Telegram Group Search
ፀፀቴ

ቀልደኝነቴ በዝቶ ቁምነገሩን እንዳላስተውል አደረገኝ ሳቄ በዛና ሰዎች የሚስቁ እየመሰለኝ ነገሩን ዘለልኩት

እኔ ሳይገባኝ ጥልቅ ሆነህ አፍቅረኸኝ ነበር...... እኔ ሳልረዳህ ብዙ ታመህ ነበር በግልጽ ነግረኸኝ አለመጠርጠሬ እንጭጩ ጭንቅላቴን ጠላሁት..... ሁሌም የሚሆነውን ነበር የምትነግረኝ እኔ ግን ሳይገባኝ ሳቅኩበት

እኔ ስነቃ ግን ሁሉም አለፈ....አንድ ነገር ብቻ ተረዳሁ በልቤ ስፈልግህ ያጣሁክ በጭንቅላቴ የአገኘሁክ ፀፀቴ ነህ።

ኦኒ

@yeneta27
Forwarded from ♡...abisinian children's___ የአቢሲኒያ ልጆች...♡ (Ŏńĩ.........ťÿpĩŋğ)
ያጠፋህ መስሎዋቸው እኮ ነው ፤ሰድበውክ 😜 አንቋሸውክ😏 ፤አትረባም😎 አትደርስም ፤አትችልም😏 ምክንያቱም አታውቅም 🙈ብለውክ ወድቀህ ሲያዩ ስቀው 😂ተሳልቀውብክ 😝፤እንደ ትንኝ ሲረግጡህ😫 ይበልጡን ስትወድቅ ፤እንደሞተ ትተውክ ሲሄዱ .......🚶🚶🏃🏃

የደማው ልብክን ተሸክመክ ተነስ በቀስታም ተራመድ 🚶🚶ያንተ ተስፋ በፈጣሪ ነውና በጉዞክ አታመንታ የተገፋከው ስለእውነት ነውና አትሽሽ በስቃይክ ተደሰት ባለማወቃቸው ሳቅባቸው 😂 በዝምታክ አሸንፋቸው 🙊ባንተ ዝምታ ፈጣሪክ ይናገራልና 🙏..........ግን ሽንፈታቸውን ለመደበቅ አንተን መኮርኮም ይጀምራሉ ።ኮርኩመውክ፣ኮርኩመውክ ፣ኮርኩመውክ ፣ከርክመውክ፣ከርክመውክ፣ከርክመውክ፣ከርክመውክ ትልቅ 👼ሰው ያደርጉሀል
💝 ብቻ ከፈጣሪ ጋራ ሁን 🙏
Forwarded from የፍቅር ተራ💞 (Ŏńĩ.........ťÿpĩŋğ)
ፍቅሮችዬ
ወዳጄ ሆይ
ጓደኝነት ከደም ትስስር በላይ ሀይል አለው ። በጓደኝነት ውስጥ የነፃነት ገደብ የፍራቻ ወደብ የለም። የመሰለክን ሀሳብ የመግለፅ ስልጣን አለህ። መልካም ጓደኛ መጥፎ ጎንህን ሳይሸሽግ ይነግርሃል በጥሩ ጎንህ ላይም ያበረታታሃል። በጥሩ የጓደኝነት መረብ ላይ ምቀኝነት፣ቅናት፣ሀሜት ብሎ ነገር የለም። አንተ አቅም ባይኖርህና የጓደኛህ ችግር በጥቅም መካፈል ባትችል በሀሳብ ከጎኑ ሆነህ አብሮነትህን ታሳያለህ። በጥሩ ጓደኝነት መስፈርት በገንዘብ መረዳዳት የጥሩነት ጥግ አይደለም ይልቁንስ ጓደኛህ ሰው ቢሸሸው፣አደጋ ቢደርስበት፣በህመም አልጋ ላይ ቢውል ከማንም በፊት አጠገቡ መገኘትህ ነው የጓደኝነት ጥግ 😘
ቸር ዋሉልኝ🙏
ልክ ነው
"የሰው ልጅ እኔ እንደማስበው ያስባል አትበል
እኔ ብቻ ትክክል ነኝ አትበል አስተውል ሁሉም ሰው በራሱ ሚዛናዊ አስተሳሰብ ልክ ነው ።"
💝ሁሉም ሰው በራሱ ልክ ነው🤔
@yeneta27
በቅርብ ቀን ይጠብቁ ውድ የፍቅርና ጥበብ ቤተሰብ አባላት #የሐሳቤ_ስዕልንም ማንበብ ጀምሬያለው ስጨርሰው እጀምረዋለው ያኔ ቤታችንን እናደምቀዋለን።በመሐል አንዳንድ ግጥሞቼን ይዤ ብቅ እላለው።በጉጉት እየጠበቃቹ ያላችሁ እንዳላቹ አውቃለው።ለሱ እክሳለው።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
መልካም በዓል ይሁንላቹ
#ይቅርታ_ልበልሽ

አጣሁ ብዙ ነገር ስለይሽ የዛኔ
አሁን ነው የታወቀኝ ሲበዛ ሀዘኔ
እንባዬ ይወርዳል ከደጅሽ ለመቆም
ይቅር ልበልና ልውደቅ ከፍቅር አለም

ከእጄ እያለሽ ጥዬ ብቆጥር እንደ መዳብ
ዛሬ ከኔ ባትሆኝ ቆጨኝ ከሰው ሆነሽ ማሰብ
ይቅርታ ልበልሽ ውሃ ሆኜ ላፅዳሽ
ቆጭቶኛል ዛሬ ስትርቂኝ ላላይሽ

መልካም ሴት ሲፈጠር አንደኛ ብትሆኝም
በኔ ስህተት ድሮ ክብርሽን ብታጪም
አሁን ማሪኝ ፍቅር ይቅርታ ልበልሽ
ይታጠብ ጥፋቴ በይቅር ባይ ልብሽ

ሰው ሲመስለው ስራው ትክክል ነኝ ይላል
እኔም መስሎኝ እንጂ የሰራሁት ስራ ቅያሜን አጭሯል
ቢገባኝም ረፍዶ አልቀረሁም ደጅሽ
ማሪኝ አጨክኚ ተንበርክኬ ከእግርሽ ዛሬም ልለምኘሽ

ዝም አትበይ ተቆጪ ደረቴንም ምቺ
ጥፋቴ ቢሰረዝ ይቅርታዬ ባንቺ
ስደት ወቷል ልቤ አንድ ነገር አሞት
ይቅርታሽን ሽቶ ለመዳን ከፀፀት

ወዴ......
ይቅር አትይኝም በቃ እኮ አመመኝ
ጥፋቴ ገብቶኛል እንታረቅ በይኝ
ናፈቀኝ ጠረንሽ ልረሳው አልቻልኩም
ካንቺ ፍቅር አለም መንጎድ አላቆምኩም

ታሞ ያልዳነ ሰው ሞቱን ይመርጥና
ተስፋ ቆርጦ ሲኖር በሱ ይማርና
ተመስገን ይለዋል አይኑን ያቀናና
እኔም ከታመመው በምን እሻላለው
ከእግሮችሽ በታች ይቅር ልል ወድቃለው
ተነስ እስክትይኝ እጠብቅሻለው
ይቅርታ አርገሺልኝ ላቅፍሽ ቸኩያለው
#ይቅርታ_ልበልሽ ማሪኝ አጥፍቻለው

ሲሳይ አሰፋ (የኔታ)
አዳማ ኢትዮጵያ
25/09/13
☆꧁༒☬🆂 🅸 🆂 🅰 🆈 ☬༒꧂☆
ይሄን ቻናል ከሞት የሚታደግ ሰው ጠፋ ማለት ነው????? በጣም ይወደድ ነበር አሁን ግን እንዴት ወደቀድሞ ሁኔታው ይመለስ አቃተኝ ከበደኝ????
Forwarded from ስለእኛ በጎ ፍቃደኞች ማህበር (መገርሴ)
ሰላም ቤተሰብ 🤗🤗🤗


እንኳን ለፋሲካ በዓል በሰላም አደረሳቹ ።
በዓሉን ምክንያት በማድረግ የእጣ ፕሮግራም እንደነበር ይታወቃል ገቢውም ነዳያን እንመግብ ብለን ቀጠሮ ይዘናል እነሆ ቀኑ እየተቃረበ ነው ሚያዝያ 23 ለሶስተኛ ግዜ #እኔስ ለእናቴ በሚል መሪ ቃል እንመግባለን ።
ቅዳሜ ሚያዚያ 23 በወረዳ 9 ሁላችንም ለምገባው የሚሆን ስራ ስላለ መታቹ እንድታግዙ ስንል በትህትና እንጠይቃለን።


ከሁለት ሰአት ጀምሮ እንድትመጡ


ለምገባ የሚያገለግሉ
*ሽንኩርት
*ዘይት
*ምስር
*ቴምር
*በርበሬ
*ድንች
*ዱቄት
*ካሮት ወዘተ መስጠት ለምትፈልኩ
0986343222 ላይ መደወል ይቻላል

በአካውንት ለማስገባት ABDI HUSSEN AND MEGERSE GULILAT AND MESELU DAMTEW

01320771345600
አዋሽ ባንክ

እንዲሁም 👇

ስለእኛ በጎ ፈቃደኞች ማህበር

1000448224108
ንግድ ባንክ


#ሁላችሁም እዚህ መልካም ተግባር ላይ በመሳተፍ ማህበራዊ ግዴታችሁን እንድትወጡ እንጠይቃለን🙏🙏🙏


"ላንተ ትንሽ የምትላት ስጦታ የብዙ ሰዎችን ህይወት ትቀይራለች"

"#ስለእኛ_ካደረገው_ሊያደርግ_ያሰበው_ይበልጣል_በርቱ_እንበርታ"
@selegna2
Forwarded from የኦኒ_ገፆች 📖
መስሎኝ ነበር

🦋 @onitwa

እንደማታፈቅረኝ አውቅ ነበር። አብረን እንደማንሆንም አውቅ ነበር። ሌላ ሴት ልታፈቅር እንደምትችልም አውቅ ነበር።

እነዚህን ቃላቶች እንደምሰማቸውም አውቅ ነበር።
አንተም ታውቅ ነበር፤ ስትነግረኝ እንደሚከፋኝ ፣እንደሚደብረኝ፣ ውስጤ እንደሚታመም፣ጠንካራ እንዳልሆንኩ፣ @onitwa ደስተኛ እንደማልሆን ፣ተከፍቼ እንደማልነግርህ፣ ልቤ ተሰብሮ ልታፅናናኝ እንደማትችል ታውቅ ነበር።

አሁን ሲገባኝ ቀድመህ ልታዘጋጀኝ እየሞከርክ ነበር፤ሲከፋኝ የማቅፈውን እንዳገኝ ስትጥር ነበር ልቤ እንዳይደሞ በብዙ ስትለፋ ነበር።

እኔም ጠንካራ እንደሆንኩ ነግሬህ ነበር። ውስጤን እንዳሳመንኩት ነግሬህ ነበር አልጎዳምም ብዬህ ነበር። የምርም እንደዛ ተሰምቶኝ ነበር... ታዲያ አሁን ለምን ውስጤን ያመኛል? ለምን የጎደለ ነገር እንዳለ ይሰማኛል? @onitwa

ያን ቀን ደስተኛ ነበርኩ የእኔ ሁሉ ነገር ስትለኝ አለም ጠባኝ ነበር። የእኔ ንግስት ስትለኝ ለደስታዬ ጥግ አጥቻለሁ... ስታቅፈኝ ዓለሜን ባንተ እቅፍ ሸሽጌአለሁ...

አሁን ልቤን በጥልቁ ያመኛል። ልፅፈው አልቻልኩም መናገርም አቅቶኛል ማልቀስም ፈልጌ ሳግ ተናንቆኛል፤ ታውቃለህ ይህ ስሜት ከዚህ በፊት በጥልቅ ስቃይ ሳይሆን በመናፈቅ ውስጥ ተሰምቶኝ ነበር፤ልናገረው ልፅፈው ያልቻልኩት የናፍቆት ሳይሆን የህመም ስሜት... @onitwa አውቃለሁ ደስታህ ሊያስደስተኝ ይገባ ነበር። ዓለምህ ዓለሜ ሊሆን ይገባኝ ነበር፤እንደዛም እንደሚሆን ጠብቄ ነበረ...

ቃሎች ከአፍህ ሲወጡ ይታወሰኛል... ስለምታፈቅራት ልጅ አቅፈህ በደስታ ፊትህ እያበራ ስትነግረኝ ምስሉ ይታየኛል... @onitwa ልብህ ስትቦርቅ ይሰማኛል .... ብታውቂያት ትወጃታለሽ አልከኝ አንተ ወደሃት እኔ ልጠላት እንደማልችል ታውቃለህ... ደጋግመህ እንዳልደበረኝ ጠየከኝ በጭራሽ አልኩህ አልዋሸሁም የእውነቴን ምንም አልተሰማኝም ነበር... ደቂቃዎች በሰዓት ሲተኩ ውስጤ በረዶ መሆን ጀመረ።

ጥልቅ ዝምታ ... @onitwa አሁን የሚሰማኝን ተወው ልነግርህ የምፈልገው የጠነከርኩ ፣እውነቱን መጋፈጥ የምችል፣ ተስፋ የቆረጥኩ፣ ደስተኛ የምሆን፣ የማይከፋኝ መስሎኝ ነበር። ለካ እውነታው ከባድ ነበር።

ተፃፈ በኦኒ

6/7/2014 ዓ.ም

ሼር ሼር

🦋@onitwa

🦋 @onitwa
2024/05/21 17:22:22
Back to Top
HTML Embed Code: