Telegram Group Search
አልኩሽ ልክ እንደዚህ.......
የሠማዬ ፀዳል፤የጨረቃዬ ውበት
የክዋክብት እምረት፤ የለሊቴ ድምቀት
ከደመና አናት ብርሃን የምትፈጥሪ
አፍሽ ሣያወራ ቃላት የምትዘሪ
እስቲ ጉዴን ልየው ዛሬ ለዓይኔ ቅሪ
.
.
.
.
ብዬ ከመስደዴ ልቤን ልፈትነው...
አትምጪ ባልኩሽ ቀን ከቃሌ ባትጎዪ
ምነው ተዚያ ወዲያ ለዓይንም አትታዪ
አሣየሺኝ ጉዴን በላው ሣር ፍዳዬን
አሣዳቹ ላህዋት የለሊትዋ ህልሜን
ታመሀል? እስክባል አብሯት ነጥፎ ወዜ
አምጡልኝ ላባብላት እስኪደርስ ደሞዜ🙃
ሀና አዲስ
@yehangetem
ከንቱነትን ለከንቱነት የዳረገች አንዲት ሴት!
***
ሳቋ እንደ መስከረም
ፈለገ ብረሃን ሠራፂ ነበልባል
አሃዱ ነፀብራቅ
ከራስ የሚስታርቅ።

ፈገግታዋ አደይ
ሃምራዊና ቢጫ ንፁህ ሠማያዊ
የዘመን ጎህ ምስራቅ
ከጊዜ ከቦታ ከይዞታ ረቂቅ።

ነፍሷ ዘለሠኛ
ምህረት ለተጠማ ልብ የሚንቆረቆር
ህዋስ የሚነዝር በደም የሚዘመር
የሠላምን ሀሴት በክንፎቹ የሚናኝ
እንስፍስፍ እርግብግብ
ከራዲዮን ርግብ።

ልቦናዋ ቅኔ
ከውበት ማህሌት ሌት ቀን የሚዘረፍ
የንመሃ አራራይ
ከፍጥረት ማአዛ ከርቤ ሆኖ 'ሚፃፍ
ቀዳማይ ዳህራይ ጊዜ ቦታ 'ሚገድፍ
ዘላለም አስጥሎ ዘላለም 'ሚነድፍ።

መንፈሷ ንፁህ ወርቅ
ሀቅን የሚፈትን የተፈተነ እንቁ
እንደ ግዮን ገነት እንዳምላክ ደምግባት
የእውነት ማይ ትጥቁ።

ኩርፊያዋ አርሂቡ
አቦል ቶና ብሎ
ከሃሳብ መከዳ ግርምት ያሠናዳ
ከፀፀት ከርግማን ከክፋት የፀዳ።

ከንቱነትን ለከንቱየት የሠጠችው
አንዲት አንድያ ብሩህ ሴት እሷ
ርግማንን የቀደሠች ህግን በፍቅር የምትሽር
ልቦናችን ነው መቅደሷ።

ይህቺ ሴት መልከ ሙሉ ናት
ይህቺ ሴት መልከ ፅኑ ናት
ይህቺ ሴት መልከ ፀጋ ናት
ይህቺ ሴት ፀሃይ አምሳል ናት
ከወዳጅነት ሠማይ ከአብሮነታችን ምእራፍ
ፋፁም ላታዘቀዝቅ
ስፈነጥቅ ካየንበት
ከብቻዋ ህይወት ምስራቅ
መስከረም ሆና የጠባች
መስከረም ሆና የፀናች
በፈገግታዋ አደይ አብሮነታችንን ገምዳለች።

እሷነቷ ለእልፍ ነፍሶች
እሷነቷ ላእላፍ ልቦች
እሷነቷ ለጊዜ እስረኞች
ቅዱስ የአዛን ጥሪ ነው
ቅዱስ መሆንን በቅፅበት
በአፍታ ቡራኬ የሚወስን።

በነፋሷ ዘለሠኛ
በሀቅ ከፍታ እንጉርጉሮ
በልቦናዋ ተመስጦ
ህልውናችን ተማግሮ
ከቢጫ ሃምራዊ ቀለሟ
ሠማያዊ ገጿ ሁለመናችን ተነክሮ
በመንፈሷ ጠብታ ማይ መንፈሳችን ተፀብሎ
አለን ከንቱ ስትለን ከንቱነታችን ተገሎ።

ወደ ፅድቀቷ መዲና
ወደ ጥራቷ ጎዳና
ወደ ውበቷ ጥሞና
በፍቅር እየሠረግን
ፈለገ ብረሃን ሆንን
ሠራፂ ነበልባል ዘራን
ዘላለምን እየሻርን
ህያው ዘላለም አነፅን
እንደ ጳግሜ ባጭር ጣፈጥን
እንደ መስከረም ገፅታ
ማበብ መፍካትን ናኘን
እውነቷ እውነት አፀና
ከሀቂቃቃ ቆረብን
ከራሳችን ጋር ታረቅን።

ተጳፈ
ለኔዋ ከንቱ መዲና
ነሐሴ 30/2014 ሞጆ
አንቺ ምላስ መላሽ አብስለሽ አጉራሽ..
ገደፍሽ ባሉሽ ጊዜ ምን ሰበብ ሰጠሽ..
እኔ ሳድስ ናድሁ በቃል መደምሰሻ..
በይ ቆርሰሽ አቅምሺኝ ለ*ንቅቡ ሟሟሻ..


ሀና....
"ያች ምስኪን ነፍሴ"
መጫወት መፈንጠዝ መዝናናት ሚያዋያት
ከአሻት ውሎ ማደር መራቀቅ ሚመስላት
" ያች ምስኪን ነፍሴ"
ባክና ከህልሟ ጥግ መክና ከአጥናፏ
ከቀመሱት ስትቀምስ መዝቀጥ ሆኖ ትርፏ
ብትሠቅል ብታወርደኝ ባይደክም ስጋዬ
ሠውነቴን ገራው ነፍሴን ለእግዜር ጥዬ😂



@yehangetem
"መታለች አትቀርም"
ጥሩልኝ አልልም ትመጣለች ቆጥራ
ፍጠሩልኝ አልል ቀድሞ አለች ተፈጥራ
ሣሙልኝ አልልም አልመኝላትም
ሠላምታም አልክም ለእሷ አይገባትም
በላሽ ወይ ጠጣሽ ወይ ብዬም አልጠይቃት
የበላችው ካለም አይውረድ ያቅራት
ይህን ሁሉ ነገር የሰማች እንደሆን
ያየች የተረዳች ያጤነችው ሰሞን
እንዴት ነሽ ሣልላት ስምንት ወር ብከርም
ዘጠነኛን ቆጥራ መታለች አትቀርም።





ፍቅርን የተረዳው አሽሞንሙኑኝ አይልም።🤷‍♀😂
..................

@yehangetem
*☕️☕️☕️☕️☕️*
የገጣሚ ዋይታ...ማረፍያው ቅዳሜ
በአቦሉ ጠብቀኝ ልርሳበት ህመሜ
መድብል ህናጣቅስ በዜማ ህንዝመም
ዘመን እንታዘብ በታሪክ ህንትመም
አጉፅለኝ ላጉፅልህ በቃላት ልረታ
ወይ እኔ አንተን ልርታ
ብቻ አንተ ጠብቀኝ ካስለመድኸኝ ቦታ
እጣንና ከርቤ ከሚጫጫስበት..
ዓውድ ዓመት(×2) ከሚሻተትበት
ጥቁር ቡና ይዘህ ሲኒዋን እንዳመል በጣትህ አቀማጥለህ
ከቶ ካፍህ ሳይወርድ ከጉንጭህ ሳይበርድ መጣው እኔ ርግብህ.....
.
.
.
ሀና አዲስ
አንቺ ባካኝ ነፍሴ ሲነግሩሽ ባትሰሚ
በሚያርፍብሽ እቶን ተይ አትታመሚ
ቀድሞስ መዳን.. ከካላትሽ ካልተዋጀ
ትውልድ ቢማስን......ዘመን ፈጀ
ቃላት ማድነቅ ሆኖ የኛ ጥበብ
ጥለቱን አጣነው ከወጋቸው መዝገብ
ሙሴ ዙፋን ሲይዝ በትሩን ከጣለ
ነብይ ተሰይሞ በቃሉ ካልዋለ
ፍርድ ተጓደለ እምነት ተጣረሰ
ዳዊት ባላት ሀገር ጓልያድ ነገሰ

ሀና አዲስ
አትምጪ ደግሞ አጠይቂኝ ከዓይኖቼ *ራቂ
ሳዝን አታፅናኝኝ....በሳቄም አትሳቂ
ለህመሜ ማስረሻ መድሃን ካንቺ አላግኝ
ከእኔ አትላመጂ.... ልቅርብሽ ቅሪብኝ
በተከፋው ሰሞን እቅፍሽ በኔ አይራድ
አቅፈሽ አትጎንትይኝ ልቤ በአንቺ አይማድ
አውቀዋለሁኛ!!!!
ዓይኖቼን እያየሽ ፍቅርን ስታጠኚ
የመውደድ እስረኛ ምርኮ ስታገኚ
ያኔ ሚስት ሳይሆን እህት ለምትሆኚ......!!!
አትምጪ!።
ሀና አዲስ
.................ናፍቀኸኛል
ትናንት እና ዛሬ የምሰናሰነው
ሌላም ምስጢር የለው አንተን ወድጄ ነው
አዎ ድሬሃለው በእምባ ሳቅ ታጅቤ
በጥቁር ቀሚስ ላይ ቀይ ጃኖ ደርቤ
ኩራ እንደ ልብህ.....
በሁለት ልቦች ላይ የተደላደለ
ማን እንዳንተ አለ.....ማንም!
እና ናፍቀኸኛል......
እስከ ቀለበትህ
እስከ ባለቤትህ!
እስካል..ተወለዱት እስከነ ልጆችህ...
አዎ ናፍቀኸኛል!!!!!
እኔ ያንተ አፍቃሪ... እኔ ያንተ ከርታታ
እኔ ያንተ ጠባቂ....እኔ ያንተ መከታ
እንደው በምናልባት እንዳል-ተመኘውት
ሰይጣን መሀል ሰፍኖ ከተለያያችሁ
እኔ ነኝ የማስታርቃችሁ.....
(ብቻ ባደረገው...)
ሀና አዲስ
አንቺን እንደማርያም ማርያምን እንዳንቺ!!
ኑዛዜ!

ስለ ማርያም!...
በዘመነ ኦሪት
በዘመነ መንሱት
ባረጀ ያንጊዜ
ባፈጀ አባዜ
በጥንት ተክዤ...
እልፍ ሴት ደናግል!
እልፍ የውበት ሰብል!
በሞላበት አለም
ማን አለ እሷን ያክል?
እላለሁ!...
***
ስለአንቺ!...
በዘመነ ኪዳን
በዘመነ አዲስ
በዘመነ መንዲስ
ዘመነ ሁካታ
ዘመነ ጫጫታ
ወጣት ተሰፍ ይዤ
በመፃኢ አባዜ
ከአሁን ተሰፍቼ
እልፍ ቆንጆ መሃል
እልፍ እንስት ሸኝቼ
እልፍ እንስት ስቀበል
አሰስ ገሠሠስ ግርዱ
በሞላበት አለም
ማን አለ እሷን ያክል!?
እላለሁ!...

ማርያም!...
ቅዱስም ንጉስም
ፈጣሪም አምላክም
ሁሉን ቻይ ልጅ ያላት
እናት ስትሆን ባርያ... ገረድ ስትሆን እናት!

አንቺ!...
እርኩስም ጭሠኛም
ተፈጣሪም ሎሌ
ደካማ ጠንካራ መጠሪያ ልጅ የለሽ
እናትም አገልጋይ ልቶኝ ያልተጠራሽ!

ማርያምን!...
እቴ ሙሽራዬ ይላታል ጠቢቡ
ከህሊናው ሸራ
ከነፍሱ ብራና
ውበት መልኳን ነድፎ
ኪዳነ ቋሏ ላይ ነብስያውን ፅፎ።
የአብራሀም እናት
የይሳቅ እመቤት
ያያእቆብ ተስፍ
የዬሴፍ መለከት።
የዳዊት ዝማሬ
የሰለሞን ቅኔ
የእሳያስ ልሳን
የህዝቅኤል ወኔ
የኦሪት ናፍቆት ታቦት
የአዲስ ኪዳን መክሊት።
ይላሉ...

አንቺን!
ዘመናይ ማርዬ
ይልሻል መንፈሴ
ፈገግታና ሳቅሽ
ተጣብቶ ከነፍሴ
ምን ጠቢብ ባትሆንም
ያይኗ ሉል
መኳኳል
የአዳም መሠናክል
የባቷ አወራድ
ከሀጢያት የሚማግድ።
ይላሉ!...

ማር ይሏት መድሃኒት
ያም ምትባል ፈውስ
የመለኮት መባ
ንፅህት ህያው ቅዱስ።
ይሏታል!...

ሬት ይሏት ምሬት
ጭራ ቀረሽ ደዌ
የጋኔል መስፈሪያ
ርኩስ...ርጉም... ክፍ የጥፍት ህላዌ
ይሉሻል!...

ቅዱስም ንጉስም
ፈጣሪም አምላክም
ኤልሻዳይ ልጅ ያላት
እናት ስትሆን ባርያ... ገረድ ስትሆን እናት።
ይሏታል!...

እርኩስም ጭሠኛም
ተፈጣሪም ሎሌ
ደካማ ጠንካራ መጠሪያ ልጅ የለሽ
እናትም አገልጋይ ልቶኝ '"ያልተጠራሽ።
ይሉሻል!...

እናልሽ!.....
አንቺን እንደማርያም ማርያምን እንዳንቺ!! ቢረግልኝ ዘመን ቢራራልኝ ጊዜ
ያበቃ ይሆናል ይህ ሁሉ ኑዛዜ።

ጥቅምት 21/2015 ሞጆ
በሀና አዲስ ተፅፎ እንደቀረበ
@yehangetem
እኔ እንደነገርኩህ አትንገራት

እንዳፈቀርካትም አታብስራት

በፍቅር ዓይንህ አታክማት

በድብቅ ስሜትህ ፧ ብቻ አስባት

በግልፅ ስታውቀው...ያኔ የአንተ ናት😊

(የሳድስ ሰስሜት)

ሀና.......
2024/03/28 13:32:22
Back to Top
HTML Embed Code: