ የማይዋጋ ከኾነ እንዴት ከቅጣት ሊያመልጥ ይችላል? ንጉሡን ምሳሌ አድርጌ ልናገረው የፈለግሁትስ ምንድን ነው? ልለው የፈልገሁት እግዚአብሔር በትንሹ ስለ ገዛ ነፍሳችን እንድንጠነቀቅ (ምግባር መያዝ እንድንችል) ኃይል (ዓቅም) ሰጥቶናል ነው፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ንስሐና ምጽዋት መጽሐፍ
#መድኃኔ_ዓለም

" ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ክርስቶስ ሆይ ቤተ ክርስቲያንህ ትሰግድልሃለች፣ ሙሽራህም ከፍ ከፍ ታደርግሃለች፣ በልዑላን ጥቅም፣ በሱራፌል ቅዳሴና በኪሩቤል ውዳሴ በመላእክትም ምስጋና፣ በትጉሃን ልመና ፣ በቅዱሳንም ፍጹምነት፣

በአዳም ንጽሕና በኖኅም መሥዋዕት በአብርሃም እንግዳ ተቀባይነት፣ በይስሐቅ ቸርነት፣ በያዕቆብ መገለፅ።

በዮሴፍ እሥራት ፣ በኢዮብ ትዕግሥት በሙሴም የዋህነት በኤልያስም ምስጋና።

በሐዋርያትም ማፍቀር፣ በቅዱሳንም ልመና፣ በተሰደዱ ሰዎች ድካም፣ ባልበደሉ ሰዎች ጽድቅ ንጽሕናን ባገኙ ሰዎች ትሕትና፣

በንጹሐን ገድል፣ ከምግብ በተለዩ ሰዎች ትምህርት፣ ፍጹማን ስለሆኑ ቅዱሳን ጽድቅ ፣

በምድር ዳርቻ ርቀት፣ በባሕር አዝዋሪም ጥልቅነት፣ በመባርቅት፣ ብልጭታ፣ በደመናትም መውጣት፣

በመላእክት ምስጋና፣በቅዱሳንም ምስጋና፣ በትጉሃን ንጽሕና፣ በልዑላንም መስማማት ፣
በመንፈሳውያን ብርሃን፣ በካህናት ቀኝ ፣ በሰማዕታት መሞት ፣ በምዕመናንም ደም፣
በብርሃናውያን መላእክትም ገናንነት።

በልጅህ መመታት በአንድ ልጅህ ሕማማት ሁሉን በያዘ ሥልጣንህም፣ ወደ ጌታችንና ወደ መድኃኒታችን ወደ ኢየሱስ ክርስቶስ አባት በምታርግ ጸሎት። "

ቅዳሴ ቄርሎስ
“በዚያ በጽርሐ አርያም የሚደነቅ ከማይታይ አብ የመወለድ ምስጋና አለው ፤ በዚህም በቤተ ልሔም ከድንግል የመወለድ ምስጋና አለው። በዚያ ከሰማያውያን ካህናት በወርቅ ማዕጠንት የዕጣኑን መዐዛ ይቀበላል ፤ በዚህም ወርቅን፣ ከርቤንና ዕጣንንም ከሰብአ ሰገል ተቀበለ ፤”
አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
"...ስለኃጢያቴ የተናቅሁ ስለእምነቴ ግን ከናዝራዊያን ወገን ስለጥምቀቴም የክርስቲያን ታላላቆች የሐዋርያት ልጅ የሆንሁ በሃይማኖት ዝናር የታጠቅሁ በሜሮን ቅባት የታተምሁ..."
መፅሐፈ ምስጢር
“የደከመውን አላጸናችሁትም የታመመውንም አላከማችሁትም የተሰበረውንም አልጠገናችሁትም የባዘነውንም አልመለሳችሁትም የጠፋውንም አልፈለጋችሁትም በኃይልና በጭቈናም ገዛችኋቸው።እረኛንም በማጣት ተበተኑ፥ ለምድርም አራዊት ሁሉ መብል ሆኑ፥ ተበተኑም።በጎቼ በተራሮች ሁሉና በረዘሙ ኮረብቶች ሁሉ ላይ ተቅበዝብዘዋል፥ በጎቼም በምድር ፊት ሁሉ ላይ ተበትነዋል፤ የሚሻም የሚፈልግም አልነበረም።ስለዚህ፥ እረኞች ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔ ሕያው ነኝና እረኛ ስለሌለ እረኞቼም በጎቼን ስላልፈለጉ እረኞችም ራሳቸውን እንጂ በጎቼን ስላላሰማሩ፥ በጎቼ ንጥቂያ ሆነዋልና፥ በጎቼም ለምድር አራዊት ሁሉ መብል ሆነዋልና ስለዚህ፥ እረኞች ሆይ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ፤ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በእረኞች ላይ ነኝ፥ በጎቼንም ከእጃቸው እፈልጋለሁ፥ በጎቼንም ከማሰማራት አስተዋቸዋለሁ። ከዚያም ወዲያ እረኞች ራሳቸውን አያሰማሩም፤ በጎቼንም ከአፋቸው አድናለሁ፥ መብልም አይሆኑላቸውም።”
— ሕዝቅኤል 34፥4-10
ከውዝግብ ባሻገር... ያዳነንን እናውቃለን!
***
1. የእግዚአብሔር የባሕርይ ልጁ ወልድ ከአብ ጋር ዘላለማዊ ሕልውና ያለው የባሕርይ አምላክ ነው። የተወለደ እንጂ ያልተፈጠረ ነው። ከአብና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በአንዲት መለኮታዊ ሥልጣን እና ኃይል ፍጥረትን ሁሉ የፈጠረ ነው፤ ከሆነው ያለ እርሱም የሆነ ምንም ምን የለም። ፈጣሪ አምላክ ነው። (ዮሐ. 1፥1-14፣ ዕብ. 1፣ 1ኛ ቆሮ. 8፥6)
2. ይህ ዘላለማዊ ህልውና ያለው እና ፍጥረት ሁሉ በእርሱ የተፈጠረበት የአብ አካላዊ ቃል በዘመኑ ፍጻሜ እኛን ለማዳን ራሱን ዝቅ አድርጎ ሰው ሆነ። ሰው ሲሆን ግን አምላክነቱን እና መለኮታዊ ክብሩን አጥቶ አይደለም፤ አምላክነት የሚቀማ እና የሚለወጥ ነገር አይደለምና። ይልቁንስ አምላክነቱን ሳይለቅ ከኃጢአት በቀር እንደኛ ሰው ሆነ። ሰው በመሆኑም የትሕትና ነገሮች ተነገሩለት። በባሕርዩ ፍጡር የሆነ ሥጋን ተዋሕዶ ሰው ስለሆነ አማናዊ ሰውነቱን ለማጠየቅ የባሕርይ አባቱን 'አምላኬ' አለው። ተራበ፤ ተጠማ፤ በላ፤ ጠጣ፤ መከራ ተቀበለ፤ ጸለየ፤ ተኛ፤ ወዘተ...። በዚህ በለበሰው ሥጋው ምክንያት ከኃጢአት በቀር ለሥጋ የሚገቡ ነገሮች ሁሉ ስለእስሱ ተብለዋል። ይህም ለእኛ ቤዛ እና መድኃኒት ይሆን ዘንድ በፈቃዱ እንጂ ግዴታ ወድቆበት አይደለም። በዚህም ፍቅሩን እንረዳለን እንጂ እንደ አይሁድ ውለታቢሶች ሆነን አምላካዊ ክብሩን ዝቅ አድርገን አናይም።(ዮሐ. 1፥1-14፣ ፊል. 2፥6-11፣ ዕብ. 4፥15)
3. ክርስቶስ ሰው ሆኖ እኛን ከማዳኑ የተነሣ ከዘላለማዊ አምላክነቱ እና ክብሩ ዝቅ ያለ አይደለም። ይልቁንም እርሱን (ከአብ እና ከመንፈስ ቅዱስ ጋር) የምናመልክበት እና ለዘላለም የምናመሰግንበት እጅግ ከፍ ያለ ምክንያት ሰጠን እንጂ። ቀድሞ ስለፈጠረን እና ስለሚመግበን እናመሰግነው ነበር። አሁን ግን የእኛን ባሕርይ ለብሶ እና እስከሞት የሚደርስ መከራ ተቀብሎ በማዳኑ የማንከፍለውን ውለታ ውሎልናል፤ አምልኳችንን በማዳን ደስታ እና ምሥጋና ሞልቶታል።
4. እነዚህ ከላይ ያነሳናቸው መሠረታዊ እና የመዳን ወንጌል ምሰሶዎች ናቸው። ክርስቶስ በቅዱሳት መጻሕፍት (በአይሁድ ነገረ ሃይማኖታዊ ብያኔ - in the paradigm of Judaism) የተገለጸው በዚህ መልኩ ነው። ከዚያ በኋላ ቤተ ክርስቲያን ከግሪክ የእውቀት ባሕል ጋር መስተጋብር ስታደርግ አስተምሮዋን በግሪክ ፍልስፍናዊ ብያኔ (Hellenistic paradigm) መግለጽ ነበረባት። ይህም ውስብስብ ነገሮችን ፈጠረ፤ ነገረ ክርስቶስን በተወሳሰበ መንገድ መግለጽን አመጣ። ቤተ ክርስቲያን ለአሕዛብም ስለሆነች በግሪክ ፍልስፍና ተጽሕኖ ሥር የነበረውን ዓለም ለማምጣት ወደዚህ ተዋሥኦ መግባቷ ትክክል ነበር።
ግን ከላይ ያልናቸውን መሠረታዊ ነገረ ክርስቶሳዊ ጉዳዮች ተምሮ እስካመነ ድረስ ሁሉም ክርስቲያን ይህን ውስብስብ ተዋሥኦ የመመርመር እና የመረዳት ግዴታ የለበትም። ከሁሉም ክርስቲያን የሚጠበቀው መሠረተ እምነትን አውቆ በዚያ በተአምኖ መኖር ነው። መምህራን ሊይዙት እና ቤተ ክርስቲያንን ከስህተት ይጠብቁበት ዘንድ የሚማሩት ረቂቅ እና ሐተታዊ (speculative) ትምህርት አለ። ሁሉም ሄዶ ሄዶ የሚያርፈው መሠረታዊው ትምህርት ላይ ነው። ሂደቱ simplicity ----> complexity -----> simplicity ነው።
ውስብስብ ጉዳዮችን ወደ ምእመናን አውርዶ በማኅበራዊ ሚዲያ መወዛገብ ግን ከጥቅሙ ጉዳቱ ይብሳል።

@Bereket_Azmeraw
" #ያለ#የነበረ፣ ዓለምን አሳልፎ ለዘላለም #ነዋሪ፣አልፋና ኦሜጋ፣ ለኩነተ ሥጋ #የመጣ፣ ዳግመኛም ይህን ዓለም ለማሳለፍ #የሚመጣ#የታመመው#የሞተው፣ ከሙታን ተለይቶ #የተነሣው፣ጻዕረ ሞትን #ያጠፋው፣ የጎሰቆለውን የአዳምን ባሕርይ #ያከበረው፣ ሟች በስባሽ ሥጋን #የተዋሐደው፣ ሞትን በሥጋ ድል #የነሣው፣ወደ ሲኦል ወርዶ ነፍሳትን ነፃ #ያወጣው፣ ሲኦልን #የበረበረው፣ የድኅነታችን መገኛ #የሆነው፣ በሚፈሩትም ሰዎች ልቡና አድሮ ዕውቀትን #የሚሰጥ፣ አስቀድሞ በነቢያት #የታወቀ፣ በሐዋርያት #የተሰበከ፣ ከሁለት ወገን ድንግል ከምትሆን ከእመቤታችን የተወለደው #የእግዚአብሔር_ልጅ፣ የዓለምን ኃጢአት ያጠፋ ዘንድ ያለ ኃጢአቱ #የሞተው፣ የጨለማውን አበጋዝ ዕውር ያደረገው ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። እርሱ ሥግው ቃል የሁሉ #አስገኚ፣ የሁሉ ፈጣሪ #እግዚአብሔር_ነው።"

✥✥✥ኤጲስ ቆጶስ ሄሬኔዎስ✥✥✥
በመምህራን አምላክ ተማጽነናል
+++++++++++++++
(ቀሲስ ስንታየሁ አባተ እንደጻፉት || Kesis Sintayehu Abate Reta )

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ አንዳንድ መምህራን በጉባኤ ቤት ለደቀ መዛሙርት በልባቸው ስፋት በእምነታቸው ጽናት መሠረት ብቻ ሊነገር የሚገባውን ምሥጢረ ሥጋዌ በማኅበራዊ ሚዲያ መከራከርያ አድርገው ጎራ ከፍለው ሲከራከሩ ማየት ከመለመድም አልፎ ስጋት እየሆነ ነው።

አንድ ሰው የተማረውን ሁሉ ተማሪዎቹን ወይም ሰማዕያኑን ሳያገናዝብ ማስተማር ከጀመረ ፍጻሜው ለራሱም ለሚሰሙትም የከፋ ይኾናል። ክቡር መልአከ ሰላም ኃይለ ኢየሱስ ከበደ የሚባሉ ሊቅ ለአእንደዚህ ዓይነት መምህራን “ዐይን የሚያየውን መሬት ሁሉ እግር አይረግጥም። ዐይን ካየው የመሬት ክፍል እግር መርገጥ ያለበትን ልብ ይመርጥለታል። መምህርም የተማረውን ያወቀውን ሁሉ በአደባባይ ላገኘው ሁሉ አያስተምርም። የተማሪዎቹን መጽሐፉን የሚያነብቡ ምእመናንን የእምነት ዳራ ማወቅ አለበት። ያለበለዚያ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል” ይላሉ።

ቅዱስ ጳውሎስ ለመንፈስ ቅዱስ ልጆቹና የረቀቀውን ምሥጢር መሸከም ላልቻሉተ “ወተት ጋትኋችሁ” ያለው መምህራን በራሳቸው የእውቀት ደረጃ ቆመው ሳይሆን በተማሪዎቻቸው ደረጃ ዝቅ ብለው በሂደት ወደ ልዕልና እንዲያደርሷቸው አርአያ ለመስጠት ነበር። ቅዱስ ዮሐንስም በመልእክቱ “እንድጽፍላችሁ የምፈልገው ብዙ ነገር ሳለኝ በወረቀትና በቀለም ልጽፈው አልወድም፥ ዳሩ ግን ደስታችሁ ፍጹም እንዲሆን ወደ እናንተ ልመጣ አፍ ለአፍም ልናገራችሁ ተስፋ አደርጋለሁ።” ያለው ተጽፎ በመልእክት የሚነገር እንዳለ ሁሉ ገፅ ለገፅ ተገናኝቶ በርጋታ የተማሪዎችን ደረጃ እየለኩ የሚነገር ስላለ ነው። 2ዮሐ 1፣12።

አንድ መምህር በአንድ ትልቅ የቤተ ክርስቲያናችን የነገረ መለኮት ኮሌጅ ሐዲሳትን ያስተምሩ ነበር። ደቀ መዛሙርቱ የመጡት ከተለያዩ የሀገራችን ጠረፋማ አካባቢዎች ጭምር ነበር። የመጻሕፍት፣ የቅኔ፣ የድጓ፣ የአቋቋም የመሳሰሉ መምህራን ነበሩ። ገና ውዳሴ ማርያም ቁጥር ያልዘለቁ ደካሞችም ነበሩ። መምህሩ ለእነዚህ ሁሉ በአንድ ክፍል “ቀዳሚሁ ቃል ውእቱ” እያሉ ትርጓሜውን ያወርዱት ጀመር።

በአጋጣሚ አንድ በመጻሕፍት መምህርነት ጥንቅቅ ያሉ ሊቅ ብፁዕ ሊቀ ጳጳስ ተማሪዎቹን ሊጎበኙ ወደ ክፍሉ ገብተው መምህሩ የሚያወርዱትን የቀዳሚሁ ቃል ትርጓሜ ያዳምጣሉ። ተማሪዎቹን አይዟችሁ ብለው ያበረታቱና መምህሩን ወደ ውጪ ይዘዋቸው ይወጣሉ። ከዚያም በኃይለ ቃል “አንተ ጨካኝ ለመላእክት ሳይቀር የረቀቀውን ነገረ ቃልን እንዴት እንዲህ አድርገህ ገና ውዳሴ ማርያም እንኳ በቅጡ ማድረስ ላልቻሉ ደቀ መዛሙርት ታሸክማለህ? እያስተማርክ ሳይሆን እየሰበርኻቸው ነው” ብለው ገሠጿቸው። እንዴት ማስተማር እንዳለባቸውም በጥንቃቄ ነገሯቸው።

እባካችሁ በማኅበራዊ ሚዲያ ነገረ ሃይማኖትን የምታስተምሩ መምህራን ለሚሰሟችሁ፣ ለምንሰማችሁ፣ ለምናነባችሁ በመምህራን አምላክ ስም አስቡልን። መጽሐፍ “ከእናንተ መካከል ብዙዎች መምህራን አይሁኑ” ያለውንም እያሰባችሁ እስቲ አንዳንዴ ዝም በሉ። ለሁሉ ጊዜ አለው። ለሁሉ ስልት አለው። የተማረ ሁሉ አስተማሪ አይሆንም። የተማረ ሁሉ በማንኛውም ጊዜ አያስተምርም። እንደ እኔ ያሉ ደካሞችን በቃል እንዳታሰናክሉ የወፍጮውን ድንጋይ አስቡ።

እግዚአብሔር ማስተዋሉን ይስጠን።
ብሒላተ አበው ወእመት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ pinned «" #ያለ፣ #የነበረ፣ ዓለምን አሳልፎ ለዘላለም #ነዋሪ፣አልፋና ኦሜጋ፣ ለኩነተ ሥጋ #የመጣ፣ ዳግመኛም ይህን ዓለም ለማሳለፍ #የሚመጣ፣ #የታመመው፣ #የሞተው፣ ከሙታን ተለይቶ #የተነሣው፣ጻዕረ ሞትን #ያጠፋው፣ የጎሰቆለውን የአዳምን ባሕርይ #ያከበረው፣ ሟች በስባሽ ሥጋን #የተዋሐደው፣ ሞትን በሥጋ ድል #የነሣው፣ወደ ሲኦል ወርዶ ነፍሳትን ነፃ #ያወጣው፣ ሲኦልን #የበረበረው፣ የድኅነታችን መገኛ #የሆነው፣…»
"ሁለቱም አንድ አካል ይኾናሉ ፤ ይህ ነገር ጥልቅ ፤ ረቂቅ ምሥጢር ነው ፤ እኔም ለክርስቶስና ለቤተክርስቲያን ምሳሌ አድርጌ እናገረዋለሁ፡፡"
     ሃይማኖተ አበው ዘስምዓት

የአብርሃምንና የሣራን ፤ የይሰሐቅንና የርብቃን ጋብቻ የባረከ አምላክ የትዳር ሕይወታችሁን ይባርክላችሁ እመብርሃን በአማላጅነቷ አትለያችሁ፡፡
2024/06/12 02:27:11
Back to Top
HTML Embed Code: