tg-me.com/Wahidcom/3721
Last Update:
ሥነ ፍጥረት
ክፍል አንድ
በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡
7፥54 ጌታችሁ ያ ሰማያትን እና ምድርን በስድስት ቀናት ውስጥ የፈጠረ አሏህ ነው፡፡ إِنَّ رَبَّكُمُ اللَّهُ الَّذِي خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ فِي سِتَّةِ أَيَّام
አምላካችን አሏህ ሰማያትን፣ ምድርን እና በመካከላቸው ያለውን ሁሉ በስድስት ቀናት ውስጥ በእርግጥ ፈጠረ፦
50፥38 ሰማያትን፣ ምድርን እና በመካከላቸው ያለውን ሁሉ በስድስት ቀናት ውስጥ በእርግጥ ፈጠርን፡፡ ድካምም ምንም አልነካንም፡፡ وَلَقَدْ خَلَقْنَا السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ وَمَا بَيْنَهُمَا فِي سِتَّةِ أَيَّامٍ وَمَا مَسَّنَا مِن لُّغُوبٍ
"ፊ" فِي ማለት "ውስጥ" ማለት ሲሆን በጥቅል ስድስት ቀናት ውስጥ ሰማያትን እና ምድርን እንደፈጠረ ጉልኅ ማሳያ ነው፦
7፥54 ጌታችሁ ያ ሰማያትን እና ምድርን በስድስት ቀናት ውስጥ የፈጠረ አሏህ ነው፡፡ إِنَّ رَبَّكُمُ اللَّهُ الَّذِي خَلَقَ السَّمَاوَاتِ وَالْأَرْضَ فِي سِتَّةِ أَيَّام
"በስድስት ቀኖች ውስጥ የፈጠረ አሏህ ነው" የሚለው ኃይለ ቃል ይሰመርበት! እዚህ አንቀጽ ላይ "ፈጠረ" ለሚለው የገባው ቃል "ኸለቀ" خَلَقَ ሲሆን "ፊ" فِي የሚለው መስተዋድድ በጥቅል አገላለጽ ፍጥረት በስድስት ቀናት ውስጥ መፈጠራቸውን አመላካች ነው። በተናጥል ሌላ አንቀጽ ላይ ምድርን በሁለት ቀናት ውስጥ መፍጠሩትን ይናገራል፦
41፥9 በላቸው «እናንተ በዚያ "ምድርን በሁለት ቀናት ውስጥ በፈጠረው አምላክ በእርግጥ ትክዳላችሁን?" ለእርሱም ባለንጣዎችን ታደርጋላችሁን? ያ ይህንን የሠራው የዓለማት ጌታ ነው፡፡ قُلْ أَئِنَّكُمْ لَتَكْفُرُونَ بِٱلَّذِى خَلَقَ ٱلْأَرْضَ فِى يَوْمَيْنِ وَتَجْعَلُونَ لَهُۥٓ أَندَادًۭا ۚ ذَٰلِكَ رَبُّ ٱلْعَٰلَمِينَ
እዚህ አንቀጽ ላይ "ፈጠረ" ለሚለው የገባው ቃል "ኸለቀ" خَلَقَ ሲሆን "ሁለት ቀናት" የተባሉት የመጀመሪያው ቀን "አል አሐድ" ٱلْأحَد እና ሁለተኛው ቀን "አል ኢስነይን" ٱلْاِثْنَيْن እንደሆኑ ሙፈሢሮች አስቀምጠዋል፦
ተፍሢር ኢብኑ ከሲር 41፥9 "ምድርን በሁለት ቀናት ውስጥ በፈጠረው" ሲል "የመጀመሪያው ቀን እና ሁለተኛው ቀን ነው" ማለት ነው"። فقوله : ( خلق الأرض في يومين ) يعني : يوم الأحد ويوم الاثنين .
፨ "አሐድ" أحَد ማለት "አንድ" ማለት ሲሆን "እሑድ" ማለት ነው፥ "እሑድ" የሚለው የግዕዙ ቃል በራሱ “አሐደ” ከሚለው ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን "አንድ" ማለት ነው።
፨ "ኢስነይን" اِثْنَيْن ማለት "ሁለት" ማለት ሲሆን "ሰኞ" ማለት ነው፥ "ሰኞ" ማለት "ሰነየ" ማለትም "ደገመ" ከሚል የመጣ ሲሆን "ሁለተኛ" ማለት ነው።
አሏህ በምድር ከበላይዋ የረጉ ጋራዎችን አደረገ፥ በውስጧም ባረከ፦
42፥10 በእርሷ ከበላይዋ የረጉ ጋራዎችን አደረገ፥ በውስጧም ባረከ፡፡ وَجَعَلَ فِيهَا رَوَٰسِىَ مِن فَوْقِهَا وَبَٰرَكَ فِيهَا
"ባረከ" بَٰرَكَ ማለት "ባረከ" ማለት ሲሆን በውስጧም ምግቦችዋን በአራት ቀናት ውሰጥ ለጠያቂዎች ትክክል ሲኾኑ ወሰነ፦
42፥10 "በውስጧም ምግቦችዋን በአራት ቀናት ውሰጥ ለጠያቂዎች ትክክል ሲኾኑ ወሰነ"፡፡ وَقَدَّرَ فِيهَآ أَقْوَٰتَهَا فِىٓ أَرْبَعَةِ أَيَّامٍۢ سَوَآءًۭ لِّلسَّآئِلِينَ
"በአራት ቀናት ውሰጥ ለጠያቂዎች ትክክል ሲኾኑ ወሰነ" አለ እንጂ "በአራት ቀናት ውሰጥ ለጠያቂዎች ትክክል ሲኾኑ ፈጠረ" አላለም፥ "ወሰነ" ለሚለው የገባው ቃል "ቀደረ" قَدَّرَ ሲሆን "መጠነ" "አዘጋጀ" በሚል ይመጣል፦
80፥19 ከፍትወት ጠብታ ፈጠረው እና መጠነው፡፡ مِن نُّطْفَةٍ خَلَقَهُ فَقَدَّرَهُ
25፥2 ነገሩንም ሁሉ የፈጠረ እና በትክክልም ያዘጋጀው ነው፡፡ وَخَلَقَ كُلَّ شَيْءٍ فَقَدَّرَهُ تَقْدِيرًا
እነዚህ አናቅጽ ላይ "ፈጠረ" ለሚለው የገባው ቃል "ኸለቀ" خَلَقَ ሲሆን "መጠነ" "አዘጋጀ" ለሚለው የገባው ቃል ግን "ቀደረ" قَدَّرَ ነው፥ በአራት ቀናት የመጠነው እና ያዘጋጀው ምግቧን እንጂ ፈጠረ አይልም። ምድርን የፈጠረበት 2 ቀናት እና ምግቧን የወሰነበትን 4 ቀናት ደምራችሁ 6 ቀናት ብላችሁ ለማጋጨት የሞከራችሁት ሙከራ ፉርሽ ሆኗል።
ሲጀመር "ተዳኹል" تَدَاخُل የሚለው ቃል "ተዳኸለ" تَدَاخَلَ ማለትም "ተጠላለፈ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "መጠላለፍ"intersection" ማለት ነው፥ አራት ቀናት ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ተዳኹል የሆኑት "አል አሐድ" ٱلْأحَد "አል ኢስነይን" ٱلْاِثْنَيْن "አል ሱላሳእ" ٱلْثُّلَاثَاء "አል አርቢዓእ" أَرْبِعَاء ናቸው፦
ተፍሢሩል ጀላለይን 41፥10 "በአራት ሙሉ ቀናት በሌላ አነጋገር በውስጧ ያለው የተራሮች አቀማመጥ ከሥስተኛው እና ከአራተኛው ቀን ጋር ተያይዞ የተከናወነው በትክክል "ሠዋእ" በተሳቢ ምክንያቱም ግሣዊ ስም ነው፥ አራቱ ቀናት ያነሱም ያልበዙም ለጠያቂዎች ሁሉ ስለ ምድር አፈጣጠር እና በውስጧ ስላለው ሁሉ በትክክል አራት ነበሩ"።
"ሠዋእ" سَوَآء ማለት "በትክክል" ማለት ሲሆን በሰዋስው አወቃቀር አራት ቀናት በሁለት ቀናት ውስጥ ተለጣጥፎ"overlap" የመጣ ነው።
፨ "ሱላሳእ" ثُّلَاثَاء ማለት "ሦስት" ማለት ሲሆን "ማክሰኞ" ማለት ነው። "ማክሰኞ" ማለት "ማግስት" ማለት ነው፥ የእሁድ ማግስት "ሦስተኛ" ቀን ነው።
፨ "አርቢዓእ" أَرْبِعَاء ማለት "አራት" ማለት ሲሆን "ረቡዕ" ማለት ነው፥ "ረቡዕ" ማለት "ረበዓ" ከሚል የመጣ ሲሆን "አራተኛ" ማለት ነው።
አምላካችን አሏህ ምድርን በፈጠረበት ጊዜ ሰማይን ጋዝ አርጎ ፈጠራት፥ ሰማይ የተገነባችበት ጋዝ ምድር በተፈጠረች ጊዜ ከእርሷ የሚወጣውን ጋዝ ነበረ፦
79፥27 ባፈጣጠር እናንተ ይበልጥ የበረታችሁ ናችሁን? ወይንስ ሰማይ? አሏህ ገነባት፡፡ أَأَنتُمْ أَشَدُّ خَلْقًا أَمِ السَّمَاءُ ۚ بَنَاهَا
ተፍሢር ኢብኑ ከሲር 42፥11 እርሱ(ጋዙ) ምድር በተፈጠረች ጊዜ ከእርሷ የሚወጣው ጭስ ነው"። وهو : بخار الماء المتصاعد منه حين خلقت الأرض
“ጭስ” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ዱኻን” دُخَان ሲሆን “ጋዝ”gas" ማለት ነው፥ ሰማይ በጋዝ ደረጃ እያለች አሏህ ለሰማይ እና ለምድር፦ «ወዳችሁም ኾነ ወይም ጠልታችሁ ኑ» አላቸው፡፡ እነርሱም፦ «ታዛዦች ኾነን መጣን» አሉ፦
42፥11 "ከዚያም ወደ ሰማይ እርሷ ጭስ ኾና ሳለች አሰበ፡፡ ለእርሷም ለምድርም «ወዳችሁም ኾነ ወይም ጠልታችሁ ኑ» አላቸው፡፡ «ታዛዦች ኾነን መጣን» አሉ፡፡ ثُمَّ ٱسْتَوَىٰٓ إِلَى ٱلسَّمَآءِ وَهِىَ دُخَانٌۭ فَقَالَ لَهَا وَلِلْأَرْضِ ٱئْتِيَا طَوْعًا أَوْ كَرْهًۭا قَالَتَآ أَتَيْنَا طَآئِعِينَ
ኢሻላህ ይቀጥላል.....
✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://www.tg-me.com/us/ወሒድ የንጽጽር ማኅደር/com.Wahidcom
ወሠላሙ ዐለይኩም
BY ወሒድ የንጽጽር ማኅደር
Warning: Undefined variable $i in /var/www/tg-me/post.php on line 280
Share with your friend now:
tg-me.com/Wahidcom/3721