Forwarded from Fuad Muna (Fuya)
ዘመቻ እንጀምር!
(ፉአድ ሙና)
.
እንደሚታወቀው ከነገ ጀምሮ በዩቲዩብ ገፄ የመንታ መንገድ ልብወለድን ትረካ ወደናንተ ማድረስ እጀምራለሁ።

በአሁኑ ሰዓት የዩትዩብ ቻናሌ አምስት መቶ ምናምን ሰብስክራይበር ብቻ ያለው ሲሆን እስከ ነገ ድረስ ከአንድ ሺህ ሰብስክራይበር ከፍ እንዲል እናድርግ!

ሁላችሁም በገፃችሁ ላይ በፈለጋችሁት መንገድ የዩትዩብ ሊንኬን እያያዛችሁ ፖስት በማድረግ ዘመቻውን ተቀላቀሉ። ዩትዩብ የሚጠቀሙ ወዳጆቻችሁን ሁሉ ወደ ቻናሌ ጋብዙ!

http://Www.YouTube.com/c/FuadMuna
.
@Fuadmu
⭕️ ነፃ ኢንተርኔት ነፃ ኢንተርኔት እያሉ ብዙ ቻናሎች Fake App እየለቀቁ ብዙ ሰዎች ገንዘባቸውን ተበልተዋል። እኛ ጋር ግን አሪፍ መፍትሄ አለን። ያለ ምንም አፕ settings በማስተካከል ነፃ ኢንተርኔት እንዴት መጠቀም እንደምችሉ መማር ትችላላቹ

እንዲሁም ሌሎች

📱 ስለ Hacking ሙሉ ትምህርት

🌎የኢንተርኔት trick + Online ብር አሰራር

🎮 ስለ ምርጥ Game እና App

💻 ስለ ኮምፒውተር Trick እና Tip

💡 ስለ ጠቅላላ ቴክኖሎጂያዊ መረጃ

🔖 ከ Youtube Video ጋር!


📱ከነጻ የሞባይል ካርድ ሽልማት እና ሙያዊ እና አዕምሮዊ እውቀት የሚያገኙበት ቻናል ነው አሁን ይቀላቀላሉን።
😲🤟እናም ብዙ በዙ ነገር.........


👇👇👇👇
https://www.tg-me.com/joinchat-AAAAAFgiL3qFeYWp3Rw3Tg
https://www.tg-me.com/joinchat-AAAAAFgiL3qFeYWp3Rw3Tg
ሰላም ቤተሰቦች እንደምን ከራረምን?

ዛሬ አንድ ሀሳብ ይዤላችሁ ተከስቻለሁ 😊

ምን መሠላችሁ በታደሰ መልኩ ከሰሞኑ ማለትም ከነገ ጀምሮ መሳጭ የፍልስፍና ወጎች እዉቀቶች እንዲሁም አዝናኝ ቁምነገሮችን እናቀርባለን!

እናም በተቻለን አቅም share በማድረግ እንተባበር🙏


@phillosophy
@phillosophy
@phillosophy
በቀጠሯችን መሠረት ለዛሬ #ጥበብ ከጲላጦስ ቅፅ ፪ ስብስብ ስራዎች አጥንት ያላቸዉን ሀሳብ በተከታታይነት የምናይ ይሆናል።

እስከዛዉ ግን share በማድረግ ይተባበሩን ስንል በአክብሮት እንጠይቃለን 🙏

ጠይም ጁምአ❤️

@phillosophy
@phillosophy
ክፍል 1⃣

<< ሰዉ የምኞቱን ማድረግ ሲችል ብቻ ነፃ ይሆናል>>

፨ በፍልስፍናዉ አለም አንዱ ዋነኛ መነጋገሪያ ነፃነት ነዉ። ነፃነት እንደየዘመኑና እንደየፈላስፋዉ የአስተሳሰብ እና የእምነት አቅጣጫ እየተቃኘ ሰፊ የመከራከሪያ ሐሳብ ሆኖ ከጥንታዊው የግሪክ ሥልጣኔ ዘመን እስከዛሬው ተደርሷል።

<<ነፃነት>> ከቃሉ ትርጉም እስከ መሠረታዊዉ ፅንሰ ሐሳብ የብዙዎችን ቀልብ የገዛና ከማስማማት ይልቅ ወደ መለያየት፣ ከመወያየት ይልቅ መከራከር የወሰዳቸው ጉዳይ ነዉ። በተለይም ነፃነት በሰዎች አእምሮ የፈጠረው የተለያየ ትርጉም ወደተለያየ የህይወትና የእምነት ዘይቤ እንደመራቸዉ ፈላስፎቹ ሲነግሩን አንዳች የምንደርስበት መቋጫ ነጥብ በእነሱም ዘንድ አለመኖሩን እግረመንገድ አስረግጠው ያስቀምጣሉ።

እንግዲህ ፈጣሪ እንደሰጠን ከሚታመነዉ የመጀመሪያው ነፃነት በመነሳት ወደ ፍልስፍናዉ እሳቤ ደግሞ እንዘልቃለን። እግዚአብሔር አስቀድሞ ለመረጠዉ ህዝቡ በሙሴ በኩል የሰጠዉ ነፃነት እንዲህ የሚል ነበር፦

<< እንግዲህ ህይወትና ሞትን በረከትንና መርገምን እንዳስቀመጥሁ እኔ ዛሬ ሰማይንና ምድርን በአንተ ላይ አስመሰክራለሁ፤ እንግዲህ አንተና ዘርህ በህይወት ትኖሩ ዘንድ ህይወትኖ ምረጥ>>(ዘዳ.30፡19)


የፈጣሪ ነፃነት ይኼ ነዉ። የሰዉ ልጅ በራሱ ፍቃድ የመኖር ነፃነቱን ሲያረጋግጥለት የነፃነቱ ዉጤት የሚያመጣለትንም እንዲሁ ለመቀበል እንዲዘጋጅ እያስጠነቀቀዉ ነዉ። << የነፃነት እሳቤ ሰጥቶ መቀበል መሆን የጀመረውም ከዚሁ አንስቶ ነዉ።>> የሚሉን ፈላስፎች፦
<< ፍፁም ነፃነት የሚባል ነገር በፈጣሪም ዘንድ ሊኖር አልቻለምና! ይልቁንም ከሰው የሚሰጥም ሆነ፣ ሰዉ ተሰጠኝ ብሎ የሚያስበዉ ነፃነት እንዴት ፍፁም ሊሆን ይችላል?>> በማለት ይጠይቃሉ?


ይቀጥላል.....!

@phillosophy
@phillosophy
@phillosophy
ስለቆየን ይቅርታ እንጠይቃለን 🙏

💫ሀሳብ ⭐️

ክፍል2⃣

<<ፈላስፋ በህይወት ጨዋታ ላይ የተገኘ ተመልካች ነዉ>>

ፍልስፍና ምንድነች? ለዚህች የአያሌ ዘመናት ጥያቄ በቀደሙት አሳብያን የተሰጡ አያሌ ምላሾች በየዘመኑ ፌርማታ እየተቀመጡ የመጡ ቢሆንም ከዚያ ይልቅ የነበሩትን ተመሳሳይ የአስተሳሰብ ፈርጆች እየፈተሹ ማለፉ በድጋሚ አሀዱ ብለን ልንጀምረዉ ጉዞ የመንደርደሪያ ያህል ያግዘናል።

እንግዲህ ፍልስፍና በየዘመናቱ ለተነሱ አሳብያን በምድር የመፈጠርን ምክንያትና ግብ(በጥቅሉ ደግሞ የህይወትን ምስጢር) የሚመለከቱበት የህሊና መነፅር አድርገው ሲማትሩበት ኖረዋል። በዚህም ምክንያት ፍልስፍና የተከታዮቿ የእምነት ኮርቻ የሚጫንባት የሃሳብ ፈረስ በመሆን ስትጋለብ ኖራለች። ፍልስፍና ለአንዳንዶቹ የፈጣሪ ህልውና ማስረገጫ፣ የሰው ልጅም የእጁ ስራ በሆነችዉ ዓለም ወስጥ እንዲኖር ለመፈጠሩ መከራከሪያ ነች።

እንደቶማስ አኩዊና፣ ጆርጅ በርክሌይና ሶረን ኪርጋርድ ዓይነቶች አሳብያን ይህንኑ እምነት አጠንክረው በመያዝ የፍልስፍና መነሻም ሆነ መድረሻ ሃይማኖታዊ እምነትና አስተሳሰብን ከማስፈን የላቀ ድርሻ የለዉም ይሉናል።

@pillosophy
@phillosophy
@phillosophy
<<<<ሞራል>>>>

ብዙዎች ፈላስፎች የሰው ልጅ ስለሞራል ሲያወራ ቅድሚያ ሊያነሳ የሚገባው የጥሩና የመጥፎ ነገርን መመዘኛ ነው ይላሉ። በአንድ ማህበረሰብ ውስጥ ጥሩ የሚባለው ነገር በሌላው መጥፎና ጎጂ ይባላል። ለምሳሌ አንድ ሰው ከሚስቱ ውጪ ከሌላ ሴት ጋር ቢዳራ ማህበረሰቡ ሀጢያት የሚያደርገው ምናልባትም የዛ ሰው መጨረሻ ገሀነም ለመሆኑ አረጋግጦ በማስተማር ነው። በሌላው ማህበረሰብ ዘንድ ደግሞ ይኸንኑ ድርጊት አለማድረግ የደካማነትና የልፍስፍስነት ባህሪይ ተደርጎ ይወሰዳል እንጂ ከገሀነምና ከገነት ጋር ጉዳዩን የሚያገናኘው የለም።
እንዳውም የዚህ ማህበረሰብ ፈላስፎች "ሀጢያት የእውቀት ማጣት ውጤት እንጂ የሞራል ጉዳይ አይደለም" ይላሉ።
ይሄ ሲብራራ "አዋቂነትህ እያደገ ሲመጣ ከሀጢያት ትርቃለህ" ነው። እዚህ ላይ የሚነሳው ጥያቄ ታዲያ "በአዋቂነት ከሀጢያት መራቅ ከተቻለ "ሀጢያት" የሚባል ጉዳይ በራሱ አለማለት ነው?" ይሆናል።

ለዚህም ደግሞ በተለይ የዘመናችን ፈላስፎች ከጥንታዊያኑ የተለየ መልስ አላቸው። ለዚህ እሳቤ የፍራሲስ ቤከን ሀሳብን ጣልቃ አስገብተን እንመልከት። በቤከን አስተሳሰብ <ሁሉም ነገር ሁለት መልካም ነገሮችን ይዟል፤ የመጀመሪያው ግላዊ ሞራል ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ ማህበረሰባዊ ሞራል ነው። ከሁለቱ ደግሞ ማህበረሰባዊ ሞራል እጅግ አስፈላጊና ጠንካራም ነገር ነው። ምክንያቱም በግላዊ ሞራል ውስጥ ሰፊውን ቦታ የሚይዘው "እኔነት" ነውና። እኔነት ደግሞ ከሰብዓዊ ሞራል ይልቅ ተቃራኒውን ለመፈፀም ሰፊ እድል አለው። ዞሮ ዞሮ ሰው ባሪያ መሆኑ አይቀሬ ነው። ምነው ቢሉ (አታድርግ) የሚል እስር ቤት ማህበረሰቡ ፈጥሮበታልና> ይላል። አልደስ ሀክስሌይ ይህን ሀሳብ ይቃወማል።

እንደ ሀክስሌይ አስተሳሰብ ሞራል ማለት ጠንካራ ሆኖ ደካማውን መርዳት ነው። ሞራል በአጭሩ <<በሰብዓዊነትና በክብር የታጠረ ነገር ነው። ከዚያ የወጣ ነገር ሞራል አልባ ድርጊት ይሆናል… ስለሆነም የሞራል ግብ ሰላም ሲሆን ከሞራል የራቀው ነገር መጨረሻ ደግሞ ጦርነት ይሆናል>> ይላል። በሀክስሌይ ሀሳብ አንዳንድ ፈላስፎች ሲሳለቁ <<ሞራል ማለት እንደብዙሀኑ ማሰብ ከሆነ የብዙሀኑ ሀሳብ ትክክለኛነት መጀመሪያ ሊጤን ይገባዋል>> ይላሉ።
ለምሳሌ መንገድ ላይ ተቀምጦ ለሚለምነው ደሀ ሳንቲም መስጠትህ በራሱ ነገሩን ሞራላዊ አያደርገውም፤ ነገር ግን የሰጠህበት እሳቤ ነገሩን ከሞራል ጋር ሊያገናኘው ይችል ይሆናል። ደሀውን የምትረዳው ከሞት በኋላ ህይወት ወይም ገነት እንደሚጠብቅህ አስበህ ከሆነ ይህ ከጥቅም እንጂ ከሞራል ጋር የሚያገናኘው ነገር የለም እንደማለት ይሆናል።
ለነገሩ የእግዚኣብሄርን የሞራል እሳቤም ብንመለከተው "ሰው የዘራውን ያጭዳል" የሚል ከሆነ ጉዳዩ ከሞራል ወይም ከህሊና ጋር የተገናኘ ሳይሆን ለምታደርገው ነገር ዋጋ እንደሚከፈልህ እንድታውቅ ነው። ፈላስፎቹ ከላይ ያነሳነውን ምሳሌ በማንሳት ሲናገሩ፦ <<ከሚስትህ ውጪ ከሌላ ሴት ጋር የምታደርገውን መዳራት ገሀነም እንደምትገባ አስበህ ከተውከው ያለመዳራትህ ምክንያት ሞራላዊ ሳይሆን ጥቅማዊ ነው>> ይላሉ። ገሀነምን መፍራት ወይም ገነትን መመኘት ከሞራል ጋር የሚያገናኘው አንዳች ጉዳይ የለምና።
ስለዚህም ሞራል የእውቀት ጉዳይ እንጂ ሌላ አይደለም የሚሉት ፈላስፎች ለእነ አናቶሌ ፍራንስ ጥያቄ ግን አንዳንድ ምላሽ ሲያጥራቸው ይስተዋላል።

ለአናቶሌ ፍራንስ ብቸኛውና ትልቁ የሰው ልጅ ሞራል (ንፅህና) ነው። ይህንንም ሲገልፀው "አንድ በሀብት የናጠጠ ከበርቴ ተመልክተህ ስታደንቀው ትኖርና ከእለታት አንድ ቀን የሀብቱ ምንጭ ሀሺሽ በመሸትጥ የተገኘ እንደሆነ ትደርስበታለህ፤ በግለሰቡ ላይ ያለህ አመለካከትም መለወጥ ይጀምራል። ለምን ቢሉ የሀብቱ ምንጭ የሌላው ሰው ጥፋት እንደሆነ ስለምትቀበል ነው። በሞራልም ተቀባይነት የሌለው ሀብት እትዲህ አይነቱ ነው" ይላል።

አሁንም በዚህ የአናቶሌ ፍራንስ አስተሳሰብ የሚሳለቁ የዘመናችን ፈላስፎች ደግሞ አልጠፉም። <<ንፅህና>> የሚለው ነገር የህሊና ንፅህና ከሆነ የንፅህናስ መለያው ምን ይሆን?>> ይሉናል።
<<አንስታይን የፈጠረው ቦምብ ለአለማችን እልቂት ሲውል ተመልከተናል። ነገር ግን አንስታይንን ከማድነቅ ውጪ የእሱን 'ሞራል አልባ' ድርጊት በማለት የኮነነው አልተገኘም>> ይላሉ።

በዚህ መንገድ ሞራል አንድም የእውቀት ሌላም ጊዜ የእምነት ጉዳይ ሁኖ እስከዘመናችን ቢዘልቅም ቢዛን ደፍቶ ያጋደለው ግን ወደ እምነቱ ሆኗል። በተለይም የፍልስፍና አባቶች ከሚባሉት ከሶቅራጥስና የእሱም ደቀመዝሙር ከነበረው ከፕሌቶ ጊዜ አንስቶ ሞራላዊ እሳቤዎች ከአምላክ ጋር የተቆራኙ በመሆናቸው ሁለቱን ለመነጠል መሞከር የሰውን ተፈጥሯዊ ዋጋ ዝቅ እንደማድረግ ነው የሚሉ በብዛት ይገኛሉ። ከዚህ በተቃራኒው የቆሙት ደግሞ እንኳን ለራሱ ቀርቶ ለአምላክም ሞራልን የፈጠረ እራሱ ሰው ነው፤ ስለዚህ ሞራል የእውቀት እንጂ የእምነት ነገር ሊሆን አይገባውም ባዮች ናቸው።

ምንጭ፦ ጥበብ ከጲላጦስ
ቅጽ .፪
ሀይለጊዮርጊስ ማሞ


@phillosophy @phillosophy
@phillosophy @phillosophy
የበሰበሰ ጥርስ
(ካህሊል ጂብራን)

📗📗📒📒📕📕

በአፌ ውስጥ በስብሶ የሚያስቸግረኝ አንድ ጥርስ አለኝ በቀን ሰላማዊ ሆኖ ይውላል ። ምሽቱ ሲገፋ፣ የጥርስ ሃኪሞቹ እንቅልፍ ሲጥላቸው እና መድሃኒት ቤቶቹ ሲዘጉ ግን ይጠዘጥዘኝ ይጀምራል ።

አንድ እለት ትዕግስት ተሟጠጠና ወደ አንድ የጥርስ ሃኪም ሄጄ ያንን ስቃይ ያበዛብኝንና የምሽቴን ፀጥታ ወደ ማቃሰት እና ማጓራት በመለወጥ እንቅልፍ የነሳኝን ጥርስ እንዲነቅልልኝ ነገርኩት ።

📖📖📖

የጥርስ ሃኪሙ ራሱን ከግራ ቀኝ እየወዘወዘ " ጥርሱን ማዳን ስንችል መንቀሉ ቂልነት ነው " አለኝ ። ከዚያም ጎንና ጎኖቹን በስቶ ቀዳዳዎቹን በማፅዳት ወደ ቀድሞ ሁኔታው ሊመልሰው እና ከብስባሴው ሐራ ሊያወጣው ያለውን መንገድ ሁሉ ተጠቀመ ። መብሳቱን ከጨረሰ በኋላ በንፁህ ወርቅ ሞላውና " የበሰበሰው ጥርስህ አሁን ከጤነኞቹ የበለጠ ጠንካራና ብርቱ ነው " አለኝ በኩራት ። አመንኩት ። ከፈልኩትና ስፍራውን ለቅቄ ሄድኩ ።

📖📖📖

ነገር ግን ገና ሳምንቱ ሳይገባደድ የተቀሰፈው ጥርስ ወደ ህመሙ ተመለሰና የነፍሴን ጥዑም ዜማ ወደ ለቅሶና ስቃይ ለወጠብኝ ። እናም ወደ ሌላ የጥርስ ሃኪም አመራሁና
" ምንም ጥያቄ ሳይጠይቀኝ ይህንን ጥርስ አውጥተህ ጣልልኝ ። የደረሰበትና ያልደረሰበት ግልግልን እኩል አያውቃትም! " አልኩት ።

ትዕዛዜን በማክበር ጥርሴን ነቀለልኝ ። ከዚያም ጥርሴን እያየ " ይህ ጥርስ እንዲነቀል በማድረግህ መልካም አድርገሃል " አለ ።

📖📖📖

በአፍ ማህበረሰብ ውስጥ እስከ መንጋጋ አጥንት ድረስ የበሰበሱ ብዙ በሽተኛ ጥርሶች አሉ ። ይሁንና ማህበረሰቡ እነዚህን የተበላሹ ጥርሶች ለማስነቀልና ከስቃዩ ለመገላገል ምንም ጥረት አያደርግም ። ራሱንም በወርቅ ፍቅፋቂ ይሞላል ። አብዛኞቹ የበሰበሱትን የማህበረሰብ ጥርሶች በሚያብለጨልጭ ወርቅ እንደሚያክሙ የጥርስ ሃኪሞች ናቸው ።

እንደዚህ ተጠጋግነው በመደለል የሚኖሩ ብዙዎች ናቸው ስቃይ ህመምና ሞት ዕጣ-ፈንታቸው ናቸው ።

📖📖📖

....ሃገር አፍ ውስጥ ብዙ የበሰበሱ እና ቆሻሻ ፣ ያመረቀዙና የሚሸቱ ጥርሶች አሉ ። ሃኪሞቹ ከመንቀል ይልቅ በወርቅ ፍቅፋቂ አክመዋቸዋል ። ህመሙ ግን እንዳለ ነው ።

የበሰበሰ ጥርስ ያለው ሃገር የታመመ ጨጓራ እንደሚኖረው እርግጥ ነው ። በዚህ ያለመፈጨት ችግር ውስጥ የሚገኙ ብዙ ሃገራት አሉ ።

...ሃገር ዳቦውን በበሰበሰ ጥርሱ እንደሚያኝክ እና አንዳንዱም ጉርሻ ከተመረዘ ምራቅ ጋር በመዋሃድ በሽታውን በሃገሩ ጨጓራ ውስጥ እንደሚያሰራጭ ስትነግሯቸው " አዎ ግን የተሻሉ የጥርስ ሙሌቶች እና ማደንዘዣዎች እየፈለግን ነው " ይሏችኋል ....

📖📖📖

ምንጭ 👉 " የጥበብ መንገድ "
ከገጽ 16 - 18 ካለው የተቀነጨበ
ደራሲ 👉 ካህሊል ጂብራን


@phillosophy @phillosophy
@phillosophy @phillosophy
" የሰው ልጅ ባህርይ የተዘረጋው በምኞቱ ውስጥ ነው "

📜📜📜

<< የሰው ልጅ ባህሪይ የተዘረጋው በምኞቱ ውስጥ ነው ፣ ስለሆነም ባህርይ የምኞት ተቀጥላ ነው ብንል ያስኬደናል >>

" በአእምሮህ እየተጠበብህ ስትመጣ ምናልባት አድናቆትን ከሰዎች ዘንድ ያተርፍልህ እንደሆን እንጂ እውነተኛ ፍቅርን ግን ልታገኝበት እንደማትችል እርግጠኛ ሁን፣ ለዚህ ነው ማንኛውም ምድራዊ ሃይማኖት ለመልካም ምኞት እንጂ ለአእምሮ ጉብዝናና ዕውቀት ዋጋ አለኝ የማይለው "....

🗒🗒🗒

ሥጋዊ አካላችን እንኳን ሳይቀር የዚሁ የምኞታችን ውጤት ነው...
" በውስጥህ የሚፈሰው ደምህ ለመኖር ያለህ ምኞት ውጤት መሆኑን አትዘንጋ ። ነገር ግን ይኽን ምኞት ሕይወት የሚል የተድበሰበሰ ስያሜ እንሰጠዋለን ። የምኞትህንና የሰውነትህን እንቅስቃሴ ሁለት የተለያዩ ነገሮች አድርገህ አትመልከታቸው ። አንዱ ምክንያት ሌላው ደግሞ ውጤት አይደለም ። ነገር ግን ሁለቱ አንድና የማይለያዩ ነገሮች ናቸው ። በሰውነትህ የምታደርገው አንዳች እንቅስቃሴ ሁሉ በዓይን የማታየው ምኞትህ ሥጋ ለብሶ ሲገለጥ ማለት እንደሆነ ተረዳ "....

🗒🗒🗒

እውቀት በግዜ ሂደት ሲደክም ምኞት ግን ከድካም የራቀች መሆኗን ማወቅም ይገባል...። ለምሳሌ የሰው ልጅ እንቅልፍ ቢወስደውም አእምሮው ምግብ መቀበሉን አያቆምም፤ ምኞት ግን በማንኛውም ሰአት ምግብ አይፈልግም ። ስለዚህ በአእምሮ ለሚሰሩት የእንቅልፍ ፍላጎታቸው የላቀ ነው ብንል ያስኬደናል ።

🗒🗒🗒

ሕይወት ከሞት ጋር ግብግብ የገጠመችው እኛነታችን ወደ ምድር ከመጣ ጀምሮ ነው ። እናም በሕይወታችን ውስጥ ሞት ማንነቱን የሚያስለምደን በእንቅልፍ በኩል ነው.....በአጭሩ ሞት ሙሉ በሙሉ እስኪወስደን ድረስ የእንቅልፍ ጉርሻ ይሰጠናል!

ይለናል አርተር ሾፐንሀወር
ምንጭ 👉 📘ጥበብ ከጲላጦስ📘

📜📜📜
ለማንኛውም ሃሳብ አስተያየተዎ
@SSR60 ላይ አድርሱን

@phillosophy @phillosophy
@phillosophy @phillosophy
#የኦሾ_የፍቅር_አገላለጽ!

አንድ ሰው በአንዲት ትንሽ የገጠር ከተማ ውስጥ "ትኩስ አሳ እዚ እንሸጣለን!" የሚል ትልቅ የቦርድ ፅሁፍ ያለው የአሳ መሸጫ ሱቅ ይከፍታል።

እናም ከእለታት አንድ ቀን አንድ ገዢ መጣና " ትኩስ አሳ እዚ እንሸጣለን!" የሚለውን ፅሁፍ ሲያየው ትክ ብሎ ሳቀ። "ትኩስ አሳ'? ሌላ ቦታስ የዋለ ነውንዴ የሚሸጡት? "ትኩስ!" የሚለው ምን ይፈይዳል?" ብሎ ሲለው ባለ ሱቁም ሰውየው የነገረው ልክ መሆኑ በማመን "ትኩስ" የሚለውን ቃል ከቦርዱ አጠፋው። አሁን "እዚ አሳ እንሸጣለን!" የሚል ሆነ።

በሌላ ቀን አንዲት አዛውንት ወደሱቁ መጣችና "እዚ አሳ እንሸጣለን!" የሚለውን ጮክ ብላ አነበበችው። በመቀጠልም " ሌላ ቦታ ላይም አሳ ትሸጣላችሁ እንዴ?" በማለት "እዚ" የሚለውን ቃል እንዲያጠፋው ነገረችው። እናም አሁን " አሳ እንሸጣለን!" የሚል ብቻ ቀረ።

በሶስተኛው ቀን አንድ ደንበኛ መጣና "'አሳ እንሸጣለን'? እና ሌላ ቦታስ በነፃ ነው የሚሰጡት?" ብሎ በመጠየቅ "እንሸጣለን" የሚለውም እንዲያጠፋው ነገረው። አሁን "አሳ!" የሚል ብቻ ቀረ።
በሌላ ቀን አንድ በእድሜ ጠና ያሉ አዛውንት ሰውየ ወደ ስቁ መጡና "'አሳ'? አይነ ስውር ሰው እንኳ ከሩቅ በሽታ ብቻ እዚ አሳ እንዳለ ይለየዋል።" አለውና "አሳ!" የሚለው ቃልም እንዲያጠፋው ነገረው። አሁን ባዶ ቦርድ ብቻ ቀረቷል።

እናም በመጨረሻ አንድ መንገደኛ ወደ ሰውየው ተጠግቶ "ባዶ ቦርድ ለምንህ ነው የሰቀልከው? አውርደው!" ሲለው አወረደውና አሁን ባዶ ሆነ። እያንዳንዱ ቃል ከጠፉ በኋላ አሁን ባዶ ቀርቷል ምንም ነገር የለም።

ፍቅርም የሚመነጨው ከባዶነት ነው። ምንም ብቻ ነው ከምንም ጋራ ሊወሃድ የሚችለው። ዜሮ ብቻ ነው ከዜሮጋ ሙሉ በሙሉ ሊቀላቀል የሚችለው። ሁለት ባዶ የሆኑ ነገሮች ናቸው ሊገናኙና አንድ ሊሆኑ የሚችሉት። ምክንያቱም አሁን ምንም አይነት መሰናክል የለም። ከዚ ውጪ ያሉት ግን ወሰን አላቸው። ባዶነት ብቻ ነው ወሰን የሌለው።

ስለዚ በመቀጠል ማስታወስ ያለብን ነገር ፍቅር የሚመነጨው ግለሰባዊነት ሲጠፋ መሆኑን ነው። እኔና እነሱ የሚሉት ስናስወግድ ነው። አሁን ላይ የቀረው "እኔ" የሚለው ጠፍቶ "ሁላችንም" ነው። በዚህም ሁሉም አይነት መሰናክሎች ይወገዳሉ።

ጉድጓድ ስንቆፍር ውሃ እናገኛለን። ውሃው የሚወጣው ከየትም ሳይሆን ከቆፈርነው ጉድጓድ ነው። ከእኛ የሚጠበቀው አፈሩንና ድንጋዮቹን ዝቀን ማውጣት ብቻ ነው። ምንድነው ያደረግነው ያላችሁ እንደሆነ ባዶነትን ነው የፈጠርነው።

ምንጭ © :- Freedom - Rajneesh Osho



@phillosophy @phillosophy
@phillosophy @phillosophy
ዘላለማዊነት በፍልስፍና ሲመዘን
/ክፍል ፩/

📜📖📖📜

በፍልስፍናው ዓለም አንቱ ተብለው ታላቅ ከበሬታ እስከዛሬ ከሚቸራቸው ፈላስፎች አንዱ ፕሌቶ ነው ። " ከሞት በኋላ ሕይወት አለና ተፅናና " ቢሉት " እኔ ዘላለማዊ የምሆነው ገነት በመግባት ሳይሆን ምድር ላይ ትቼው በምሄደው ሥራዬ ነው " አለ ።

📖📖📖

ብዙዎች ከሞት በኋላ ሕይወት " በመኖሩ " ይፅናናሉ ። አንዳንዶች ደግሞ የለም ዘላለማዊ ሕይወት ብሎ ነገር የለም ይላሉ ፤ እንዲያውም በእንዲህ ዓይነቱ ሐሳብ ይሳለቃሉ ። ፊሮ የተባለው ፈላስፋ ደግሞ " እኔ የዘላለም ሕይወት ከሞትኩ በኋላ የማገኝ ከሆነ ውሻዬ ለምን ይቀርበታል? " ይላል " እንዲያውም በዘላለም ሕይወት መለኪያ ውሻዬ እንደ እኔ እያታልልም ፣ አይክድም ፣ አይሰርቅም ፣ አይዋሽም...ወዘተ..ስለዚህ ከእኔ ይልቅ በብዙ መመዘኛ ውሻዬ ለዘላለማዊ ሕይወት የተገባ ነው " ብሏል ።

📖📖📖

ብ ዙዎቹ ፈላስፎች የዘላለም ሕይወት አሊያም ከሞት በኋላ ሕይወት የሚለው ሃሳብ መሠረቱ ሕንድ እንደሆነ ይናገራሉ ። ቱስካሮራ የተባሉ የሕንድ ጎሳዎች " አንድ ሰው ሲሞት ሟቹ መልካም ሰው ከሆነ ወደ አንድ የመንፈስ ዓለም ይወሰዳል ፤ በዚያም የአደን አውሬ ታድኖ የማያልቅበት ዓለም ውስጥ ይገባል " ሲሉ " ሟቹ ክፉ ከነበር ደግሞ ምግብ ከሌለበት እባብ ከሚርመሰመስበት ዓለም ውስጥ ይወድቃል " የሚል ነው እምነታቸው ።

ከዚያ ቀጥሎ ግብፆች ይነሳሉ ። ጥንታዊ ግብፃውያን እዚህ የምንኖርበት ቤት ወደፊት (ከሞት በኋላ) ከሚጠብቀን ቤት ጋር ሲነፃፀር እንደ ትንሽ ጎጆ ነው ይላሉ ። ( ይኸ እንግዲህ አሁን በጎጆ ውስጥ የሚኖርን ሰው አይመለከትም ) !

📖📖📖

ከሞት በኋላ ሕይወት አለ የሚለው አስተሳሰብ ምንጭ ናቸው ተብለው የሚታመኑት ሕንዶች በሌላው የእምነት ክፍላቸው ደግሞ " ከሞትክ በኋላ ነፍስህ በሌላ ዓለም በድሎት ፣ ወይም በችግር ራሷን ችላ አትኖርም ፣ ነገር ግን እንደ ሰራኸው ሥራ በሌላ ፍጡር አካው ውስጥ ትገባለች እንጂ " ይላሉ ።...

ይቀጥላል...

/ ክፍል ፪ / ይቀጥል ዘንድ በንባብ አብራችሁን መሆናችሁን እቺን ( 📜 ) በመጫን አሳዩን
(15 📜 )ሲሆን ቀጣዩን እንለቃለን ።



@phillosophy @phillosophy
@phillosophy @phillosophy
👋ሰላም መንደዱ ላይቀር መጨሱ ይህ ከታች የላክንልዎ የእርሶ መለያ ቁጥር ነው ይህን ለ 25 ሰዎች በመላክ እና Start እንዲሉ በመጋበዝ የ 500 ብር የሞባይል ካርድ ተሸላሚ ይሁኑ።
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.tg-me.com/AwashBankRefferalBot?start=r0147902056

💞 መልካም እድል 💞
💎Awash Bank💎
ተገረም


ታላቁ ፈላስፋ አርስቶትል «ፍልስፍና የሚጀምረው በመገረም ነው» ይለናል። ይህ አስደናቂ ገለጻ ማንኛውም ተመራማሪ ዘንድ የግድ ሊኖር የሚገባ የህይወት ስንቅ ነው። በየቅጽበቱ ከሚለዋወጠው የዓለም ነበራዊ ሁኔታ ጋር እየተጋፈጠ «አግራሞት» በውስጡ የማይሰርጸው አካል አዲስ ነገር መፍጠር አይቻለውም። ውስጡን የጥያቄዎች ሱናሚ የማይንጠው ሰው ለህይወት የሚያበረክተው አዲስ ነገር ቅንጣት አይኖረውም።
.
.
«መገረም» በአራት ፊደላት ተዋቅራ የቆመች ቀላል ቃል ናት። ግና ጥልቀቷ መጨረሻ የለውም። አዋቂ ስለ አንድ ጉዳይ አሊያም ሥረ ነገር ምርምር ሲያከናውን ብዙ ይማስናል። አግራሞትን የሚያጭሩ ጥያቄዎች ይሰነዝራል። ከራሱ ጋር በሃሳብ ይፋለማል። እሰጣ ገባ ውስጥ ይገባል። ውስጣዊ ኃይሉን ያፈረጥማል። ይህን ወሳኝ ሂደት መሻገር ያልቻለ አዲስ ነገር ለማቅረብ ይሰንፋል። ኃይል ያለው ዕውቀት ላይ ነው። ዕውቀት ደግሞ የጥያቄዎች ውጤት ነው። ዕውቀት «ለምን?»ወይም «እንዴት?»የሚሉ ጥያቄዎች ህብር ፈጥረው ያመጡት ሐብት ነው። እነኝህ ጥያቄዎች ከህይወት መስክ ላይ ሲነጥፉ በሰው እና በአህያ መካከል የተሰመረው ድንበር ይጠፋል።
.
.
ጥያቄዎችየዕውቀት ሙዳየ ቃላት ናቸው። ጥርጣሬ የምርምር መወጠኛ መሳሪያ ነው። ቋሚ የሆነ ዕይታ የማሰላሰል መክፈቻ ቁልፍ ነው። ዘውታሪ የሆነ ንባብ የማይቋረጥ ስጦታ ነው። ስለዚህ አይምሮ የማይቋረጥ ጥያቄ ሊያመነጭ ግድ ይለዋል። እንዲሁ በጭፍኑ እጅ ከመስጠት ጥርጣሬን ማስቀደም ይሻላል። የህይወትን ሙሉ ገጽታ ከብዙ አቅጣጫዎች ለመቃኘት ጥልቅ እና ተከታታይ ንባብ ወሳኝ ነው።
.
.
ሁሌምጠያቂ ሁን። የሆነ ቀን ፈላስፋ ትሆናለህ። በሃሳብ የሚናጥ ማንነት አዳብር። አንድ ቀን አዋቂና አሰላሳይ ትሆናለህ። ሕይወትን ከብዙ ማዕዘናት ለመመልከት ጥረት አድርግ። የሆነ ጊዜ የፈጠራ ሰው ትሆናለህ። ሁሌም የማይጠግብ አንባቢ ሁን። አንድ ቀን በህይወት ውስጥ ለሌሎች እንደ ኦክሲጂን አስፈላጊ ትሆናለህ።
.
.
አይምሮህንስርዓተ-ትምህርት ብቻ እያነበቡ የህይወት ዘመናቸውን ለሚገፉ ታካች ምሁራን አታስረክብ። እነርሱ የወጡት ከሁሉ አቀፍ መሃይምነት ወደ ከፊል መሃይምነት ነውና። የሚኖሩት ባለፈው ዘመን ንቅፈ ክበብ ውስጥ ነው። ዕውቀት ከልደት እስከ ሞት መሆኑን ዘንግተዋል። የህይወት ጥያቄ ማሳረጊያ እንደሌለው ረስተዋል። አውቃለሁ ብሎ ያሰበ በርግጥም አላወቀም።
.
.
ፍልስፍና«ሐራም» ነው የሚልህን ሰው ጆሮ አትስጠው። ምክኒያቱም ምኞቱ የርሱ የምንግዜም ተማሪ ሆነህ አራት በአራት ክፍል ውስጥ ወሽቆ ማስቀመጥ ነውና። ፍልስፍና ያልታየን ነገር መመርመር ነው። የተሸፈነን ነገር ለመግለጥ ማሰብ ነው። ግና በምን መልኩ መያዝ እንዳለብህ የግድ መማር ይጠይቃል። ፍልስፍናን እንዴት ማስተናገድ እንደምትቸል ጠንቅቀህ ማወቅ ሳትችል ዘው ብለህ አትግባ። ለመማርም አታንገራግር። ፍልስፍና እንደ ውቅያኖስ ሰፊና ጥልቅ ዓለም ነው። በዳርቻው ጥርጣሬን ብታገኝም በጥልቀቱ ምቾትን ትጎናጸፋለህ።
.
.
የውስብስብጉዳዮችን ድርና ማግ ፈትተህ ይበልጥ ለማወቅ ያስችልህ ዘንድ ሁሌም «የሚገረም» ሰው ሁን። በተወሳሰበ የህይወት ተጨባጭ ፊት ተራ ሰው አትሁን። መገረም የሌለውና ድግግሞሽ የበዛበት የህይወት እንቅስቃሴ ከመምራት ተቆጠብ። የህይወትን ሚስጢራት በመገረም እንጂ እንዲሁ ማወቅ ከቶም አይቻልም። አርስቶትል «ፍልስፍና በመገረም ይጀምራል» ሲል ምንኛ እውነትን ተናገረ !!!
.
.
መገረምከሌለ ስልቹ ትሆናለህ። ለሰዎች አስተሳሰብ እጅ ትሰጣለህ። የሚባለውን ሁሉ ታምናለህ። የሰጡህን ትቀበላለህ። ያጎረሱህን ወሬ ታመነዥጋለህ። መገረም የሌለበት ህይወት አይነቱ አንድ ነው። አዲስ ነገር የሚባል አይኖርም። እድገትና ለውጥ አይታሰብም። ግርምት አልባ ከሆንክ የአስተሳሰብ ጀብዱ ከውስጥህ አይኖርም። አንተም ሆንክ ማሰብ የማይችለው ፍጡር አንድ ትሆናላችሁ። አይምሮ የተፈጠረው ለመገረም እንጂ እጅ ለመስጠት አይደለም። እናም ተገረም !!!
የታየህን ያህል ተንቀሳቀስ

አንድ ምሽት ላይ አባት ልጁን ወደ ሲኒማ ቤት ሊወስደው ውጪ መንገድ ላይ መኪና ውስጥ እየጠበቀው ነው፡፡ ልጅ ከቤት እንደወጣ በጣም ስለጨለመበት ስልኩን አውጥቶ አባቱ ጋር ደወለ፡፡

• ልጅ፡- “አባዬ እንዴት ልምጣ? ጨለማ ስለሆነ አይታይም”፡፡
• አባት፡- “ምን ያህል ይታይሃል?”
• ልጅ፡- “አምስት እርምጃ ያህል ብቻ ነው የሚታየኝ”
• አባት፡- “አምስት እርምጃ ተራመድ”
• ልጅ፡- “እሺ” (አምስት እርምጃ ተራመደ)
• አባት፡- “አሁንስ ምን ያህል ይታይሃል?”
• ልጅ፡- “አሁንም ሌላ አምስት እርምጃ ያህል ርቀት ይታየኛል”
• አባት፡- “በፊትህ የሚታይህን አምስት አምስት እርምጃ እያልክ ከመጣህ እኔ ጋ ትደርሳለህና የታየህን ያህል ተንቀሳቀስ”

ልጅ ብዙም ሳይቆይ አባቱ ጋር ደረሰ፡፡

ሁሉም ነገር ጥጉ ድረስ እስኪታይህ አትጠብቅ፡፡ በሚታይህ መጠን ተራመድ፡፡ የሚታይህን ያህል ስትራመድ፣ ከመራመድህ በፊት ያልታየህን ማየት ትጀምራለህ፡፡

ሁሉንም ነገር እስከምታውቅ አትጠብቅ፡፡ በምታውቀው ልክ ስራን ጀምር፡፡ በምታውቀው እውቀት መጠን ስራን ስትጀምር፣ ያንን ከመጀመርህ በፊት ያልነበረህ ልምድና እውቀት ወደ አንተ ይመጣል፡፡

ሁሉም ሰው እስኪቀበልህ አትጠብቅ፡፡ የሚቀበሉህ ላይ በማተኮር ተሰማራ፡፡ በሚቀበሉህ ላይ ስታተኩርና ደስተኛ ስትሆን፣ ቀድሞ የማይቀበሉህ ሁሉ አንተን ከመቀበል ውጪ ምርጫ አይኖራቸውም፡፡

የጠየከው ነገር ሙሉ በሙሉ እስኪሰጥህ አትጠብቅ፡፡ የተሰጠህን ተቀበልና በዚያ በመጀመር የምትችለውን አድርግ፡፡ በተሰጠህ በጥቂቱ የምታደርገው ጥረትና የምታከናውነው ነገር የቀረው እንዲለቀቅልህ መንገድ መክፈቱ አይቀርም፡፡

አትቀመጥ! የታየህን ያህል ተንቀሳቀስ!
#ስሜት_ፍላጎት_ንዴት
➷➷➷➷➷➷➷➷➷➷
ስሜት ጨለማን እንደሚገልጥ ብርሃን ነው።
ብርሃኑን ተከትለን ብዙ ነገሮችን ስለማየት እንቀላዉጣለን ብርሃኑ ባይኖር ግን አይናችን ማየት ስለማይችል ሀሳባችን ይሰበሰብ ነበር። ስሜታችንም በዙሪያው የሚቀርባቸውን ፍላጎቶችና ክስተቶች መሰረት አድርጎ በውስጣችን የሚጭረዉ ያልተመጠነ እሳት ለንዴት ይዳርገናል።


#የስኬት_ፈለግ_ቁጥር-1 ገጽ 23
ዝግጅት:- መሀመድ አሊ(ቡረሃን)
መጽሐፍ ቤት:
     “ጥያቄ አብራክ ነው፤ መፍትሄ የሚወልድ”
                            
              መቼም ይህች ዓለም ፈጽማ ”እፎይ ጨረስኩ!“ ያለችው አንድም ነገር የለም! ያልተፈጸመ ነገር ካለ ሁሌም የሚጀመር ነገር አለ፤ መጀመሪያ ምሳችን ጥያቄ ነው። በእርግጥ ጥያቄ  መልስ ዓልባ ሊሆን ይችላል። ግን አሮጌ የዘመን ብራና ታጥፎ ሌላ አዲስ የዘመን ብራና ሲዘረጋ ጥያቄው መልስ ያገኛል። ገጣሚው እንዳለው፤ አንኳኩ ይከፈትላችኋል፤ ስትገቡ ሌላ በር ይጠብቃችኋል። ጥያቄ ሌላ ጥያቄ ይወልዳል። በጥያቄው መልስ መፍትሄ ይፈተልበታል፤ መፍትሄው የችግር እንቅርት በአንገቱ ማንጠልጠሉ አይቀርም፤ ችግሩ በድጋሚ ጥያቄ ያነሳል። እንዲህ እንዲህ እያለ ዘመን፤ጥያቄ እንዲሁም መፍትሄ በአንድ ተሿርበው፤ የነተበ ቀን ሌላ አዲስ ቀን እየለበሰ፤ ሰውን ሞት የሚሉት የመቃብር አፍ እየበላው፤ ትውልድ በሌላ ትውልድ እየተተካ እዚህ ደርሰናል።
ሰው ያሰበውን ሃሳብ የሚንዱ፤ሰውየውም በተናደው ሃሳቡ ብዙ ሳይቆዝም፤ ሃሳብ ለመካብ ሌላ የሃሳብ ዲንጋ የሚሰጡ መጽሐፎች በገበያ ላይ ለዓይን እንኳ ብዙም አይታዩም፤በተለይ ባለፉት ጥቂት ወራት አዲስ የፍልስፍና መጽሐፍ በገበያው አልነበረም ማለት ይቀላል። ከሰሞኑ የሕትመት ብርሃን ያየው የፍሬው ማሩፍ “ጥያቄዎቹ” የተሰኘው መጽሐፍ በገበያ ላይ መዋሉ ለተደራሲው ዘርፈ ብዙ ጥቅም ይኖረዋል ብዬ አስባለሁ፡፡ እኔም ገበያ ላይ ሳየው በፍጥነት ነበር የገዛሁት፡፡ መጽሐፉ በሦስት ክፍሎች በአንድ መቶ ዘጠና አንድ ገጾች ተቀንብቧል። የሽፋን ምሥሉ በሠዐሊ ዮናስ ሞገስ ሳይወሳሰብ፣ ለተደራሲ በሚማርክና ትርጉም በሚሰጥ መልኩ መሰራቱ አንብቡኝ ብሎ በዝምታ እንዲጣራ አድርጎታል፡፡ በሦስቱም ክፍሎች ከጥንት ጀምሮ እስካሁን ለፈላስፎችና ለአሳቢያን (Re-Thinkers) አልፈታ ያሉ ሦስት ቁጥርጥሮችን ሰውን፣ ፈጣሪንና ሰይጣንን ከፈላስፎች፣ ከጥናቶች፣ ከሃይማኖት ድርሳናት ሃሳብ እየተዋሰ የራሱንም ሃሳብ እያከለ፤ሌላ ‘ጥያቄ’ መልሶ እያጫረብን በሚስብ መልኩ ይዳስስልናል፡፡  
“ጥያቄ?”
የዓለም ስልጣኔ የተገነባው ነፍሳቸውን ከልባቸው በጥያቄ አሟግተው፤ ከውስጠ-ሕሊናቸው ለችግር ሐቃዊ መፍትሄ ባመነጩ ሰዎች ነው። መነሻው ግን ጥያቄ ነው። ቶማስ ኤዲሰን ዓለም ለምን ጨለማ ሆነች? ብሎ በመጠየቁ አምፖል ተሰራ፤ ኤለን መስክ ለምን በኤሌክትሪክ ሃይል የሚሰራ መኪና አልተሰራም? ብሎ ሲጠይቅ፣ በኤሌክትሪክ ሃይል የሚሰራ መኪና ተሰራ፤ ጥያቄ አብራክ ነው። መፍትሄን የሚወልድ ጥያቄ እንጂ ሌላ ነገር ለችግር መፍትሄ አይሆንም፤ ነፍስ ከሥጋ ከተለየ ሥጋ እንደሚበድን፤ ጥያቄም በራሱ አዕምሮን እንደ ወርቅ በእሳት ፈትኖ ለችግር መፍትሄ ካልሆነ፤ ‘ጥያቄው’ በድን ይሆናል። ለመሆኑ የችግርና የችጋር ጥቁር አሞራ መንቆሩን ቁልቁል ዘቅዝቆ ጫጩት አቅማችንን ሊጠቀጥቀው በሠማያችን አንዣቦ፥ ስልጣኔ እንደ ምጽዐት ቀን ‘ርቆን፣ ለምንድነው የማንጠይቀው?
አመክንዮ (1)
ሥርዓተ-መንግስታቶቻችን በፊትም አሁንም ‘ሰውነትን’ ባለማስቀደማቸው በሚፈጥረው ውጥንቅጥ ሰበብ ሕዝብ በፍርሃት ጥርስ ሲላመጥ፣ሰላም ለዓይኑ እንደ ቅድቡ ሲርቀው፣ የብሔርተኝነት እሳቤ የወለዳቸውን ሕይወት ዓልቦ ሐሳቦች እንደ ጡብ እየጠፈጠፈ፤ አንሶ በሥጋት እየኖረ፣ ሕዝብ ከልዕለ-ተፈጥሮ ጋር በጥያቄ ለመቆራኘት እንዴት ይቻለዋል?
አመክንዮ (2)
የሐይማኖት አባቶች እውነት በርዷቸው፤ ከሐሰተኛ ትምህርት ጋር ተቃቅፈው፤ ሕዝብን አሜን! አሜን! እንጂ ለምን ለምን? አትበል እያሉት፣ እንዴት ነው የእምነቱ ተከታይ የሆኑት ምዕመናን ጠያቂ የሚሆኑት? ምን እውቀት አለና? ምን እምነት ይኑር? ሁሌ ሳስታውሰው የሚያስፈግገኝ አንድ ቀልድ አለ፤ ቄሱ የዲያቆኑን ሚስት ያማግጡ ኖሯል። በዚህም ሰበብ ቄስና ዲያቆን እልህ ተጋብተዋል። ታዲያ አንድ ዕለት ሥርዓተ-ቅዳሴ እየከወኑ ጽጌ ብሩ (የዲያቆኑ ሚስት) አለፍ ትላለች፤ ይህን ጊዜ....
ቄሱ :-”ጽጌ ብሩ ያዩሽ ሁሉ ደነበሩ!” ይላሉ
ዲያቆኑም:- “መምሩ ያዩትን ሁሉ አይምሩ” ብሎ ተቀበላቸው
ቄሱ በንዴት:- “ምናባህ ታመጣለህ፣ ታራለህ፣ ትደብናለህ፣ ከሥራህም ትባረራለህ..." ሲሉ፤ መቅደስ ውስጥ የነበሩት አስቀዳሽ ምዕመናን አንድ ላይ አሜን! አቤቱ ይቅር በለን! አሉ ይባላል። ለምን? ያላለ ሕዝብ እንደ ሲሲፈስ መግፋት የማይገባውን የመከራ ዲንጋይ እየገፋ አሜን! አሜን! እያለ ጣዕም ያጣ ሕይወት ይኖራል። የሐይማኖት አባቶችም ለምዕመኑ ለነፍስ የሚሆኑ፤ ጣፋጭ መንፈሳዊ ፍሬዎችን መመገብ ሲጠበቅባቸው፤ የምዕመናኑን ጥያቄ በአግባቡ ማስተናገድ ሲኖርባቸው፤ ግን አማኙን ያለማሕተብ በክር ብቻ እራቁቱን አስቀሩት፤ መገን እንጂ ሌላ ምን ይባላል? “በጥያቄዎቹ” ድርሳን ላይም በገጽ አንድ መቶ ሰማኒያ ሦስት ላይ ይህ ሃሳብ በስፋት ተዳስሷል።
አመክንዮ (3)
የዩኒቨርሲቲ መምህራን (ምሁራን) ስለ ሃሳብ ነጸነት፣ ስለ መጠየቅ ጥቅም፤ ለተማሪዎቻቸው አላስተማሯቸውም፤ ተማሪዎቹም የቱ እውነት? ከማለት ይልቅ ይህ ወገንህ አይደለም፤ የሚለው የውሸት ትርክት ከደም ሥራቸው ይቀርባቸዋል። ‘የሆነ ቦታ ላይ ያለው የትምህርት ተቋም ውስጥ ረብሻ ተነሳ’ የሚል ወሬ የጆሯችን ነፍስ ደጋግማ ሰምታለች፥ በዚህም ሰበብ ተፈጥሮ በነጻ የሰጠቻቸውን የመጠየቅና የመመራመር መብት ወደ ጎን ትተው፤ ‘ለአለማወቅ’ ቅኝ ለመገዛት ሲጓዙ እናያለን፤ በዚህ ድርሳንም በገጽ አስር ላይ “መማር እንዲህ ከሆነ ቢቀርስ” በሚል ርዕስ ሥር፣ የትምህርት ሥርዓታችን የገጠመውን ሳንካ ገልጦ፤ መፍትሄ ጠቁሞ ገጹን ወደ ሌላ ሃሳብ አጥፏል። ወደ የትም ጉዞ ከመጀመራችን በፊት የትኛው መንገድ የእውነትና የእውቀት መንገድ ነው? ብለን መጠየቅ ይኖርብናል። “የዩኒቨርሲቲ የፍልስፍና የትምህርት ክፍል መምህር ናቸው። ለተማሪዎቻቸው የቤት ሥራ ሰጡ፤ የቤት ሥራው ክፍል ውስጥ ያለው አንድ ‘ነጠላ ወንበር’ እንደሌለ በአመክንዮ ማስረዳት ነበር፤ በማግስቱ የቤት ሥራው ሲታረም፥ ብዙ ተማሪዎች ‘ወንበሩ’ ስላለመኖሩ የሚያስረዳ ብዙ ገጽ ጽፈው መጥተዋል፤ አንድ ተማሪ ግን አንድ መስመር ነበር የጻፈው፤ መልስም የሆነው ይህ መስመር ነው። መስመሩም “የቱ ወንበር?” ይላል። ‘ጥሩ ጥያቄ ሌላ ጥያቄ ቢፈጥርም ለጥያቄው መልስ ይሆናል’ መምህራን ተማሪዎቻቸውን ‘የቱ እውነት?’ ብለው እንዲጠይቁ ካላደረጓቸው፤ የቀጣይ ትውልድን ነፍስ የሚቀጣ የእሳት አለንጋ ትተን ማለፋችን አይቀርም!
(4 ‘አለመሰልጠናችን’)
ክቡር ዶክተር ከበደ ሚካኤል “ስልጣኔ ምንድናት?” በሚለው ድርሳናቸው፣ ስልጣኔን በሁለት ይከፍሉታል። የመጀመሪያው ‘ሰው’ ከግብረገብነቱ አንጻር ስልጣኔው ይፈከርለታል። ይህም ሲባል በትህትናው፣በርሕራሄው፣መንፈሰ ሰፊ ልብ ከያዘ ሰለጠነ እንላለን (ገጽ ሃያ) በአንጻሩ ክፉ፣ትዕቢተኛ፣ጨካኝ ሲሆን ደግሞ ያልሰለጠነ ነው እንላለን፤ ሌላው የስልጣኔ ዐይነት ግዙፉ ብለው ይጠሩታል። ይህ ሲባል “በአለባበሱ፣ በአመጋገቡ፣ በኪነ- ጥበብ፣ በኪነ ሕንጻ ማህበረሰብ ሲሰለጥን እንደ ስልጣኔ ማስረጃ ይሆናሉ” ይላሉ። አንድ ጸሐፊ በአንድ ወቅት እንዲህ ብሎ ሞግተው ነበር፤ ክቡር ዶክተር ከበደ ሚካኤል “ጃፓን እንደምን ሰለጠነች?” ብለው ከሚጽፉልን ይልቅ “ኢትዮጵያ ለምን አልሰለጠነችም?” ብለው ቢጽፉልን ለስልጣኔ ጉዟችን ማመላከቻ ካርታ ይሆነን ነበር ይላሉ። ልክ ናቸው ከለምን? የተነሳ ትውልድ፣ የልቡናውን መቅለዝ “በጥያቄ” ዘይት ከሞላ በዳልቻ መደብ የመጽሐፉ ሽፋን ላይ እንደተሳለው የመጨረሻ ፋኖስ ለጨለማው ዘመኑ
ብርሃን መሆን

ባይችል፣ ለቀጣዩ ዘመን የተስፋ ብርሃን መርጨቱ አይቀርም!
“ሰው!”
ሰው ፍጠር (ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ) አወዛጋቢው ፈላስፋ ዲዮጋን በቀን ፋኖስ ይዞ ሲንከራተት ሰዎች አይተው ምን ጠፋህ? ቢሉት ሰው እየፈለግሁ ነው። ብሎ መለሰላቸው ግን ሰው ምንድነው? ሰው የሚባለው ፍጡር ቅዠት እንዳልሆነ ምን ተጨባጭ ማስረጃ አለን? የሚሉም አሳቢያን ተነስተው ነበር፤ ቢሆንም አለሁ የለሁም ብሎ መጠየቁ በራሱ “እንዳለን” ማስረጃዎች ይሆናል፥ የሚሉ አሳቢያንም አሉ፤ በእርግጥ ይህንን ውትብትብ ጥያቄ ለመመለስ ፈጣሪ መሆን ይጠበቅብናል ይመስለኛል። ቢሆንም የሰውን ምንነትና አፈጣጠር ከሐይማኖት ድርሳናት፣ አቧራ ከጠገቡ ከፍልስፍና መዛግብት አቧራውን እፍ እያልን ከሆነ ንጻሬ መተንተን እንችላለን፡፡ “ጥያቄዎቹ” ላይም ፍሬው ከገጽ 18-39 ድረስ “ሰው እንዴት እና ከምን መጣ?” የሚለውን ጥያቄ ከተፈጣሪነት ጽንሰ ሃሳብ (Creationism Theory) አንጻር ቅዱስ ቁርዐንንና ቅዱስ መጽሐፍን እያጣቀሰ፣ ከዝግመተ ለውጥ (Evolution Theory) አንጻር፣ ብሎም ከላምራክ ጽንሰ ሃሳብ አንጻር (Theory of lamarck) “ሰው እንዴት ተፈጠረ?” ለሚለው ጥያቄ የመልስ ሕብስት ጋግሮልናል። ነፍሳችን የሚጠግባትን መርጦ መመገብ የኛ ፋንታ ነው። እንደው ሃሳብ ወዳዶች ከሆንንና ረቂቅ ነገሮችን የመመርመር ፍላጎቱ ላለን ሰዎችም ስለ ነባቢት፣ልባዊት፣ሕያዊት ነፍስም ጥልቅ ትንታኔ አስቀምጦልናል (በገጽ-40-45)፡፡ ፍሬው ጥልቅ ንባብና አረዳድ አለው፤ በአጸደ-አዕምሯችን የሚመላለሱብን፣ፈራ ተባ እያልን ችላ ያልናቸውንም ሃሳቦች አልማራቸውም፤ ሞትን፣ በተለይ ራስን ስለ ማጥፋት በዚህ ጉዳይ የዓለምን በእጅጉ ተጨንቃለች፤ ብዙ ሕዝብም እንደ ቅጠል እያረገፈ ነው።  የወለፈንዲ ፍልስፍና አቀንቃኙ አልበርት ካምዩ ስለ ራስ ማጥፋት እንዲህ ይላል፡- “በመጨረሻም ሰው ራሱን ከመግደል፥ በበለጠ ለመኖር ጽናትን ሊያዳብር ይገባል።” ፍሬው ፈላስፋውና የሙዚቃ ባለሙያው ኤልያስ መልካ ስለ ራስ ማጥፋት አሉታዊነት የገጠማቸውን ግጥሞች በጥቂቱ አብራርቶልናል። (ገጽ-61)..አለፍ ሲልም የሰውን ተፈጥሮ ምንነት ይዳስሳል።  
ፍጥረት ከመፈጠሩ በፊት ያለው የወደኋላ ዘለዓለም እና የወደፊት ዘላለም በሰው የንቃተ ሕሊና ደረጃ ምን ሊባል ይችላል? ምንም ባለመባሉ ሰበብ አሁንም ድረስ ስለ የፈጣሪ ኅልዮት ብዙ ያጨቃጭቀናል። ታዲያ ፍሬው ከተለያየ አንጻር በምልከታውም በሌላም ሃሳብም ላቅ አድርጎ አንጽሮልናል። ሰይጣንም ሳይጎረብጠኝ ምንና ከየት እንደተነሳ በቅጡ አወቅሁ፡፡ “ጥያቄዎቹ” ወርቅ አዕምሮዬን በሃሳብ እፈትናለሁ የሚል ሁሉ ሊያነበውና ራሱን በሃሳብ የቱ ጋ ነኝ ብሎ ሊፈትሽበት የሚገባ መጽሐፍ ነው፡፡

ምንጭ:-Adisadmas.com
@metsihafbet
🎉 የ 10,000 ብር ቦነስ ስጦታ ለቴሌግራም ተጠቃሚዎች ይፍጠኑ አሁኑኑ ቦቱን በማስጀመር አሸናፊ ይሁኑ 🎁

🎁  የ 2022 የአለም ዋንጫ አዘጋጅ ኳታር የአለም ዋንጫ መረጃዎች የምትለቅበትን የቴሌግራም ቻናል ለብዙዎች  ተደራሽ ለማድረግ በማሰብ ቻናሉን ለሚቀላቀሉ በሙሉ የ 10,000 ሺህ ብር ቦነስ አዘጋጅታለች 🤑🤑

📉 የአለማችን ቱጃር የአረብ ሀገር የሆነችው ኳታር በዘንድሮው የአለም ዋንጫ ላይ ከ 220 ቢሊዮን ዶላር በላይ በማውጣት የአለማችንን በአይነቱ የመጀመርያውን ዘመናዊውን ስታድየም በመገንባት የአለም ዋንጫውን አስጀምራለች!!

🎁 በዚህም የኳታር መንግስት ለኢትዮጵያ እና ለሌሎች 8 የአፍሪቃ ሀገራት ከ 20,000,000 ብር በላይ በመመደብ ዜጎች ስልኮቻቸውን ( ቴሌግራማቸውን) ብቻ ተጠቅመው ወደ አለም ዋንጫው የቴሌግራም ገፅ በመግባት ወይም ሌሎች ወዳጆቻቸውን ወደ ገፁ ሲጋብዙ ተሸላሚ የሚሆኑበትን መንገድ አዘጋጅቷል!!

🗝 ማብራርያ

1/ ከስር ያለውን ሊንክ በመንካት  ቦቱን ሲያስጀምሩ  10,000 ብር ማስጀመርያ ቦነስ ወደ አካውንቶ ገቢ ይሆናል👇👇
https://www.tg-me.com/Qatar_WorldCup2022Bot?start=r0240892782 https://www.tg-me.com/Qatar_WorldCup2022Bot?start=r0240892782

2/ በመቀጠል  ቦቱ ላይ ካሉ ምርጫዎች መሀል '' የኳታር አጋር ለመሆን '' የሚለውን ምርጫ በመንካት የሚመጣልዎን መልዕክት ለወዳጅ ዘመድዎ በማጋራት 1 ወዳጆ በእርሶ ግብዣ ቦቱን መጠቀም ሲጀምር እርሶ ተጨማሪ 500 ብር ያገኛሉ !!

ማሳሰብያ የክፍያ መንገድ :- በቴሌብር እና በ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ !!

መልካም ዕድል በቀን እስከ 50,000 ብር ድረስ ማውጣት ይችላሉ!!
2024/04/29 08:52:27
Back to Top
HTML Embed Code: