Telegram Group Search
ኢሕአፓ ምን አለ ?

የኢትዮጵያ ሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ / #ኢሕአፓ / ፥ " ኢትዮጵያ እንደ አገር እንድትቀጥል በአገራችን የሕግ የበላይነት ሊኖር ይገባል " አለ።

ፓርቲው በላከው መግለጫ ላይ ፥ " የአገር ሕገ -መንግሥት ዜጎች ብቻ ሳይሆኑ መንግሥትም የሚገዛበት የአገሪቷ ሉዓላዊ ሕግ መሆኑ መታወቅ ይኖርበታል " ብሏል።

" የመንግሥት ፈርጣማ ጉልበት በሕገ መንግሥት የሚገታ ካልሆነ አንድ መንግሥት ሕዝብን ብቻ እንዳፈተተኝ አስተዳድርበታለሁ ካለ ሕገ መንግሥቱ ቅቡልነት አይኖረውም " ሲል ገልጿል።

ፓርቲው " የመንግሥት አካላት ዜጎችን እንደፈለጉ ፦
- ማሰር፣
- መግደል፣
- ማፈናቀል፣
- መደብደብ፣
- ማፈን፣
- ማንገላታት፣
- ማሳደድ፣
- ቤት ንብረታቸውን መቀማት ከጀመሩ መንግሥትንና ሕዝቡን የሚያስተሳስረው ሕግዊ ሥርዓት ትርጉም-አልባ ሆኗል ማለት ነው " ብሏል።

" መንግሥት በቅድሚያ ሕግ አክባሪ ሲሆን ነው ሕግን ማስከበር የሚችለው " ሲልም አክሏል።

" በኢትዮጵያ ውስጥ እስከዛሬ ድረስ የፈሰሰው የደም ጎርፍ ሊበቃ ይገባል " ያለው ኢሕአፓ " የብልጽግና መንግሥት በአገራችን ሠላምን ለማስፈን ተቀዳሚ እርምጃ ፦
° በሕዝብ ላይ ጦር መስበቁን፣
° ሠራዊት ማዝመቱን፣
° በድሮን
° በአየር ኃይል ሠላማዊ ሕዝብን መፍጀቱን በአስቸኳይ ማቆም ይኖርበታል፡፡ ሕዝብን ከዕልቂት ሀገርንም ከውድመት ማዳኛው ብቸኛው መንገድ ዛሬም ሠላማዊ የትግል መንገድ ነውና " ብሏል።

ፓርቲው በመግለጫው ሊቀመንበሩ፣ ረ/ፕሮፌሰር ዝናቡ አበራን ጨምሮ  የታረሱ አባላቱ እንዲፈቱ ጠይቋል።

አባላቱና ሌሎች የእስረኞች አያያዙ እና ቆይታው ሰቅጣጭ በሆነበት " አዋሽ አርባ "  እንደታሰሩ ነው ያመለከተው።

" እስር እና ማሰቃየት የስልጣን መንበርን ለአጭር ጊዜ ሊያጸና ይችል ይሆናል እንጂ ዘለቄታ የለውም " ያለው ፓርቲው " ገዢው ፓርቲ አገራችን እንደ አገር እንድትቀጠል እንዲሁም የወገኖቻችን ደህንነት እንዲጠበቅ ፣ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን እስራቱ ፣ አፈናው ፣ ግድያው ፣ ወከባው ፣ ማስፈራራቱ ፣ ሕግን መጣሱ ማብቃት አለበት " ብሏል።

" የተለየ ሃሳብ ያላቸውን ሁሉ ማፈን አምባገነናዊ የሆነ ሥርዓትን ማንበርና በፍርሃት እየተናጡ ሌሎችንም እፎይታ ነስቶ መቆየትን እንጂ ለአገር ሠላም እና መረጋጋትን አያመጣም፣ ወደ ማኅበራዊና ኤኮኖሚያዊ እድገትም በፍጹም አይወስድም " ሲል አሳውቋል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@tikvahethiopia
#ቢሾፍቱ

ቢሾፍቱ ከተማ የሚገኘው የመከላከያ ሪፈራል ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ዛሬ ተመርቆ ወደ ስራ ገብቷል።

ሆስፒታሉ የኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በተገኙበት ነው የተመረቀው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሆስፒታሉ ፦
- እጅግ ዘመናዊ የሆነ የሞሎኪዩላር ላብራቶሪ፣
- የአጥንት ምርመራ ማዕከል፣
- ባዮሜዲካል ኢንጂነሪንግ ክፍል
- እንደ የኩላሊት እጥበት፣ የነርቭ፣ የሳምባ እና መተንፈሻ አካላት የህክምና አገልግሎቶችን የሚሰጥ እንደሆነ ገልጸዋል።

" በሀገራችን ውስጥ ካሉ ግምባር ቀደም ዘመናዊ ሆስፒታሎች አንዱ ነው " ብለውታል።

ፊ/ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በበኩላቸው " ሆስፒታሉ ለሰራዊቱ ብቻ ሳይሆን ለህዝባችንም ትልቅ ጠቀሜታ ይዞ መጥቷል " ብለዋል።

" ታካሚዎችን ውጭ አገር ሲላኩበት የነበረውን የአሰራር ሂደት ይቀይራል ፤ በሀገር ወስጥ ከፍተኛ ሕከምና መሰጠት ስለሚያስችል የውጭ ምንዛሬ ወጪን ያስቀራል " ብለዋል።

ሆስፒታሉ 425 የህሙማን ተኝቶ መታከሚያ አልጋ አለው ተብሏል።

@tikvahethiopia
#ሀላባ

- " ባለቤቴ ከወንድሙና እህቱ ጋር በመሆን ፊቴ እስኪበላሽ ደበደቡኝ " - ተበዳይ

- " እንዲህ አይነቱን የሴት ልጅ ጉዳት አንታገስም " - የሀላባ ዞን ሰላምና ጸጥታ ቢሮ ሀላፊዉ አቶ ሙደሲር ጉታጎ

በሀላባ ከተማ " ባለቤቴ ከእህትና ወንድሙ ጋር በመሆን አደጋ አድርሶብኛል " ያለች ተበዳይ የህግ ድጋፍ ስጡኝ ስትል በማህበራዊ ሚዲያ ጥያቄ አቅርባለች።

ጉዳዩን የተመለከተው የሀዋሳ የቲኪቫህ ቤተሰብ አባል ባደረገዉ ማጣራት ፥ ተጎጅዋ ፊቷ ላይ ጉዳት መደረሱን በተጨማሪ የሷና የመጀመሪያ ልጇ ሰዉነት ትክሻቸዉ አካባቢ ' ጥርስ ንክሻ ' እንደደረሰባቸዉ ለማወቅ ችሏል።

የግል ተበዳዩዋ እናት ለቲክቫ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ፤ ልጃቸዉና የልጅ ልጃቸዉ በደም ተዘፍቀዉ በምሽት ወደቤት እንደመጡና በወቅቱ ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ ገንተው እንደነበር ገልጸዋል።

የግል ተበዳዩዋ ወ/ሮ አበባ ቦረና ፤ " ምንም እንኳን የጋራ አራት ልጆች ቢኖሩንም ካሁን በፊት በመካከላችን በነበረ ግጭት ምክኒያት በፍርድ ቤት ለመለያየት ጫፍ ከደርሰን በኋላ  በሽማግሌ ተመልሰን አንድ ላይ መኖር ከጀመርን 3 ወር አልሆነም " ብላለች።

" ምንም እንኳን ቀን ላይ ቀላል ጭቅጭቅ ውስጥ ብንገባም ከቤተሰቡ ጋር ሆኖ እንዲህ ያደርጋል ብዬ ፍጹም አልጠበኩም " ስትል ተናግራለች።

" በተለይ ተሰብስበዉ ሲደበድቡኝ ለመገላገል የገባዉን የመጀመሪያ ልጃችን ላይ ላይ በዚህ ልክ ይጨክናል ብዬ አላሰብኩም ነበር "  ብላለች።

ጉዳዩን በተመለከተ የጸጥታ አካላት ምን እየሰሩ ነዉ ? በማለት የጠየቅናቸው የሀላባ ዞን ሰላምና ጸጥታ ሀላፊ አቶ ሙደሲር ጉታጎ ፤ " እንዲህ አይነቱን የሴት ልጅ ጉዳት አንታገስም " ብለዋል።

ጉዳዩን በሰሙ ቅጽበት የከተማው ፖሊስ በፍጥነት ችግር ፈጣሪዎችን  ይዞ እንዲያጣራ ማዘዛቸዉንም ነግረዉናል።

አቶ ሙደሲር  ጉዳዩ ተጣርቶ የሚደረስበትን ውጤት እንደሚያጋሩን ቃል ገብተዋል።

#TikvahEthiopiaFamilyHawassa

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#Update የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆነ። የ2016 የትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) ፈተና የሚሰጥበት ቀን ይፋ ሆኗል። የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከሐምሌ 3 እስከ ሐምሌ 5 ለማህበራዊ ሳይንስ ፤ ከሐምሌ  9 እስከ ሐምሌ 11/2016 ዓ/ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተፈታኞች በበይነ መረብ (Online) እና በዩኒቨርሲቲ ውስጥ በወረቀት…
#Update

የ2016 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ (12ኛ ክፍል) የበይነ መረብ (Online) ተፈታኞች መፈተኛ ይፋ ሆነ፡፡

የ2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በወረቀትና በበይነ መረብ ይሰጣል።

በዚሁ መሠረት በበይነ መረብ ፈተናውን የሚወስዱ ተፈታኞች ከላይ በተገለጸው አድረሻ ብቻ የሚፈተኑ ይሆናል፡፡

ፈተናውን ከመውሰዳቸው በፊት ሁሉም ተፈታኞች በቂ ልምምድ ማድረጋቸው አስፈላጊ በመሆኑ ከዛሬ ቅዳሜ ግንቦት 10 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በአድራሻው ተፈታኞች በሚገኙበት ክልል የተደለደሉ ስለሆነ ልምምድ ማድረግ ይችላሉ ተብሏል።

ተፈታኞች ልምምድ ለማድረግ ከዚህ በፊት ለክልል / ከተማ አስተዳደር ቀድሞ የተላከውን የይለፍ ቃልና ስም (User Name and Password) ከየትምህርት ቤቶቻቸው ማግኘት እንደሚችሉ ተገልጿል።

መጀመሪያ ወደ መፈተኛ ሲሰተሙ እንደገቡ የማይረሱትን የግላቸውን የይለፍ ቃል የሚቀይሩ ይሆናል፡፡

ተፈታኞች #ከተደለደሉበት_ክለስተር_ዉጪ ሲሰትሙን መጠቀም #የማይችሉ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

@tikvahethiopia
2024/05/19 06:40:49
Back to Top
HTML Embed Code: