Telegram Group Search
አሁን ላይ ብቻችንን እያወራን የምንሄድ ሰው ካያችሁ exit ወይም Entrance ተፈታኝ ነን 😁🙂🥺

👇👇👇
@fezekiru
« ቀስ…
ስለ ተፋቀራችሁ ብቻ አትዛለቁም!
ቀስ… ረጋ በሉ
በደንብ ተዋወቁ… ተግባቡ ስለነሸጣችሁ ብቻ በሙገሳ ቃላት አትጨመላለቁ።
ሰከን…
ትዳራችሁ በእግሩ ይቁም… የትዳር አጋራችሁን በትክክል ተረዱት… የሚታረሙ እና ደስ የሚያሰኙ ባህሪዎቹን በደንብ እወቁ።
አደባባዩ ፍቅር እና መውደዳችሁን እንዲያውቅላችሁ አትጣደፉ። በጎጇችሁ መፈቃቀር መሞጋገስን በደንብ ተካኑ።
ቀስ… ረጋ በሉ
እኩል ጊዜ ስላገኛችሁ፣ አጋጣሚዎች በተደጋጋሚ ስለሚያገናኛችሁ፣ ከአስተሳሰባችሁ ጋር የሚገጥም ሰው ወድያው ስላገኛችሁ ስለዛ ሰው ቅድስና ለማውራት አትጣደፉ። ትንሽ እስከምትቃረኑ… እኩል ጊዜ እስከምታጡ… የሚያገናኛችሁ ነገር እስከሚቀንስ … ዱንያ እስከሚያቀያይማችሁ ድረስ ስለምትቀድሱት ሰው በእርግጠኝነት አታውቁም።
አደብ… ሀያዕ ይኑራችሁ
የትላንት መልካም ጊዜያትን በዛሬ ኩርፍያዎች ውሸት ለማድረግ፣ ትወዱት ታከብሩት የነበረውን ሰው መልካም ነገሩን ለመክዳት አትሽቀዳደሙ!
ስትለያዩ ከልባችሁ ሰዎችን ስታርቁ አደብ ይኑራችሁ!
ረጋ… ቀስ… ሰከን…
የምትወዱት፣ የምታከብሩትን የልብ ወዳጃችሁ አደባባዩ ካላወቀው ፍቅራችሁ ልክ አይደለም ማለት አይደለም። ያ የልባችሁ ሰው በደንብ እሱ ይወቅ! ወጪ ወራጁ እንደሆነ ሰሞንኛ ነው እንደሁኔታው ያጨበጭባል!
አደብ… ሀያዕ ይኑራችሁ
ስለ ሰዎች የልብ ጉዳይ አውቃለሁ የሚል ዘግናኝ ድፍረት መላበስን፣ ባስ ሲልም ሰዎችን ጀነትና ጀሀነም የመዶል ጨካኝ አረመኔነትን መታጠቅን አምርራችሁ ጥሉ።
ለሚወዱት ለሚያከብሩት በአደባባይ ፍቅራቸውን የሚገልፁትን ስለ ፍቅራቸው ለመጠራጠር፣ አስመሳይ ለማለት አትድፈሩ። የልባቸውን አታውቁም!
ለፍቅር ለአክብሮታቸው ዱዓ አድርጉላቸው፣ ከእነሱ ከተዋደዱት የተሻለው እንዲገጥማችሁ ተመኙ!
ለፍቅር፣ ለአድናቆት ለጥላቻም ቀስ… ረጋ… ሰከን በሉ።
አደባባዩ ልባችሁ እንደሚያስበው አይደለም፣ ደጋሚና ቀናተኛ ፈራጅ ሞልቶበታል።
ትንሽ ኑሩ…
ገና ወፌ ቆመች የሆነው ወዳጅነታችሁ በደንብ ጠንቶ እስኪራመድ መዋደድ መፋቀራችሁ ከወደዳችሁት ካፈቀራችሁት ሰው ጋር በደንብ ይዋሐድ!
ግድ የላችሁም ትንሽ አብራችሁ ኑሩ፣ ከመፋቀር አለፍ ብላችሁ መርረዳት ላይ ድረሱ። ስለተፋቀራችሁ ብቻ አትዛለቁም!
ቀስ… ሰከን… ረጋ… ብቻ ውስጤ እንዲህ ይለኛል! »

@fezekiru
@fezekiru
ኢብኑ አቢ ለይላ እና ሁለቱ ሴቶች 👌

የሴቶች ሴራ😂


አንዲት አሮጊትና ወጣት ሴት ተካሰዉ በዘመኑ ታዋቂ ወደነበረዉ ቃዲ ኢብኑ አቢ ለይላ ይሄዳሉ

ዳኛዉ መጀመሪያ ማን ይናገር አለ አሮጊቷ አንቺ ተናገሪ አለች ወጣቷም የሁለታችንም እኔ እናገራለሁ ከተሳሳትኩ ትመልሰኛለች አለች


ከዚያም አንተ ቃዲ ሆይ! ይህች አጠገቤ ያለችዉ አሮጊት አክስቴ ነች አባቴ ሲሞት የቲም አድርጎ እሷ ጋ ተወኝ እሷም ባማረ አስተዳደግ አሳደገችኝ በዚህም እንደ እናቴ ስለሆነች እናቴ በማለት ነዉ የምጠራት አለች

ዳኛዉም ከዚያስ አላት

እድሜዬ ለትዳር ሲደርስ የአጎቴ ልጅ ለትዳር  ጠየቀኝ አክስቴም በትዳር አጣመረችን

በጣም እንዋደድ ነበር እኔ ለሱ እሱም ለኔ ብቻ እንደተፈጠርን ከአለም ሌላ እንደሌለን እናስብ ነበር።

ከሶስት አመታት በፍቅር የተሞላ ትዳር በኋላ  የባሌን መልካምነት ስትመለከት ሃብቱም እየሰፋ ሲመጣ ለልጇ ተመኘችዉ

ከዚያም ያማረ ልብስ አልብሳ አስዉባ ወደ ባሌ አስገባቻት እሱም ሲያያት ወደዳት አክስቴም ይህችን ልጄን  እንዳጋባህ  አንድ መስፈርት አለኝ አለችዉ ምን እንደሆነ ሲጠይቃት የመጀመሪያዋ ሚስትህን (የወንድሜን ልጅ)  ሃላፊነት በእጄ ልታረግና ፍቿን እኔ ልሰጣት አለችዉ

እሱም ተስማማ በሰርጉ ቀይ ወደኔ መጥታ ባልሽ ልጄን አግብቷታል ያንቺም ጉዳይ በእጄ አድርጎታል አናም ተፈትተሻል አለችኝ በሌሊትና በረፋድ ፈት ሆንኩ

ከአጭር ጊዜ በኋላ ለረዥም አመታት ሌላ ቦታ የቆየዉ ባሏ ከመንገድ ተመለሰ ታዋቂ ነጋዴ ነበር (ገጣሚም ነዉ ተብሏል)  ስለኛ ሲጠይቃትም እኔ አግብቼ እንደተፋታሁ ልጁም እንዳገባች ነገረችዉ እሱም የመዘየር ሃቅ  አለብኝ በማለት ሊጠይቀኝ መጣ

በዚህ ጊዜ የአክስቴ ባል ሆይ! ታገባኛለህን? አልኩት እሱም መስማማቱን ገለፀልኝ

ነገር ግን አንድ መስፈርት አለኝ እሱም የሚስትህን ጉዳይ  በኔ እጅ ልታደርግ  አልኩት እሱም ተስማማ

ከዚያም ለአክስቴ ባልሽ ያንቺን ጉዳይ በእጄ አድርጎታልና ከርሱ አፋትቼሻለሁ በማለት መልእክት ላኩላት። ከዚያም አገባሁት አክስቴም ፈት ሆነች
አንተ ቃዲ ሆይ!  አላህ እድሜህን ያስረዝመዉና  በዚህ መልኩ አንድ እኩል ሆንን አለች

በዚህ ጊዜ ቃዲዉ በሚሰማዉ ነገር ደንግጦ በመቆም ያአላህ! አለ  እሷም ገና ታሪኩ አልጀመረም ተቀመጥ አለችዉ

እሺ ቀጥይ አላት

ባሌ ከትንሽ የትዳር ቆይታ በኋላ ሞተ እኔም ንብረቱን ወረስኩ

ታዲያ በዚህ ጊዜ አክስቴ መጥታ ለብዙ ዘመናት ለንግድ ሲሄድ ርቀቱን የታገስኩ ልጁን ያሳደግኩ እኔ ነኝ ከዚህ ሃብት ሃቅ አለኝ ብላ ዉርስ ጠየቀች  እኔም እኔ የባሌ ሃብትና ሃቄ ነዉ  አንቺ ከዉርሱ ምን አገባሽ አልኳት

ኢዳዬ ከተጠናቀቀ በኋላ አክስቴ ልጇንና በዉርስ ጉዳች እንዲያሸማግለን የድሮ ባሌን የአሁን የአክስቴ ልጅ ባል ይዛ መጣች።

ወጣቷ ትረካዋን ትቀጥላለች

ከዚያም የድሮ ባሌ ሲመለከተኝ ያሳለፍናቸዉን ጊዜያት አስታወሰ ድጋሚም ከጀለኝ

እኔም ትመልሰኛለህን? አልኩት  መስማማቱን ገለፀልኝ እኔም ግን አንድ መስፈርት አለኝ እሱም የአክስቴን ልጅ ጉዳይ በእጄ ልታደርግ አልኩት። በመስፈርቴ ተስማማ ለአክሰቴ ልጅ ተፈትተሻል አልኳት።

በዚህ ጊዜ ቃዲዉ ኢብኑ አቢ ለይላ እጁን ጭንቅላቱ ላይ አድርጎ ጥያቄዉ የታለ 😳 አለ

አክስትም ተነስታ አንተ ቃዲ ሆይ!  ይህ እንደ ሸሪዓ ሃራም አይደለምን? እኔና ልጄ ፈት ሆነን ይህች ሴት ሁለት ባልና ዉርስ የምትወስድ? አለችዉ

ቃዲዉም በዚህ ዉስጥ ሃራም ነገር አላየሁበትም አንድ ወንድ ሁለት ጊዜ አግብቶ ሁለት ጊዜ መፍታቱና ዉክልና መስጠቱ ምኑ ላይ ነዉ ሃራምነቱ? አለ 

ከዚያም በዘመኑ ከአባሲያዎች የነበረዉ ዋሊ መንሱር ጋር ሄዶ ታሪኩን አጫወተዉ

መንሱርም ከሳቁ ብዛት እግሩን ከመሬት ያማታ ነበር ከዚያም እንዲህ አለ "ቃተለላሁል አጁዝ ለወንድሙ ጉድጓድ የቆፈረ ራሱ ይወድቅበታል ይህችን ግን ባህር ላይ ወደቀች😂😂"


👇👇👇
@fezekiru
ካልተነበቡ መስመሮች....

<<.....ናፍቆት ያቀላቸውን አይኖችሽን ሸሽቼ ስርቅሽ ካየሽኝ.... የመቆየት ጉጉትሽን እያወኩ ወጉን በአጭሩ ሳስቀረው ልብ ካልሽ.... እንደ ሰው ፍረጂኝ!.... ስሜቴን ለማወቅ የተጠማሽውን ያህል መልሴ ሳያረካሽ ሲቀር.... መሄድሽም መምጣትሽም.... የመንጋትና የመምሸት ያህል እንኳ ኢምንት ያላጎደለብኝ ሲመስልሽ.... እንደ ሰው ፍረጂኝ!.... <ጨካኝ>..... <ልበቢስ>..... <የማይገባህ>.....በዪኘኝ፤ ጥዪኝ.... ሽሺኝ.... በእምባዎችሽ መሃል ጠንካራ ለመሆን በምትጥሪበት ትንቅንቅ ውስጥም ሆነሽ ግን.... እንደ ሰው ፍረጂኝ!.... እ.ን.ደ.ሰ.ው!.... ነገ በጌታሽ ፊት ተናንሶ እንደሚቆም አቅመቢስ ሰው!.... ከጥያቄሽ ጀርባ የሚመጣውን ቋጥኝ ወንጀል መሸከም እንደማይችል ሰው!..... ከእይታ በኋላ መስበርን.... ከመቅረብ በኋላ መራቅን.... ከማፍቀር በኋላ መርሳትን እንደማይችል ደካማ ሰው..... ባንቺ ተፈትኖ የጌታውን ፈተና መውደቅን እንደማይቋቋም ሰው ፍረጂኝ..... ምናልባት አንድ ቀን..... ዶሴው በጌታሽ ፊት ሲከፈት..... ካንቺ በላይ ስላንቺ ማንባቴን ድብቅ ዱዐዎቼ ይመሰክሩብሽ ይሆናል..... ማን ያውቃል...>>

@fezekiru
@fezekiru
ናፍቀው ናፍቀው ቢያወሷቸው
ይርባሉ አይጠግቧቸው።
ቃል ሰድረው ቢያልቋቸው
በ’ዝም ሰጥመው ቢያስቧቸው
ይርባሉ አይጠግቧቸው።
ወዳጃቸው!
ነቢ ውዱ
ሙሀመዱ
ተጠምቶ ከረካ፣ በልቶም ከጠገበ
እጅጉን ብርቱ ነው አንቱን የተራበ።

@fezekiru
@fezekiru
« በመልካምነታቸው ልባችንን ፈገግ ለሚያስብሉ፣ ስናስታውሳቸው ስማቸው ሲጠራ ወደ አዕምሯችን ባማረ ትውስታቸው ለተሳሰረ፣
ሰውነትን ባላረከሱ ላይ ሁሉ ሰላም ይስፈን!
ሰላም ለእናንተ የልቦችን ፈገግታ ባላበላሻችሁ ሁሉ! ሰላም ከዱዓ ባልተዘነጉት ሌሎችንም በሚያወሱት ላይ ይሁን!

@fezekiru
@fezekiru
.ስለ ሰዎች ምስጢር ማወቅ ምንም ምቾት የለውም። ግድ ሆኖ ሰብዓዊነት አስገድዶ እንጂ ሰዎችን ’አብሽሩ’ ለማለትም ህመማቸውን ማዳመጥ ልብ ላይ ጥሎ የሚያልፈው ጠባሳ አለ።
የሰዎችን ጉዳይ አውቆ በህመም ስቃያቸው ለመሳለቅና ለማሽሟጠጥ እንከፍ የሆነ ደነዝ ጭንቅላት ይጠይቃል። ጤነኛ ሰው እንዴት በሰዎች መከፋት ይሳለቃል?
ስለ ሆነ ሰው ተፈላፍሎ ለማወቅ ላይ ታች የምትኳትኑ ሰዎች ካወቃችሁ በኋላ " ከዛስ…? " ለሚለው ጥያቄ በቂ መልስ አላችሁ?
ከዛስ… ምን?
ስለ ሰዎች የሆነ ጥሩም ይሁን መጥፎ ነገር ስናውቅ ከውስጣችን ጋር የሚወሐድ አንዳች ነገር ይኖራል። ቀስ በቀስ… እየተላመድነው የምንመጣው፣ ቀስ በቀስ… ስሜት አልባ እያደረገን የሚመጣ፣ ቀስ በቀስ… ተስፋ መቁረጥ የሚያለማምደን… ቀስ በቀስ… ሁሉንም በጅምላ የሚያስደፈጥጠን…ሻል ካልን አልሀምዱሊላህ ማለትን የሚያስታውሰን የሆነ የማናውቀው ስሜት እናዳብራለን።
ለሰዎች ለደስታቸው ሰበብ የሚሆን ነገር ማዋጣት ከቻልን እሰየው ካልሆነ ግን ስለ ሰዎች ምስጢር መስማትና ማወቁ በራሱ ሌላ ህመም ነው።
ግን… ግን…በእውነቱ ሰዎች ሁሉ መልካም ናቸው ብሎ እንደማሰብ ሰላም የሚሰጥ ነገር የለም። ብቻ ልቤ እንዲህ ይለኛል።
........
@fezekiru
@fezekiru
የማለዳ ማስታወሻ..
.
ሌቦች ባገኘኸው አጋጣሚ ሁሉ የምትሰርቅ ይመስላቸዋል። ውሸታሞች ንግግርህ ሁሉ ውሸት ነው ብለው ያምናሉ። የማያምኑህ ሰዎች ብዙ ሰዎችን የከዱ ናቸው። ገዳዮች አንተ ፊት እንቅልፍ አይጥላቸውም፣እንደምትገድላቸው እርግጠኛ ስለሚኾኑ። "ማንንም አላምንም!" የሚሉት ለማንም የማይታመኑ ሰዎች ናቸው።
.
በአዕምሮዋቸው የፈጠሩት ማንነትህ ያንተ ባሕሪ ላይ የተመሠረተ ሳይኾን በእነሱ ልምድ ላይ የቆመ እውነት ነው። ስጋታቸው የሚመነጨው ከስብዕናቸው ነፀብራቅ እንጂ ካንተ ጉድለት አይደለም። በውንጀላቸው ውስጥ ማንነታቸውን ታያለህ።

.
@fezekiru
@fezekiru
አስታውስ
« በመልካምነታቸው ልባችንን ፈገግ ለሚያስብሉ፣ ስናስታውሳቸው ስማቸው ሲጠራ ወደ አዕምሯችን ባማረ ትውስታቸው ለተሳሰረ፣ ሰውነትን ባላረከሱ ላይ ሁሉ ሰላም ይስፈን! ሰላም ለእናንተ የልቦችን ፈገግታ ባላበላሻችሁ ሁሉ! ሰላም ከዱዓ ባልተዘነጉት ሌሎችንም በሚያወሱት ላይ ይሁን! @fezekiru @fezekiru
አንዳንድ አይኖች ለእንባ እንጂ የተፈጠሩ አይመስሉም ሰላም ለእነዛ በውስጣቸው ሀዘንን  ስቃይን ለተሸከሙ ሰዎች💔

ፈገግታቸው ከፊታቸው ለማይጠፋ ሰዎች የረበና ሰላም በእናንተ ላይ በሀዘንተኛው ልባችሁ ላይ ይሁን

👇👇👇
@fezekiru
ባጠፉ ቁጥር "አጥፍቻለሁ፣ ኅጢአተኛ ሆንኩ" የሚለው ስሜት ኅጢአትን በሠራንና በተላመድነው ቁጥር በውስጣችን እየሞተ የሚሄድ ነው። ተከላከሉ፣ እጅ አትስጡ፣ ያ እስኪሆን አትጠብቁ። በወደቃችሁ ቁጥር መውደቃችሁን እሺ ብላችሁ አትቀበሉ። ከወደቃችሁበት ተነሱ።

"ያ አጥፍቻለሁ፣ ነፍሴን በድያታለሁ" የሚለው የቁጭት ስሜት በዉስጣችሁ ከሚሞት እናንተ ራሳችሁ ብትሞቱ ይሻላችኋል ።


@fezekiru
🤠ህልም ሲኖርህ
በዱዓዎችህ ውስጥ እንዲበራ እና
በልብህም ውስጥ እንዲመታ አድርገው
⇘ የማይሆን ነው/impossible ለሚልህ ሁሉ
ጆሮህን አትክፈትላቸው ።

👇👇👇
@fezekiru
ልስቅ ፈልጋለሁ…

ችግር ቢወረኝም አቅሜ ቢደክምም
ልስቅ ፈልጋለሁ…
ሳግ ቢተናነቀኝ፣ ጉልበቴ ቢዝልም
😁ፈልጋለሁ…
የሚወደኝ ባጣ፣ ጓድ ባይኖረኝም
😁 ፈልጋለሁ…
ሰው መቅረብ ብፈራም፣ ሲቀርቡኝ ብሸሽም
😁 ፈልጋለሁ...
ጨለማው ቢያይልም፣ ንጋቴ ቢርቅም
😁 ፈልጋለሁ…
ረሃቡ ቢጠናም፣ ሰላሜ ቢናጋም
😁ፈልጋለሁ…
ማጣቴ ቢከርም፣ ልቤ ቢሰበርም
😁 ፈልጋለሁ…
ያመንኩት ቢከዳም፣ የጠበቅኩት ቢቀርም
😁 ፈልጋለሁ…
ዱዓዬ ምላሹ ራቀ እንጂ፣ መመለሱ አይቀርምና!
ልስቅ ፈልጋለሁ…

@fezekiru
@fezekiru
እኛ እንዲህ ነን…

ብዙ የደስታ አመታት ብናሳልፍም ያሳለፍነው አንድ የሀዘን አመት ገዝፎ ይታየናል። ከተሰጡን ብዙ ሪዚቆች ይልቅ የጎደሉን ጥቂት ነገሮችን ለይተን የማወቅ የተለየ ችሎታ አለን፣ ያሉንን የመዘንጋትም!
እኛ እንዲህ ነን…
ደስታን በነፃ ከመቀበል ሀዘንን መግዛት ይቀለናል። ፊታችንን ማዞር ባለመቻላችን ምክንያት ጌታችንን "ለምን?" ብለን የምንጠይቅ ደፋሮች ነን።
እኛ እንዲህ ነን…
ጌታችን የተንከባከበንን እልፍ አመታት ዘንግተን፣ በአንድ የጨለመች የመፈተኛችን ቀን ፈጣሪያችንን የምንወቅስ አሳፋሪወች ነን። የታዘዝነውን ትተን ከበታቻችን ያሉትን በመተው የበላዮቻችንን በማየት፣ ላንጎዳው እሱን፣ ራህማኑን ምስጋና የነፈግን ነን። እኛ ምስጋና ቢሶቹ ነን። እኛ እንዲህ ነን…


@fezekiru
@fezekiru
ሀላል ካፕ ዛሬም ቀጥሎ ውሏል ዛሬ በተደረገው ጨዋታ ቢላል ከአንሳር ጋር ባደረጉት ጨዋታ ቢላል አንሳርን 3 2 በሆነ ውጤት አሸንፏል። በተደረገው ሌላኛው ጨዋታ ሰላም ከኑር ሰላም ኑርን 1 0 በሆነ ውጤት አሸንፏል።
https://www.tg-me.com/halale_merdaja_dilla
2024/05/26 15:02:20
Back to Top
HTML Embed Code: