Telegram Group Search
.ለደስታዬ ያለምኳት ፡ የኔዋ አንድ ቀን ፣
ልክ እንዳ'ንድ ቀኖች
ቂያማ አጠብቅም የላትም ሌላ አቻ
ፍካት የሚወ'ርሳት ባንተ መውጣት ብቻ።

አልሃምዱሊላህ ይቺ ቀን ብሩክ ናት!

በሀሴት ታውጄ መንፈሴ እንዲረካ
ማንም ምንም ለኔ
አንተን ማየት ብቻ ይሰጣል በረካ።
አጀብ የዚህችስ ቀን!

ድንገት በቀትሩ
አጮልቃ ካየች ከእግዜር ተደብቃ፣
'እኔስ መች ተዋብኩኝ!?' ትላለች ጨረቃ።
ብርሃንም ቢሆን
የቱን ታክል በርቶ ስሙ እንደተሰጠው
አንተን ባየ ቁጥር አምርሮ አምላኩን እንደጠየቀው ነው።
እኔማ ድኩም ነኝ
ምኔንም ከምንህ ጋር ውድድር ይቻለኝ!?
ብቻ ይህቺ ቀን ትመስገን!

ለባይተዋር ልቤ
ለነፍሴ ራህመት ያቀርብኩት ዱዓ፣
እነሆ አጃኢብ!
ውብ አድርጎ ፈጥሮህ ሰቶኛል ጁምዓ። #FIYAM❤️ 🏠 @YETBEB_BET 🏠
." ከአንድ እርምጃ ቡኋላ እሾሁ ይታይሻል አይደል!? ታድያ ስለምን ለመራመድ ታኮበኩቢያለሽ?" ጠየቀኝ

" መሄድ ስላለብኝ። ከመጣሁበት የጭቃ እሾህ መንገድ ይሄ ኢምንት መስሎ ስለታየኝ ወይ ደሞ እኔንጃ! ግን'ኮ ምናልባት ይህ እሾህ ቢወጋኝ እግሬን ነው የሚያደማው ፤ በርግጥም መርቅዞ ሲታከክ ሰላም የሚሰጥ ቁስል ይሆነኛል። እመነኝ! አትስጋ ፤ እሄዳለሁ። ይልቅ የሆነ ጥያቄ ልጠይቅህ ? የልብን ቁስል በየት በኩል ገብተው ቢያኩት ይሆን እረፍት የሚሰጠው?" አይኑን እያየሁ ጠየኩት። ትንፋሹን እንኳን ለመልስ'ነት አላቀረበልኝም። በቀስታ አቀፈኝ። ከቃሉ በላይ እቅፉ መልስ ሆነኝ መሰለኝ እኔ ቀጠልኩ።

" ታውቃለህ እጄን ከእጁ መፈልቀቄ አጥብቆ እንዲይዘኝ ነበር! ግራውን መርጬ ስሄድ መንገዴን እንዲወደው ነበር! ስገፋው እኮ እንዲፈልገኝ አጥብቄ መፈለጌ ነበር ! ራስ ወዳድ ነኛ!? የምርም ዝም ሲለኝ ምንምነቴን እየነገረኝ ይመስለኝ ነበር፤ በርግጥም ነው። ነፍሴን ሳቀርብለት ከሌለኝ ላይ ሞልቼ ቢሆንም ነፍሱን የሰጠኝ ግን የተረፈለትን ነበር። ምናልባት ለምን ብዬ አለመጠየቄ ስህተት ቢሆንም ማስመሰሉን እንዳይደግም ማድረጌ ግን ልክ ነበርኩ። በመሆን መጉደል ግን ምንኛ ህመም ነው!? " እቅፉ ሰላም ሰቶኛል፤ አልፌው እንዳልሄድ ጨርሶውኑ አድክሞኛል።

"የልብ ቁስል እንዴት ነበር የሚታከከው!?" ስለመንገዴ እያመነታሁ ጠየኩት
"እንደዚ" ደግሞ አቀፈኝ። ልቤ ውስጥ የማላውቀው እፎይታ ተሰማኝ
"እወድሃለሁ!" አልኩት
"አፈቅርሻለሁ!"

ዳግመኛ እጆቼን ያዛቸው፤ ሊለቀኝ አይፈልግም። አይኖቼ ውስጥ ምስሉን ፍለጋ ተተከለ ፤ ራሱን የማያውቀው ያህል ሊያጣው አይፈልግም። የተረፈ ነፍሴን ሳይሆን በእቅፉ አድሶ ሰላም የሰጣትን ነፍስ ያለማንም ከልካይ አስረኩብኩት።

ወትሮውኑም ያላየነው አንድ ማንም ነበር....!

◊ ፊያሜታ
.እና እንደፈራሁት...
ከመገኘት ቀድሞ
ንጥል የበዛ እንደው ፣
መስከኑ ተሽሮ ድፍርስ ጣ'ም ከሆነው ፣
ነገ ትርጉም ያጣል፤
የሰጡትን ንቆ የራሱን ይፈጥራል።
ድፍርሱም ሲመረው ትላንትን ይደግማል።

ልክ እንደሚያስፈራው...
የሰዓት እላፊ ነጎድጓዳ ዝናብ
የኔ እና ያንተም ነገር
ልቡ ርዷል መሰል ማስገምገም ጀምሯል።
ውዴ...!
ያስፈራል ሂደቱ
አኳኋን ሁነቱ
ሰቅዞ የያዘን የነፍስ አለም ፍቅር
መናፈቁ ቀርቶ አይሏል ቁጭቱ።
ያስፈራል...!
ያስፈራል ሂደቱ
ምን ብዬ ልጀግን ሁሉም ላንተ አብረው
ሲያገሉኝ ቀናቱ!?
ብቻ ይሄም ያስፈራል...
የህይወት ሁነቱ!!

ፊያሜታ

@YETBEB_BET
"ሞቼ እንኳን ላልረሳሽ ቃሌ ለሰማይ ነው!"
ያልከኝን ሰምቼ
በሞትክበት ቅፅበት
ተከትዬህ መጣሁ፣
ለቃልህ እንደታመንክ ላምን 'ባይኔ አይቼ ፤
ግን ነፍስህ እኔን ዘንግታ
ተላምዳለች ፃድቃን
ተሳሳትኩኝ መሰል መለየት ተስኖኝ ነፍስን ከስጋ ጋር

እባክህ አምላኬ....!
ነፍሴን ስጋ አላብሰህ ሸኘኝ ወደ ምድር
አልረሳኝ እንደሆን አካሉን ጠይቄ እድሌን ልሞክር!

ፊያሜታ

@YETBEB_BET
አልኖረችም...!

"ኧረ ይቅርብኝ" እያለችኝ ነበር ያስጀመርኳት። በኔ መንገድ ያመጣት ምናልባት ብቸኝነቴን ተመልክቶ ይሆናል የሚል እሳቤ ነበረኝ። ደስ የምትል ልጅ ናት።
"ሮዚ ነይ እዚ ምሳ በልተን እንሄዳለን" ፊት ለፊታችን ካለው ትንሽዬ፣ ነገር ግን የሰፈሩ ስፔሻል ምግብ ቤት ዘው ብዬ ገባሁ። ውስጥ ያሉትን ሰላም ብዬ ላስተዋውቃት ስዞር በር ላይ እንደተገተረች ነው። በመቆጣት 'ምን ሆንሽ' አይነት አስተያየት አየኋት።
"ለመግባት ፈራሁ፤ እነሱ ሲወጡ እንብላ እ አይሻልም?" በልምምጥ እያየች ጠየቀችኝ። መልስ አልመለስኩላትም ጎትቼ አስገባኋት።

"ኧረ አልችልም ደሞ አልጫወትም እንዴ ሰው እያየን?" የዋህነቷ ገረመኝ። "የገጠር ልጅ ስለሆንሽ ነው እዚ እኮ ሁሏም ሴት ፑል ትጫወታለች" የፑሉን እንጨት አስጨበጥኳት...

ከመንገድ ድንጋይ ፈላጭ(ፓስቲ) ገዝቼ አንድ ለኔ አንድ ለሷ ሰጠኋት። ተቀብላኝ በእጇ ስትይዘው ብዪ አይነት ምልክት እየበላሁ አሳየኋት
"እህ መንገድ ላይ ሰው እያየን?"
"ሮዚ የሚያይሽ የለም ምን ሁኚ ምን አድርጊ ማንም ቼክ የሚያደርግሽ የለም ፤ ደሞ ቢያይሽስ ምን ጨነቀሽ?" ከራሷ የምትደበቅ ያህል እየተርበተበተች ገመጠችው።
'ኧረ ይቅርብኝ' ያለችው ነገር ብዛቱ ዘርዝሬ አልጨርሰውም.... ለብዙ ነገር ድንግል ነበረች።
"ኧረ ይሄ ነገር ይቅርብኝ ሞክሬውም አላውቅምኮ" ራሷን እየተጠራጠረች ነበር። ላስረዳት ብሞክር እንቢ እንደምትል ስለገባኝ በድፍረት ሲጋራውን ከከንፈሯ አያይዤ እንድትስበው አደረኳት። ከሁለት ስበት ቡኋላ በጭስ ውስጥ ፈገግ አለችልኝ። (እንዲህ ቆንጆ ናት እንዴ!?)

"ርብቃ አቦ በናትሽ ነይ እንውጣ" ንዴቷ ድምጿ ውስጥ ያስታውቃል። ለመጀመሪያ ጊዜ ትንሽዬዋ ልጅ አዛኝ እሺ ብዬ ተከተልኳት። ሸገርን ከገጠር እየተመላለሰች እንዳየቻት እንጂ አንደኛዋን ለመኖር ስትመጣ የመጀመሪያዋ እንደሆነ ነግራኛለች። ከአክስቷ ቤት ከኔጋ ስራ ትሰሪያለሽ ብዬ ሳስወጣት ፍርሃት እንጂ ንዴት አልነበራትም። ወንዶች በተሰበሰቡበት ቦታ ይዣት ስሄድ ልምምጥ እንጂ ቆራጥነትን ከፊቷ አላነበብኩም። ሲጋራ እንድታጨስ ስገፋፋት 'አይ' አይነት ልምምጥ እንጂ 'አይሆንም' አይነት ቆራጥነት አላሳየችኝም (ምናልባት ሴት ስለሆንኩ አምናኝ ይሆን!?)

"ምን ሆነሽ ነው" ንዴቷን እያየሁ ጠየኳት
"ከዚ ቡኋላ እዚ መምጣት አልፈልግም" አለች። ግራ ገብቶኝ አየኋት። ለደቂቃዎች ያለማቋረጥ ሳያት
"ይቅርታ ከማንም ጋር መተኛት አልፈልግም" ይሄኛው ድምጿ ግን ትንሽዬ ተስፋ ነበረው። ዛሬ ከማንም ሸሽታ ነገ ማንን እንደምትሆን ሳስበው በጣም ኢምንት ተስፋ በሷ ላይ ሽው አለብኝ። ከዚህ በላይ እኔን እንድትመስል ማድረግ የነበረብኝ ሀጥያት በእጥፉ ደጋግሞ ማባዛት መሰለኝ።

ይቀጥላል

©ፊያሜታ

@YETBEB_BET
ሀሴት የፊልም የፎቶ እና የቪዲዮ ግራፊ ማሰልጠኛ
በብቁ መምህራኖች የፊልም እና የፎቶግራፊ ስልጠናዎችን በተለየ መልኩ እየሰጠ ይገኛል ።
ለቀጣይ ዙር ምዝገባ ጀምረናል ።
ፈጥነው በመረጡት ላይ ባለሞያ ይሁኑ።
በወንጅዋን የኪነ ጥበብ ማዕከል የሚሰሩ እንዲሁም የተዘጋጁ ቪዲዮዎችን በቅርቡ መልቀቅ እንጀምራለን። ይሄን ሊንክ ሰብስክራብ አድርጉና ተያይዘን እንደግ። ኪነ ጥበብንም እናዳብር
Forwarded from Ercole Pictures
የጥበብ ቤት
Photo
eski geba geba belu
aykerim..... endayameltot
yemariam nigs let🙏🙏🙏
2024/04/29 04:38:56
Back to Top
HTML Embed Code: