Telegram Group Search
የትዝታ ወልዴ ግጥሞች
Photo
አልገባትም-ንበድምፅ አዘጋጅቻለሁ አፍንጫዬን ግን ትንሽ አፍኖኛል ቤተሰብ🙏🏽
Audio
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
በትዝታ ወልዴ✍🏽
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
@Tizitawolde_poems
@Tizitawolde_poems
Audio
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
እንዲህ አለቺኝ

በአካልና በሀሳብ ከማዉቃት አንቺ እርቀሻል

ደህና ነሽ?
።።።።።።።
።።።።።።።
።።።።።።።
ፈግታሽን ማን ሰረቀዉ?
እብደትሽን ማን ወሰደዉ?
በልክ አርጐ ማንነዉ የሰፋሽ?
ከስህተት መንገድ ያራቀሽ?

ጥንካሬሽ የሚያስፈራ
ቁም ነገርሽ ከመግዘፉ ሆነብኝ ትልቅ ተራራ————-

ፈገግ አልኩ በጨረፍታ
ፈገኩላት የብልጭታ

ደህና ነኝ።

መገፋት አድክሞ አድክሞ አደንድኖኛል ልበላት?
ሰዉ ነበር ብዬ እንዳልኖርኩ ብቸኝነቴን ልንገራት?

ደህና ነሽ የዉነት አለቺኝ
ደህና ነኝ ደግሜ አልኳት

ጥርሴን ገለጥ አድርጌ
የቅርብ እሩቅ ዘመዴን
ደህና ናት የሚያስብለኝን
ነጫጭ የጥርስ ድርድሬን
።።።።።።።።።።።።።።።።

ምን ሆንኩኝ ብዬ እላታለሁ————-

ልቤን ስብርብር አርገዉ አንክተው እንደበተኑት
ቅንጣት እምነት እንዳጣዉ ሳቄን እንደነጠቁት
እንደ አጫሽ ሰዉ ጉበት
ተስፋዬን እንዳከሰሉት

እንዲህ ብዬ ልንገራት?

ወይስ——————

ልክነት አንገሽግሾኛል
ጠንካራ መምሰል ደክሞኛል
ልቤን እንዴት ላሳይሽ
ሰዉ መቅረቡ ያስፈራኛል
የድሮ እኔ ናፍቆኛል
ቁጥብ መሆኔ ቀፎኛል።

ብላትስ?

ደግማ ደጋግማ እያየች ቅንድቧን እየሰቀለች
ከተናጥኩበት ሀሳብ መንጭቃ እያወረደች

በእርግጥ ደህና ነሽ አለች?

ይመስገን ደህና ነኝ 🙏🏽😢 አልኳት
ደህና ሁኚልኝ አለች
ደህና የሆንኩ መሰላት።

❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️

ትዝታ ወልዴ ✍🏽

❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️

@Tizitawolde_poems
@Tizitawolde_poems
@Tizitawolde_poems
@Tizitawolde_poems
ያገባ ባል ፈልጉልኝ…………… ግጥም
አንዳንዱ በመሀል ገብቶ ?ይሄስ ነዉር ይለኛል
ተምራ ብለዉ ያሙኛል
እኔ ምን ይጨንቀኛል?

ብቻ………………..

ያገባ ባል ፈልጉልኝ🤗

በነገር ሲጠበስ ኖሮ ትዕግስት የተሸለመ
የት ገባህ የት ወጣህ መሮት ከሶፋ የተሰየመ

ያገባ ባል ፈልጉልኝ😒

አማቱ በአሽሙር ቄንጧ መፈጠር ያስረገመችዉ
የአከራዪ ልጅ በግልምጫ የጨረሰችዉ።

ያገባ ባል ፈልጉልኝ😌

ጏረቤት ዉለድ እያሉት በምክር የጠነከረ
በኑሮ ብዙ የተማረ
ያለእድሜዉ የተሰበረ

ከኔ በአምስት የፙበልጥ
ባይኖረዉ በኔ የሚያጌጥ

በጭራሽ ግን ከምሽቱም ያልፈታ
የሚያከብረኝ አዳማጩን ይስጠኝ ጌታ።

በኔ ቢካስ
ይሁን ብሎ…………..


ላግባዉ
ላኑረዉ
ላቆየዉ ከቢሮዬ
ማማከር ነዉ ስራዬ😇

ትምጣ እሷም
ላግባት
ላቆያት በቢሮዬ
ማስማማት ነዉ አላማዬ😇

❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
በትዝታ ወልዴ እንደ✍🏽
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️

@Tizitawolde_poems
@Tizitawolde_poems
@Tizitawolde_poems
እኔ የምላችሁ🤔
ባለፈዉ ጊዜ ተስፋ አዲስ ካሉት የካንሰር ታማሚ ህፃናት ጋር አብራችሁኝ ለሄዳችሁም ላልሄዳችሁ ቤተሰቦች እነዛ ዉብ ንፁህ ልብ ያላቸዉ ህፃናት ቢናፍቁኝ ደህንነታቸዉን ለመጠየቅ ጓደኛዬ ጋር ብደዉል በደም ማጣት እየሞቱ መሆኑን ስሰማ ከልቤ አዘንኩ። አሁን እኔ ያን ማድረግ ባልችል እና እናንተን ለመጠየቅ ምን ባልበቃ ማድረግ የምችለዉ ይሄን ነዉና ጀባ አልኳችሁ።

ክበሩልኝ ትዝታ ነኝ
አልረሳችሁኝም አይደል😊 አለዉ ለማለት ያክል😁
ስሙኝማ ለገና ልብስ ወይም ጫማ ለጐዳና ልጆች ብላ እየተንቀሳቀሰች ነዉ እና ማገዝ የምትፈልጉ

@fifiyami

👆በዚ ፃፋላት።

ትዝታ ነኝ።
ወይኑ ጐምርቶ ባናይ
ምን በለሷ ባታፈራ
የዘራነዉ ጭንጫ ቢቀር
ህልማችን ቢወርድ መቃብር
ምድር ፍሬ ከልክላ
ብናጣም ጥጋት ከለላ

ተመስገን!
::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::


💕ትዝታ ወልዴ

@Tizitawolde_poems
@Tizitawolde_poems
Forwarded from የትዝታ ወልዴ ግጥሞች (TIZITA21)
መልካም ልደት

አንዳንዴ ህይወቴን ባንተ ጫማ መሀል ከትቼ ሳረገዉ
ወይ አይጠብ አይሰፋኝ
ወይ በቅቶ አያረካኝ

እሱም እዚያ ማዶ
የኔም ልብ ሰርዶ
ያንተም ቅዝም ወዲያ
እንደተላለፍን ላንገናኝ🙈 ኤ.......ዲ........ያ

እንዲሁ ግርም አለኝ
አጃ....ኢብ ነዉ አቦ
አምላክን የሚያህል ከግዝፈቱ ጠቦ

ባጭር ቁመትና በሚጢጢ ደረት
ከማህፀን ወጥቶ ሲወለድ በበረት

አጃ.....ኢብ

ባለስልጣን ሳለ እንደ ሎሌ ወርዶ
በዳይን ለማዳን ዳኛዉ አገርድዶ

አጃ.....ኢብ ነዉ አቦ..........

የምድርስ ድፍረቷ እንደምን ቻለችህ
ምን ቃል ብትነግራት ነዉ?.........
ጌታዋን አምላኳን በበረት ወስና ፀንታ ያቆየችህ

እንደምን ብትወደን
እንዴት ብታፈቅረን
እንዴት ብታከብረን
አረ እንደምን ብለህ ታናሽነት መረጥክ
አንድ የምትለዉን ልጅህንም ሰደድክ።

አጃ.....ኢብ ነዉ አቦ

የትህትናህ ድንቁ
ምስጢርህ መርቀቁ
አለምን ከመፍጠር ሰ'ዉን የማዳንህ እጅጉን መድነቁ

መልካም ልደት ላንተ
ከክብሩ ወርዶ ለተንከራተተ

መልካም ልደት ለኔ
ከበረት ወጥቼ ለከበርኩኝ እኔ

።።።።።።።።።
።።።።።።።።።
አጃኢብ🙈
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
በትዝታ ወልዴ እንደተፃፈ
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
@Tizitawolde_poems
@Tizitawolde_poems
@Tizitawolde_poems
@Tizitawolde_poems
እንኳን አደረሰን💕
ግጥም መፃፍ አቁማለች ብላችሁ ያልራቃችሁኝ ቤተሰቦቼ😊😁
ተመስገን ዛሬ ልደቴ እኮ ነዉ 💕
በአይኑ አተያይ ያየኛል
ገርበብ አርጐ ከጥቅሻ ይፈጥንና ይሸሸኛል
.

ጨረፍታ ነዉ ንግግሩ
ብልጭታ ነዉ የሳቅ ቅጥሩ
.

ለራሱ እንኳን አይሰማ
እንዴት አርጐ ጆሮን አልፎ ልቤ ሰማ?


::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::


💕ትዝታ ወልዴ

@Tizitawolde_poems
@Tizitawolde_poems
Audio
ስንት ጊዜ ይፈጃል ምን ያህል አመታት
ስንት ሰዉ ይበቃል ትዝታን ለመርሳት

ምን የሚሉት ጂኒ ካንተ ጋር አሰረኝ
የትኛዉ መለኮት በፍቅርህ ጠፈረኝ

በየትኛዉ ጥበብ በየትኛዉ ዘዴ
በየትኛዉ ብልሀት አወከዉ የሆዴን

እንጃ................
ጊዜም መልሱ ጠፋበት መሰለኝ
ካንተ ጋር ይነጉዳል ጥያቄ እያጫረኝ

ስንት ዘመን ቀረኝ
ስንት እድሜ ይተርፈኝ
መቼ ያሳርፈኝ

ትዝታህ ጠቢቡ
ትዝታህ ብልሁ

ትዝታህ ብልጥ ወዳጅ
እያሳሳቀ ነዉ አብሮ ሚያሳቅቀኝ
እያጫወተ ነዉ እድሜዬን የቀጨኝ

ወይ እሱ ይተወኝ ወይ አንተ ደግመህ ና
ትዝታህን ዉሰድ እኔን መልስና።
.........................
.........................

ትዝታ ወልዴ

@Tizitawolde_poems
@Tizitawolde_poems
@Tizitawolde_poems
Forwarded from የትዝታ ወልዴ ግጥሞች (Tizita21)
ኪራላይሶን ማረን አባ አባታችን
ለተወጋዉ ጎንህ
ለበትረ መስቀልህ
ለፈሰሰዉ ደምህ
ቀራንዮ ሞትህ
ጎለጎታ ቤትህ
ኪራላይሶን ማረን ለዛ ህማማትህ።
አባ አባታችን
በጥፊ ስመታህ እጆቼን ይዘሀኝ ልማርህ ብለሀል
ዉሀ አልሠጥም ብዬ በከርቤ ኮምጣጤ ጉንጭህን ሞልተሀል
ጠማኝ አባቴ ስል ይሄ አይጠቅምም ብለህ
የዘላለም ዉሀ ለኔ አዘጋጅተሀል።
ኪራላይሶን ማረን
አባ አባታችን..........
መፃጉ ሆኜ ሳለሁ መዳኔን ሽተሀል
አልጋህን ተሸከም ብለህ ምረሀኛል
ሰንበት አፈረሰ እያልኩ መክሰሴን
ጌታ አረሳሁትም ማራት ይህቺን ነፍሴን።
ጎንህን ወጋሁት በጦሩ ጎርጉሬ
አቤቱ ማዳንህ አይኖቼን አበራህ ትተህ መነወሬን።
የሀጥያቴ መብዛቱን አይተህ ሳትጠየፍ
ፈራሽ ሰዉነቴን አፈር ማንነቴን ተመልክተህ ሳታልፍ
እኔ የከንቱ ከንቱ ፊትህን ተጠይፊ
የማይፈርስ አካልህን ፍቅርህን ጠፍፌ
ማረዉ ብለህ ስትል ሰዉነቴ ቀፎት
ምራቅ ተፋዉብህ ለኔ መምጣትህን እኔነቴ ክዶት።
ኪራላይሶን ማረን
ስለናትህ ማረን................
ሸክማችሁን በኔ ጣሉት ብለህ ስትል
ችግሬን ጥዬብህ
እንቅልፍና እረፍትን ባንተ አገኘዉብህ
ችግሬ አንሶብኝ
መስቀል ማሸከሜን ጌታ አትይብኝ
ከኃላ እንድትፈጥን እየገፈተርኩ
ከፊት ቀስ እንድትል እየገፈተርኩ
መሬት ስትወድቅ እያንቀለቀልኩ
ስትነሳ ደግሞ እያወዛገብኩ
መቼ ይረሳኛል እንዳንከራተትኩህ።
ኪራላይሶን ማረን
አባ አባታችን...............
መዳፍህ ይታየኛል
ጭቃ አበጃጅቶ እኔን የሰራልኝ
ዳብሶ የፈወሰኝ
እኔ የእፉኝት ልጅ
አዴራ አላዶር ሳዳርና ዳናት በሚባል ችንካሮች
መዳፍህን በሳዉ አለምን በያዙ በነዛ ድንቅ እጆች።
እግርህን ቸነከርኩ ምድርና ሰማይ ሊችሉት ያልቻለ
አልፋና ኦሜጋ በመስቀል ላይ ዋለ።

ኪ..ራ..ላ..ይ..ሶ..ን ማረን


በትዝታ ወልዴ እንደተፃፈ


@Tizita_wolde
@Tizita_wolde
@Tizita_wolde
2024/05/25 22:04:52
Back to Top
HTML Embed Code: