tg-me.com/mezmur_Zedawitt/195
Last Update:
ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ ❤️ እንዲህ ያስተምረናል
+++ ለራስህ ነው +++
👉አንተ ሰው! ቊጥር የሌላቸው ክፋቶች ቢኖሩብህም እንኳ በጎ ምግባር በልጅህ ይኖር ዘንድ በማድረግ አካክሰው፡፡
👉 ለክርስቶስ የሚኾን ተሽቀዳዳሚ (ሯጭ) አሳድግ! ወዳጄ ሆይ! እንደዚህ ብዬ ስነግርህ አትፍራ፤ አትሸበርም፡፡
👉ልጅህ እንዳያገባ አድርገው አላልኩህም፡፡ ወደ ገዳም ወስደህ እንድታመነኩሰው ወይም የብሕትውና ሕይወትን እንዲመራ አድርገው አላልኩህም፡፡ እያልኩህ ያለሁት ይህን አይደለም፡፡
👉 ልጅህ ቢመነኩስ እወድ ነበር፡፡ ብዙዎች ወደዚህ ሕይወት እንዲገቡ የዘወትር ጸሎቴ ነውና፡፡ ነገር ግን የምንኵስና ሕይወት [ሳይጠሩ ከገቡበት] ከባድ ሸክም ስለ ኾነ ሰዎች መነኰሳት ካልኾኑ ብዬ ግድ አልልም፡፡
👉ለአንተም እንደዚህ በግድ አመንኩሰው አልልህም፡፡ እያልኩህ ያለሁት ለክርስቶስ የሚኾን ተሸቀዳዳሚ አሳድግ ነው፡፡ በዚህ ዓለም አግብቶ፣ ልጆችንም ወልዶ የሚኖር ቢኾንም እንኳን ገና ከሕፃንነቱ አንሥቶ ሰውን የሚያከብር እንዲኾን አድርገህ አሳድገው ነው፡፡
👉ገና ጨቅላ እያለ በጎ በጎ ትእዛዛት በሕሊናው ጓዳ በልቡናው ሰሌዳ ላይ ከተቀረጸ፥ በሰም እንደ ታተመ ጸንቶ ይኖራል እንጂ ሲያድግ እነዚህን ትእዛዛት ሊያጠፋበትና ሊፍቅበት የሚችል ማንም አይኖርምና፡፡
👉 ልጅህ አሁን ያለበት ዕድሜ ደግሞ በሚያየውና በሚነገረው በሌላም ነገር ኹሉ የሚንቀጠቀጥበት፣ የሚፈራበትና የሚደነግጥበት ዕድሜ ነው፡፡ ስለዚህ ልክ እንዳልደረቀ ሰም እንደምትፈልገው አድርገህ ቅረጸው፡፡
👉እንደዚህ አድርገህ ስታበቃ፥ መልካም ልጅ ቢኖርህ የመጀመሪያው ተጠቃሚ የምትኾነው አንተው ራስህ ነህ፡፡ እግዚአብሔር የሚጠቀመው ከአንተ በኋላ ነው፡፡ ስለዚህ የምትደክመው ለሌላ አካል ሳይኾን ለራስህ ነው፡፡
https://www.tg-me.com/ar/telegram/com.mezmur_Zedawitt
BY መዝሙር ዘዳዊት
![](https://photo.tg-me.com/u/cdn4.cdn-telegram.org/file/tmjrRLQQHLE43laBRm1n1vIkP-iklRexI23ReAc-YBb_TohW4i4WodlFLYED1w90-FBqfCNBAQP81Okw4MxQE7gfbkNnEeMSVcxvGPYSAg14aRyeweKyRUd_OrRpsyF0iAkbzEcuf78z5pJwWSC5vPTRE9iQwPbe2N0tbUZYI9LYbYha02k5A3ZQn-U8e_XVrlwI9aAXM3z_XjLznVY71T5ZpWRg840iF87dg9rNaDmLXRW48iu2l7-IT-bHx3vQME1duCDmHhflVaKU5Z_pVemOOV4wo07Rk0DxDXG5aWdhwEnnLV7m0BQ0CDbeC-m34VeihNRATfATj7ZEOPtfyQ.jpg)
Share with your friend now:
tg-me.com/mezmur_Zedawitt/195