Telegram Group Search
#አንቃን_በጥበብህ 🙏
   መውደድ ስንችል ጠልተን ፣
    መሆን   ሳለም   መስለን ፣
አስታርቁ ስንባል ለማኳረፍ ቋምጠን፣
ከቦታችን ወርደን ሰው ከመሆን ጎለን ፣
ከሙገሳ ይልቅ ቀሎን መወቃቀስ ፣
በእልህ ተቃርኖ አብሮነት ስናፈርስ፣
በሳቃችን   ጀርባ   ቅናት   ተለጥፎ ፣
ባንደኛው መደሰት ሌላኛው አኩርፎ፣
ደርሰን ተከፋፍለን ፀንተን በልዩነት፣
ድንበር   እያበጀን  ርቀን  ከእምነት ፣
የውሼት እንደኖርን እንዲሁ እንዳንሞት
አንቃን በጥበብህ ሰው አርገን የእውነት
#ሼን
👇👇👇
@seanlph
                   👇
በትናንት ስህተት ፣ ዛሬህን አትውቀስ
አሁንህን ኑረው  ፣ በድሮ ተው ማልቀስ
ሲያደርጉ ስላየህ ፣ ካላደረኩ አትበል
ከሮጠው አትሩጥ ፣ቁምና ከዛስ በል
ከማይሆንህ ነገር  ፣  እራቅ  አሁኑኑ
ከረፈደ ዃላ ፣ አይጠቅምም ማዘኑ
                   *
ፍራ ላለመባል  ፣ አጉልም አሰልጥን
በመምሰል አታጊጥ ፣ አንተነትህን ሁን
ዛሬ የቱ ጋር ነኝ  ፣እንዴት ነው ነገየስ
እያልክ ጠይቀህ  ፣ስጠው ለራስህ መልስ
                     *
አንተው ለራስህ ቁም ፣ ሌላን  አትደገፍ
ለማይዘልቅ ፍቅር ፣ ከድሜህ ቀን አትዝረፍ
የሂዎት ጉዞህን ፣ አስበህ ተራመድ
የተወህን ተወው ፣ የወደደን ዉደድ
                    *
ሳቅና ደስታህን  ፣ ከሌላ አትጠብቅ
ያጣኸውን ትተህ ፣ ባለህ ነገር ቦርቅ
ጎበዝ ብርቱ እንደሆንክ፣ ለራስህ ንገረው
አልችልም የሚልን ፣ በፍፁም አታውራው 
                       ሼን
ልቧ ችሎበታል _ የናቀውን መናቅ
የተወውን መተው _ የራቀውን መራቅ
መውደዷ ያልታየው  _ ያነሰበት ፍቅሯ
ዛሬው ጥርግ ይበል _ አትለማመጥም
             ዋጋዋ ገብቷታል
ግድ ቆዩ ብላ    _ ክብሯን አትጥልም
#ሼን
👇👇👇
@seanlph
#እናቴ_ናት_ለኔ 😘🌹

ህልምና ምኞቴን ፣ ግቤን እንዳሳካ፣
ከጎኔ  ሳትርቅ  ፣  በድሎት  በሳካ ፣
አለሁኝ  እያለች ፣ ተስፋ ምትለግሰኝ ፣
መንገዴ ሲሳሳት ፣ መክራ ምትመልሰኝ፣
ቃላት ሳላወጣ ፣  የውስጤ ሚገባት ፣
ከድክመቴ ይልቅ ፣ ብርታቴ ሚታያት ፣
የኑሮን ጎደሎ፣  የመኖርን ሽንቁር ፣
አብራኝ ልትደፍን ፣ ያቅሟን የምትጥር፣
ከራሷ አስቀድማ  ስለኔ ምታስብ
እድሜዋን በሙሉ ፍቅር የምትመግብ
ስደማ ምትደማ፣  አብራኝ ምትቆስል ፣
       እናቴ ናት ለኔ  የኔነቴ ምስል
#ሼን
👇👇👇
@seanlph
........ 🚶‍♀
የጊዜና እድሜ  _ የሁለቱ  ትርጉም
ለሴትና ለወንድ _ ፍፁም አንድ አይደሉም 
               ይሄን አትዘንጋ 
ጊዜ ከወንድ ይልቅ _ ለሴቷ አለው ዋጋ

እናም እልሀለሁ .....

አብራህ ያለችን ሴት _ የእውነት ካልወደድካት
እቅድህ ካልሆነ _ ሚስትህ ልታደርጋት 
ውስጥህ እያወቀው _  እንደማታገባት
አለሁልሽ እያልክ _ ባዶ ተስፋ አትሙላት

ያለፈው ይበቃል .....

ቀኗ ላይ አትቁም _  አትጋርድ እድሜዋን
ውበቷን አታርግፍ   _ አትስረቅ አሁኗን 
ማስመሰሉ ይብቃህ _   ከሂወቷ ውጣ
         እሷም ቁርጧን ትወቅ 
ሳይረፍድባት ትኑር _ የራሷን ሰው መርጣ
#ሼን ✍️
@seanlph
እንባ ለሴት ብቻ  _ የተሰጠ  ያክል
ለሱ ነውር ሁኖ _ተደርጎበት ክልክል
ወንድ አይደለህ እንዴ _ እንዴት ታለቅሳለህ
ቆፍጠን በል እንጂ _ ምን እንዲህ አረገህ
          እየተባለ አድጎ
         ያን ልማድ አድርጎ 

ብሶቱን ሀዘኑን  _  ውጋቱን ሸሽጎ
           ብዙ ወንድ ይኖራል _
ከፍቶት እንዳልከፋው _ እንባውን ዋጥ አርጎ
#ሼን
አንዳንዴ ደህና ነን የምንለው  የእውነት ደህና ሁነን ሳይሆን አሞናል ብንልም ህመማችንን የሚረዳልን ስለሌለ ነው  🤔

ዝም የምንለውም የምናወራው ስለሌለን ፣ስላልተጎዳን ፣ ስላልቆሰልን፣ ስላልተገፋን አይደለም  ቁስላችንን ብናወጋውም በኛ ቦታ ቆሞ በኛ ልክ ተረድቶ የሚያደምጠን ሰው ስለሌለ ነው 🤔

.....  አንዳንዴ ተገለን ዳር የምንቆመው ብቸኛ  የምንሆነውም ሰው ስለጠፋ አይደለም ለእኛ ልክ የሚሆን ፡ እኛን በእኛነታችን አምኖ የሚቀበል የራስ ሰው የምንለው ስለሚቸግረን ነው 🤔
#ደግ_ምሽት 🙏
@seanlph
የማፍቀሬኔ መጠን  ልቤን ስለፈተሽክ
አንዴ ወዳኛለች _ የትም አቴድ  ብለክ
እንዳሻህ እየሆንክ _ በስሜቴ ስትስቅ
ዋጋዬን ዘንግተህ  _ ሴትነቴን ስትንቅ

ካቅሜ በላይ ሁኖ መቻሌ ተሟጦ
ልቤም እነገሽግሾት ባንተ ተስፍ  ቆርጦ

ያሳየሁህ እንደሁ ....


በወደድኩት መጠን መጥላት እንደምችል
መርሳትም እንደማውቅ የማሰቤን  ያህል

ሌላ ሴት መስዬህ ...

እንዳትወዛገብ _  እንዳይገባህ ግራ
እስከዛው ድረስ ግን _ ደስ እንዳለህ ኩራ
#ሼን ✍️
👇👇
@seanlph
👇👇👇👇👇
@heartypoems ላይ ያናግሩኝ
ምስቅልቅል አድርገው  ሰላም ሂወትህን
ትርጉም አሳጥተው የሂወት ግብህን
ልብህን ሰባብረው ውስጥህ አድምተው
በጊዜህ ቀልደው ተስፋህን ቀምተው
መልካም ሂወት እመኝልሀለሁ
ብለውህ ይሄዳሉ
"ከባድ ነው ስሜቱ"
መጣ ያልከው ቀርቶ ደግ ያልከው ሲከፋ
አምነህ ያስቀመጥከው ከቦታው ሲጠፍ
ይወደኛል ባልከው ደረትህን ነፍተህ
በድንገት ስትደማ ልብህን ተወግተህ
ምንም ብትሆን ብርቱ
ከባድ ነው ስሜቱ ...
ማውጋት እየፈለክ ሲቸግርህ ሰሚ
ከቀድሞው ሳትሽር ሲያምህ በድጋሚ
ዙሪያህን ተከበህ አጂቦህ እልፍ ሰው
ልክህን ስታጣ ሆድህን ሲብሰው
ምንም ብትሆን ብርቱ
ከባድ ነው ስሜቱ ...
ማልቀስ አየፈለክ እንባህ ግን ሲደርቅ
የደላው ሊመስል ጥርስህ ደግሞ ሲስቅ

እንዴት ነህ ስትባል ታሞ ሳለ ጎንህ
ውጋቱን ደብቆ ደህ ነኝ ሲል አፋህ
ምንም ብትሆን ብርቱ
ከባድ ነው ስሜቱ ....
#ሼን
በብቻ ጓዳችን _ በእንባ በመራስ
       .. ያለፍነውን ጊዚያት ..
ስለማያወራ አፍ  አውጥቶ ትራስ
ማንም አይገባውመም ....
ከቀኑ ሳቃችን  _ ፈገግታችን  ጀርባ
ዕልፍ ህመም እንዳለ _ ሆድን የሚያባባ
ትራሱ ግን ያውቃል ..
ባይተነፍስም  ቃል ...
#ሼን
#እባክህ_አንድዬ 🙏🇪🇹
ሁሉንም አድራጊው የበላዩ ዳኛ
ህመማችን ፀንቷል ላክልን መዳኛ
በክፋት ተነክረን ጨቅይተን በ በደል
እጅግ ቆሽሸናል ስራ ሁኗል መግደል
🙏 እባክህ አንድዬ 🙏
በማያልቅ እዝነትህ በምረትህ አፅዳን
'ሰው' ነት አላብሰን እውሬነቱ ይብቃን
#ሼን
በደሉን እያወኩ _  የዝቋላውን ግፍ 
ሙስሊም ስለሆንኩኝ _ ችላ ብዬ ባልፍ
ይህ ያሁኑ ሴራ _ ነገ ላይ ውሎ አድሮ
መድረሱ ማይቀር ነው _ ከኔ ከመስጊዴ ጓሮ

እናም ዝም አልልም _ አወግዛለሁ ግፉን
እስከመች ድረስ ነው _ ልጥሉ ምትገፉን
በዘር ማባላቱ  _ ብሏችሁ  አልበቃ
መጫወት ያዛችሁ _ በእምነት እንደቃቃ
😢
እኛን እሺ ናቁ _ አትቁጠሩ እንደሰው
በሟችም አፊዙ _  ደሙ በሚፈሰው 
እንዴት ጥቂት እንኳ _ ፈጣሪን አትፈሩም
ህሊናስ አለ አይደል _ እንዴትስ አትራሩም
😢

የማይፋቅ ስህተት  _ በደም  ስትፅፉ
እንዴት ሰው አጣችሁ_ የሚል ተው እረፉ

ዛሬ ቀን ቢስቅም _ አይቀርም ማኩረፍ
ወቅት አመቼን በሚል  _ ድንበር አትለፍ
ቆይቶ ሰንብቶ _ ጊዜ ሲገለበጥ
         የበደላችሁ መልስ
ቤታችሁ ይመጣል _  ካሁኑ በመብለጥ
#ፍትህ_በዝቋላ_በግፍ_ለሞቱት 🙏🙏

#ሼን
2024/04/23 15:09:57
Back to Top
HTML Embed Code: