Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የኃጢአት ሸክም ያጎበጠህ፣ በሁሉ የተናቅህ፣ አላፊ አግዳሚው ምራቁን ጢቅ እያለ ስድብ የሚያዋጣብህ ጎስቋላ ትሆናለህ። ሌሎች እነርሱን ስላልመሰልክ ይንቁህና ያንቋሽሹህ ይሆናል። ነገር ግን በፈጣሪህ ዘንድ ያለህን ተፈላጊነት ሰዎች በሚያሳዩህ ዝቅ ያለ አመለካከት አትለካ። ዛሬ የሚሰድቡህና የሚያዋርዱህ ሰዎች በአንተ መፈጠርና ሰው ሆኖ መኖር ላይ ምንም ዓይነት አስተዋጽዖ የላቸውም። የሕያውነት እስትንፋስ አልሰጡህም ሞተህ እንዳትቀር ስለ አንተ አልተሰቀሉልህም። ላንተ ሲሉ የከፈሉት ዋጋ ስለሌለ ለእነርሱ ከቁስ ያነስክ ልትሆን ትችላለህ።
••
ነገር ግን በእጁ የለወሰህ፣ ቁርበትና ሥጋ ያለበሰህ፣ በአጥንትና በጅማት ያጠረህ ሕይወት ሰጥቶ ሰው ያደረገህ እግዚአብሔር ከአንተ የሚበልጥበት ሀብት የለውም። በፀሐይና በጨረቃ በሌሎች ብርሃናት ሁሉ ያላስቀመጠው በአንተ ውስጥ ብቻ የቀረጸውን መልኩን ፈጽሞ ሊረሳ የማይችል አምላክ ይፈልግሃል። ጥበቡን አፍስሶ ስለ ፈጠረህ ስትጠፋ ዝም አይልም። ከዚህ ሁሉ በላይ ደግሞ ደሙን ስላፈሰሰልህ ፈጽሞ አይተውህም።
••
የሆሣዕና በዓል በሰዎች ፊት እንደ ምናምንቴ ለሆንን ለእኔ እና ለአንተ ነው። ጌታ ከኢያሪኮ ወደ ቤተ መቅደስ ይዟቸው የመጣው እንደ በርጤሜዎስ ያሉ የተናቁ ነዳያንን፣ እንደ ዘኬዎስ ያሉ የተጠሉ ኃጢአተኞችን ነበር። "ሆሣዕና በአርያም" የሚለው መዝሙራቸውም እንደዚያ ያማረው በመገፋት እና በመጠላት ልባቸው የቆሰሉትን በፍቅርና በምሕረቱ ፈውሶ መድኃኒትነቱን ስላቀመሳቸው ነው።
••
ለጌታ እናስፈልገዋለን‼️ በዓሉን በዓለ ክብር በዓለ ፍስሐ ያድርግልን፡፡
••
ቴሌግራም - https://www.tg-me.com/️ የአማኑኤል ልጆች ️/com.Terbinos
ቲክቶክ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡክ - https://www.face.com/terbinos

👉 #የሰሙነ_ሕማማት_ሰኞ - መርገመ በለስ የተፈጸመበት ዕለት ነው
••••
ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሆሣዕና ዕለት ቢታንያ አድሮ በማግሥቱም ከቢታኒያ ሲመጡ ተራበ፡፡ (ማር.11፤11-12) ቅጠል ያላት በለስ ከሩቅ አይቶ ወደ በለሲቱ ቀረበ፤ ነገር ግን ከቅጠል በቀር አንዳች ፍሬ አላገኘባትም፡፡ ከአሁን ጀምሮ ማንም ከአንቺ ፍሬ አይብላ ብሎ ረገማት። በለስ የተባለች ቤተ እስራኤል ናት፤ ፍሬ የተባለች ሃይማኖትና ምግባር ናት፤ ከእስራኤል ፍቅርን፤ ሃይማኖትን፤ ምግባርን ፈለገ አላገኘም፤ እስራኤል (ሕዝበ እግዚአብሔር) መባልን እንጂ፤ ደግ ሰው አይገኝብሽ ብሎ ረገማት፤ በመርገሙ ምክንያት እርሱ ከለያቸው በስተቀር ደግ ሰው ጠፋባት፡፡
••
በለስ ኦሪት ናት፤ ኦሪትን በዚህ ዓለም ሰፍና ቢያገኛት ኦሪትና ነቢያትን ልሽር አልመጣሁም ልፈጽም እንጂ በማለት ፈጸማት፤ ሕገ ኦሪትን ከመፈጸም በቀር በእርሷ ድኅነት አላደረገባትምና፤ ፍሬ በአንቺ አይሁን አላት፤ ደኅነት በአንቺ አይደረግብሽ ብሏታልና እንደመድረቅ ፈጥና አለፈች፡፡

በለስ ኃጢአት ናት፤ የበለስ ቅጠል ሰፊ እንደሆነች ሁሉ ኃጢአት በዚህ ዓለም ሰፍታ ሰፍና አገኛት፡፡ በለስ ሲበሉት ይጣፍጣል፤ ቆይቶ ግን ይመራል፤ ኃጢአትም ሲሰሩት ደስ ደስ ያሰኛል፤ ኋላ ግን ያሳዝናል፤ ወደ እርሷም ሄዶ ማለትም ከኃጥአን ጋር ዋለ፤ ኃጥእ ከመባል በቀር በአንደበቱ ሐሰት፤ በሰውነቱ ክፋት እንዳልተገኘበት ለማመልከት ፍሬ አላገኘባትም አለ፤ በአንቺ ፍሬ አይገኝ የሚለውም፤ በኃጢአት ፍዳ ተይዞ የሚቀር አይኑር ለማለት ነው፤ ስትረገም ፈጥና መድረቋም፣ በአዳም ምክንያት ያገኘችን ዕዳ በደል በእርሱ ካሣነት እንደጠፋችልን ለመግለጽ ነው፡፡
••
👉 አንጽሆተ ቤተ መቅደስ የተፈጸመበት ዕለት ነው ፦
•••
ጌታችን በለስን ከረገማት በኋላ ወደ ቤተ መቅደስ ሄደ፤ ቤተ መቅደስ፣ ቤተ ጸሎት፣ ቤተ መሥዋዕት መሆኑ ቀርቶ ቤተ ምስያጥ (የንግድ ቤት) ሆኖ ቢያገኘው ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች፤ እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋችኋት ብሎ የሚሸጡበትን ሁሉ ገለበጠባቸው፤ ገርፎም አስወጣቸው፤ ይህም የሚያሳየው ማደሪያው ቤቱ የነበርን የአዳም ልጆች ኃጢአት ሰፍኖብን ስንኖር ቢያገኘን ኃጢአታችንን ሁሉ እንዳራቀልን የሚገልጽ ነው፡፡
•••
በዚህ በሰሙነ ሕማማት ካህናትና ምእመናን በቤተክርስቲያን ተገኝተው ወዛቸው ጠብ እስኪል ድረስ በነግህ፤ በሠለስተ፣ በስድስቱ ሰዓት፤ በተሰዓቱ ሰዓትና በሠርክ መላልሰው ሲሰግዱና ሲጸልዩ ይሰነብታሉ፤ በተለይም ካህናት በማንኛውም አገልግሎት ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ፤ ምክንያቱም የደረሰብን መከራ ኀዘኑን እና 5ሺ ከ5መቶ ዘመን የሰው ልጅ በጨለማ ይኖር እንደነበረ ለማዘከር ነው፡፡
••••••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/️ የአማኑኤል ልጆች ️/com.Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
👉 የሰሙነ ሕማማት ማክሰኞ - የጥያቄ ቀን ይባላል
•
ሰኞ ባደረገው አንጽሖተ ቤተመቅደስ ምክንያት ፣ ሹመትን ወይም ሥልጣንን ለሰው ልጅ የሰጠ ጌታችን ፣ ስለ ሥልጣኑ በጸሐፍት ፈሪሳውያን ተጠይቋልና ፤ የጥያቄ ቀን ይባላል፡
•
ጥያቄውም ከምድራውያን ነገሥታት ፣ ከሌዋውያን ካህናት ያይደለህ ትምህርት ማስተማር ፣ ተዓምራት ማድረግ ፣ ገበያ መፍታትን ፣ በማን ሥልጣን ታደርጋለህ? ይህንንስ ሥልጣን ማን ሰጠህ? የሚል ነበር፡፡ /ማቴ. 21፥23-27፣ ማር. 11፥ 7-35፣ ሉቃ.21፥23-27፣ ማር.11፥27-33፣ ሉቃ. 20፥1-8/፤ እርሱም ሲመልስ፤ «እኔም አንድ ነገር እጠይቃችኋለሁ፣ እናንተም ብትነግሩኝ በማን ሥልጣን እነዚህን እዳደርግ እነግራችኋለሁ፡፡ የዮሐንስ ጥምቀት ከወዴት ነበረ ፣ ከሰማይ ነውን? ወይስ ከሰዉ? በእግዚአብሔር ፈቃድ ፣ ወይስ በሰው ፈቃድ?» አላቸው፡፡ እነርሱም ከሰማይ ብንል ለምን አልተቀበላችሁትም ይለናል፤ ከሰው ብንል ሕዝቡ ሁሉ ዮሐንስን እንደ አባት ያከብሩታል ፣ እንደ መምህርነቱ ይፈሩታልና ሕዝቡን እንፈራለን ፤ ተባብለው ከወዴት እንደሆነ አናውቅም ብለው መለሱለት፡፡ እርሱም እኔም በማን ሥልጣን እነዚህን እንደማደርግ አልነግራችሁም አላቸው» ይህንንም መጠየቃቸው እርሱ የሚያደርጋቸውን ሁሉ በራሱ ሥልጣን እንዲያደርግ አጥተዉት አልነበረም ፣ ልቡናቸው በክፋትና በጥርጥር ስለተሞላ እንጂ፡፡
•
👉 የትምህርት ቀንም ይባላል፡- በማቴ. 21፥28፣ ማቴ. 25፥46፣ ማር.12፥2፣ ማር.13፥37፣ ሉቃ. 20፥9፣ ሉቃ. 21፥38 የሚገኙት ትምህርቶች ሁሉም የማክሰኞ ትምህርት ይባላሉ፡፡ በዚህ ዕለት በቤተ መቅደስ ረጅም ትምህርት ስላስተማረ፣ የትምህርት ቀን ይባላል፡፡ ክርስቲያን የሆነ ሁሉ ከሥጋዊ ነገር ርቆ በዚህ ሰሞን የሃይማኖት ትምህርት ሲማር ሲጠይቅ መሰንበቱም መጽሐፋዊ ሥርዓት ነው፡፡

👉🏻 ረቡዕ || ሰሞነ ሕማማት
••
1. ምክረ አይሁድ ይባላል - ምክንያቱም የአይሁድ ሊቃነ ካህናትና ጸሐፍት ጌታን እንዴት መያዝ እንደሚገባቸው ምክር ያጠናቀቁበት ቀን ነውና፡፡በዚህ ምክራቸው ላይ በጣም ትልቅ ጭንቀት ነበር፡፡ ምክንያቱም ወቅቱ የፋሲካ በዓላቸውን የሚያከብሩበት ቀን የተቃረበ በመሆኑ ብዙው ሕዝብም በጌታችን ትምህርት የተማረኩ ተአምራቱንም የሚያደንቁ ስለ ነበር ሁከት እንዳይፈጠር ነው፡፡በዚህ ጭንቀት ሳሉ ከደቀ መዛሙርቱ አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ በመካከላቸው በመገኘት የምክራቸው ተባባሪ ሆኖ ጭንቀታቸውን አስወግዶላቸዋል።
••
የሐዲስ ኪዳን ካህናትና ምእመናን በዚሁ ዕለት በቤተ ክርስቲያን ተሰብስበው መላ ሰውነታቸውን ለእግዚአብሔር አስገዝተው የሞት ፍርዱን በማሰብና በማልቀስ ሐዋርያት ከጌታችን መያዝ በኋላ በኀዘን በፍርሐት እንደነበሩ እያሰቡ መጻሕፍትን በማንበብ በጾም በጸሎትና በስግደት ተወስነው ይቆዩና ከአሥራ ሁለት ሰዓት በኋላ ወደ ቤታቸው ይሄዳሉ፡፡

2. የመልካም መዓዛ ቀንም ይባላል - ምክንያቱም ጌታችን በዚህ ዕለት በቤተ ስምዖን ዘለምጽ ተቀምጦ ሳለ መላ ሕይወቷን ለዝሙት አስገዝታ ትኖር የነበረችው ማርያም እንተ እፍረት / ባለ ሽቶዋ ማርያም / « ከእንግዲህ ወዲህ በኃጢአት ተበላሽቶ ይኖር የነበረውን ሕይወቴን እንደዚህ መልካም ሽቱ የሚያጣፍጥ ኃጢአትን ይቅር የሚል አምላክ መጣ » ስትል ዋጋው እጅግ በጣም ውድ የሆነ ከሦስት መቶ ዲናር በላይ የሚያወጣ አልባስጥሮስ ብልቃጥ የተሞላ ሽቱ ይዛ በመሔድ በጠጉሩ / በራሱ / ላይ በማርከፍከፍ ስለቀባችው የመዓዛ ቀን ይባላል።
•••
3. የእንባ ቀን ይባላል - ባለሽቱዋ ሴት ( ማርያም እንተ እፍረት ) ኃጢአቷን ይቅር እንዲላት እየለመነች በእግሩ ስር ተደፍታ በእንባዋ እግሩን አርሳለችና ማር ፲፬፥፱ የእንባ ቀን ይባላል። ጌታ ሆይ መከራህን ስቃይህን ረሃብ ጥማትህን ሞትህን እያሰብኩ የማነባበት እንባ አብራህ ስለተንከራተተችው በመስቀል ላይ ሳለህም አንዴ ከድንጋይ አንዴም ከእሾህ ላይ እየወደቀች እየተነሳች ወየው አንድ ልጄ እያለች ስታነባ በነበረችው በአዛኝቱ እናትህ ስጠኝ አቤቱ ይቅር በለኝ ኢትዮጵያን ተዋሕዶን አስባት ኪርያላይሶን!
••••
ኪራላይሶን
አቤቱ ማረን ይቅር በለን
•••••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/️ የአማኑኤል ልጆች ️/com.Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
•••
3. የእንባ ቀን ይባላል - ባለሽቱዋ ሴት ( ማርያም እንተ እፍረት ) ኃጢአቷን ይቅር እንዲላት እየለመነች በእግሩ ስር ተደፍታ በእንባዋ እግሩን አርሳለችና ማር ፲፬፥፱ የእንባ ቀን ይባላል። ጌታ ሆይ መከራህን ስቃይህን ረሃብ ጥማትህን ሞትህን እያሰብኩ የማነባበት እንባ አብራህ ስለተንከራተተችው በመስቀል ላይ ሳለህም አንዴ ከድንጋይ አንዴም ከእሾህ ላይ እየወደቀች እየተነሳች ወየው አንድ ልጄ እያለች ስታነባ በነበረችው በአዛኝቱ እናትህ ስጠኝ አቤቱ ይቅር በለኝ ኢትዮጵያን ተዋሕዶን አስባት ኪርያላይሶን!
••••
ኪራላይሶን
አቤቱ ማረን ይቅር በለን
•••••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/️ የአማኑኤል ልጆች ️/com.Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
👉 #የሰሙነ_ህማማት_ሐሙስ
•••
❤️ #ጸሎተ_ሐሙስ ፦ በቤተ ክርስቲያን የተለያዩ ስያሜዎች ያሏቸው በርካታ ድርጊቶች የተፈጸሙበት ዕለት ነውና ጸሎተ ሐሙስ ይባላል፡፡ የዓለም መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ሥጋን የተዋሐደ አምላክ፣ መሆኑን ለመግለጥና ለአርአያነት ጠላቶቹ መጥተው እስኪይዙት ድረስ ሲጸልይ ያደረበት ነውና ጸሎተ ሐሙስ ተባለ፡፡ (ማቴ. 26፥36-46 ዮሐ.17)
•••
❤️ #ሕፅበተ_ሐሙስ_ይባላል ፦ ጌታችን በዚህ ዕለት የደቀመዛሙርቱን እግር በፍጹም ትሕትና ዝቅ ብሎ አጥቧል፡፡ ይህም የሚያሳየው የዓለምን ሁሉ ኃጢአት ለማጠብ የመጣ መሆኑን ነው፡፡ ይህን ለማስታወስ ዛሬም ካህናት በተለይም ሊቃነ ጳጳሳት፣ የደብር አስተዳዳሪዎች፤ «በመካከላችን ተገኝተህ የእኛንና የሕዝብህን ኃጢአት እጠብ እኛም የአንተን አርአያ አንዘነጋም የሌላውን እግር እናጥባለን፤» ሲሉ በቤተ ክርስቲያን የተገኙትን ምእመናንን እግር በወይንና በወይራ ቅጠል ያጥባሉ፡፡
•••
❤️ #የምስጢር_ቀን_ይባላል ፦ ከሰባቱ ምስጢራት አንዱ በዚህ ዕለት ተመሥርቷልና፡፡ ይኸውም «ይህ ስለ እናንተ በመስቀል ላይ የሚቆረሰው ሥጋዬ ነው፡፡ እንካችሁ ብሉ» ጽዋውንም አንስቶ አመሰገነ «ይህ ስለ እናንተ ነገ በመስቀል የሚፈስ ደሜ ነው ከእርሱም ጠጡ» በማለት፤ እኛ ከእርሱ ጋር፣ እርሱ ከእኛ ጋር አንድ የምንሆንበትን ምስጢር ከጠላት ዲያብሎስ ሰውሮ፣ ለደቀ መዛሙርቱ የገለጠበት ቀን በመሆኑ የተሰጠ ሥያሜ ነው፡፡ በዚህ ዕለት ክርስቲያን የሆነ ሁሉ በንስሐ ታጥቦ ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን ለመቀበል ይዘጋጃል፡፡

❤️ #የሐዲስ_ኪዳን_ሐሙስ_ይባላል ፦ ምክንያቱም መሥዋዕተ ኦሪት ማለትም በእንስሳት ደም የሚቀርበው መሥዋዕት ማብቃቱን ገልጦ፣ ለድኅነተ ዓለም ራሱን የተወደደ መሥዋዕት አድርጎ ያቀረበበት ዕለት በመሆኑ ነው፡፡ «ይህ ጽዋ ስለ እናንተ በሚፈሰው በደሜ የሚሆን ሐዲስ ኪዳን ነው፡፡ ከእርሱ ጠጡ» በማለቱ ይታወቃል (ሉቃ. 22፥20) ኪዳን ማለት በሁለት ወገን መካከል የሚደረግ ውል፣ ስምምነት፣ መሐላ ማለት ነው፡፡ በዚህ መሠረት ጌታችን ለአዳምና ለልጆቹ ሁሉ ዘለዓለማዊውን ቃል ኪዳን በራሱ ደም የፈጸመበት ዕለት ስለሆነ የሐዲስ ኪዳስ ሐሙስ ተባለ፡፡
•••
❤️ #የነጻነት_ሐሙስ_ይባላል ፦ ለኃጢአትና ለዲያብሎስ ባሪያ ሆኖ መኖር ማብቃቱ፣ የሰው ልጅ ያጣውን ክብር መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን ስለሆነ ነው፡፡ ጌታችን ስለ ሰው ልጅ ነጻነት ሲናገር «ከእንግዲህ ወዲህ ባሮች አልላችሁም ባርያ ጌታዉ የሚያደርገውን አያውቅምና ወዳጆች ግን ብያችኋለሁ» በማለት (ዮሐ. 15፥15)፤ ከባርነት የወጣንበት ልጆች የተባልንበትን ቀን የምናስብበት በመሆኑ ሊቃውንቱ የነጻነት ሐሙስ አሉት፡፡ እያንዳንዱ ክርስቲያንም ከኃጢአት ባርነት ርቆ፣ ከእግዚአብሔር ጋር የሚያወዳጀውን መልካም ሥራ በመሥራት ሕይወቱን መምራት ይኖርባታል፡፡ ባሮች አልላችሁም ተብለናልና፡፡
••••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/️ የአማኑኤል ልጆች ️/com.Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
•••
❤️ #የነጻነት_ሐሙስ_ይባላል ፦ ለኃጢአትና ለዲያብሎስ ባሪያ ሆኖ መኖር ማብቃቱ፣ የሰው ልጅ ያጣውን ክብር መልሶ ማግኘቱ የተረጋገጠበት ቀን ስለሆነ ነው፡፡ ጌታችን ስለ ሰው ልጅ ነጻነት ሲናገር «ከእንግዲህ ወዲህ ባሮች አልላችሁም ባርያ ጌታዉ የሚያደርገውን አያውቅምና ወዳጆች ግን ብያችኋለሁ» በማለት (ዮሐ. 15፥15)፤ ከባርነት የወጣንበት ልጆች የተባልንበትን ቀን የምናስብበት በመሆኑ ሊቃውንቱ የነጻነት ሐሙስ አሉት፡፡ እያንዳንዱ ክርስቲያንም ከኃጢአት ባርነት ርቆ፣ ከእግዚአብሔር ጋር የሚያወዳጀውን መልካም ሥራ በመሥራት ሕይወቱን መምራት ይኖርባታል፡፡ ባሮች አልላችሁም ተብለናልና፡፡
••••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/️ የአማኑኤል ልጆች ️/com.Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
🔴 ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን ➠ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሣ
🔵 በዐቢይ ኃይል ወስልጣን ➠
••
🔴 አሰሮ ለሰይጣን ➠ ሰይንን አሠረው
🔵 አግዓዞ ለአዳም ➠
••
🔴 ሰላም ➠
🔵 እም ይእዜሰ ➠
••
🔴 ኮነ ➠ ሆነ
🔵 ፍስሐ ወሰላም ➠ ደስታ እና ሰላም
••
" አሁንስ ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተነሥቶአል። " 1ኛ ቆሮ 15-20
••••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/️ የአማኑኤል ልጆች ️/com.Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
🔵 በዐቢይ ኃይል ወስልጣን ➠
በገናና ኃይልና ሥልጣን••
🔴 አሰሮ ለሰይጣን ➠ ሰይንን አሠረው
🔵 አግዓዞ ለአዳም ➠
አዳምን ነጻ አወጣው••
🔴 ሰላም ➠
ፍቅር አንድነት ሆነ🔵 እም ይእዜሰ ➠
ከእንግዲህስ••
🔴 ኮነ ➠ ሆነ
🔵 ፍስሐ ወሰላም ➠ ደስታ እና ሰላም
••
" አሁንስ ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተነሥቶአል። " 1ኛ ቆሮ 15-20
••••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/️ የአማኑኤል ልጆች ️/com.Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
👉 እንኳን ለትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ‼️
👉 Baga ayyaana Du'aa Ka'u Kiristosin nagaan gessan!‼️
👉 እንኳዕ ንበዓል ትንሳኤ ኣብፀሓኩም‼️
••
ዛሬ .... " ሞት ድል በመነሣት ተዋጠ " 1ኛ ቆሮ 15፣54
••
👉🏻 እባካችሁ ለሌሎች አካፍሉት ክርስቲያናዊን ወደዚህ ይጋብዙ‼️
•••••••

በመጸሐፍ ቅዱስ ቤዛ ማነው? ቃሉ የዋለው ለኢየሱስ ብቻ ነው ? ወይስ እንደ አገባብ ይተረጎማል?
•••
1ኛ- በመጸሐፍ ቅዱስ ብር ቤዛ ነው
“አንተ የእስራኤልን ልጆች ቍጥር ተቀብለህ፥ በቈጠርሃቸው ጊዜ መቅሰፍት እንዳይሆንባቸው ፥ በቈጠርሃቸው ጊዜ ከእነርሱ ሰው ሁሉ እንደ ቍጥራቸው መጠን የነፍሱን ቤዛ ለእግዚአብሔር ይስጥ።”ዘጸአት 30፥12
•••
2ኛ- በመጽሐፍ ቅዱስ ሀብት ቤዛ ነው
“ለሰው ነፍስ ቤዛው ሀብቱ ነው፤ ድሀ ግን ተግሣጽን አይሰማም።” ምሳሌ 13፥8
•••
3ኛ- በመጸሐፍ ቅዱስ ኅጥእ እና በደለኛ ሰው ቤዛ ተብሏል “ ኀጥእ የጻድቅ ቤዛ ነው ፤ በደለኛም የቅን ሰው ቤዛ ነው።” ምሳሌ 21፥18
•••
4ኛ- በመጸሐፍ ቅዱስ አገር ቤዛ ተብሏል “ እኔ የእስራኤል ቅዱስ አምላክህ እግዚአብሔር መድኃኒትህ ነኝ ፤ ግብጽን ለአንተ ቤዛ አድርጌ፥ ኢትዮጵያንና ሳባንም ለአንተ ፋንታ ሰጥቻለሁ።” ኢሳይያስ 43፥3
•••
5ኛ- በመጸሐፍ ቅዱስ መሪ ቤዛ ተብሏል
“ ሹምና ፈራጅ እንድትሆን የሾመህ ማን ነው? ብለው የካዱትን ፥ ይህን ሙሴን በቍጥቋጦው በታየው በመልአኩ እጅ እግዚአብሔር ሹምና ቤዛ አድርጎ ላከው። ”
ሐዋርያት 7፥35
•••
6ኛ- በመጸሐፍ ቅዱስ ቀን ቤዛ ተብሏል “ ለቤዛም ቀን የታተማችሁበትን ቅዱሱን የእግዚአብሔርን መንፈስ አታሳዝኑ። ” ኤፌሶን 4፥30

‹‹ ቤዛ ›› ማለት ምን ማለት ነው? እናታችን ቅድሥት ድንግል ማርያም ቤዛ ትባላለችን ?
ብዙ ጊዜ ድንግል ማርያም እንዴት ቤዛ ትባላለች ? ይላሉ ፤ በእርግጥ ግን እናታችን ቅድሥት ድንግል ማርያም የአለም ቤዛ ናት ።‹‹ ቤዛ ›› በቁሙ ሲተረጐም ዋጋ አለው ወይም ጥቅም አለው ማለት ነው ። እንዲሁም ቤዛ የሚለው ቃል "ቤዘወ"፦ ከሚለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ሲሆን ቤዛ በቁሙ ሲተነተን እንዲህ ማለት ነው ። ዋጋ ፣ ካሳ ፣ ለውጥ ፣ ምእትክ ፣ ሀላፊ ፣ ዋቢ ፣ ዋሥ ፣ መድኅን ፣ ተያዥ ፣ ጥላ ፣ ጋሻ ... ማለትነው ።ቤዛ በደቂቅ አገባብ ሲፈታ ደግሞ ሥለ ፣ ፋንታ፣ ምክንያት የሚሆንተብሎም ይተረጐማል ።
•••
አለቃ ኪዳነ ወልደ ክፍሌ መፅሐፍ ሠዋሠው ውግሥ በመዝገበ ቃላት ሐዲሥ 1948 ዓ ም ገፅ 266፡፡ ወይምደግሞ በሌላ መንገድ ከሣቴ ብርሐን ተሠማ መፅሐፋቸው ቤዛ ሲተረጉሙ እንዲህ ብለው አሥቀምጠውልናል ለውጥ ፣ ካሣ ፣ ወይም ደግሞ በአንድ ሠው ላይ መከራና ሞት ተላልፎ መሞትማለት ነው ወይም ታደገኝ ወይም ምትክ ሆነኝ ማለት ነው ወይም ደግሞ ለመከራ ለሞት ለወጠኝ ማለት ነው ወይም ቤዛ ሆነኝ ማለትነው ። የበለጠ ለመረዳት አልያም ቤዛ ሥለሚለው ቃል በደንብ ለማወቅ እነዚህን መፅሐፍቶች መመልከት ይቻላል ።
•••
እንደዚሁም ቤዛ የሚለው ቃል ፦ ካሣ ፣ የደም ቤዛ ፣ አንዱ ሠው የሠውንደም ሥለሚያፈሠው ለውጥ ወይም ዋጋን ፣ ገንዘብን ፣ ካሣን መሥጠት ወይም መዋጀት ማለት ነው ።ከሣቴ ብርሐን 1951 ዓ.ምገፅ 532 ድንግል ማርያምን ስለምን የአለም ቤዛ እንላታለን? የእመቤታችን ቤዛነትም ከላይ በተረዳነው መሠረት ቤዛ ከሚሉት የትርጓሜ ቃላት መካከል ምትክ ፣ ዋሥ ፣ ምክንያት ... ከሚሉት መካከል ምትክ የሚለውን ስንወስድ ድንግል ማርያም የህይዋን (ሔዋን) ምትክ በመሆኗ ነው ፤ ‹ምክንያት› የሚለውን ስንወስድ ደግሞ ቅድስት ድንግል ማርያም ለኛ መዳን ምክንያት ስለሆነች ነው። እግዚአብሔር ለአለም መዳን በድንግል ማርያም ታላቅ ስራን አድርጉአልና ቤዛዊት ዓለም እንላታለን። የድንግል ማርያም በእምነት መታዘዝ ለዓለም መዳን ምክንያት ሆናለች። አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከድንግል ማርያም ከስጋዋ ስጋ ከነፍስዋ ነፍስ ነስቶ ዓለምን ስለተቤዤ ቤዛዊት ዓለም እንላታለን።
•••
ቤዛ የሚለው ቃል ለሙሴም ተሰጦት እናነባለን። ( የሐዋ ሥራ 7:35) በመልአክ እጅ እግዚአብሔር ሹምና ቤዛ አድርጎ ላከው።እንግዲህ ይህ የፍጡር ቤዛነት የእግዚአብሔርን ቤዛነትይሽራልን? አይደለም፡፡ እንዲያውም ቸር እግዚአብሔርለወዳጆቹ የሚሰጠውን የባለሟልነት ስጦታ ብዛት ይገልፃልእንጂ፡፡ ሙሴ ወገኖቹን ከመጥፋት እንደምን አዳናቸው ( ተቤዣቸው )( ታደጋቸው )? እንደክርስቶስ ደሙን በማፍሰስ ነውን? አይደለም በእግዚአብሔር ዘንድ ‹ይህን ኀጢአታቸውን ይቅር በላቸው ፤ ያለዚያ ግን ከጻፍኸው መጽሐፍኽ እባክኽ ደምሰሰኝ› በማለትየተወደደፀሎቱን በማቅረብእንጂ ( ዘጸ.32፤32 )፡፡
•••
ዳዊትም ‹ ሙሴ በእግዚአብሔር ፊት ባይቆም ኖሮ ›› ሲል የገለፀው ይሄንኑ ነው፡፡ስለዚህም መጽሐፍ የፃድቅ ሰው ፀሎት በስራዋ እጅግ ሃይልን ታደርጋለች ይላል፡፡የእመቤታችንና የድንግል ማርያም ቤዛነት ከጌታችን ከኢየሱስ ክርሥቶስ ቤዛነት ጋር ያለው ልዩነትእጅግ የሚራራቅ ነው ።ጌታችን በሞቱ የተደረገ ቤዛነት ነው ። እንዲሁም በደሙ ዋጅቶ በሞቱ የተደረገ ቤዛነት ነው። ቤዛ ማለትእራሥን ሥለሌሎች አሣልፎ መስጠት ማለት ሥለሆነ ጌታችንም ሥለበጐቹ እራሱን አሣልፎ ሠጥቷል ሆኖም የአለም ቤዛ ነው ። ታዲያ የአለምቤዛ ክርስቶስ ከሆነ ድንግል ማርያምስ ቤዛዊት አለም መባሏ ስለምን ነው ቢሉ፦ ክርስቶስ አለምን ሁሉ ከሞት ወደህይወት ያሻገረበት፣ ሃጢአታችንን ሁሉ የደመሰሰበት ፣ የሚደመስስበትም ክቡር ደሙ ፣ ቅዱስ ስጋው ከእመቤታችን ስለነሳው ነው ፤ በዚህም ክርስቶስ ከመወለዱ አንስቶ በቤተልሄም የከብት ግርግም ተጀምሮ፡ በግብፅ ስደቱ በቀራኒዮ ስቃዩና ሞቱ ሁሉ አብራው አለችና በክርስቶስ የድህነት ስራ ውስጥ የእመቤታችን ስራ ጉልህ ሆኖ ይታያልና ነው፡፡ለማጠቃል ያክል፡- ሙሴ ምክንያት ሆኖ ነጻ ያወጣቸው ለጥቂት ነገዶች ወይም ‹ለእስራኤላውያን› ብቻ በመሆኑ ‹‹ቤዛ›› ብቻ ተብሏል፡፡
••
ወላዲተ አምላክ ድንግል ማርያም ግን ምክንያተ ድኅነት ሆና ነጻ ያወጣችው ‹ዓለም ሙሉ›ስለሆነ (ክርስቶስ ለዓለም ሁሉ ተሰቅሏልና) ‹‹ቤዛዊተ ዓለም›› ትባላለች፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛነት የባሕርይ ገንዘቡ ሲሆን ለቅዱሳንም በጸጋ ተሰጥቷል፤ በመጸሐፍየጸጋ አምላክነት ለቅዱሳን ተሰጥቶ እናያለን ‹እግዚአብሔርም ሙሴን አለው፦እይ፥እኔ ለፈርዖን አምላክ አድርጌኻለኹ›፤ ክርስቶስየዓለም ብርሃን እንደሆነ እንዲሁ ደግሞ ቅዱሳንንም ‹እናንተየዓለም ብርሃን ናችኹ› በማለት በጸጋ የዓለም ብርሃን እንደሚባሉ መጽሐፍ ምስክርነው ( ዘጸ7፤1 ማቴ 5፤14) የቤተክርስቲያን ትምህርት እንዲህ ነዉ ፤ ክብርና ምሥጋና ለቤዛዊት አለም ለእመቤታችን ለቅድሥት ድንግልማርያም ይሁን አሜን።

👉 የምህረት እናት
👉 ኪዳነ ምህረት
••
የእውነት እና የህይወት ባለቤት የሆነንን አምላክ ያየንብሽ ሠላምን የወለድሽ የሠላም እናት ኪዳነምህረት የአምላክ እናት የምህረት ቃልኪዳን የድህነታች ምልክት ኪዳነ ምህረት።
••
ምልጃሽ አይለየን

ባንች ጠገቡ የቀደሙት ሁሉ
በቀን በለሊት ቅድስት ሆይ እያሉ
የእንጀራ ቤት ነሽ ሀገረ ሰላም
ቤዛዊት ኩሉ ድንግል ቅድስት ማርያም
•••
👉 እናታችን #ቤዛዊት_ማርያም የልባችንን መሻት ትሙላልን ምልጃዋ አይለየን ፤

👉🏼 እንኳን ለዳግም ትንሣኤ በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ‼️
••
ዳግማይ ትንሳኤ ማለት ዳግም መነሳት ( ሁለተኛ መነሳት )
••
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ በተነሳ በስምንተኛው ቀን በዕለተ እሁድ ደቀ መዛረሙርቱ አይሁድን ፈርተው በተሰበሰቡበት ዝግ ቤቶ " ሰላም ለእናንተ ይሁን "ብሎ ዳግም ስለ ተገለጠ #ዳግማይ\ትንሳኤ ተብሏል። ሁለተኛ ለምን ተገለጠ?
••
👉 ለሐዋርያው ቶማስ ትንሳኤውን ለማሳመን
••
የጌታችን ትንሳኤ ቶማስ ስለ ተጠራጠረ ጌታችን ቶማስ በተገኘበት ዝግ ቤት ተገልጦ ለቶማስ ና ወደኔ የተቸነከረውን እጄና ጉኔን ዳስስ ብሎታል።
••
ቶማስም የተቸነከረው እጁን አይቶ የተወጋውን ጉኑ በእጁ ዳስሶ የጌታችን ትንሳኤ አምኗል። ሃገረ ስብከቱም በሕንድ ስለ ነበረ ተጋድሎውም የፈጸመው እንዲሁም ሰማዕትነት የተቀበለው በሕንድ ነው ። ያቺ የጌታችንን ጎን የነካች ( የዳሰሰች ) እጅ ሳትበሰብስ ከታቦት ጋር በመንበሩ ላይ ተቀምጣለች። እስካሁን ድረስ የሕንድ ሊቀ ጳጳስ ሲሾም በዛች እጅ ተመርጦና ተባርኮ እንደሚሾም አንዳንድ ሊቃውንት ይናገራሉ።

👉 ሰንበትን ሊያጸናልን
••
የአይሁድ ሰንበት ፣ እግዚአብሔር 22 ፍጥረታትን ፈጥሮ ያረፈባትና እረፉባት ብሎ ያዘዘን ሰንበት ቀዳም (ቅዳሜ) ናት ። በሐዲስ ኪዳንም ጌታችን የተጸነሰባት ፣ ከሙታን መካከል የተነሳባት ፣ አንዲሁም ደግሞ ለማጽናት ሁለተኛ የተገለጠባት (ዳግማይ ትንሳኤ) ፣ መንፈስ ቅዱስ የወረደባትና ሐዋርያት ከመጀመርያዋቹ ክርስቲያኖች ጋር በኅብረት ሆነው መንፈሳዊ ስራዋች የሚሰሩባት ቀን ዕለተ እሁድ ነበረች። ቤተ ክርስቲያናችን ለቅዳሜ ቀዳሚት ሰንበት ለእሁድ ደግሞ ሰንበተ ክርስቲያን እያለች ለሁለቱም ቀናት እኩል ታከብራቸዋለች። ጌታችንም ይቺ ቀን እረፍትነቷን ለማጽናት ሁለተኛ የተገለጠባት ቀን ናት። እረፍት ስንልም ስራችንን ትተን ቁጭ ብለን (ተኝተን) የምናሳልፈው ማለት አይደለም። እንደውም ከማንም ቀን በላይ አብዝተን መንፈሳዊ ስራዎች የምንሰራባቸው ቀናት ናቸው እንጂ
••
👉 ምትሐት አለመሆኑ ለማስረዳት
••
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምትሐት እንዳልሆነና ቀድሞ የተዋሃደው ስጋና መለኮት ፣ ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ መሆኑ ለማስረዳት ለሁለተኛ ጊዜ ተገልጦላቸዋል። በዝግ ቤት መግባቱ ደግሞ መለኮት እንዳልተለየውና ስጋ ብቻው እንዳልሆነ ለማስረዳት ነው ። " ብጹዓን እለ እንዘ ኢይሬእዩ የአምኑ " ( ዮሐ20:29 )
••
የተሣተውን ፤ የተረሳው ፤ የተገደፈውን ፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት
••
ስለ ማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይባርክ !
•••••••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/️ የአማኑኤል ልጆች ️/com.Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
••
የአይሁድ ሰንበት ፣ እግዚአብሔር 22 ፍጥረታትን ፈጥሮ ያረፈባትና እረፉባት ብሎ ያዘዘን ሰንበት ቀዳም (ቅዳሜ) ናት ። በሐዲስ ኪዳንም ጌታችን የተጸነሰባት ፣ ከሙታን መካከል የተነሳባት ፣ አንዲሁም ደግሞ ለማጽናት ሁለተኛ የተገለጠባት (ዳግማይ ትንሳኤ) ፣ መንፈስ ቅዱስ የወረደባትና ሐዋርያት ከመጀመርያዋቹ ክርስቲያኖች ጋር በኅብረት ሆነው መንፈሳዊ ስራዋች የሚሰሩባት ቀን ዕለተ እሁድ ነበረች። ቤተ ክርስቲያናችን ለቅዳሜ ቀዳሚት ሰንበት ለእሁድ ደግሞ ሰንበተ ክርስቲያን እያለች ለሁለቱም ቀናት እኩል ታከብራቸዋለች። ጌታችንም ይቺ ቀን እረፍትነቷን ለማጽናት ሁለተኛ የተገለጠባት ቀን ናት። እረፍት ስንልም ስራችንን ትተን ቁጭ ብለን (ተኝተን) የምናሳልፈው ማለት አይደለም። እንደውም ከማንም ቀን በላይ አብዝተን መንፈሳዊ ስራዎች የምንሰራባቸው ቀናት ናቸው እንጂ
••
👉 ምትሐት አለመሆኑ ለማስረዳት
••
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ምትሐት እንዳልሆነና ቀድሞ የተዋሃደው ስጋና መለኮት ፣ ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ መሆኑ ለማስረዳት ለሁለተኛ ጊዜ ተገልጦላቸዋል። በዝግ ቤት መግባቱ ደግሞ መለኮት እንዳልተለየውና ስጋ ብቻው እንዳልሆነ ለማስረዳት ነው ። " ብጹዓን እለ እንዘ ኢይሬእዩ የአምኑ " ( ዮሐ20:29 )
••
የተሣተውን ፤ የተረሳው ፤ የተገደፈውን ፤ የነጠፈውን በቀና መንፈስ አቃንታቹ አንብቡት
••
ስለ ማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይባርክ !
•••••••
የቴሌ ግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ - https://www.tg-me.com/️ የአማኑኤል ልጆች ️/com.Terbinos
የቲክ ቶክ የገፃችን ይመልከቱ - https://www.tiktok.com/@yeamanuelljochi
የፌስቡኩ ገፃችን ይመልከቱ - https://www.facebook.com/terbinos
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
❤️ ድንግልን ይዞ ያፈረ የለም ‼️
•••
“ #ድንግል ሆይ ፣ ቅድስት ሆይ ፣ ንጽሕት ሆይ ፣ የተመሰገንሽ ቡርክት ሆይ የድግልናሽ ምስጋና በኹሉ መላ ውዳሴሽም በዓለም ዙሪያ ሰፈረ
•••
የውቅያኖስ ባሕር በምልአቱ ውሱን ነው
የሐኖስም ባሕር በመጠኑ ልክ አለው ፤
•••
ለአንቺ ምስጋና ግን ልክና መጠን ወሰንና መስፈርት ፣ ማለቂያም የለውም አእምሮም አይወስነውም አንደበትም ተናግሮ ሊፈጽመው አይችልም “ ( አርጋኖን ዘሰኑይ ፰ ÷ ፲ - ፳፰ )

አቤቱ በፍጥረት ሁሉ አንደበት የምትመሰገን ለአንተ #ለመድኃኔዓለም_ክርስቶስ ክብር ምስጋና ይገባል ።
••
አቤቱ ለተራቆቱት ልብስ ይምትሆናቸው ለአንተ ለኢየሱስ ክርስቶስ ክብር ምስጋና ይገባል ።
••
አቤቱ ነፍስና ሥጋን አዋህደህ በምግባር በሐይማኖት አጽንተህ የምታከብራቸው ለአንተ #ለመድኃኔዓለም_ክርስቶስ ክብር ምስጋና ይገባል ። አቤቱ በመንግሥትህ ሽረት በሕልውናህ ሕልፈት የሌለብህ ለአንተ ለንጉሥ ክርስቶስ ክብር ምስጋና ይገባል ።
••
አቤቱ የቅዱስ አብ አካላዊ ቃል የዓለሙ ሁሉ መድኃኒት ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ለአንተ ክብር ምስጋና ይገባል ለዘለዓለሙ አሜን። / መልክዓ መድኃኔዓለም /