tg-me.com/yenetube/50179
Last Update:
የቀድሞ ተዋጊዎችን ትጥቅ የማስፈታት እና ወደ ማህበረሰቡ መልሶ የማዋሃድ የቅድመ ማስጀመሪያ ምክክር በመቀለ ተጀመረ!
የቀድሞ ተዋጊዎችን ትጥቅ የማስፈታት፣መበተን እና ወደ ማህበረሰቡ መልሶ የማዋሃድ የቅድመ ማስጀመሪያ ምክክር በትግራይ መዲና መቀለ ተጀመረ።ትናንት ግንቦት 5/ 2016 ዓ.ም በተጀመረው በዚህ ምክክር ላይ የፌደራል መንግሥት ተወካዮች፣ የትግራይ ጊዜያዊ መንግሥት አመራሮች እና የአፍሪካ ኅብረት የስምምነት ክትትል፣ አረጋጋጭ እና አስከባሪ ኮሚቴ አባላት መገኘታቸውን የብሔራዊ ተሐድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ተመስገን ጥላሁን በኤክስ ገጻቸው አስታውቀዋል።
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዚዳንቶች ጄነራል ታደሰ ወረደ እና ጄኔራል ጻድቃን ገብረትንሳኤን ጨምሮ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በዚህ ምክክር ላይ ተዋጊዎችን በመበተን እና ሁለንተናዊ በሆነ መልኩ ወደ ህብረተሰቡ ለማዋሃድ ፕሮግራም፣ ፕሮጀክቶች መንደፍ እንዲሁም የመጀመሪያው የትግበራ እቅድ ላይ ውይይት እንደሚደረግ ተጠቅሷል።
ኮሚሽነሩ በተጨማሪም “ተዋጊዎች የሚበተኑበት የተመረጡ ስፍራዎች የመስክ ጉብኝት እንደሚካሄድም” በትናንትናው ዕለት ባሰፈሩት የኤክስ መልዕክታቸው ጠቁመዋል።ለሁለት ዓመት የዘለቀውን ደም አፋሳሽ የቋጨው የፕሪቶሪያው ግጭትን በዘላቂነት የማስቆም ስምምነት እና የናይሮቢ የትግበራ ሰነድ የትግራይ ኃይሎች የከባድ መሳሪያ ማውረድ የሚካሄደው የውጭ እና የፌደራሉ መከላከያ ሠራዊት ያልሆኑ የክልል ኃይላት ከትግራይ በተመሳሳይ ወቅት ሲወጡ እንደሆነ ጠቅሷል።
ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ:-
https://www.bbc.com/amharic/articles/cv2001z2zdxo
@YeneTube @FikerAssefa
BY YeneTube
Share with your friend now:
tg-me.com/yenetube/50179