Telegram Group Search
የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል በአሪ ዞን ደቡብ ኦሞ ሀገረ ስብከት በጅንካ ደብረ ምጥማቅ ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን የሀገረ ስብከቱ ዋና ፀሐፊ መሪጌታ ኤልያስ ዘውዴ ፣የአድባራት አስተዳዳሪዎች ፣ በርካታ ምእመናነሰ በተገኙበት በድምቀት ተከብሯል።

ግንቦት 21 ቀን 2016 ዓ.ም(ተ.ሚ.ማ/ጅንካ)

ዘጋቢ:- ዲ/ን ሴኮ ከጅንካ
የቅዱስ ሲኖዶስ ሰባት አባቶችን በአጀንዳ አርቃቂነት ሰየመ !

ግንቦት 21 ቀን 2016 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ$

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ዛሬ ግንቦት 21 ቀን 2016 ዓ.ም ባደረገው የጠዋቱ የግንቦት ርክበ ካህናት የቅዱስ  ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ስብሰባ ሰባት አበው ሊቃነ ጳጳሳትን በመወያያ አጀንዳ አርቃቂነት ሰየመ።

በዚሁም መሰረት በመወያያ አጀንዳ አርቃቂነት የተሰየሙት ሰባት አበው ሊቃነ ጳጳሳት  ሕገ ቤተ ክርስቲያን በሚያዘው መሰረት ከቋሚ ሲኖዶስ ለምልአተ ጉባኤ እንዲቀርቡ የተመሩ እና ተጨማሪ የሚባሉ አጀንዳዎችን በመቅረጽ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የማስጸደቅ ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል።

በቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በጀንዳ አርቃቂ ኮሚቴነት የተመረጡት አበው ሊቃነ ጳጳሳት የሚከተሉት ናቸው።

1.ብፁዕ አቡነ ዲዮስቆሮስ
2.ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ
3.ብፁዕ አቡነ ማርቆስ
4. ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ
5. ብፁዕ አቡነ ሩፋኤል
6. ብፁዕ አቡነ ሕርያቆስ
7. ብፁዕ አቡነ ገብርኤል
ብፁዕ አቡነ ድሜጥሮስ በተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ የአርመን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሜሶብ ሳርኪሲያኒን ጋር ተወያዩ !

ግንቦት 23 ቀን 2016 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ) ብፁዕ አቡነ ድሜጥሮስ በተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ የአርመን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሜሶብ ሳርኪሲያኒን ጋር ተወያይተዋል። በውይይቱ ወቅት በሻርጃ ፣ዱባይ እና አጅማን በስደት የሚኖሩ ምዕመናን ለ25 ዓመታት ሲገለገሉበት የኖሩት የአርመን ቤተ ክርስቲያን በተፈጠረው ክፍተት በቦታው ላይ የማገለገል ክልከላ መደረጉን ተከትሎ በብፁነታቸው አቡነ ዲሜጥሮስ አባታዊ ጸሎት እና ውይይት ችግሩ ተፈትቶ አገልግሎቱ ወደ ነበረበት እንዲመለስ መደረጉ ነው የተገለጸው። #Ethiopia
#Tewahedo_Media_Center
#TMC_Addia_Ababa

ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል
እውነተኛ የተዋሕዶ ድምፅ

ማንኛውንም መረጃዎች እና የዜና ጥቆማ በስልክ ቁጥር +251913502324 በቀጥታ በመደወል ወይም በቴሌግራም መልዕክት ይላኩልን !

የዩቲዩብ ቻናላችንን ሰብስክራይብ ያድርጉ
https://youtube.com/@TMC1

የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ ፤ ፈጣን መረጃዎችን ያግኙ https://www.tg-me.com/ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል Tewahedo Media Center TMC/com.tewahedomediacenter

አጫጭር ትምህርታዊ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኘት የቲክ ቶክ አማራጫችንን ይመልከቱ
https://vm.tiktok.com/ZM8WVucY7/

የኢንስታግራም ገጻችንን
www.Instagram.com/tewahedo_media
የርክበ ካህናት ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ልዩ ልዩ ውሳኔዎችን በማስተላለፍ ጉባኤውን ቀጥሏል።

የግንቦት 2016 ዓ.ም የቅዱስ ሲኖዶስ ርክበ ካህናት ምልዓተ ጉባኤ በትናንትናውና በዛሬው የጉባኤ ውሎው የኮሪደር ልማቱን በተመለከተ ባደረገው ውይይት የልማቱ ሥራ በተያዘው ፍጥነት ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት መሆኑን በመወሰን ከመንግሥት በምትክነት በተሰጡ ቦታዎች ላይ የልማት ሥራው በፍጥነት መከናወን ይችል ዘንድ የመሰረት ድንጋይ እንዲቀመጥ ሲል ውሳኔ አስተላልፏል።

በሌላ በኩል ቅዱስ ሲኖዶስ የሃይማኖት ተቋማት ረቂቅ አዋጅን በተመለከተ ረቂቅ አዋጁን በንባብ ካዳመጠና በረቂቅ አዋጁ ዙሪያ ሰፊ ውይይት ካደረገበት በኋላ የሃይማኖት ተቋማት ረቂቅ አዋጁ በቤተክርስቲያናችን ዙሪያ ያለው ጠቃሚ እና ጎጂ ጎን በዝርዝር ተጠንቶና ለውሳኔ አሰጣጥ በሚያመች መልኩ ተዘጋጅቶ እንዲቀርብ ወስኗል።

ጉዳዩን በጥልቀት ተመልክተው የሚያቀርቡ በአባቶችና በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን የሚመራ ቡድን እንዲሁም ከሕግ ባለሙያዎች ሦስት ባለሙያዎች ተካተውበት በሚገባ ተዘጋጅቶ በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲያቀርቡ ውሳኔ አስተላልፏል።

በዛሬው ዕለት ባደረገው ጉባኤም ከታክስ አከፋፈል፣ የልዩልዩ ደንቦች ዝግጅትን፣ ዝውውር የጠየቁ ብፁዓን አባቶችን ጉዳይ፣ የሀገረ ስብከት ስያሜን ጉዳይ በተመለከተ በጥልቀት ተወያይቶ ውሳኔ ካስተላለፈ በኋላ የቤተክርስቲያናችንን የ፳፻፲ወ፯ ዓ.ም በጀትንምአጽድቋል።

ቀሪ የመወያያ አጀንዳዎችንም በነገው ዕለት በሚያደርገው ስብሰባ በጥልቀት በመመወያየት ውሳኔ የሚያስተላልፍባቸው ይሆናል።
2024/05/31 19:52:16
Back to Top
HTML Embed Code: