Telegram Group Search
ስድስት ኪሎ ላይብረሪው አካባቢ ካለው መናፈሻ መሳይ ቦታ ላይ ቁጭ ብዬ ወጪ ወራጁን ቃኛለው። ድንገት ገሊላ መፅሀፍ ይዛ ወደኔ አቅጣጫ እየፈነደቀች ከሩጫ ትንሽ ዝቅ ባለ ዱቡዱብ በፈገግታ ታጅባ መጣች። "ካሊድዬ የፈለከውን ጥያቄ ጠይቀኝ ስሩ የተባልነውን ሁሉ ጥያቄ ከማኪ ጋር ሆነን ዶርም ውስጥ ሰርተናል አለችኝ" በመሮጥዋ በተፈጠረው ያተነፋፈስ ልዩነት ለመረጋጋት እየሞከረች።


እሺ ብዬ መፅሀፉን ተቀብዬ የተለያዩ ገፆች ላይ ያሉ ወደ አስር የሚጠጉ ጥያቄዎች ጠየኳት ሁለቴ ማሰብ ሳይጠበቅባት ነው ከአፌ መንትፋ መልሶቹን የምትነግረኝ። "እውነትም አልተቻልሽም!" አልኳት ደስታዋ ተጋብቶብኝ አብርያት ፈገግ እያልኩ ። ግን ከዚህ መፅሀፍ ውጪ ጥያቄ አለኝ አልኳት መልስ በሚፈልግ ድምፀት
"እእ አስተማሪው ከተናገረው ነው የምትጠይቀኝ ? "

"አይደለም ልቤ ከተናገረችው ነው"

በስሱ ፈገግ ብላ " ይሁና እስኪ ልጠየቀዋ " አለች ድምፅዋን ቀንሳ

የልቤን ገፆች በለሆሳስ ገልጬ አንድ ጥያቄ ሆና ሺህ መልስ የምታስከትል ጥያቄ አሻገርኩ ።

" የወሰድሽውን ልቤን መልሺልኝ " የማፍቀር ጉም በሸፈነው ድምፀት ።


የዚህን መፅሀፍ ጥያቄዎች ለመመለስ ኬኔዲ ላይብረሪ ሳነብ እንደነበርኩ አንተንም በህይወት ላይብሪሪ ካንተነትህ ባሻገር ልወቅህ መፈለግ ውስጥ ነው ያለው ማግኘት ፍቅር ከማየት ባሻገር ማጤን ይጠይቃል ገረፍታ አንብቢህ ልብህን ልመልስልህ ማለት የሞኝ ጥናት ነው ለመጠየቅ ብሎ ማጥናት እና ለማወቅ ብሎ ማጥናት መንገዱም ማብቂያውም ይለያያል እና..... ብላ እጄን ጎትታ ከተቀመጥኩበት አስነሳቺኝና ወደ ካፌው አቅጣጫ ጉዞ ጀመርን ......


( ካሊድ አቅሉ)
ሰው ለመሆን አፈቀርኩሽ
(ካሊድ አቅሉ)

በጠዋቱ ባጥቢያ ጉልበት
ባልተፈታ አፍላ አንደበት
ጭስ ባለው አፍ አበሰርኩሽ
ሰው ስለሆንሽ ሰው ለመሆን አፈቀርኩሽ !


ማከልን ለመጎናፀፍ ፣ መሆንን ስሬ ላስገባ
ሳቂን ወዳንቺ እረጨው ልጠፋ ስል
እንድረባ ፥

ለመቁጠር የህይወት ስንኞች
እንዲፈቅደኝ አቦጊዳ
ከጋራሽ ትንሽ ወርጄ መንፃትን
ከልብሽ ልቅዳ ፤

ስታርቂ ፈትል ጥበብ
ስትሸምኚ ሙሉ ኩታ
ያልኖርኩትን አለም ስጪኝ
ነገን ልየው በትዝታ ፤

መልስ ስሻ በራሴ አለም
መጠበቅ ነው የሚቀጨኝ
በድን ገላ ከሚሆን ጎርፍ
ነፍስ ያለው ጠብታ ይርጨኝ ፤

ልመለስ ከምድር ግርጌ
ማዕበልሽ ያድርገኝ ከፍ
ጋንን ከቆልፍ ሳይደረደር
መክፈት ያውቃል ያንቺ
መቆለፍ !

በጠዋቱ ባጥቢያ ጉልበት
ባልተፈታ አፍላ አንደበት
ጭስ ባለው አፍ አበሰርኩሽ
ሰው ስለሆንሽ ሰው ለመሆን አፈቀርኩሽ !
~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~
Forwarded from ካሊድ አቅሉ (Kalido 12)
ያንተውስ አጂቡ ነው!
ይርቃል ይረቃል
ነፍስ ለመቀጠል ምትመጣበት ሰዓት
እጅጉን ይደንቃል ፤
እንድንደገፍህ እንዳንወድቅብህ
አጥብቀህ ስትሻ
በረከት ሰጠህን ሐጥያቱን ማርከሻ ።
~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~ ~

ረመዳን 🤲
ስሙን እስኪ አስተውሉት ይነግረናል
ስለመዳን !!

(ካሊድ አቅሉ)
ያሻኝ ቦታ ሄጄ ያሻኝን ከመምረጥ
እኔን ሚያስደስተኝ
መንገድ ለመሻገር እናቴን መጨበጥ !

( ካሊድ አቅሉ)

ልጅ እያለው ነፍስ በቅጡ ሳላውቅ እናቴ ነበረች ትምህርት ቤት ምታደርሰኝም ምትመልሰኝም ፣ ጠዋት ከቤት ስንወጣ ነፃነት እንዲሰማኝ ስለምትሻ የተወሰነ መንገድ አስባልቱ አቅራቢያ እስክንደርስ ትለቀኝና ዋና መንገዱን ልንደርስ አንድ ቅያስ ሲቀረን "ያዘኝ አለሜ" ብላ እጇን ወደኔ አቅጣጫ ሰዳ አጥብቃ ትይዘኝና ወደ ዜብራው አቅጣጫ ሄደን ሁለት ሶስት ግዜ ግራ ቀኝ ከቃኘች ብሃላ ይዛኝ ታልፋለች ። ነፍስ ካወኩ ብሃላ ሳሰላስለው እጅጉን ይገርመኛል እናቴ እንዳሻገረችኝ አስባልት መንገድ እጄኑ ይዛ ብዙ የህይወት ፈተናዎችን አልፋለች ፣ ማሻገር ማለት ማሳለፍ ብቻ አይደለም ማድረስም እንጂ መንገዱን አሳልፋኝ አትመለስም ትምህርት ቤት ግቢ አስገብታኝ ነው ወደ ቤት ምታቀናው ። እንደዚህ የህይወት ቅጥልጥሎቼን እየሰፋች በዘመን ሂደት ድርብ ኩታ አልብሳኛለች ፣

አሁንም ጭንቅ ሲለኝ እና በኔ ጥበብ ብቻ ማላልፈው ችግር ሲጠናብኝ የእናቴን ልብ እጆች በልቦቼ እጆች ዳብሼ ፈልጋለው አጥብቀው ይዘው እንዲያሳልፉኝ ብዙ ሰዎች እኔ አሻግርሀለው እጅህን ስጠን ይላሉ ችግሩ ግን አጥብቀው አይዙኝም መሀል ላይ ልሩጥ ስል አጉል ቦታ ይለቁኛል እናት አጥብቃ መያዝዋ ልጄ መሀል መንገድ ለቆኝ ቢሮጥስ ሚል ፍርሃት ነው ፍርሃቱ ከምን መነጨ ተዝቆ ከማያልቅ ለልጅዋ ካላት ፍቅር ..
የረመዳን ጁመዓ (2)

ከቁርዓን አንድ ታሪክ . . . . .


" ኢማን አለን ማለት ሁሉም ነገር ይጨመርልናል ማለት አይደለም። እዚህ ጋር አንድ ምሳሌ ልጥቀስላቹ ያዕቆብ አለይሂ ሰላም ያዕቆብ የእውቀት ባለቤት የተባለ መንፈሳዊ አባት ነው የሚገርም ኢማን የተጎናፀፈ ሰው ነበር ፣ ግን የያዕቆብ ልጆች የሚበላ የሚጠጣ ቤት ውስጥ ጠፍቶ ተርበው ወደ ግብፅ ተሰደዋል ። ኢማን የልብ እርካታና ደስታ ነው ኢማን ከአላህ ጋር ያለን ውብ ግንኙነት ነው ። ዱዓም ስናረግ ዱንያንና አኬራን ሚዛን ያረገ መሆን አለበት። "

ኡስታዝ : ካሊድ ክብሮም
አንድ ታሪክ . . . . . . .

ሰይዲና ከድር እና ሰይዲና ሙሳ መርከብ ላይ ተሳፈሩ መርከቢትዋ ላይ ቁጭ እንዳሉ አንዲት እርግብ መጣች እርሷም መርከቡ ላይ ቁጭ አለች ከዛም በአፎችዋ ከትልቁ ባህር ላይ ውሃ መጎንጨት ጀመረች። ሰይዲና ከድር ይሄንን አጋጣሚ መጠቀም ፈለጉና "ከዚህ ከትልቁ ውርቅያኖስ ውስጥ እቺ እርግብ ምን ያህል ውሃ ይዛለች ?" በማለት ሙሳን ጠየቁ ሰይዲና ሙሳም መለሱ " ምን ትይዛለች የአፍዋን ያህል ብትይዝ ነው እንጂ " አሉ ሙሳ ከዛ ሰይዲና ከድር ተግባራዊ ትምህርት ሰጧቸው " አዎ አየህ ሙሳ የእኔም እውቀት ይሁን የአንተም እውቀት ከአላህ እውቀት ጋር ሲነፃፀር እቺህ ወፍ ከዚህ ትልቅ ውርቅያኖስ ከያዘችው ጋር የተለየ አይደለም !" ፤ አላህ እወቀቱ ሰፋ ነው እሩቅ አዋቂ ነው ወንዙ ባህሩ እኮ የጌታህን ቃል ለመፃፍ እንደ መድ ቢሆኑ የአላህ ቃል ቢፃፍ የጌታዬ ቃል ከማለቁ በፊት ወንዞቹ ያልቁ ነበር ፤ ተከታታይ ወንዞችን ብንጨምር ባህሮችን ብንጨምር ወንዞቹ ያልቃሉ የአላህ ቃል አያልቅም ! በማለት ከድር ለሙሳ በምሳሌ የተደገፈ ትምህርት ሰጧቸው ።

ምንጭ ፡ ኡስታዝ ያሲን ኑሩ ካቀረበው የከድር እና ሙሳ ታሪክ የተቀነጨበ ።
 فَصَبۡرٞ جَمِيلٞ
መልካም ትዕግስት

ሱረቱል: ዩሱፍ 18 ፥11
እፉዬ ገላ ነፍስ
( ካሊድ አቅሉ)


ጉራማይሌ ነፍስ ቀለም
ጅምር ምናብ የአለቀ አለም
እንጭጭ ሀሳብ ቃል ያከሳ
ሁሌ ሚፃፍ ሊነበብ ሲል የተረሳ !

ነግቶ ስነቃ አካሌ ከብዶ ፥ ነፍሴ ቀለለኝ
በዝሆን ስጋ ውደቅ ሲለኝ ፥ ላባ አሳከለኝ
ላባዋ ነፍሴ እየበረረች ፥ እፉዬ ገላ
ክምር አካሌ እሷን ፥ ለመያዝ ሲሮጥ ከሃላ
ስትነፍስ አየው ፥ ክብደቷ ቀሎ
ማን አማለላት ? እንዲህ የሚያስኬድ ቅዬ
አስጥሎ፤

መች ደረስኩባት ፍጥነቴ ኤሊ ሸክም
እርምጃ
አድጎ ያልደረሰ በንጭጭ የቀረ ሀሳቤ
ጥጃ !

እየበረረች እየበረረች
የጋራው ዛፍ ላይ ነፍሴ አረፈች
አል ወጣ ነገር አካሌ አልሰጠኝ
ይህም ለሮጥኩት ላብ አሰመጠኝ
ነፍሴ ከስታለች ብናኝ ነች ትንኝ
ልቧ የታወረ መልኳ ማይገኝ ፤


ለዚህ ሁሉ ያበቃኝ ጥንስስ ፥
ታምራቱን ማስተንተን የአምላክን ቃል
ሰው ሲረሳ
ባዶ ፌስታል ይመሰላል በትንሽ ንፋስ
የሚነሳ ።
የወንዝ ዳር ድንጋይ አምነው
የማይረግጡሽ
ለማለፍ ባትሆኚ ለጌጥነት አጩሽ !

( ካሊድ አቅሉ)
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
እረመዳንን በከይር ስራ እንሸኘው !

በምስሉ ላይ ምትመለከቱት መስኪድ አማራ ክልል ቻግኒ ላይ የሚሰራ መስኪድ ነው የአቅማቸውን አስኪደውታል አሁን የኛን ድጋፍ ይሻሉ ትንሽም ሳንል የአቅማችንን እንወርውር አላህ ረመዳን መዝጊያ ላይ ተጠቀሙ ብሎ ያመጣልን የመጨረሻ እድል ይሆን ይሆናል ።

ንግድ ባንክ አካውንት : 1000532676782

@Kalu30 = በዚህ ቴሌግራም አድረሻ የአስገባቹበትን screenshot ላኩልን እናም በቻናላችን በኩል የሰበሰብነውን ለማወቅ ይረዳል ኢድ ሙባረክ ።
Forwarded from ካሊድ አቅሉ (Kalido 12)
እርቃኑን የቀረ ህሊና
(ካሊድ አቅሉ)

ልክነትን በሀጥያት መዝገብ ሲያሰፍር አኑሮ ምርቃትን እንዳይደርስብኝ እያለ እየተደበቀ ለሚኖር ትውልድ " አታስብም እንዴ? " የሚለው ንዴት ያዘለ ጥያቄ ለእሱ የልዕልዕናው መገለጫ የማወቁ ልኬት አርጎት" አንበሳ BRAVO " ብሎ በእራሱ እጅ የራሱን ትከሻ ይዳብሳል ።

እርቃኑን የቀረ ህሊና አለማገናዘብ መብቱ ሳይሆን ግዴታው ነው ። "ምን ሆነናል?" ከባነንን ብሃላ ያነሳነው ጥያቄ ሊሆን ይችላል አውሪን የሚያስንቅ አውሬነትን እንዲያው በአንድ ምሽት የፈጠርነው ቅፅበት አይደለም ። ሰው ለመሆን በሀሳብ ልቆ ለመገኘት ሂደት እንዳለው ሁሉ ከሰው ጎራ ለመውጣት ከአውሪነት በብዙ ከፍ ለማለትም የሄድነው የጨለማ ቁልቁለት መንገድ አለ ሲነጋ ያለንበትን ቦታ ወገግ አርጎ ያሳየን ።

ጋሽ ብርሃኑ ድንቄ ' አልቦ ዘመድ' በተሰኘው ውብ ታሪካዊ ልቦወለዳቸው ላይ ከላይ ያነሳሁትን ሀሳብ አጠንካሪ ነገር ያጋሩናል ። " ኧረ ለመሆኑ ዛሬ በኢትዮጵያ የሚያሳፍር የሚባል ነገር ይገኝ ይሆን ? ሌብነት አያሳፍርም፣ ውሸት አያሳፍርም፣ ውሸት አያሳፍርም፣ ከዳተኝነት አያሳፍርም፣ በቀዝቃዛ ደም ሰውን መግደል አያሳፍርም፣ ... ሐፍረት የሚሰማው ሕዝብ እኮ ሕሊና ያለው ነው! ያ ሼክስፔር የተባለ የእንግሊዝ ተውኔት ጸሀፊ ሐምሌትን እንዲህ ሲል አናገረው ፦
O shame! where is thy blush?
ሐፍረት ሆይ ! ቅላትሽ ወዴት አለ ?
ይህ እንደጦር የተወረወረ ጥያቄ ለዛሬዎቹ ኢትዮጵያውን እየተደጋገመ መቅረብ አለበት። ምን ይመልሱ ይሆን?"
አንተ ቀደም ብለህ " ህሊና ያለው ህዝብ ብቻ ነው ሐፍረት የሚሰማው !" ያልከው ትክክለኛ አገላለጥ ነው ። ስሜት በሌለው ህዝብ ዘንድ O Shame ! Where thy blush ? ያለው አገላለጥ የጦር ስለት እንዴት ሊኖረው ይችላል ?

እኔም እንዲህ ብዬ አሳርጋለው ስንራመድ ያልጨነቀን መንገድ ያልሆነ ቦታ ሲያደርሰን መከፋት የለብንም። እርምጃ ስንጀምር ነበር ወዴት ነው ወዴት ነው ተባብለን መመለስ የነበረብን ።
-----------
@kalidakelu
የመሀል ገፅ
( ካሊድ አቅሉ)
' አንድን ነገር ለመርሳት ከመሞከር በላይ ማስታወስ የለም።'

አንድ ቀን በተዋወቅን ስድስት ወራችን ከእናትዋ ጋር ወደ ምትኖርበት ቤት መፅሀፎቼን ላስጎብኝህ ብላ ይዛኝ ሄደች። እናትየዋ ቤት አልነበሩም ከሳሎኑ አንድ ጥግ አስቀምጣኝ ጉድ ጉድ ልትል ወደ ውስጥ ገባች እንዲያጫውተኝ ቆሎ አቅርባልኝ ፤ ቤቱን በሆልሳስ ስቃኘው እድሜ የጠገበ ተለቬዥን፣ የድሮ ሀብታም ቤት መለያ የሆነ ጨርቅ ሶፋ፣ ከዲኮደሩ በታች ሲዲ ማጫወቻ ዴክ አለ ። ከሁሉም ከሁሉም እድሜ ጠገቡና ብዙ መፅሀፍ አጭቆ የያዘው መፅሀፍ መደርደርያ ማርኮኝ አይኔን ጥዬበት ባለሁበት ቅፅበት በሸክላ ማጫወቻ ከፍታው የሄደችው ሙዚቃ ቀልቤን ገዝቶት ምልስ አልኩኝ የጥላሁን ገሰሰ " አንዳንድ ነገሮች " የተሰኘው ሙዚቃ ነበር . . .

" አንዳንድ ቀን አለ የቀን አጋጣሚ
አስመስሎ ሚያሳይ ሁሉንም ተስማሚ "


እውነቱን ነው ጥሌ ማየውን ሁላ ቁስ አካል የሷን ነፍስ አስገብቼባቸው እያየዋቸው ቤቱ በሷ ገፅ አበራ ፣ ሻይና ቀለል ያለ ጣፍጭ ነገር ለሁለታችን ይዛ መጣችና ጠረፔዛው ላይ አስቀምጣው ሻይ መቅዳት ጀመረች።

እርጋት ማለት እሷ እሷ ማለት እርጋታ ሰው እንዴት ሻይ መቅዳት ያምርበታል ለካ ውበት ያለው ጥቃቅን ብለን የናቅናቸው ነገሮች ውስጥ ነው ።

ሻይ እየጠጣን ሙያዋን እያደነኩ ስናወራ ቆየንና በመሀል ብድግ ብላ ወደ መፅሀፎችዋ አቀናችና " ባለፎ ስፈልገው ስድስት ኪሎን አሰስኩ ያልከኝን የሰለሞን ደሬሳ 'ልጅነት' ይህውልህ እንዳትረሳው ያዘው። " አለችኝ " ኦ እውነትሽን ነው ብዬ ተቀበልኳት ከመፅሀፎች ጥግ ተንጠልጥላ የተቀመጠች ደብተር መሳይ ግዙፍ ጥራዝ አንስታ " ይሄ ደግሞ ባለፎ ስለ ልጅነት ዘመንሽ ስለ Highschool ግዜሽ ንገሪኝ ስትለኝ ቆይ ጠቅለል አርጌ ነግርሀለው አላልኩህም ነበር ዛሬ ይህው ከ diary ላይ አንዳንድ ክፍሎችን እየዘለልኩ ላንብብልህ ሰዓት ካለህ " አለችኝ እኔም " አረ አንብቢልኝ አልቸኩልም አልኳት ( ላንቺ ስል አይደለም ደቂቃ ዘመንስ ባረፍድስ) አልኩኝ በውስጤ.......


መሀል ገፅ ገፃ ታሪክዋን ጀመረችልኝ የአንዳንድ ሰው የመሀል ገፅ የሌላው መጀመርያ ነው ፣ በተመስጦ በልጅነት ጣትና በልጅነት ልብ የከተበችውን ፈገግ እያለች አንዳንዴም ደብዘዝ ብላ አነበበችልኝ ፤ ካነበበችልኝ ታሪክ በላይ የዘለለችውን ታሪክ ከፊትዋ አነበብኩ አንድን ነገር ለመርሳት ከመሞከር በላይ ማስታወስ የለም በደንብ ያልሻረችባቸው ህመሞች በደህና ነኝ ዳገት ስትወጣቸው ሲሰነጣጠቁ አየው ፤ ምንም አላልኳትም ከታሪክዋ በላይ የፊትዋን ገፆች እየገለጥኩ እኮሞኩማት ገባው ገፁ ሊያልቅ አራት ወይንም አምስት ገፅ ሲቀረው ይሄን ይመስላል ብላ ታሪክዋን ዘጋችው ፤ ማን ያውቃል የአንድዬን ስራ በቀሩት ገፆች የሁለታችንን ታሪክ መዝኪያ ብሎ ይከትበው ይሆናል ።
አንድ ቀን ቤት ውስጥ ከአያቴ ጓደኛ ጋር ቁጭ ብዬ ስለወጣትነት ዘመናቸው ስላሳለፉት መልካም እና አሳዛኝ አጋጣሚ ሲያወጉኝ ከተማና ከተሜነትን መሰረት አድርገው ያካፈሉኝን ድንቅ ንግግር ላጋራቹ።

በከተማ አሊም ( ምሁር) እና ጨረቃ አይከበርም። ከተማ ውስጥ ሁሉም እኔ እውቃለው ስለሚል እውቀት ያለው ሰው የሚገባውን ቦታ አያገኝም፣ ጨረቃም ጥቅምዋ አናውቃትም ከተማ በመብራት የተንቆጠቆጠ ስለሆነ አብዛኛው ሰው የጨረቃን ብርሃን አያጣጥማትም ።

@Kalidakelu
Forwarded from ካሊድ አቅሉ (Kalido 12)
" የተኙ መስሎ ህያጅን ማሳለፍ "

(ካሊድ አቅሉ )

በሩን ስትከፍተው ፣ ደግሞም በቀስታ
ከእንቅልፌ አለም፣ ላይ እንዳልባንን ፈርታ
ቀስ ብላ ከፍታ ፣ ሄደች እየሮጠች
የተኛ መስዬ ሳያት እንደነበት ምናለ
ባወቀች።
@kalidakelu
አንዳንድ ጉዳይ አለ ፤ አመጣጡን ከመንገር ይልቅ ውጤቱን ማሳመን የሚቀል . . .

( ካሊድ አቅሉ)
ተሳፈርን በአንድ አውቶቢስ
በህይወት መንገድ ጫፍ ለመድረስ
እንዳጋመስን ግማሽ መንገድ
ለመናፈስ ብለን መውረድ ፤

ስንመለስ .. .
" አጠገባቹ የቀረ ሲባል ?"
ጎኔን ቃኘው ባይንዋ በኩል
ልብዋ ሲሄድ አየው እኩል
አካል ይዛ ከጎኔ አለች
ነፍስ ካሉ ግን ጎላለች !

(ካሊድ አቅሉ)
የአምላክ ምርኩዝ
( ካሊድ አቅሉ)

' ያጣነው ነገር ሁሉ ለእኛ ሚገባ
አይደለም። '

ንጉሴና አለሙ ለበርካታ አመታት በጉርብትና የኖሩ መልካም ጎረቤቶች ናቸው ። ንጉሴ ከውጪ የኤሌክትሮኒክስ ገመዶችን እያመጣ ሚያከፋፍል ከአንድም ሁለት ቤት አይነታቸው የተለያዩ መኪናዎች ያሉት ዲታ ነው ፣ እድሜው ሀምሳዎቹን የተሻገረ ነገር ግን ፈጣሪ በትዳር እና ልጅ ያልባረከው ጎልማሳ ላጤ ነው ። አለሙ ባንፃሩ ጀርመን ኢንባሲ በአትክልተኝነት ሚሰራ አራት ያክል ለአቅመ አዳምና ሄዋን ያልደረሱ ታዳጊ ልጆች ያሉት ታታሪ የገንዘብ ደሃ ነው ፤ በጠዋት ተነስቶ ወደ ስራው ሚያቀናው በእግሩ ነው ፤ " የታክሲውን ገንዘብ ለልጆቼ ዳቦ ይዤበት አልገባም !" ይላል ሰዎች የእሱን በእግር መኳተን አይተው ሲጠይቁት ፥


ከስራ መምጫው ሰዓት ልጆቹ ውጪ እየተጫወቱ መድረሱን በጉጉት ይጠብቃሉ ገና የቤታቸውን ቅያስ እንደታጠፈ " አባዬ አባዬ" እያሉ እያበረሩ ሄደው ይጠመጠሙበታል ፤ ንጉሴ በዛ ሰዓት ከስራው ገብቶ በሩ ላይ ያሉ አትክልቶቹን ውሃ ሚያጠጣበት ሰአት ነው እናም ልጆቹ ወደ አባታቸው ሲከንፉ አፉን ከፍቶ ስራውን ትቶ ይመለከታቸዋል አንዳንድ ደስታዎች አሉ ምን ገንዘብ ቢከማች ሊገዛቸው የማይችል ። አባት ልጆቹን አቅፎ ፊቱን እያበራ ከቤቱ ቀደም ብሎ ያለው ንጉሴ ቤት ሲደርስ የእንደምን ዋልክ ሰላምታ በትልቁ ይለዋወጣሉ የገንዘብ ሀብታም እና የልጅ ሀብታም ፊትና ፊት ቆመው በፈገግታ የታጀበ ሰላምታ ተለዋውጠው ይለያያሉ ።


አምላክ እንዳንወድቅበት የሚያበጀው መደገፍያ አለ ገንዘብ ከነሳህ ሳይሰስት ጤንነትን ይቸረሀል ። ካሻው ደግሞ ቆጥረህ ማትጨርሰው ገንዘብ አሸክሞህ የአይን ማረፍያ አንድ ልጅ ይነሳሀል ፣ ያጣነው ነገር ሁሉ ለኛ ሚገባን አይደለም ። ፈረንጆቹ እንዳሉት ብርጭቆ ጎዶሎ ነው ከማለት ብርጭቆ ግማሽ ውሃ ይዟል ማለቱ ህይወትን እንድናጣጥም መንገድ ይከፍታል ።
ቅንድቦችዋን ለማየት አይኔን ብሰደም ኩልዋ ነው ጎልቶ ሚታየው ፣ ያን ቅንድብ ለምን ኩል ደረበችበት ? እንዳይታይ ምትፈልገውን ትናንት ትናንትን በመሰለ ዛሬ ለመሸፈን መጣር ካለመታየት ይልቅ መታየትን አያጎላም ?

( ካሊድ አቅሉ)
የደመቁ ገፆች . . . . .

ሶቅራጦስ ሲያስተምር ተማሪዎቹን በማወያየት ያምናል ? እያልከኝ ነው። አዎን እኔም በማወያየት አምናለሁ ። ትምህርት አሰጣጤ ግን ድብልቅ ነው ። የማያውቁትን አዲስ ነገር ዘርዝሮ ማስረዳት ፣ እንደገባቸው ለማየት ሆኔታዎቹን ማመዛዘን በሚፈለግበት ጊዜ ማወያየት ተገቢ ነው። ነገር ግን በጭራሽ የማያውቁትን ነገር በውይይት ድረሱበት ማለት አይቻልም ።


ለማሰብ ተግባርም ቲዎሪም በጣም ወሳኝ ነው ። አንድታስብ የምታየውን ነገር ያስፈልጋል። መነሻ የሚሆን። ያየከውን ለማያያዝ ደግሞ በማሰብ መጣር አለብህ። ሁለቱም ነው ፤ እንዲሁ ማሰብ ብቻ ከሆነ እውነታውን ከህልም ከቅዥት መለየት ያዳግታል። ግን አስቤው የመሰለኝ ልክ ነው ወይ ? ብሎ ከእውነታ ጋር ማመሳከር ይጠይቃል። ሁለቱን ማድረግ የማይችል አስተማሪ ፣ የበሰሉና ማሰብ የሚችሉ ተማሪዎች ሊያፈራ አይችልም ።
-----------------------------------

የምድራችን ጀግና በእውቁ ፕሮፌሰር ተወልደብርሃን ገ/እግዚአብሔር የሕይወት ታሪክ ላይ የተሰነደ የዘነበ ወላ መጽሐፍ ነው። አንብቡት ታተርፉበታላቹ !
2024/04/26 01:23:30
Back to Top
HTML Embed Code: