“ፍቅራችሁ ያለ ግብዝነት ይሁን። ክፉውን ነገር ተጸየፉት፤ ከበጎ ነገር ጋር ተባበሩ፤”
  — ሮሜ 12፥9
📖 “በኃጢአት የተገኘ መዝገብ ጥቅም የለውም፤ ጽድቅ ግን ከሞት ያድናል።” 📖
  — ምሳሌ 10፥2

ክርስቲያኖች በዚች ምድር በተሰጠን ዘመን በቅጥርም በግልም በምንንቀሳቀስባቸው ሁኔታዎች ውስጥ አገልግሎታችን ከእግዚአብሔር ጋር በማይጣላ መልኩ መሆኑን እርግጠኛ መሆን አለብን።

በሀጢዓት የተገኘ መዝገብ ጥቅም የለውም ማለቱም ይህ ነው። ነጋዴዎች ከሆንን ለህዝብ የተበላሸን ነገር ቀባብተን ከሸጥን አገልግሎትን የጨረሰ እቃ አዲስ አስመስለን ከሸጥን በሀጢአት የምንሰበስበው ገንዘብ መልሶ ይበላናል።

በቅጥር ህይወት የምንንኖር ከሆነም አለቃችን አላየንም ብለን በግድየለሽነት ስራችንን በአግባቡ ማንሰራ ከሆነ ነገም አድገን ሰራተኛ ስንቀጥር እደራሳችን ያለ ቅጥር ነው ሚያጋጥመን ምክንያቱም የዘራነውን ነው የምናጭደውና።

ምንም አለቃችን መጥፎ ቢሆን እሱን የበደልን መስሎን እንክርዳድ ከምንዘራና የወደፊት ህይወታችንን ከምናበላሽ ለሱ "እሺ" ብንል ከእግዚአብሔር ሺ እንረከባለን ምክንያቱም ቃሉ ፅድቅ ግን ከሞት ያድናል ይላልና።
“አቤቱ፥ በልቤ ሁሉ አመሰግንሃለሁ፥ ተአምራትህንም ሁሉ እነግራለሁ።”
— መዝሙር 9፥1
2025/05/12 11:20:54
Back to Top
HTML Embed Code: