​​ፆመ ሐዋርያት

አንዳንዶች የሰኔ ፆም የቄስ ፆም ነው በሚል ከመፆም ወደኋላ ሲሉ ይታያሉ ነገር ግን ቅድስት ቤተክርስቲያን በአዋጅ ከምትፆማቸው ሰባት አፅዋማት አንዱ እንደመሆኑ መጠን እያንዳንዱ ክርስቲያን ቢፆመው እጅግ በርካታ በረከቶችን ያገኝበታል ከነዚህም ጥቂቶችን እነሆ

1.በረከተ ሐዋርያት ይገኝበታል
ይህን ፆም መጀመርያ ፆመው እንድንፆመው ሰርዐት የሰሩልን ሐዋርያት ናቸዉ ስለዚህም ፆሙ መታሰቢያነቱ የሐዋርያት ነው የጻድቅ መታሰቢያ ደግሞ ለበረከት ነው ። ምሳ.10፥7 እኛም የሰኔን ፆም ብንፆም የሐዋርያቱን በረከት እናገኛለን ሐዋ.13፥1-3 ሐዋ.14፥23

2. በስራችንና በአገልግሎታችን በረከት እናገኛለን
ሐዋርያት ይህን ፆም የፆሙት አገልግሎታቸው እንዲከናወንላቸው እንዲባረክላቸው ነው ነብዩ ነህምያም እየሩሳሌምን የመስራት ተግባሩ እንዲባረክለት በፆመው ፆም ስራው ሁሉ ተባርኮለታል። ነህም.1፥4። እኛም የሰኔን ፆም ብንፆም በዕለት ተዕለት ተግባራችን በረከት እናገኛለን።

3. ዝናብ ምህረትን ጠለ በረከትን እናገኛለን
የሰኔ ፆም በአገራችን የክረምቱ መግቢያ ላይ የሚፆም ፆም ነው ይህም መጪው የክረምቱ ወራት የተስተካከለ የምህረት ዝናም እንዲኖረው ያደርጋል በነብዩ ኢዩኤል ዘመን ዝናብ ጠፍቶ ዛፎቹ ሳይቀር በደረቁ ጊዜ በፆም በፀሎት ወደ እግዚአብሔር በተማፀኑ ሰዓት ዝናመ በረከትን አግኝተዋል። ኢዩ.1፥13-14

4. በረከተ ምርትን እናገኛለን
የሰኔ ፆም በሃገራችን ገበሬው ዘር መዝራት በሚጀምርበት ጊዜ የሚፆም ፆም ነው ሰለዚህም በዚህ ሰዓት የሚፆመው ፆም ዘርን እንዲባረክ በረከት እንዲበዛ ያደርጋል ይህም አገር ወገን ከረሃብ ከችግር ነፃ እንዲወጣ ያደርጋል በነብዩ ኢዩኤል እንደተገለጸው በፆም የዕህል የመጠጥ በረከት ይገኛል ። ኢዩ.2፥12-14

5. የነፋስ በረከትን እናገኛለን
ፆም በመንፈስ የደከመች የዛለች ነፍስን ያበረታል የነፍስን ቁስል ይፈውሳል ስጋዊ ኃይልን ያደክማል የሥጋን ፈቃድ ለነፍስ ያስገዛል መዝ.108፥24 ፤ ገላ.5፥24 የዓለምን ሃሳብ ያስወግዳል ከእግዚአብሔር ያስታርቃል ማቴ. 17፥21 ሚስጥር ይገልጣል ዘስ.34፥27-28 ፤ ዳን. 10፥1-3 "በአምላካችን ፊት እራሳችንን እናዋርድ ዘንድ ከርሱም የቀናውን መንገድ ለእኛና ለልጆቻችን ለንብረታችንም ሁሉ እንለምን ዘንድ ...... ፆምን አውጃለሁ " መጽሐፈ ዕዝራ.8፥21 ከመዋዕለ ፆሙ ረድኤት በረከት ያሳትፈን !

ፆሙን የኃጢአት መደምሰሻ የዲያብሎስ ድል መንሻ የመንግሥተ ሰማያት መውረሻ ያድርግልን አሜንንንን !!!
ስለ ንቅሳት

🎤ክፍል አንድ

‹‹በጎውን ማን ያሳየናል የሚሉ ብዙ ናቸው›› (መዝ. 4፥6)፡፡

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን
‹‹ስለ ሞተውም ሥጋችሁን አትንጩ፥ ገላችሁንም አትንቀሱት እኔ እግዚአብሔር ነኝ›› (ዘሌ 19÷28)፡፡
ንቅሳት በሰው ቆዳ ላይ የሚደረግ ቋሚ ሥዕል፣ ጽሑፍ ነው፡፡ ይህም የሚደረገው ከሰው ቆዳ ሥር በመርፌ ቀለም በመርጨት (በማስገባት) ነው፡፡ ቀለምን ከደም ጋር ማዋሃድ ምን ዓይነት ኪዳን (ስምምነት) መግባት ይሆን? ከደም ጋር ተያይዘው የሚሠሩ ሥራዎች ሁሉ አደገኛ ናቸው፡፡ ምክንያቱም በደም ውስጥ ሕይወት አለና (ዘሌ. 17÷11)፡፡ በሰይጣናዊ የአምልኮ ሥርዓትም ውስጥ ደም ስውር ኃይል እንዲለቀቅ ማድረጊያ ነው ተብሎ በከፍተኛ ሁኔታ ይታመናል፣ ይተገበራልም፡፡ (Dictionary of witches and witchraft) በጨለማው ዓለም አሠራር ውስጥ ደም ከጥልቁ የጨለማው ኃይል ጋር ግንኙነት የመፈጠሪያ ትልቁ (በላጩ) መንገድ ነው፡፡ የበዓል ነቢያት አምላካቸው አልሰማ፣ መልስ አልሰጥ ያለ በመሰላቸው ጊዜ ምን አደረጉ? ‹‹በታላቅም ቃል ይጮኹ፥ እንደ ልማዳቸውም ደማቸው እስኪፈስስ ድረስ ገላቸውን በካራና በቀጭኔ ይብዋጭሩ ነበር›› (1ነገ. 18÷28)፡፡
ንቅሳትን፣ መነቀስ ላለፉት ሺህ ዓመታት የተለመደ ቢሆንም በአሜሪካ ተቀባይነትን እያገኘ የመጣው ከ1980ዎቹ አጋማሽ ጀምሮ ነው፡፡ እንግዲህ ከአሜሪካ ተነሥቶ ነው አሁን ዓለምን ሁሉ እያዳረሰ ያለው፡፡ ብዙዎች ንቅሳት ምንም እንዳይደለ ለመከራከር ቢፈልጉም ሰይጣናዊ ምልክት ለመሆኑ ግን ብዙ ማስረጃ ማቅረብ ይቻላል፡፡
1. በንቅሳት ላይ የተሰማሩ ምን ዓይነት ሰዎች ናቸው? የንቅሳት ሥራዎች እየተመሩ ያሉት እግዚአብሔርን በሚፈሩ፣ መልካም ሰብዕና ባላቸው ሰዎች አይደለም፡፡ እንዲያውም ሰዎቹ ለሚመለከታቸው አስደንጋጭ አስፈሪ ማንነት የሚነበብባቸው ናቸው፡፡ ፀጉራቸውን ሙልጭ አድርገው ተላጭተው፣ መላ ሰውነታቸውን በንቅሳት ተዥጎርጉረው፣ በጆሯቸው ላይ ጉትቻ (ሎቲ) አንጠልጥለው ይታያሉ፡፡ ‹‹አመንዝሮች ሆይ፥ ዓለምን መውደድ ለእግዚአብሔር ጥል እንዲሆን አታውቁምን? እንግዲህ የዓለም ወዳጅ ሊሆን የሚፈቅድ ሁሉ የእግዚአብሔር ጠላት ሆኖአል›› (ያዕ. 4÷4፤ 2ቆሮ. 6÷14-17)፡፡ ወንዶችና ሴቶች በጉንጫቸው ላይ ጭምር ሎቲ አድርገው፣ በምላሳቸው ላይ ቀለበት አድርገው መታየታቸው ምሥጢሩ ምን ይሆን? መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ንቅሳት በመደገፍ የጻፈበትን ቦታ አናገኝም፤ እንዲያውም ይህ ልምምድ ከእግዚአብሔር ተለይቶ የጠፋው፣ የሚጠፋው የአሕዛብ ክፉና ከንቱ ሥራ ነው፡፡
ይቀጥላል ....
@ortodoxian
ክፍል 2
ስለ ንቅሳት

2. ንቅሳትን የሚነቀሱ ምን ዓይነት ሰዎች ናቸው? በዓለም ባሉ ሴቶች መካከል ከወገባቸው በታች በዳሌአቸው ላይ፣ ቁርጭምጪሚቶቻቸው ላይ፣ ከእንብርታቸው በታች፣ በአጠቃላይ የወንድን ዕይታ ለዝሙት ፈቃድ በሚማርክ ስፍራ ላይ ሲነቀሱ ይታያል፡፡ በዝሙት ሥራ ላይ የተሠማሩ፣ ግብረ ሰዶማውያን፣ ጠንቋዮች፣ በወንጀል ውስጥ ያሉ የውንብድና ቡድኖች፣ አስገድደው የሚደፍሩ ንቅሳትን መለያቸው ያደርጋሉ፡፡ በእውነተኛው የእግዚአብሔር ቃል ከሚመሩ ክርስቲያኖች መካከል የሚነቀስ አይገኝም፣ ቀድሞ በዓለም ሳሉና ወደ ጌታ ኢየሱስ ሳይመጡ ተነቅሰው የነበሩ እንኳን ቢሆኑ ወደ ወንጌል ከመምጣታቸው በፊት በንቅሳቱ የተነሳ ሰይጣን ምን ያህል ተቆጣጥሯቸው እንደነበር ሊመሰክሩልን ይችላሉ፡፡

3. በመጽሐፍ ቅዱስ የምናውቃቸው ክርስቲያኖች አንዳቸውም ንቅሳት አልነበራቸውም፡፡ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ እኛ ሲል ከተቀበለው መከራ፤ በእጆቹ፣ በእግሮቹ፣ በጎኑ ካለው የቁስል ምልክት በስተቀር ንቅሳት የለበትም፡፡ ሐዋርያትም ከእነርሱ በኋላ የመጡት ሐዋርያነ አበውም ንቅሳት አልነበራቸውም፡፡

4. ንቅሳትን የበለጠ ታዋቂና ተፈላጊ ያደረገው የሮክና ሮል ሙዚቃ አቀንቃኞች ስለሚጠቀሙበት ነው፡፡ ብዙ ጊዜ ሰዎች ካለማስተዋል የተነሣ በእነርሱ ዕይታ ‹‹ታላላቅ፣ ታዋቂ›› ያሏቸውን ሰዎች ሁኔታ መከተል፣ መገልበጥ
ይፈልጋሉ፡፡ እነዚህ ሰዎች ለምን እንደሚያደርጓቸው ሳያውቁ አድናቂ ነኝ በማለት እነርሱን መከተል አደጋ አለው፡፡ እነርሱ ዝናንና ገንዘብን ለማግኘት ከሰይጣን ጋር በገቡት ኪዳን መሠረት ራሳቸውን ለገሃነም ሰጥተው ሌላውን ለዲያቢሎስ የሚያጠምዱ ናቸው፡፡ ለምሳሌ የሰይጣን ቀንድ የሚባለውን የአውራና የትንሿ ጣትን ምልክት፣ አንድ ዓይንን የፒራሚድ ቅርጽ እንዲመስል በተስተካከለ እጅ ውስጥ አድርጎ ማሳየት፣ የተገለበጠ ወይም የተለየ ቅርጽ ያለው “መስቀል” አድርገው የሚታዩት ዓለም “ታላቅ” አድርጋ ያስቀመጠቻቸው ነገር ግን የመልካም ሥነ ምግባርና የሕይወት ምስክርነት የሌላቸው ሰዎች ናቸው፡፡ በመጠጥና አደንዛዥ ዕጽ የተጠመዱ፣ ደስታ የራቃቸውና ፍጻሜአቸው በአብዛኛው አሳዛኝ የሆነ፤ ራሳቸውን በአሰቃቂ ሁኔታ የማጥፋት ታሪክ ያላቸው ናቸው፡፡

ንቅሳት ማድረግ የሚገባን ቢሆን ኖሮ እግዚአብሔርን አስቀድሞ ከዚህ ጋር በፈጠረን ነበር፡፡ አንድ ሰው፡- “እግዚአብሔር ሰዎች ሲጋራ እንዲያጨሱ ቢፈቅድ ኖሮ ከራሳችን ላይ፣ በአናታችን በኩል አብሮ የጭስ መውጫን ይፈጥርልን ነበር” ብሏል፡፡ ሰው ፈልጎ ንቅሳትን ሲያደርግ ሰይጣን ሆይ ና እደርብኝ ብሎ በራስ ፈቃድ የመጋበዝ ያህል መሆኑ መታወቅ አለበት፡፡

ይቀጥላል......
@ortodoxian
ወላዲተ አምላክ ስለመሆኗ

ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ መሆኗን እናምናለን ። ይኸውም ወልደ አብ ኢየሱስ ክርስቶስን በግብረ መንፈስ ቅዱስ በሥጋ ወልዳዋለችና ። ለዚህ ማስረጃ የሚሆኑንን ጥቅሶች እንመልከት ምክንያቱም ድንግል ማርያምን እንደ ማህደር ተጠቀመባት እንጂ ወላዲተ አምላክ አትባልም ብለው የሚያምኑ ስላሉ ፦ "እነሆ ድንግል ትፀንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ትለዋለች " ትን ኢሳ 7:14 ይህ ቃል የሚወለደው ሕፃን አማኑኤል ተብሎ ይጠራል የወለደቺውም ድንግል ናት ካልን ከቃሉ ከፍ ብሎ እንዲህ ይለናል፦

"እርሱም አለ እናንተ የዳዊት ቤት ሆይ ስሙ በውኑ ሰውን ማድከማችሁ ቀላል ነውን አምላኬ ደግሞ የምታደክሙ ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣቹዋል " ኢሳ 7:13 ይህን ቃል ልናጤነው ይገባል የእስራኤል ቤት ብቻ ሳይሆን አለሙ ሁሉ ለመትረፍ በሰው ድካም አልሆነም ። አሁን ግን አምላክ ሊደክም የኛን መከራ ተሸክሞ ሊያድነን መጣ ። እርሱም #ምልክት ሰጠን #ምልክታችንም ድንግል ማርያም ነች አምላኬን የምታደክሙ ያለው ደግሞ ከድንግል የሚወለደው አምላክ መሆኑን ለማመልከት ነው

እናቱንም ወላዲተ አምላክ ያልናት ለዚህ ነው ። ሌላ ጥቅስ እንይ ፦ "ሕፃን ተወልዶልናልና ወንድ ልጅም ተሰጥቶናል አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል ስሙም ድንቅ መካር ኃያል አምላክ የዘላለም አባት የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል "ኢሳ 9:6 ሕፃን ተወልዶልናል እርሱ ደግሞ ኃያል አምላክ ነው ። ስለዚህ የወለደቺው ድንግል ማርያምን ወላዲተ አምላክ እንላታለን ። ይኸውም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ በ#ተዋህዶ ከብሮ ተወልዷልና ። ሌላም ጥቅስ እንጨምር ፦ "የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል " ሉቃ 1:43 አስተውሉ ስራው የመንፈስ ቅዱስ ነው ኤልሳቤጥ አክስት መሆኗን እንጂ ድንግል ማርያም የጌታ እናት ትሁን አትሁን የምታውቀው ነገር የለም

ነገር ግን መንፈስ ቅዱስን ተሞልታ ስለነበር የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆናል ስትል የጠየቀቺው ስለዚ ነው ። መንፈስ ቅዱስን የተሞላ ድንግልን ያውቃታል ፣ ያከብራታል ፣ ያመሰግናታል እርሱ ጌታ ነውና ወላዲተ እግዚዕ እርሷ ድንግል ማርያምን ወላዲተ አምላክ ያልናት ለዚህ ነው ። ሌላም እንይ ፦ "ቃል ሥጋ ሆነ ፀጋንና ክብርን ተመልቶ በኛ አደረ " ዮሐ 1:14 ያ ቃል ይለናል መጽሐፍ ቅዱስ በዮሐ 1:1 ላይ "ቃል እግዚአብሔር ነው " ስለዚህ የተወለደው የኛን ሥጋ የተዋሀደውን ክርስቶስ ኢየሱስን በሥጋ የወለደቺው ድንግል ማርያም ወላዲተ አምላክ ናት ። ሌላ ፦ "ነገር ግን የዘመኑ ፍፃሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከሕግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ " ገላ 4:4 ሴቲቱ ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም ነች

በአጭሩ ፦
👉 እርሱ አምላክ ስለሆነ እርሷም የአምላክ እናት ትባላለች
👉 እርሱ እግዚአብሔር ስለሆነ የእግዚአብሔር እናት ትባላለች
👉 እርሱ ጌታ ስለሆነ እርሷም የጌታ እናት ትባላለች
👉 እርሱ ብርሃን ስለሆነ እርሷም የብርሃን እናት /እመብርሃን/ ትባላለች። ጌታ አምላክ እናቱን ማደሪያው ስላደረጋት ከፈጣሪ በታች በሰማይና በምድር ከከበሩ ሁሉ የከበረች ንጽሕተ ንጹሐን ቅድስተ ቅዱሳን ናት ስለዚህም ትውልድ ሁሉ ብፅዕት እያሏት እያመሰገንዋት ይኖራሉ ስሟንም እየጠሩ በደስታ እየዘለሉ ይዘምራሉ ሉቃ 1:39-55 ልጇ አምላክ ነው እርሷ እናቱም ወላዲተ አምላክ ናት


💛 @ortodoxian 💛
❤️ @ortodoxian ❤️
​​​​ሰኔ 21 ለሚከበረው የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

#ሰኔ_20_እና_21

👉 ከእመቤታችን 33ቱ በዓላት አንዱ ነው፤ ህንጸተ ቤተክርስቲያን ይባላል።

የመጀመሪያዋ ቤተክርስቲያን የታነጸው በዛሬዋ ቀን ነው አናጺውም እራሱ ባለቤቱ ጌታችን መድሐኒታችን እየሱስ ክርስቶስ ነው፤ ቦታው ፊልጰስዩስ ነው፤ ቤተክርስቲያኗ የተሰየመችው ደግሞ በእመቤታችን ስም ነው።

ጴጥሮስ፤ ዮሐንስ በርናባስና ሌሎችም ሐዋርያት በፊልጰስዩስ ተሰብስበው ሳለ ጌታችን መድሐኒታችን እየሱስ ክርስቶስ በኪሩቤል ጀርባ ላይ ሆኖ እልፍ አእላፍ መልአክትን አስከትሎ ይወርዳል እመቤታችን በቀኙ ነበረች፤ 3 ድንጋዮችን አንስቶ ጎተታቸው እንደ ሰም ተለጠጡ እንደ ግድግዳም ሆኑ ዳግመኛም የብርሃን ምሰሶ ወረደ በሰማያዊቷ እየሩሳሌም አምሳያ አድረጎ አነጻት ሁለንተናዋም ተጠናቀቀ፤ ዳግመኛ በበነጋው ሰኔ 21 ቀን እመቤታችንን እና ቅዱሳን መልአክትን አስከትሎ ይወርዳል ቅዳሴ ቀድሶ ለሐዋርያቱ አቆረባቸው ፍጹም ደስታም ሆነ።

ከዚህ በኃላ ሐዋርያት ከጌታ እንዳዩት በዓለም ዞረው ቤተክርስቲያን አንጸዋል። ከዚያ በፊት የነበረው የነሶሎሞን ቤተ መቅደስ የአይሁድ ምኩራብ የአይሁድ ስርዓተ አምልኮ መፈጸሚያ እንጂ የአዲስ ኪዳን የቁርባንም ሆነ የጥምቀት ስርዓት መፈጸሚያ አልነበረም፤ ታዲያ ሐዋርያት የት ነበር ህዝቡን የሚያጠምቁት የሚያቆርቡት ካሉ በየሰው ቤት ነበር።

ዳግመኛ በዛሬዋ ቀን ታላቁ ነብይ ኤልሳዕ አረፈ። ይህ ነብይ በ 12 ጥማድ በሬ ሲያርስ ቴስቢያዊው ነብዩ ኤልያስ ተከተለኝ አለው ምንም ሳያቅማማ ሀብት ንብረቱን ትቶ ተከተለው፤ ኤልያስ በእሳት ሰረገላ ከማረጉ በፊት ምን እንዳደርግልህ ትፈልጋለህ ይለዋል ባንተ ላይ ያደረ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ እጥፍ ድርብ ሆኖ ይደርቢኝ ይለዋል፤ እንደ ቃሉ ሆነለት ተደረገለት፤ ኤልያስ አንድ ሙት ሲያስነሳ ኤልሳዕ ሁለት ሙት አስነስቷል፤ ኤልያስ አንድ ጊዜ ባህር ሲከፍል ኤልሳዕ ሁለት ጊዜ ባህር ከፍሏል።

የእምቤታችንን የኤልሳዕ ጋን ይላታል ኤልሳ የመረረውን ውኃ እንዳጣፈጠ እመቤታችንም ይህን መራራ ዓለም ጌታን በመውለዷ አጣፍጣዋለች፤ የዚህ ነብይ ድንቅ ታሪኩ 2ኛ ነገስት ላይ በስፋት ተጽፏል ሰኔ 20 ቀን እረፍቱ ነው ቤተክርስቲያን የዛሬውን ቀን እመቤታችንን እና ነብዩን አስባ ትውላለች።

ከበዓሉ ያሳትፈን የእመቤታችን ምልጃና ረዳትነት አይለየን!
@ortodoxian
@ortodoxian
++ በሰንበት መፍረስ ++

የኢያሪኮ ሰዎች የሠራዊት ጌታ የእግዚአብሔርን ኃይል በመናቃቸው ምንኛ ተጎዱ?! እርሱ ዓለምን የፈጠረ መሆኑን ስላላመኑ እንዳልተፈጠሩ የሆኑት የኢያሪኮ ሰዎች መጨረሻ እጅግ አሳዛኝ ነበር፡፡

ቅጥራቸው ከመፍረሱ በፊት እስራኤል የእግዚአብሔርን ታቦት ይዘው ለስድስት ቀናት ያህል በዝምታ ኢያሪኮን ዞሯት፡፡ ዓለምን በስድስት ቀናት የፈጠረውን ጌታ እንዲያስተውሉ ስድስት የዝምታ ቀናት ተሠጧቸው፡፡ በሰባተኛው ቀን ግን ጮኹ የኢያሪኮም ቅጥር ፈረሰ፡፡

ሰባተኛ ቀን የዕረፍት ቀን ነው፡፡ ለኢያሪኮ ግን የመፍረስ ቀን ሆነባት፡፡ ሰባተኛ ቀን ፈጣሪን ለሚያምኑ የተቀደሰ ቀን ነበር ፤ ለኢያሪኮ ግን የመረገም ቀን ሆነባት፡፡
እግዚአብሔር የፈጠረው ሁሉ መልካም እንደሆነ ባየበት ሰባተኛ ቀን ኢያሪኮ ግን ከፉ እንደሆነች ታየባት፡፡

እግዚአብሔር የሌለበት ሕይወት እንዲህ ነው፡፡ ወዳጄ እግዚአብሔር በሕይወትህ ውስጥ ከሌለ የሰንበት ቀን የነፍስህ ዕረፍት ቀን መሆኑ ይቀርና እንደ ኢያሪኮ የመፍረስ ቀን ይሆናል፡፡ በዚያ ቅዱስ ቀን ቅጥርህን በመጠጥ ፣ ብስካር ብዝሙት ስታፈርስ ትውልና ታድራለህ፡፡ ራስህን አንድደህ ትሞቃለህ ፤ እያራገብህ ትቃጠላለህ፡፡ ታቦት ይዘው ቢዞሩህም የኃጢአት ግንብን አጥረሃልና አትሰማም፡፡ በላይህ ላይ ቢቀደስብህም እንደ ኢያሪኮ ሰዎች ካህናቱን እያየህ ‘ዝም ብሎ መዞር ምንድር ነው?’ እያልክ ትስቃለህ፡፡ የካህናቱ የቅዳሴ ዜማ ለአንተ የሚያፈርስ ጩኸት ይሆንብሃል፡፡ የኢያሪኮ ሰው ከመሆን ፣ በሰንበት ፈራሽ ከመሆን ያድንህ!

ቅዳሴያችን መካከል ካህኑ ዕጣን እያጠኑ ዞረው ሲመለሱ የዚህች አጭር ጽሑፍ መነሻ ሃሳብ የሆነውን ይህንን ጸሎት ይጸልያሉ፦ አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ አስቀድመህ በባሪያህ በነዌ ልጅ በኢያሱ እጅ የኢያሪኮን ግንብ እንዳፈረስከው የእኔንና የሕዝብህን የኃጢአታችንን ግንብ አፍርሰው፡፡

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ ጸልዩ! ሌሎች እንዲያነቡትም የሚከተሉት አድራሻዎች Like እና Share ያድርጉ
@ortodoxian
@ortodoxian
#የወጣቶች_ሕይወት /ሕይወተ ወራዙት
(በቀሲስ ህብት የሺጥላ)

#ክፍል_3

#ግብረ_አውናን (Masterbation) #ምንድነው ?

እግዚአብሔር ለምህረትና ለመቅሰፍት ያዘጋጃቸው ልዩ ልዩ ግዳጆችን የሚፈፅሙ መላእክት እንዳሉት ሁሉ ሰይጣንም ሰውን በልዩ ልዩ መንገድ እንዲፈትኑ ድርሻ ሰጥቶ ያዘጋጃቸው አጋንንት አሉት ። ከእነርሱም ውስጥ አንዱ #ሰይጣነ_ዝሙት ነው ። ሰይጣነ ዝሙት የሰው ልጆችን የሚፈትንበት መንገድ የተለያየ ነው ። እንደውም አንዳንዶቹ ፈተናዎቹ የዝሙት አይመስሉም

#ፆር_የለመዱ (የሰይጣንን የፈተና ስልት በደንብ ለይተው ያወቁ ) አበው ቅዱሳን ግን ሽንገላ የሞላበትን የሰይጣንን ፈተና አሸንክላ ምን እንደሚመስል መጪ ትውልድ እንዲያውቀው በሕይወታቸው ያዪትንና መንፈስ ቅዱስ ያቀበላቸውን ፅፈው አስቀምጠዋል ። ለምሳሌ ሰይጣነ ዝሙት የሰውን ልጅ ወደ ዝሙት ተግባር ከሚስብባቸው መንገዶች አንዱና ዋነኛው ገሢሥ ነው ። #ገሢሥ ማለት ማሻሸት፣ መነካካት ፣ መዳበስ ማለት ነው ። ነብዩ ሕዝቅኤል "ግልሙትናቸውንም አፍስሰውባት ነበር " (ሕዝ 23:3) በማለት እንደተናገረው ለዘር የደረሱ ወንዶች ከሴቶች ጋር ሲላፋና ሲዳሩ ሩካቤ ሳይፈፅሙ ዘራቸው የሚፈስበት ጊዜ አለ ። ይህን ድርጊት እንደ ተድላ በመቁጠር ብዙ ወጣቶች ሆን ብለው ያደርጉታል

በቅዱስ መፅሐፍ "የድንግልናዋንም ጡቶች ዳብሰው ነበር " እንደተባለው ቦታ ሳይመርጡና ሰው ሳይለዩ የሴት ልጅን ገላ በመዳበስ "ግልሙትናን ማፍሰስ " ያሳፍራል ። ይህ መጥፎ ልማድ የተጠናወታቸው ሰዎች ግርግርና በሰው ብዛት የተጨናነቀ ስፍራ የሴቶችን ገላ እንደ ሐሳባቸው ለመነካካት ምቹ ሁኔታን ይፈጥርላቸዋል። ከነዚህ ውስጥ አንዳንዶቹ ሰው ስራቸውን አይቶ እንዳይነቅፋቸው የተለያዪ ዘዴዎችን ይፈጥራሉ። ለምሳሌ አንዳንዶቹ ምንም ሳያውቁና በእንቅልፍ ልባቸው ያደረጉት ለማስመሰል እንደ ተኛ ሰው እየተገላበጡና እያንኮራፋ በልዩ አጋጣሚ አጠገባቸው የተኛችውን ሴት ገላ ሲዳብሱ ያድራሉ

ይህ ድርጊት ያለ ሩካቤ የወንድ ዘር ከሚፈስባቸው መንገዶች መካከል አንዱ ነው ። ሌሎች ደግሞ በአድካሚ የጉዞ ወቅት ደጋፊ ፣ በሕመም ጊዜ ደግሞ አስታማሚ ... እየመሰሉ ከወሊድ ጋር ተዛምዶ ያላቸውን አካላት ለመደባበስ የሚሞክሩ ናቸው ። አንዳንዶች ደሞ እነርሱ ፈፅሞ ለመንካት እንዳላሰቡ ነገር ግን የተፈጠረው ሁኔታ እንዲጋፋ ወይም እንዲነካኩ እንዳደረጋቸው ለማስመሰል ይሞክራሉ ። በብዛት እንደዚ የሚያደርጉት ሕዝባዊ ስብሰባዎች በሚደረግባቸው እለታትና መጨናነቅ በሚኖርባቸው ስፍራዎች ነው ። ለምሳሌ እንደ ጥምቀት ፣ መስቀል ፣ ኤግዚብሽኖች ፣ የሞሉ ሚኒባሶች ሀይገሮች ባሶችና ባቡሮች መጥቀስ ይቻላል


ሌሎች ደግሞ ውጫዊ ይዘታቸው ሲታይ በዚህ ዓይነት ዘርን በማፍሰስ የመርካት ተግባር የማይጠረጠሩ አይነት ናቸው ። ለምሳሌ እድሜያቸው በጣም የገፋ ፣ በአስተሳሰብ የበሰሉ ፣ በአለባበስና በምጣኔ ሀብት የተከበሩ የሚመስሉ ወይም አስተማሪ የሆነ መንፈሳዊ አቋምና መልካም ስም የያዙ ናቸው ። እንደዚ ያሉት ሰዎች የሌሎችን ህዋሳት ለመነካካት የሚያደርጉት ጥረት "ይህን አስበው አይደለም " እየተባለ ብዙ ጊዜ በበጎ ይተረጎምላቸዋል

ሌላው ዝንባሌያቸው ደግሞ ታዳጊ ህፃናትን ማባለግ ነው ። በቅጡ ጡት ያላጎጠጎጡ ሕፃናትም እንኳን የእነዚህ ሰዎች የጥቃት ሰለባዎች ናቸው ። ህፃናቱ እነዚህ ሰዎች ምን እያደረጉ እንደሆነ አያስተውሉም ፣ አያውቁም ፣ ቢያውቁም አይቃወሟቸውም አይከሷቸውም ። ወይም በትንሽ ነገር ሊባበሉና ሊታለሉ ይችላሉ ።ሕፃናቱን ያጫወቱና ያሳሳቁ በመምሰል ሲታገሉና ሲላፋ በፍትወት እየተቃጠሉ ልብሳቸውን በዘር ጭቃ የሚለውሱትን ወንዶች ቁጥር ቤት ይቁጠረው


... ይቀጥላል

💚 @kokuha_haymanot 💚
💛 @kokuha_haymanot 💛
❤️ @kokuha_haymanot ❤️
#የወጣቶች_ሕይወት /ሕይወተ ወራዙት
(በቀሲስ ህብት የሺጥላ)

#ክፍል_3

#ግብረ_አውናን (Masterbation) #ምንድነው ?

እግዚአብሔር ለምህረትና ለመቅሰፍት ያዘጋጃቸው ልዩ ልዩ ግዳጆችን የሚፈፅሙ መላእክት እንዳሉት ሁሉ ሰይጣንም ሰውን በልዩ ልዩ መንገድ እንዲፈትኑ ድርሻ ሰጥቶ ያዘጋጃቸው አጋንንት አሉት ። ከእነርሱም ውስጥ አንዱ #ሰይጣነ_ዝሙት ነው ። ሰይጣነ ዝሙት የሰው ልጆችን የሚፈትንበት መንገድ የተለያየ ነው ። እንደውም አንዳንዶቹ ፈተናዎቹ የዝሙት አይመስሉም

#ፆር_የለመዱ (የሰይጣንን የፈተና ስልት በደንብ ለይተው ያወቁ ) አበው ቅዱሳን ግን ሽንገላ የሞላበትን የሰይጣንን ፈተና አሸንክላ ምን እንደሚመስል መጪ ትውልድ እንዲያውቀው በሕይወታቸው ያዪትንና መንፈስ ቅዱስ ያቀበላቸውን ፅፈው አስቀምጠዋል ። ለምሳሌ ሰይጣነ ዝሙት የሰውን ልጅ ወደ ዝሙት ተግባር ከሚስብባቸው መንገዶች አንዱና ዋነኛው ገሢሥ ነው ። #ገሢሥ ማለት ማሻሸት፣ መነካካት ፣ መዳበስ ማለት ነው ። ነብዩ ሕዝቅኤል "ግልሙትናቸውንም አፍስሰውባት ነበር " (ሕዝ 23:3) በማለት እንደተናገረው ለዘር የደረሱ ወንዶች ከሴቶች ጋር ሲላፋና ሲዳሩ ሩካቤ ሳይፈፅሙ ዘራቸው የሚፈስበት ጊዜ አለ ። ይህን ድርጊት እንደ ተድላ በመቁጠር ብዙ ወጣቶች ሆን ብለው ያደርጉታል

በቅዱስ መፅሐፍ "የድንግልናዋንም ጡቶች ዳብሰው ነበር " እንደተባለው ቦታ ሳይመርጡና ሰው ሳይለዩ የሴት ልጅን ገላ በመዳበስ "ግልሙትናን ማፍሰስ " ያሳፍራል ። ይህ መጥፎ ልማድ የተጠናወታቸው ሰዎች ግርግርና በሰው ብዛት የተጨናነቀ ስፍራ የሴቶችን ገላ እንደ ሐሳባቸው ለመነካካት ምቹ ሁኔታን ይፈጥርላቸዋል። ከነዚህ ውስጥ አንዳንዶቹ ሰው ስራቸውን አይቶ እንዳይነቅፋቸው የተለያዪ ዘዴዎችን ይፈጥራሉ። ለምሳሌ አንዳንዶቹ ምንም ሳያውቁና በእንቅልፍ ልባቸው ያደረጉት ለማስመሰል እንደ ተኛ ሰው እየተገላበጡና እያንኮራፋ በልዩ አጋጣሚ አጠገባቸው የተኛችውን ሴት ገላ ሲዳብሱ ያድራሉ

ይህ ድርጊት ያለ ሩካቤ የወንድ ዘር ከሚፈስባቸው መንገዶች መካከል አንዱ ነው ። ሌሎች ደግሞ በአድካሚ የጉዞ ወቅት ደጋፊ ፣ በሕመም ጊዜ ደግሞ አስታማሚ ... እየመሰሉ ከወሊድ ጋር ተዛምዶ ያላቸውን አካላት ለመደባበስ የሚሞክሩ ናቸው ። አንዳንዶች ደሞ እነርሱ ፈፅሞ ለመንካት እንዳላሰቡ ነገር ግን የተፈጠረው ሁኔታ እንዲጋፋ ወይም እንዲነካኩ እንዳደረጋቸው ለማስመሰል ይሞክራሉ ። በብዛት እንደዚ የሚያደርጉት ሕዝባዊ ስብሰባዎች በሚደረግባቸው እለታትና መጨናነቅ በሚኖርባቸው ስፍራዎች ነው ። ለምሳሌ እንደ ጥምቀት ፣ መስቀል ፣ ኤግዚብሽኖች ፣ የሞሉ ሚኒባሶች ሀይገሮች ባሶችና ባቡሮች መጥቀስ ይቻላል

ሌሎች ደግሞ ውጫዊ ይዘታቸው ሲታይ በዚህ ዓይነት ዘርን በማፍሰስ የመርካት ተግባር የማይጠረጠሩ አይነት ናቸው ። ለምሳሌ እድሜያቸው በጣም የገፋ ፣ በአስተሳሰብ የበሰሉ ፣ በአለባበስና በምጣኔ ሀብት የተከበሩ የሚመስሉ ወይም አስተማሪ የሆነ መንፈሳዊ አቋምና መልካም ስም የያዙ ናቸው ። እንደዚ ያሉት ሰዎች የሌሎችን ህዋሳት ለመነካካት የሚያደርጉት ጥረት "ይህን አስበው አይደለም " እየተባለ ብዙ ጊዜ በበጎ ይተረጎምላቸዋል

ሌላው ዝንባሌያቸው ደግሞ ታዳጊ ህፃናትን ማባለግ ነው ። በቅጡ ጡት ያላጎጠጎጡ ሕፃናትም እንኳን የእነዚህ ሰዎች የጥቃት ሰለባዎች ናቸው ። ህፃናቱ እነዚህ ሰዎች ምን እያደረጉ እንደሆነ አያስተውሉም ፣ አያውቁም ፣ ቢያውቁም አይቃወሟቸውም አይከሷቸውም ። ወይም በትንሽ ነገር ሊባበሉና ሊታለሉ ይችላሉ ።ሕፃናቱን ያጫወቱና ያሳሳቁ በመምሰል ሲታገሉና ሲላፋ በፍትወት እየተቃጠሉ ልብሳቸውን በዘር ጭቃ የሚለውሱትን ወንዶች ቁጥር ቤት ይቁጠረው

... ይቀጥላል

💛 @ortodoxian💛
❤️ @ortodoxian ❤️
ሐምሌ 19

ቅዱስ ቂርቆስና እናቱ ቅድስት ኢየሉጣ

ሐምሌ ዐሥራ ዘጠኝ በዚህች ቀን ሕፃኑ ቅዱስ ቂርቆስና እናቱ ኢየሉጣ በሰማዕትነት መከራ ተቀበሉ። ይህም ሕፃን ዕድሜው ሦስት ዓመት ሲሆነው ከሮሜ አገር ወደሌላ ሀገር እናቱ ይዛው ሸሸች በዚያም የሸሸችውን መኰንን አገኘችው

ሰዎችም ነገር ሠሩባት ወደርሱ አስቀረባትና ስለ አምልኮ ጠየቃት እርሷም መኰንን ሆይ ዕድሜው ሦስት ዓመት የሆነው ሕፃን አለ አማልክቶችህን ማምለክ መልካም እንደሆነ ወይም እንዳልሆነ ያስረዳን ዘንድ እርሱን ጠይቅ አለችው

ሕፃኑም ወደአለበት ጭፍራውን ልኮ ወደርሱ አስመጣው ሕፃኑንም ፊቱ ብሩህና ደስተኛ እንደሆነ አየውና አንተ ደስተኛ ሕፃን ሆይ እንዴት ነህ አለው። ሕፃኑም መልሶ አዎ ለእኔ ደስታ ተጠብቆልኛል ላንተ ግን ኀዘንና ልቅሶ ጥርስ ማፋጨትም ነው መጽሐፍ ለዝንጉዎች ተድላ ደስታ የላቸውም ብሏልና አለው እግዚአብሔር ኃይልና ንግግርን ሰጥቶታልና ብዙ ተናገረ በዚያም ያሉትን እስከ አስደነገጣቸው ድረስ ንጉሡን መኳንንቱንና ጣዖታቱን ረገማቸው ከብርታቱም የተነሣ አደነቁ

መኰንኑም በአፈረ ጊዜ በየአይነቱ በሆነ ሥቃይ ታላላቆች የማይችሉትን ታላቅና አስጨናቂ የሆነ ሥቃይን አሠቃየው እናቱንም ከርሱ ጋር እንደ እርሱ አሠቃያት እግዚአብሔርም ያለምንም ጉዳት ያነሣቸው ነበር። ብዙዎች አሕዛብም ይህን አይተው አደነቁ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም አምነው በሰማዕትነት ሞቱ የሰማዕትነትንም አክሊል ተቀበሉ

በሕፃኑ ላይም የመንፈስ ቅዱስ ጸጋ አደረበት። ታላላቅ ድንቆችና ተአምራቶችንም አደረገ ብዙዎች በሽተኞችንም አዳናቸው

ከዚህም በኋላ መኰንኑ በታላቅ የናስ ጋን ውስጥ ውኃ ጨምረው በእሳት ያፈሉት ዘንድ አዘዘ የፍላቱም ድምጽ እንደ ክረምት ነጐድጓድ ሆነ ያን ጊዜም ፍርሀትና የሃይማኖት ጉድለት በእናቱ ላይ ደረሰባት ሕፃኑም ስለ እናቱ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ

ያን ጊዜ ጌታችን ልቧን ወደ ሰማይ አሳርጎ ለቅዱሳን ሰማዕታት የተዘጋጁ የብርሃን ማደሪያዎችን አየች ከዚህም በኋላ ጸናች እግዚአብሔርንም አመሰገነችው ልጅዋንም ልጄ ሆይ ከእንግዲህ አንተ አባቴ ነህ እኔም ልጅህ ነኝ አለችው

ያቺ ከኔ የተወለድክባትም ቀን የተባረከች ናት አለች ወደዚያ ወደ ጋኑ ውስጥ በገቡ ጊዜም የውኃው ፍልሐት እንደ ንጋት ጊዜ ውርጭ ቀዘቀዘ ከእግዚአብሔር የታዘዘ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ገብርኤል ከሰማይ ወርዶ የእሳቱን ኃይል አቀዝቅዞታልና

ከዚህም በኋላ መኰንኑ ሥጋቸው ተቆራርጦ እስከሚወድቅ ድረስ በመቃጥን ውስጥ አድርገው እንዲጐትቷቸው አዘዘ ከእግዚአብሔርም የታዘዘ መልአክ አዳናቸው መኰንኑም በታላቅ ሥቃይ ያሠቃያቸው ዘንድ አስቦ እስኪመክር ድረስ በወህኒ ቤት ዘጋባቸው

ያን ጊዜም ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሕፃኑ ቂርቆስ ወርዶ አጽናናው አረጋጋውም። ስሙን ለሚጠራና መታሰቢያውን ለሚያደርግ ቃል ኪዳን ሰጠው

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በቅዱስ ቂርቆስና በኢየሉጣ ጸሎት ይማረን በረከታቸውም ትድረሰን ለዘላለሙ አሜን

(ስንክሳር ዘወርኀ ሐምሌ)
ምንጭ:- ቤተቅዱስ ዮሃንስአፈወርቅ

💛 @ortodoxian💛
❤️ @ortodoxian❤️
ነገረ ክርስቶስ

ክፍል 1

በመጋቢ ሀዲስ ሮዳስ ታደሰ (ዶ/ር)

የእግዚአብሔር ልጅ ለምን ሰው ሆነ ?

"እግዚአብሔር ዓለምን ከፈጠረበት ጥበቡ ሰው ሆኖ ያዳነበት ጥበቡ ይበልጣል " እንዲሉ በነቢያት አድሮ እንደሚወርድ ከቅድስት ድንግል ማርያም እንደሚወለድ ትንቢት ያናገረው ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው የእግዚአብሔር ልጅ ሰው ሳይሆን ማዳን ሲቻል ለምን ሰው መሆንን ፈቀደ ? ያልንን እንደሆነ

1ኛ.ለአዳምና ለሄዋን ከልጅ ልጃቸው ተወልዶ እንደሚያድናቸው የገባላቸውን ቃል ኪዳን ለመፈፀም ።ይህንንም ሊቁ ቅዱስ ዮሀንስ አፈወርቅ እንዲህ ይገልጠዋል ( ክብሩ ተለይቶት የነበረ ስጋን ክቡር አምላክ ሊያደርገው ፣ የፀጋ ገዢነት አጥቶ የነበረ ስጋንም የባህርይ ገዢ ሊያደርገው ወደደ ፣ አዳም ከእኛ እንደ አንዱ ሆነ ያለውንም ሰው በመሆን ሊገልጠው ወደደ )

2ኛ.ተምኔተ መላእክትን ተምኔተ አበውን ለመፈፀም ። ቀድሞ ሥጋዌውን ለአበው እየተላኩ የሚነግሩ መላዕክት ነበሩ ፤ ከዚህም የተነሳ አምላካችን በጠባብ ደረት በአጭር ቁመት ተወስኖ ባየነው እያሉ ይመኙ ነበርና ። ቅዱስ ቄርሎስም ስለዚህ ነገር እንዲህ ይላል ( ሥጋን በመልበስ ሰው ባይሆን ኖሮ ፍጡራን ሊያዩት ባልቻሉ ሊያዩት ማይችሉትም ሰዎች ብቻ አይደሉም ፤ መልካቸው ልዩ ልዩ የሚሆን የሚያመሰግኑ መላዕክትም ጭምር እንጂ )

አበው ነብያት ሊያዩት ይመኙ እንደ ነበር ጌታ " የእናንተ ግን አይኖቻችሁ ስለሚያዩ ዦሮቻቹም ስለሚሰሙ ብፁዓን ናቸው ፤ እውነት እላችዋለው ብዙዎች ነብያትና ፃድቃን የምታዩትን ሊያዩ ተመኝተው አላዩም የምትሰሙትንም ሊሰሙ ተመኝተው አልሰሙም " ማቴ 13:16 በማለት አስተምሯል ። ለምሳሌም ከነብያት አንዱ ሙሴ ከእግዚአብሔር ጋር ካለው ጥልቅ ግንኙነት የተነሳ " እባክህ ክብርህን አሳየኝ " ብሎ አምላኩን ለማየት ልመናን አቀረበ እግዚአብሔርም " እኔ መልካምነቴን ሁሉ በፊትህ አሳልፋለው ፡ ሰው አይቶኝ አይድንምና ፊቴን ማየት አይቻልህም " ነገር ግን ጀርባዬን ታያለህ ብሎታል ዘፀ33:16-23

ይህም ዠርባ በስተሁዋላ እንደሚገኝ ሁሉ በሁዋላ ዘመን አካላዊ ቃል ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ ሰው ሆኖ በታቦር ተራራ ላይ እንደሚገለፅለት ሲያመለክተው ነው ።ቅዱስ ጎርጎርዮስም ተምኔተ አበውን ሊፈፅም ሰው እንደሆነ እንዲህ ሲል ተንትኖታል ።የሰውን ባህርይ እስኪዋሀድ ዘመዳቸውም ሆኖ ሰውን ሁሉ ወደርሱ እስኪያቀርብ ድረስ ሰው ፊትህን አይቶ ህያው መሆን አይቻለውም

አስቀድሞ ልዑል እግዚአብሔር በስነ ፍጥረት እና በቅዱሳት መፃህፍት ላይ ራሱን ቢገልጥም አህዛብ ይህንን ባለመረዳት የሚታይ ፣ የሚዳሰስ አምላክን በመሻት እንጨትን እየጠረቡ ማምለክ ዠምረው ነበርና ፡ ግዙፍስ አምላክ ከፈለጉ ብሎ ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ ፍፁም ሰው ሆኖ ምኞታቸውን ፈፅሟል

አናጢዎች የእንጨት ምስልን ጣዖትን ወድደዋልና ስለዚህ ርሱ በእውነት በሰው አምሳል ተገለጠ ፤ ምስልን ጣዖትን የሚሰሩ ሰዎች ሁሉ ያዩት ዘንድ የአምላክን መልኩን አይተው ይገዙ ዘንድ ይላል
... ይቀጥላል ...

💛 @ortodoxian 💛
❤️ @ortodoxian ❤️
ቡሄ ማለት ምን ማለት ነው ? ችቦ ለምን እና መቼ ይበራል? ሙልሙል ልምን ይታደላል? በቡሄ ወቅት ጭራፍ ለምን ይጮሃል ?

ቡሄ

ቡሄ ማለት ብራ፣ ብርሃን፣ ደማቅ ማለት ነው፡፡ ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት በዓል የሚዘከርበት እና ለበዓሉም ችቦ ስለሚበራ የብርሃን በዓል በማለት የቡሄ በዓል እንላለን፡፡ ወቅቱ የክረምት ፤ጨለማ አልፎ የብርሃን የሚወጣበት፤ ሰማይ ከጭጋጋማነት ወደ ብሩህነት የሚለወጥበት የመሸጋገሪያ ወቅት ነው፡፡ “ቡሄ ከዋለ የለም ክረምት፤ ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት” እንዲሉ፡፡ በሌላ በኩልም “ቡኮ/ሊጥ” ተቦክቶ ዳቦ የሚጋገርበት “#ሙልሙል” የሚታደልበት በዓል በመሆኑ ቡሄ ተብሏል

ጅራፍ

በደብረ ታቦር በዓል በትውፊታዊ መልኩ የሚታየው ምስጢር፤ በኢየሩሳሌም ስለሚሆነው የጌታችን ምስጢራዊ ሞቱ ነው፡፡ ጅራፍ መገመድ(መጥለፍ) እና ጅራፍ ማጮኽ ሁለት ዓይነት ምስጢር የያዘ ትውፊታዊ ተግባር ነው፡፡ የመጀመሪያው ግርፋቱንና ሞቱን እናስብበታለን፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ፤ድምፁን ስንሰማ የባሕርይ አባቱን የአብን ምስክርነት ቃል፤ እንደ ነጎድጓድ ድምፅ ያስታውሰናል፡፡
የጅራፍ ትውፊታዊነት /ውርስ/፣ መጽሐፋዊ ትምህርትና ምስጢር ጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍ ለማድረግ ጨዋታውን በተራራማ አካባቢ፣ ከመኖሪያ ቤት ርቆና፣ በሜዳ ማድረጉ ጠቃሚ ነው፡፡ ጅራፍን #በርችት መቀየር የሚያመጣውን የምስጢር ተፋልሶ ብቻ መመልከት ከማኅበራዊ ጎጂ ገጽታው በላይ እንድናስወግደው ያስገድደናል

ችቦ

ችቦ የጌታችንን ብርሃነ መለኮት መገለጥ የሚያመለክት ነው፡፡ በመሆኑም ችቦ ለኩሰን በዓሉን እናከብራለን፡፡ የዚህ ትውፊታዊ አመጣጥ በብርሃኑ ድምቀት የቀኑን መምሸት ያልተረዱ እረኞች በሜዳ ቀርተዋልና ወላጆች ከመንደር ችቦ ለኩሰው ልጆቻቸውን ፍለጋ ሔደዋልና ታሪኩን እያዘከርን በዓሉት እናከብራለን፡፡ የችቦው መንደድም ሌላ ትርጉም አለው፡፡ አንድ ምእመን ለሌላው ምእመን መካሪ አስተማሪ መሆኑን፣ መከራ እየተቀበለም አርአያ፣ ምሳሌ፣ ብርሃን መሆኑን ያሳያል፡፡ በሃይማኖትም አርአያ ምሳሌ ይሆንላቸዋል፡፡ ከዚህ ጋርም ተያይዘዞ ችቦ በ13 ምሽት ይበራል ፣ብርሃኑ የተገለጠው በዚችው ዕለት ነውና

ሙልሙል

በችቦ ብርሃን ልጆቻቸውን ፍለጋ የወጡ ወላጆች ዳቦ ጋግረው ይዘውላቸው ወጥተዋል፡፡ ስጦታው ቤተሰባዊነትን፣ ፍቅርንና መተሳሰብን መግለጫ ነው፡፡ ወደ ቤታችን “ ቡሄ ” እያሉ ለሚመጡ አዳጊዎችም፤ ዘምረው እንዳበቁ የሚሰጥ “ሙልሙል” ዳቦ አለ፡፡ ሕፃናቱም ሊዘምሩ ሲመጡ ዳቦ መስጠት ልማዳዊ ብቻ አይደለም

ሕፃናቱ የደቀመዛሙርት ምሳሌ ናቸው፡፡ መዝሙራቸው ደግሞ ሐዋርያት “የምሥራች” ይዘው የመምጣታቸው ምሳሌ ነው፡፡ ሐዋርያት በገቡበት አገር አስተምረው አጥምቀው የጸጋ ልጅነትን አሰጥተው በረከት አድለው እንደሚሔዱም፣ ልጆችም ዘምረው፣ አመስግነው፣ መርቀው “ውለዱ ክበዱ፣ ሀብት አግኙ፣ የመንግሥተ ሰማያት ወራሾች ያድርጋችሁ ….” ይላሉ

በአጠቃላይ በዓለ ደብረ ታቦር ከእነዚህ ምስክር ካላቸው ትምህርቶቹ፣ ምሥጢር ከሚራቀቅባቸው ትርጓሜያቱና ከትውልድ ትውልድ በቅብብል በተላለፈው ቅዱስ ትውፊት ጋር ሃይማኖታዊ ባሕል ሆኖ ሊቀጥል ይገባዋል፡፡ ይህን ማድረግ የሚቻለው ግን አዳጊዎች ሃይማኖታዊ ትውፊቱን ይዘው እንዲያድጉ ጥቆማ በመስጠት፣ ግጥም በመግጠምና

ምሥጢሩን በማብራራት የመጀመሪያዎቹ ባለድርሻዎች ወላጆች ናቸው፡፡ አንዳንድ ጊዜ የሚሰሙ ግጥሞች ስድብ፣ ፌዝና ሥላቅ የተቀላቀለባቸው ይሆናሉ፡፡ ሕፃናቱም ዝማሬውን ሲጀምሩ “ከሰጡን እንነሣ ከነሱን እናርዳ” ብለው ይጀምሩታል፡፡ ከሰጡን እንመርቃለን ካልሰጡን እንራገማለን በማለት፡፡ አሳሳቢው ነገር ደግሞ ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን ወደ ገንዘብ ማግኛነት የቀየሩ ሁኔታዎች መታየታቸው ነው

ዳቦ /ሙልሙል/ ትምህርቱንም፣ ምስጢሩንም፣ ትውፊቱንም በአግባቡ ልንጠቀምበት ይገባል ከዚም ጋር ተያይዞ ሰንበት ት/ት ቤታችን ለበርካታ ዓመታት ሲወረድ የመጣውን የዝማሬ ሥርዓት ለአጥብያው ምእምን በየቤቱ በመሄድ የብሄን ዝማሬ ከነሥርዓቱ በመዘመር አገልግሎት ይሰጣል ፤የደብር ታቦርን በዓል በተመለከትም የወረቀት ጽሑፎችን ይበትናል በዝማሬ መኃል ያድላል ፡፡
ቤተክርስቲያን የምሥጢር ግምጃ ቤት ናት፤ የምታከናውነውን ሁሉ ከበቂ መረጃ ጋር ነው ተግባራዊ የምታደርገው

@ortodoxian
@ortodoxian
@ortodoxian
❍ㅤ     ⎙ㅤ    ⌲ ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ ˢᵃᵛᵉ ˢʰᵃʳᵉ
​​​​
የእመቤታችን ትንሣኤና ዕርገት

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዚህ ምድር የኖረችው ስልሳ አራት ዓመት ነው፡፡ እነዚህ ዓመታት ሲተነተኑ ሦስት ዓመት በወላጆቿ ሐናና ኢያቄም ቤት፣ ዐሥራ ሁለት ዓመት በቤተ መቅደስ፣ ሠላሣ ሦስት ዓመት ከሦስት ወር ከልጇ ከወዳጇ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር አሥራ አምስት ዓመት ከሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ጋር ነው

ያረፈችውም ጥር 21 ቀን በ50 ዓ.ም ነው፡፡ ባረፈችበት ወቅት ቅዱሳን ሐዋርያት ክቡር ሥጋዋን ለማሳረፍ ወደ ጌቴ ሴማኒ ሲሔዱ አይሁድ "ቀድሞ ልጇ በሦስተኛው ቀን ሞትን ድል አድርጎ ተነሣ፤ በአርባኛውም ቀን ወደ ሰማይ ዐረገ፤ ተመልሶም ይህን ዓለምን ለማሳለፍ ይመጣል እያሉ በማስተማር ሕዝባችንን ወስደውብናል፡፡ አሁን ደግሞ ዝም ብለን ብንተዋት እርሷም እንደ ልጇ ተነሳች እያሉ በማስተማር ሊያውኩን አይደለምን? ኑ! ተሰብስበን በእሳት እናቃጥላት" ብለው ክፉ ምክር ተማከሩ

ከመካከላቸውም ብርቱ ሰው የሆነው #ታውፋንያ የተባለ ቅድስት ሥጋዋን ከሐዋርያት ነጥቆ ለማስቀረት ክቡር ሥጋዋ ያለበትን የአልጋ ሸንኮር ሲይዝ በመልአከ እግዚአብሔር እጁ ተቆርጣ ከአልጋው ላይ ተንጠልጥላ ቀረች፤ ከዚህ የጥፋቱ ሥራው ተምሮ እመቤታችንን በመለመኑ እመቤታችን የተቆረጠች እጁን መልሳለታለች

ከዚህ በኋላ መልአከ እግዚአብሔር የእመቤታችንን የተቀደሰ ሥጋዋን ጌታችን ይወደው የነበረ ተብሎ የተነገረለት ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስን ይዞ በገነት በዕፀ ሕይወት ሥር አስቀመጠው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስም የሆነውን ሁሉ ለወንድሞቹ ቅዱሳን ሐዋርያት ነገራቸው፡፡ እነሱም የእመቤታችን ሥጋ በክብር ለማሳረፍ ካላቸው ጉጉት የተነሣ ከነሐሴ 1 ቀን ጀምሮ ሱባኤ ገቡ

ከሁለተኛ ሱባኤ ቆይታቸው በኋላ በአሥራ አራተኛ ቀናቸው ጌታችን የእመቤታችንን ትኩስ ሥጋ ሰጣቸው፡፡ ሐዋርያትም በዝማሬና በታላቅ ምስጋና በጌቴ ሴማኔ ቀበሯት፡፡ ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዳዊት ‹‹አቤቱ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ አንተና የመቅደስህ ታቦት› › ተብሎ ትንቢት የተናገረውን ሲተረጉሙት ‹‹ፈጣሪያችን እግዚአብሔር ሆይ፥ ወደ መንግሥተ ሰማያት የምታሳርፈው የመቅደስህ ታቦት የሆነችውን ድንግል ማርያምን ይዘህ ተነሥ›› ብለው ያመሰጥሩታል፡፡ /መዝ. 131፥8/

የእመቤታችንን ቅድስት ሥጋዋን ሐዋርያት ሲቀብሯት በሀገረ ስብከቱ ሕንድ የነበረው ሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ከሀገረ ስብከቱ ሲመለስ እመቤታችን ስታርግ ያገኛታል ለምልክት እንዲሆነው ሰበኗን (የመግነዟን ጨርቅ) ተቀብሏት ይለያያሉ፡፡ ለወንድሞቹ ሐዋርያት ያየውን ይነግራቸዋል

ለበረከት የሰጠችውንም ሰበን ያካፍላቸዋል፤ ሐዋርያት ‹ ‹ዕርገቷን እንዴት እሱ ብቻ ተመልክቶ ለምን እኛ ይቀርብናል› › ብለው በዓመቱ ነሐሴ አንድ ቀን ሱባኤ ገቡ፡፡ ነሐሴ 16 ቀን የልባቸው መሻት ተፈጸመላቸው፡፡ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እመቤታችንን መንበር፣ ቅዱስ ጴጥሮስን ንፍቀ (ረዳት) ቄስ፣ ቀዳሚ ሰማዕት ቅዱስ እስጢፋኖስን ገባሬ ሰናይ (ዋና ዲያቆን) አድርጎ ቀድሶ ሁሉንም አቆረባቸው

በትኅትና የያዙት ሱባኤም የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያምን ዕርገቷን ለማየት አበቃቸው፡፡ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንም ይህን መሠረት አድርጋ ከነሐሴ 1-16 ጾመ ፍልሰታ በማለት ከሰባቱ አጽዋማት አንዱ አድርገን እንድንጠቀምበት ሥርዐት ሠራችልን

በነቢያና በሐዋርያት መሠረት ላይ የታነጽን ኦርቶዶክሳውያን የተዋሕዶ ልጆች በየዓመቱ ይህን ጾም በሱባኤ በማሳለፍ ከእመቤታችን ጸጋና በረከት ተሳታፊዎች እንሆናለን፤ ሆነናልም፡፡ የዓመት ሰዎች ይበለን

💛 @ortodoxian❤️
❤️ @ortodoxian❤️
ጥብቅ ማሳሰቢያ
****
ነሐሴ ፳፯ ቀን ፳፻ ፲ወ፬ ዓ.ም
"""""""""""""""""""""""""""""
አዲስ አበበ -ኢትዮጵያ
""""""""""""""""""""""

ሰምኑን የቤተክርስቲያናችን ባልሆኑ ማኅበራዊ መገናኛ ብዙሃን አማካኝነት የቤተክርስቲያናችንን አርማ በመጠቀምና የቤተክርስቲያናችን ማኅበራዊ መገናኛዎች በማስመሰል ልዩ ልዩ ዜናዎችን በመሥራት ሕዝበ ክርስቲያኑን ለማደናገር የሚሞክሩ ድረ ገጾች እየተሰራጩ መሆኑን ደርሰንበታል።

እነዚሁ ድረ ገጾች ላይም በተለይ የቤተክርስቲያናችን ጠቅላይ ሥራ አስኪያጅና የባህርዳር ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብርሃም የሰጡት መግለጫ በማስመሰል የሚያስተላልፏቸው ዘገባዎች ሐሰተኞች ከመሆናቸውም በላይ በብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ስም የተከፈቱ የቲዩተርም ሆነ የፌስ ቡክ አካውንት የሌለ መሆኑን እየገለጽን ብፁዕ ጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ማስተላለፍ የሚፈልጉት መልዕክት ካለ በቤተክርስቲያናችን መገናኛ ብዙሃንና በሕዝብ ግንኙነት ድረ ገጾች ብቻ የሚያስተላለፉ መሆኑን እየገለጽን ሕዝበ ክርስቲያኑ ከነዚህ ህጋዊ የቤተክርስቲያናችን መገናኛ ዘዴዎች ውጪ የሚተላለፉ መልእክቶች ሁሉ የሐሰት መረጃዎች መሆናቸውን በመረዳት ህዝበ ክርስቲያኑን ለማደናገር ከተከፈቱ ሐሰተኛ የማኅበራዊ ድረ ገጾች ራሱን በመጠበቅና ለክፉ ዓላማ ማሳኪያ ተብለው የተከፈቱ መገናኛ አውታሮችን እንዲጋለጡ እንዲያደርግ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መልዕክቷን ታስተላልፋለች።

መረጃው ለሁሉም እንዲዳረስ ሼር በማድረግ እንዲተባበሩን ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ቤተክርስቲያን ጥሪዋን ታቀርባለች።
የኢኦተቤክ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ
👉ቤተክርስቲያንን በሁለት መንገድ ማወቅህን አረጋግጥ።

👉 እንደ አሕዛብ ጠላቷ እንዳትሆን በትምህርት_ዕወቃት፤ እንደ ፈሪሳውያን እንዳትሆን በኑሮ_ዕወቃት።

👉ለሥርዓቷ ታማኝ ሁን፥ አንተ ወደ ሥርዓቷ እደግ እንጅ ሥርዓቷ ወደ አንተ ፈቃድ እንዲወርድልህ አትውደድ፤ ሰማያውይቷን ቤተክርሰቲያን ምድራዊት እንድትሆንልህ አትፍቀድ።

👉በቤተክርስቲያን መንፈሳዊ አንድነቶች ካልተሳተፍክ ከቤተክርስቲያን አንድነት እየተለየህ እንደሆነ እወቅ።

👉እነዚህም ኪዳን ማስደረስ፥ ማስቀደስና ንስሐ ገብቶ መቁረብ፥ በምህላ ጸሎቶቿ በአዋጅ አጽዋማቷ መተባበር ናቸው።

👉ከቤት ከሚጸለይ አሥር ጸሎት ይልቅ በቤተክርስታያን የሚደረግ አንድ ጸሎት እንደሚበልጥ አውቀህ  በየቀኑ ወደ እርስዋ ገሥግሥ። 

👉በሕይወትህ ሁሉ ቤተክርስቲያናዊ ሁን!

ርዕሰ_ሊቃውንት_አባ_ገብረ_ኪዳን
#መቁጠርያ_በቤተክርስቲያን  (Prayer Ropes)

በተለያዩ መናፍቃን ዘንድ እንደ ባዕድ ነገር ነው የሚታየው የሚገርመው ለዚህ ንግግራቸው ምክንያት እንኳ ማስቀመጥ አይችሉም። አባቶቻችን መቁጠርያን የሚጠቀሙት በፀሎት ጊዜያት ነው። አብዝተው ለመፀለይ ይጠቀሙበታል። መቁጠርያን ለፀሎት ስለተጠቀሙ መክሰስ አይገባም። ቅዱስ ጳውሎስ በ 1ኛ ተሰ 5፥18 ላይ "ሳታቋርጡ ፀልዩ በሁሉ አመስግኑ..." በማለት እንዳስተማረን አብዝቶ መጸለይ ያስፈልጋል። የጸሎት  ተቃዋሚም ጠላት ሰይጣን ነው፡፡ ጌታም "ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ፀልዩ" ማቴ 26:41 ብሏል፡፡ በተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ላይም ፀሎትን አብዝተን እንድናደርግ መፅሀፍ ቅዱስ ይመክራልና

#እኛ_ኦርቶዶክሳውያን_መቁጠርያን_የምንጠቀመው

#1ኛ በትኩረትና በተመስጦ ሆነን ለመፀለይ
#2ኛ ይዘነው በመጓዝ ፀሎትን መፀለይ እንድናስታውስ
#3ኛ እንዳንፀልይ ከሚያግዱን ክፉ መንፈሶች ለማሸነፍ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን አብዛኛውን ጊዜ የሚጠቀሙባቸው መቁጠርያዎች ባለ 41 መቁጠርያ (Beads) (በውስጡ 41 ድብልብሎችን) እና ባለ 64 መቁጠርያ (በውስጡ 64 ድብልብሎችን) ናቸው

41_የመሆኑ_ምስጢር_የጌታችንና_የመድሃኒታችን_የኢየሱስ_ክርስቶስን_41_ግርፋት_ቁስል_ለማሰብ_ሲሆን
#64_የመሆኑ_ምስጢር_ደግሞ_የእናታችን_የእመቤታችን_በምድር_ላይ_የኖረችበት_እድሜ_ለማሰብ_ነው

አንዳንድ ቀሳውስትና መነኮሳት 150,300 ወይም ከዛም በላይ ድብልብሎች በመቁጠርያ ውስጥ
ይጠቀማሉ። ባለ 41 መቁጠርያ ላይ በመደጋገም የሚፀለዩ ፀሎቶች አሉ።እነርሱም፦

👉 1ኛ ጌታ በመዋዕለ ስጋው እንድንፀልይ ያስተማረን ፀሎትን እና የቅዱስ ገብርኤል ሰላምታ።
ይህም፦ አባታችን ሆይ በሰማያት የምትኖር ስምህ ይቀደስ
መንግስትህ ትምጣ... እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ በመልዓኩ በቅዱስ ገብርኤል ሰላምታ ሰላም እልሻለሁ...(12 ጊዜ)
👉 2ኛ አቤቱ ማረን! (41 ጊዜ)
👉 3ኛ ስለ ድንግል ማርያም ብለህ             
          ማረን! (41 ጊዜ)
👉 4ኛ ኪርያላይሶን(41 ጊዜ)
👉 5ኛ ሳዶር፣አላዶር፣ዳናት ፣አዴራ፣ 
          ሮዳስ (41 ጊዜ)
👉 6ኛ. ኦ! አምላክ(41 ጊዜ)
👉 7ኛ .ኦ! ክርስቶስ (41 ጊዜ)
👉 8ኛ ስለ እናትህ ስለ ድንግል ማርያም
          ብለህ ከመአቱ አድነን፣ሰውረን
          ምህረትንም ላክልን (ማረን)41 ጊዜ)
👉 9ኛ አቤቱ አምላካችን መድሃኒታችን ሆይ ስማን! (41 ጊዜ)
👉 10. ኤሎሄ (አምላኬ) (41 ጊዜ)
👉 11. ወዮልኝ! ወዮልኝ!ወዮልኝ!አምላኬ ሆይ እየኝ (ተመልከተኝ)
👉 12.አቤቱ እንደ ምህረትህ
እንጂ እንጂ እንደ በደላችን አይሁን! (12 ጊዜ)
👉 13. አቤቱ በመንግስትህ አስበን! (12 ጊዜ)
👉 14. እመቤቴ ሆይ (7 ጊዜ) ከዚህ በላይ የተጠቀሱት 14ቱ በፀሎት ጊዜ በመቁጠርያው በመደጋገም የሚፀለዩ ናቸው። እኚህ የተለመዱ ስርዓት ወጥቶላቸው በመደጋገም የሚፀለዩ ፀሎቶች ሲሆኑ ከዚህ በላይም የራስን የግል መሻት(ጨምሮ) ጨምሮ መፀለይ ይቻላል።ባለ ስልሳ አራቱን ( 64) መቁጠርያ ስንጠቀም ደግሞ 41 ጊዜ ተደጋግመው የሚፀለዩትን 64 ጊዜ ማድረግ ሲሆን ሌሎቹ ደግሞ 12 እና 7 የነበሩት እንደዛው ሆነው ይቀራሉ። ወስብሐት ለእግዚአብሔር!
በወንድም ተክለማርያም

💛 @ortodoxian 💛
❤️ @ortodoxian ❤️
💛 @ortodoxian 💛
በቶሎ ይነበብ ልንነቃ ይገባል
ለማንበብ 15 ደቅቃ ብቻ ስጥ ህይወትን ይቀየራል አትሳሳት
share አድርገው
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ዓለም ወዴት እየሄደች ነው? 1. - መጽሐፍ ቅዱስን ማቃጠል በኡጋንዳ በይፋ ተረጋግጦአል
* በደቡብ አፍሪካ ውስጥ ፣ ወንድ ወይም ሴት በዝሙት ምክንያት ሌላውን የመክሰስ መብት የለውም
*በአሜሪካ እየታየ ያለው የወንድ ለወንድና የሴት ለሴት ጋብቻ
*ጀርመን ወንድም እህቱን ማግባት እንደሚችል ፣ አባት ልጁን:እናት ልጆአን የማግባት ፍቃድን መስጠቱ ፡፡
*የmiami ከተማበመንገድ ላይ ፣ በቤተ ክርስቲያን ፣ በገቢያ ፣ በእግር ኳስ ሜዳ ወዘተ ውስጥ ወሲባዊ ግንኙነት በማንኛውም መንገድ ማግኘት እንዲችሉ መፍቀዶአ
.*ካናዳ (ከእንስሳት ጋር የ sexታ ግንኙነትን መፍቀዶአ
* በስፔን ውስጥ-የወሲብ ፊልሞች በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እና በዩኒቨርሲቲዎች መፈቀዱ *- ለአካለ መጠን ያልደረሱ ዝሙት አዳሪዎች ፈቃድ ማሪ ሉክ በህግ መፈቀዱ *በመጨረሻም ዩኤስ አሜሪካ የሰይጣንን ቤተ ክርስቲያን ከፍታለች ፡፡ በይፋ።
የተከበራችሁ ወንድሞች እና እህቶች ፣ መጨረሻው ተቃርቧል ፣ ጌታ ኢየሱስ በቅርቡ ይመጣል! ማርታናታ!!!
ክርስትያኖች ትኩረታቸው እየተከፋፈሉ ሲሆን ዲያቢሎስ መለኮታዊውን ምህረት ለማስቆም ከፍተኛ ቁጥር ያላቸውን ነፍሳት ከእርሱ ጋር ሊወስድ ይፈልጋል ፡፡ ደቂቃ ካለዎት ... ይህንን መልእክት ያጋሩ ፡፡ ለምን በቤተክርስቲያን ውስጥ እንተኛለን ? ስለ እግዚአብሔር ማውራት ከባድ የሆነው ለምንድነው ሐሜት ለመናገር በጣም ቀላል የሆነው ለምንድነው? የእግዚአብሔርን መልእክት ችላ ማለት ለምን ቀላል ሆነ?
ይህንን መልእክት ለጓደኞችዎ ይልካሉ ወይም ችላ ይላሉ? እግዚያበሔር “በሰዎች ፊት ብትክዱኝ በአባቴ ፊት እክድዳችሁአለሁ” አለ ፡፡ እግዚያበሔር ከወደዱ ይህንን መልእክት ለምርጥ ጓደኞችዎ እና በቡድን በ 60 ሴኮንድ ውስጥ ያጋሩ ፡፡ እግዚአብሔር ይባርኮት. ኣሜን
የአለም መጨረሻ ተቃርቧል አትዘናጉ
አሁን ያለንበት 2013 ዓም + 5500 ዘመን=7513 ስለዚህ ከ 8ኛው ሽ ላይ ቀንሱት ።
8000 – 7513= 487 ዓም ይቀራል።
ነገር ግን ሰምታችሁ ከሆነ ዘንዶ 400 ዓመት ገዝቷል ይባላል እስኪ ጠይቁ።
እና የዘንዶው ሲቆጠር 487 – 400 =87 አመት ቀረው።ትንቢቱም እየተፈፀመ ነው። ሌላው ይህ በንዲህ እንዳለ ደሞ
666 አሁን እዚህ በደጃችን ነው፡፡ አጠንክረን እንፀልይ፡፡ የአውሬው
ቁጥር 6 6 6 የሚፈፀምበት የትንቢት ጊዜ አልቋል/ተፈፅሟል፡፡
የአሜሪካ የህግ መወሰኛ ምክር ቤት ባስተላለፈው የኦባማን የጤና
ሽፋን ረቂቅ በህግ እንዲካተት ተደርጓል፡፡ የህግ ተግባሩ በቅርቡ
ይጀምራል፡፡ ይህን የጤና ሽፋን ረቂቅ በእያንዳንዱ የአሜሪካ ዜጋ
የሰውነት ክፍል ላይ ግላዊ የሬዲዬ ፍሪኩዌንሲ ቺፕስ መልክ (RFID
CHIPS) እንዲተከል ታዟል፡፡ ይህ ቺፕስ በግንባር ወይም በክንድ ላይ
ይደረጋል፡፡ ይህ ደግሞ በመጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገረው በራዕይ 13 :
15 -18 የተቀመጠውን የአውሬው ምልክት ይፈፀም ዘንድ ነው፡፡ እና
አሁንም ስለ ፍፃሜው ትጠራጠራለህ? ታውቃለህ ለኦባማ የተለየ
መኪና እንደተሰራ አውሬው የሚባል? ተዘጋጅ ንጥቀት አሁን
ይጀምራል፡፡ ራዕይ 13ን ቀድመው ተጫውተውታል፡፡ ብዙዎች ግን
ይህን አልተገነዘቡትም፡፡ 1. ለምንድን ነው ይህ ችፕስ ከባንክ
አካውንት ጋር የተቆራኘው ወይም የተገናኘው? አስታውሱ መጽሐፍ
ቅዱስ እንደሚለው ካለ አውሬው ቁጥር 666 ልትገዙም ወይም
ልትሸጡም አትችሉም ስለሚል፡፡ እስኪ ገምቱ ይህ ቺፕስ ከገንዘብ
ዝርዝር መረጃ ጋር ለምን ተገናኘ? እንዲያውም በጣም ያሳዘነኝ
በቤተክርስቲያን ያሉ ብዙዎች ሰዎች ጌታ ሲመጣ ይህን ሁኔታ
ሊያልፉት አይችሉም፡፡ ደግሞም ብዙዎቹ መጨረሻው እንደቀረበ
አያውቁም፡፡ የቴክኖሎጂ በጣም መራቀቅ ምክንያት ነው ብላችሁ
መልስ እንዳትሰጡኝ፡፡ በማንኛውም የህይወት ጎዳናችሁ
ከእግዚአብሔር ጋር ካልተስማማ አሁኑኑ ንሰሀ ግቡና ተለወጡ፡፡
ካለበለዚያ መንግስተ ሰማያትን ካጣችሁት ገሀነምን አታጡትም፡፡
ስለዚህ አስቡበት፡፡ ገሀነም መልካም ስፍራ አይደለም በጣም
አስከፊው ክፍሉ እንደ መንግስተ ሰማያት ዘላለማዊነት እንዳለበት
እዚህም እንደዛው ነው፡፡ ጆሮ ያለው ይስማ መንፈስ ለአብያተ
ክርስቲያናት የሚለውን ይስማ፡፡ ጠቃሚ ያልሆነ ነገር ከምትልኩ ይህን
ለሌላው ብታስተላልፉ መልካም ነው፡፡ ለምታውቋቸው ቅርብ
ለሆኗችሁ ሰዎች ላኩላቸው፡፡ እስኪ የወንጌላዊ ስራ እንስራ፡፡
እባካችሁ ለምታውቋቸው ለእያንዳንዳቸው በየስማቸው ላኩላቸው፡፡
ለሞባይል እንደምንጠነቀቅ ያክል ለእግዚአብሔር ቃል ብንጠነቀቅ
ምን እንደሚሆን ልትገምቱ ትችላላችሁ፡፡ ከዚህ ደግሞ በጭራሽ
ልንላቀቅ ነፃ ልንሆን አንችል፡፡ ስለዚህ የቻልነውን ያክል እንትጋ
እንጋደል፡፡ 7% የሚሆኑቱ ናቸው መልዕክቱን የላኩት በድጋሚ 93%ቱ
ግን አልላኩም አላወቁም ስለዚህ ጠንክረን እንስራ፡፡ ሰይጣን
እንዲህ ይላል፡- " የሚገርመኝ ሰው እግዚአብሔርን እወዳለሁ እያለ
አይታዘዝም እኔን ይጠላኛል ግን ይታዘዘኛል፡፡" ይህን መልዕክት በኋላ
እንዳትልኩት አሁኑኑ ላኩት!!!

ቅዱስ ለ #15 ሰው እባካችሁ 🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

@ortodoxian
@ortodoxian
2024/06/10 10:43:35
Back to Top
HTML Embed Code: