tg-me.com/yenetube/50169
Last Update:
የአሳማ ኩላሊት በንቅለ ተከላ ለመጀመሪያ ጊዜ የተለገሰው ግለሰብ ህይወቱ አለፈ!
በዘረመል ምህንድስና የተሻሻለ የአሳማ ኩላሊት በንቅለ ተከላ ለመጀመሪያ ጊዜ የተለገሰው ግለሰብ ከህክምናው ሁለት ወራት በኋላ ህይወቱ ማለፉን ሆስፒታሉ አስታወቀ።የ62 ዓመቱ ሪቻርድ "ሪክ" ስላይማን ቀዶ ህክምናውን በመጋቢት ወር ከማድረጉ በፊት በከፋ የኩላሊት ህመም ይሰቃይ ነበር።
ህይወቱ ያለፈው በንቅለ ተከላው ምክንያት ስለመሆኑ ምንም ምልክት የለም ሲል የማሳቹሴትስ አጠቃላይ ሆስፒታል (ኤምጂኤች) እሑድ ዕለት አስታውቋል።በዘረመል ምህንድስና ከተሻሻሉ አሳማዎች የተገኙ ክፍሎችን ሌሎች የመተካት ሙከራ ቀደም ሲል አልተሳካም ነበር። የስላይማን ቀዶ ህክምና ግን ታሪካዊ ምዕራፍ ነው ተብሎ ተወድሷል።
ከኩላሊት ህመም በተጨማሪ ስላይማን የስኳር በሽታ እና የደም ግፊት ነበረበት።እአአ በ 2018 የሰው ኩላሊት ንቅለ ተከላ ቢያከናውንም ከአምስት ዓመታት በኋላ መሥራት ማቆሙ ተነግሯል።የአሳማ ኩላሊት ንቅለ ተከላውን ተከትሎ፤ አዲሱ ኩላሊቱ በጥሩ ሁኔታ እየሠራ በመሆኑ የኩላሊት እጥበት (ዳያሊሲስ) እንደማያስፈልገው ዶክተሮቹ አረጋግጠው ነበር።
"ስላይማን በዓለም አቀፍ ደረጃ ስፍር ቁጥር ለሌላቸው ህሙማን የተስፋ ብርሃን ፈንጣቂ ሆኖ ይታያል። ‘የዜኖትራንስፕላንቴሽን’ መስክን ወደፊት እንዲራመድ ላሳየው እምነት እና ፍቃደኝነት በጣም እናመሰግናለን" ሲል ሆስፒታሉ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።ዜኖትራንስፕላንቴሽን ህይወት ያላቸው ሴሎችን ወይም የአካል ክፍሎችን ከአንድ ዝርያ ወደ ሌላ ዝርያ መተካት ነው።
Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
BY YeneTube
Share with your friend now:
tg-me.com/yenetube/50169