Telegram Group Search
ስልኮትን ለመቀየር አስበዋል?

  አዳዲስ እንዲሁም በመጠኑ ያገለገሉ ስልኮችን ከተሟላ ዋስትና እና ጥገና ጋር ይዘን ቀርበናል📱ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን ይጎበኙ

https://www.tg-me.com/phonehub27

📞 0996544119

📩 inbox @kidaa3535

📍አድራሻ- ቦሌ ከሸገር ህንፃ አጠገብ

📨 ክፍለ ሀገር ላላቸሁ ደንበኞችቻችንም በ DHL መላክ ጀምረናል
የፕላስቲክ አምራቾች የወረቀትና የጨርቅ ከረጢቶችን በአፋጣኝ ማምረት እንዲጀምሩ ማሳሰቢያ ተሰጠ

አካባቢን ሊበክሉ የሚችሉ ስስ ፕላስቲኮችን የሚያመርቱ ድርጅቶች የአካባቢ ብክለትን የሚቀንሱ የወረቀትና የጨርቅ ከረጢቶች በአፋጣኝ ማምረት እንዲጀምሩ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን አሳሰበ፡፡

ፕላስቲክ በማምረት የተሰማሩ ድርጅቶችና ባለቤቶች ከተፈቀደላቸው 0.03 ማይክሮ ሜትር በታች ሲያመርቱ ከተገኙ፣ ከመዝጋታቸው ባሻገር፣ ከሦስት ዓመት እስከ አሥር ዓመት የእስር ቅጣት እንደሚያስከትልባቸው ሪፖርተር አስነብቧል።

በተጨማሪም ለኅብረተሰቡ ዳቦ የሚያከፋፍሉና ሌሎች ሸቀጦችን በፕላስቲክ ምርቶች ጠቅልለው የሚሸጡ ቸርቻሪዎችም ሆኑ አከፋፋዮች፣ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ይደረጋል ተብሏል።

ሸማቾች ማንኛውንም ዕቃ ሲሸምቱ የፕላስቲክ ውጤቶችን ከመጠቀም ይልቅ፣ ከወረቀትና ከጨርቅ የተሠሩትን መጠቀም ይገባል በማለት ባለስልጣኑ አመልክቷል።

@TikvahethMagazine
የፌደራል መንግሥት በኤሌክትሪክ እና በውሃ አገልግሎት ላይ ቫት የሚጥል ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ አቀረበ

የኤሌክትሪክ እና የውሃ አገልግሎት በገደብ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) እንዲከፈልባቸው የሚያደርግ ረቂቅ አዋጅ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀረበ።

ከታክሱ ነጻ የሚሆኑት የገንዘብ ሚኒስቴር በሚያወጣው መመሪያ ከሚወሰን በታች የኤሌክትሪክ እና ውሃ ፍጆታ ያላቸው እንደሆኑ ተገልጿል።

አዋጁ ሲጸድቅ ለሁለት አስርት ዓመታት በስራ ላይ ቆየውን የተጨማሪ እሴት ታክስ አዋጅ እና ከዛ በኋላ እሱን ለማሻሻል ሁለት ጊዜ የወጡትን የማሻሻያ አዋጆች ሙሉ በሙሉ የሚሽር ነው ተብሏል።

“አነስተኛ ገቢ ያለው የህብረተሰብ ክፍል ያለበትን ወጪ ለማርገብ ሲባል” የኤሌክትሪክ እና የውሃ አገልግሎት ከታክሱ ነጻ ተደርገው እንደነበር ሲገለፅ ረቂቁ “የተጨማሪ እሴት ታክስ ከሚታይበት ጉድለት አንዱ እና ዋነኛው በርካታ ዕቃዎች እና አገልግሎቶች ከታክሱ ነጻ መደረጋቸው ነው” ይላል።

በረቂቅ አዋጁ ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ በማድረግ የተሰጠውን “ልዩ መብት” እንደገና በመፈተሽ ማስተካከያዎች መደረጋቸውን ማብራሪያው ይገልጻል።

ከታክስ ነጻ ተደርገው አሁን ታክስ እንዲከፈልባቸው ከተደረጉ አግልግሎቶች መካከል የውሃ እና ኤሌክትሪክ እንዲሁም የትራንስፖርት አገልግሎቶች ይገኙበታልም ተብሏል።

በስራ ላይ ያለው አዋጅ የኤሌክትሪክ፣ የኬሮሲን [ናፍጣ] እና የውሃ እንዲሁም የትራንስፖርት አገልግሎትን ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነጻ እንዲሆኑ እድርጎ ነበር።

ይህን አዋጅ የሚሽረው አዲሱ ረቂቅ አዋጅ ግን የውሃ የኤሌክትሪክ፣ የውሃ እና የትራንስፖርት አገልግሎቶች በገደብ ታክስ እንዲከፈልባቸው አድርጓልም ነው የተባለው።

Credit: BBC Amharic

@TikvahethMagazine
ቦይንግ የ346 ሰዎችን ህይወት በቀጠፈው የ737 ማክስ አውሮፕላን አደጋ ክስ ሊመሰርትበት እንደሚችል ተገለፀ

በኢትዮጵያው አየር መንገድ እና የኢንዶኔዥያው የ737 ማክስ 9 አውሮፕላን አደጋዎች የ346 ሰዎችን ህይወት በቀጠፈው አደሳ ምክንያት ቦይንግ ላይ ክስ ለመመስረት እያጤነ እንደሆነ የአሜሪካ የፍትህ መስሪያ ቤት አስታወቀ።

ቦይንግ የሚያመርታቸውን አውሮፕላን ምርቶች ደኅንነት እና ጥራት ለማስጠበቅ ከ3 ዓመት በፊት ከአሜሪካ የፍትህ ሚኒስቴር ጋር የገባውን የቁጥጥር መርሃ ግብር ስምምነት መጣሱንም መስሪያ ቤቱ ስለመግለፁ ቢቢሲ በዘገባው አመልክቷል።

ቦይንግ ስምምነት ጥሷል የተባለውን ክስ አስተባብሏል። ይህ አስከፊ የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን አደጋ በኢትዮጵያው 157 እንዲሁም በኢንዶኔዥያው አየር መንገድ 189 ሰዎች ህይወት መቅጠፉ ይታወሳል።

@TikvahethMagazine
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Big5Ethiopia

ቢግ ፋይቭ ኮንስትራክት ኢትዮጵያ አውደ ርዕይ ያካተተው የሲፒዲ ነጥብን የሚያስገኘው መድረክ ስድስት የሙያ ዘርፎችን የያዘ ነው። እነዚህም ቴክኖሎጂ፣ የፕሮጀክት አስተዳደር፣ አርክቴክቸርና ንድፍ፣ ዘላቂነት(ሰስተነብሊቲ)፣ ምህንድስና እና መሠረተ ልማት ናችው።

ሁሉም ውይይቶች በየራሳቸው ብቁ ባለሙያዎች የሚመሩ ሲሆን፣ ፋይዳ ያላቸው እይታዎችንና አመለካከቶችን ያጋራሉ።

የውሃ አቅርቦት መሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች፣ ሞጁላር ግንባታ በዲጅታል ንድፍ ልምምድ ውስጥ፣ የመገኛ ቦታ(geospatial) ቴክኖሎጂና ቢም እንዲሁም አርክቴክቸር በከተማ ቅየሳ ውስጥ ያለው ሚና፣ ከሚዳሰሱ ርዕሶች መካከል ይገኛሉ።

በነጻ ለመጎብኘትና ለመታደም አሁኑኑ ይመዝገቡ፡- https://bit.ly/3UsrL5I
የሁነቱን የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉ፡-https://www.tg-me.com/big5ethiopia
ስልኮትን ለመቀየር አስበዋል?

  አዳዲስ እንዲሁም በመጠኑ ያገለገሉ ስልኮችን ከተሟላ ዋስትና እና ጥገና ጋር ይዘን ቀርበናል📱ለበለጠ መረጃ ቻናላችንን ይጎበኙ

https://www.tg-me.com/phonehub27

📞 0996544119

📩 inbox @kidaa3535

📍አድራሻ- ቦሌ ከሸገር ህንፃ አጠገብ

📨 ክፍለ ሀገር ላላቸሁ ደንበኞችቻችንም በ DHL መላክ ጀምረናል
ትምሕርት ቤቶች በተዘጉባቸው የአማራ ክልል አካባቢዎች ሴት ተማሪዎች በግዳጅ እየተዳሩ ነው ተባለ

በአማራ ክልል የሰላም እጦት ሰበብ በአንዳንድ አካባቢዎች ትምህርት ቤቶች በመዘጋታቸው፣ ሴት ተማሪዎች ወደ ጋብቻ በግዳጅ እየገቡ እንደሆነ ነዋሪዎችና ወላጆች መናገራቸውን ዶይቼ ቬለ ዘግቧል።

በክልሉ ባለፉት 9 ወራት 1132 መዳር ከሚገባቸው እድሜ በታች የሆኑ ሴቶች ለመዳር መዘጋጀታቸውን ጥቆማ እንደደረሳቸው የአማራ ክልል ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የህፃናት መብትና ድህንነት ማስጠበቅ ዳይሬክተር አቶ አሻግሬ ዘውዴ ተናግረዋል።

በዚህም መሰረት የ335ቱ ተማሪዎች የጋብቻ ዝግጅት እንዲቋረጥ የተደረገ ሲሆን 216 ደግሞ የእድሜ ምርመራ ተደርጎ እድሜያቸው ባለመድረሱ የትዳር ዝግጅቱ መቋረጡን ዳይሬክቱሩ ጠቁመዋል።

ያም ሆኖ 192 ሴቶች ከእድሜያቸው በታች መዳራቸውንና ድርጊቱን ለመከላከል አሁን ያለው የፀጥታ ሁኔታ አንድ አንቅፋት እንደሆነም ተናግረዋል።

በ9 ወሩ 41 ጠለፋ በክልሉ ሲመዘገብ 354 ደግሞ አስገድዶ መድፈር ሪፖርት እንደተደረገና በድርጊቱ የተሳተፉ 79 ግለሰቦች ከ3 አስከ 14 ዓመት በሚደርስ የፍርድ ቤት የእስር ቅጣት እንደተወሰነባቸውም ነው የተገለፀው።

@TikvahethMagazine
ከ12 ሀገራት 122 ተሳታፊዎች አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች እና መፍትሄዎችን የሚያቀርቡቡት የንግድ ትርኢት ተከፈተ

ፕራና ኢቨንትስ እና የጀርመኑ ፌርትሬድ በጋራ ያዘጋጁት እና ከ12 ሀገራት 122 ተሳታፊዎች አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን እና መፍትሄዎችን ለኢትዮጵያ ገበያ የሚያቀርቡቡት 6ኛው አግሮ ፉድ ፕላስት ፕሪንት ፓክ ኢትዮጲያ የንግድ ትርኢት  ተከፈተ።

የንግድ ትርኢቱ ከግንቦት 8-10 /2016 ዓ/ም በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ የሚቆይ ሲሆን በግብርና፣ በምግብና መጠጥ ግብዓትና ማቀነባበሪያ ቴክኖሎጂ፣ እንዲሁም በፕላስቲክ ህትመት እና የማሸጊያ ቴክኖሎጂ እና መፍትሄዎች ላይ ትኩረት ያደረጉ ኩባንያዎች ይሳተፉበታል ተብሏል።

ተሳታፊዎቹ ከቻይና፣ ኢትዮጵያ፣ ፈረንሳይ፣ ጀርመን፣ ህንድ፣ ጣሊያን፣ ኬንያ፣ ታይዋን፣ ታይላንድ፣ ቱርክ፣ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ እና እንግሊዝ የተውጣጡ ሲሆን 122 ተሳታፊዎች አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን እና መፍትሄዎችን ለኢትዮጵያ ገበያ ያቀርባሉም ነው የተባለው።

@TikvahethMagazine
ለፆታዊ ጥቃት ሰለባዎች ባደረገችው ድጋፍ ከካናዳው ድርጅት ዕውቅና የተሰጣት ሲስተር ካህሳ ሀጎስ . . .

በአዲግራት ሆስፒታል ነርስ የሆነችው ሲስተር ካህሳ ሀጎስ በትግራይ ጦርነት ወቅት ጾታዊ ጥቃት ለደረሰባቸው ሴቶች ላደረገችው ሙያዊና ሰብአዊ ድጋፍ ግሎባል አፌይርስ ከተባለው የካናዳ ድርጅት ሽልማት ተበርክቶላታል።

ሲስተር ካህሳ ሀጎስ፤ የካናዳ ድርጅት ከተባበሩት መንግስታት ጋር በመተባበር የሚያበረክተው “ሰላምና ደህንነት በሴቶች” የተሰኘው ሽልማት ተቀባይ ሆናለች።

ካህሳ “ከ2013 ጀምሮ ላበረከትኩት አስተዋጽዖ የተሰጠኝ ነው። ለሁለት ዓመታት ያህል የፆታዊ ጥቃት ሰለባዎችን እንከባከብ ነበር” ስትል ለቢቢሲ ተናግራለች።

የትግራይ ኃይሎች እና የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ለሁለት ዓመታት ባደረጉት ጦርነት ምክንያት በርካታ ሴቶች፣ እናቶች እና ሕፃናት የፆታዊ ጥቃት ሰለባ መሆናቸውን በርካታ የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች አረጋግጠዋል።

ጦርነቱ ሲቀሰቀስ ሲስተር ካህሳ ሀጎስ በአዲግራት ሆስፒታል የእናቶች እና ህጻናት እንክብካቤ ክፍል አስተባባሪ ሆና ትሰራ ነበር።

ውጊያው ሲባባስ የጾታዊ ጥቃት ሰለባ ሆነው ወደ ሆስፒታል የሚመጡ ሴቶች እና እናቶች ቁጥር እየጨመረ መጣ። ሲስተር ካህሳ እንደምትለው ጦርነቱን ተከትሎ ከ4 ሺህ በላይ ተጎጂዎች ወደ አዲግራት ሆስፒታል መጥተው ሪፖርት አድርገዋል።

ሲስተር ካህሳ በጦርነቱ ምክንያት ተጎጂ ለሆኑ ከ400 በላይ ለሚሆኑ ሰዎች ቤት ተከራይታ፤ ሙያዊ ክትትልና ድጋፍ ማድረጓ ተነግሯል።

እሷ ተጎጂዎችን ለመርዳት በምታደርገው ጥረት በሆስፒታሉ ፆታዊ ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶች የሚረዱበት የሥነ-ልቦና፣ የሥነ-አእምሮ እና የሥነ-ተዋልዶ ማዕከል እንዲከፈት ተደርጓል። ለአበርክቶዋም አፌይርስ ከተባለው ድርጅት እውቅና ማግኘቷ ነው የተገለፀው።

@TikvahethMagazine
አቅማችሁን መፈተሻ ምርጥ ቻሌንጅ ከExam Time

የ9ኛ እና የ11ኛ ክፍል ትምህርቶችን በቀረችው አጭር ጊዜ ሙሉ ለሙሉ ከልሳችሁ መጨረስ ትፈልጋላችሁ?

Exam Time አፕሊኬሽን Challenge Phase ይዞላችሁ ቀርቧል። አፕሊኬሽኑ የተስተካከለ እና ለመከተል ቀላል የሆነ የጥናት ፕሮግራምን ጨምሮ አጫጭር ኖቶችን እንዲሁም አጋዥ ቪዲዮዎችን አንድላይ ይዟል። ከ Playstore ላይ በማውረድ Exam Timeን ተቀላቀሉ።

Download from here ➝ Playstore

Follow us on:

Instagram | Telegram | Youtube | Facebook | Tiktok |
🏠 ለ 1 ወር ብቻ የሚቆይ ልዩ የበአል ቅናሽ !!

📌ጊዜዉን የሚመጥን አስተማማኝ እና ትርፋማ የሚያደርግዎትን የኢንቨስትመንት አማራጮችን በብስራተ ገብርኤል ,በቦሌ ደምበል, በገርጂ መብራት ሃይል,በጃክሮስ,በአያት,በመካኒሳ አቅርበንልዎታል።

📌በዚህ ወቅት የገንዘብ የመግዛት አቅም በወደቀበት ዘመን ተሻጋሪ አማራጮችን ማየት ብልህነት ብቻ ሳይሆን ትልቅነትም ጭምር ነው።

📌 ከዘመን ዘመን እንደደመቁ እና እንዳማሩ የሚዘልቁ ቅንጡ አፓርትመንት ቤቶችን 15% ቅድመ ክፍያ ስንጋብዝዎ በደስታ ነው።

📌ግንባታቸው 100% ያለቀ እንዲሁም በግንባታላይ ያሉ ቤቶችንና የንግድ ሱቆችን

📌 የባንክ ብድር የተመቻቸለት

📲+251-924833733
📲+251-947996316

https://www.tg-me.com/Selinarealestate1
" በሀገር ውስጥ ለ47 ሺ ከሀገር ዉጭ ደግሞ ለ2 ሺ 583 ወጣቶች የስራ እድል ፈጥሬአለሁ " - የሲዳማ ክልል ስራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች ልማት ቢሮ

የሲዳማ ክልል ስራ ክህሎትና ኢንተርፕራይዞች  ልማት ቢሮ ከሀገር ውስጥ ከ47 ሺ በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች ከሀገር ዉጭ ደግሞ ለ2 ሽህ 583 ወጣቶች የስራ እድል መፍጠሩን አስታወቀ።

በዚህም ቢሮው እቅዱን ከ100 ፐርሰንት በላይ ማሳካቱን ሲገልፅ በሚቀጥሉት ስድስት ወራት ከሰላሳ ሽህ በላይ የስራ እድል እንዲፈጠር ለመስራት በእቅድ መያዙን ገልጿል።

ለዚህ ሲባል በክልሉ አምስት መአከላት ማለትም በአራቱ ዞኖችና በሀዋሳ ከተማ ለርካታ ወጣቶች የማይንድ ሴት ስልጠና መሰጠቱ ሲገለፅ ከዚህ ቀደም በጥቂት ባለሀብቶች ተይዞ የቆየው የመአድን ዘርፍ አሁን ላይ በዲግሪና በዲፕሎማ  ለተመረቁ ወጣቶች መሰጠቱ ተገልጿል።

@TikvahethMagazine
በአዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ ዋርካ አካዳሚ የተሰኘ አንደኛና መለስተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቀ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 አቤም አቤም ሆቴል ጀርባ ከካባቢ፣ ዋርካ አካዳሚ የተሰኘ አንደኛና መለስተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መርቋል።

አካዳሚው በ2017 የትምህርት ዘመን ከ1ኛ እስከ 8ኛ ክፍሎችን በመክፈት ትምህርት እንደሚጀመር ተጠቁሟል።

በተጨማሪም ትምህርት ቤቱ የበለጠ ውጤት የሚያመጡ ተማሪዎችን ለማበረታታት በየዓመቱ በሚኖር መስፈርት መሰረት የአንድ ዓመት የትምህርት ቤት ክፍያ ስኮላርሽፕ እንደሚሰጥ የትምህርት ቤቱ ኃላፊዎች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ጠቅሰዋል።

@TikvahethMagazine
በአሶሳ ዞን ባምበሲ ወረዳ ሁለት የ8 አመት ህፃናትን የደፈረ ጎልማሳ በ10 አመት ፅኑ እስራት ተቀጣ

በአሶሳ ዞን ባምበሲ ወረዳ መንደር 44 ቀበሌ በሁለት የ8 አመት ህፃናት ላይ የግብረ- ስጋ ድፍረት ወንጀል የፈፀመ የ41 አመት ጎልማሳ በ10 አመት ፅኑ እስራት መቀጣቱን የአሶሳ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አስታወቀ።

ተከሳሽ አብዱ ወዚር መሀመድ ነዋሪነቱ አሶሳ ዞን ባምበሲ ወረዳ መንደር 44 ቀበሌ ሲሆን በጥር 3/2016 ዓ/ም ከቀኑ 9 ሰዓት በአካባቢው የማሽላ ሰብል ማሳ ውስጥ በመደበቅና ህፃናቱን " ጥንቅሽ ልስጣችሁ ብሉ " ብሎ በመጥራት ወደ ውስጥ ካስገባቸው በኋላ ሁለቱንም በሀይል አስሮ የግብረ ስጋ- ድፈረት መፈፀሙ ተገልጿል።

በተጨማሪም በህፃናቱ ላይ ያደረሰባቸውን ሁለንተናዊ ጉዳትም ለማንም ትንፍሽ እንዳይሉ አስፈራርቶና በገንዘብ አታሎ ከቦታው መሰወሩ ተጠቁሟል።

በጉዳዩ ዙሪያ ከአካባቢው ህብረተሰብ ጥቆማና  መረጃ የደረሰው ፓሊስም ወንጀለኛውን በቁጥጥር ስር አውሎ በሰውና የሰነድ ማሰረዳዎች አረጋግጦ ውሳኔ እንድያገኝ ለባምበሲ ወረዳ ፍርድ ቤት አቅርቧል።

የወረዳው ፍርድ ቤትም የክስ መዝገቡን ዝርዝር ማስረጃ በመመርመር አቃቢ ህግ በከሰሰው ወንጀልና ባቀረባቸው የሰውና የህክምና ማስረጃዎች መሰረት ግለሰቡን በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ደ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 60(ሐ)እና 627(1)ስር የተደነገገውን በመተላለፍ ጥፍተኛ በማድረግ በ10 አመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ወስኗል።

ይሁን እንጅ ግለሰቡ የወረዳው ፍርድ ቤት ሚያዝያ 17/2016 ዓ.ም የወሰነበት ውሳኔ ላይ ቅር በመሰኘት ሚያዝያ 19/2016 ዓ.ም ይግባኝ ብሎ ጉዳዩ በአሶሳ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በኩል እንዲታይ ተጠይቋል።

የባምበሲ ወረዳ ፍርድ ቤት የሰጠውን የእስር ውሳኔ ሲያከራክርና ሲመለከት የነበረው የአሶሳ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ከትላንት በስቲያ በዋለው ሁለተኛ የምድብ ወንጀል ችሎት  የ10 አመት ፅኑ እስራት ውሳኔውን " በአስተማሪነቱ በማፅደቅ መዝገቡን ዘግቷል" በማለት የአሶሳ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት አሳውቋል።

@TikvahethMagazine
#ጥቆማ

የኢትዮጵያ ደም እና ህብረ ህዋስ ማዕከል በነገው እለት ግንቦት 10/ 2016 ዓ/ም ስታዲየም በሚገኘው የቀይ መስቀል ማህበር ጊቢ ውስጥ ከጠዋቱ 4 እስከ 11 ሰዓት የደም ልገሳ መርሃ ግብር ማዘጋጀቱን ለቲክቫህ በላከው መረጃ ገልጿል። ስለሆነም በመርሃግብሩ ላይ እንድትሳተፉ ጥሪ አቅርቧል።

ደም ሁሌ ተፈላጊ እንዲሆን የሚያረጉት ምክንያቶች ምንድናቸው ?

- የተፈጥሮ እና የ ሰው ሰራሽ አደጋዎች መጨመር
- የድንገተኛ ወረርሽኝ መከሰት
- ዘመናዊ የህክምና አገልግሎት መስፋፋት
- የደም እና የደም ተዋፅኦ የአገልግሎት ጊዜ አጭር መሆን/ ፕላስማ 1 አመት
- ደም አማራጭ/መትክ/ የሌለው መድሀኒት መሆኑ 
- ደም በ አይነት ብቻ ለ ታካሚው የሚሰጥ መሆኑ

ደም የሚያስፈልጋቸው እነማን ናቸው?

- የደም ማነስ ህመምተኞች
- ከፍተኛ የቀዶ ህክምና የሚስፈልጋቸው እና የካንሰር ህመምተኞች
- በወሊድ ወቅት ብዙ ደም የሚፈሳቸው እናቶች
- በተለያዩ የጤና ችግሮች ሳቢያ እንደተወለዱ ደም ሚፈሳቸው ህፃናት
- በዘር ውርስ የሚመጡ የደም መድማትና መሟሸሽ ችግሮች ያሉባቸው።

ደም ከመለገስ የሚገኙ ጥቅሞች ምንድናቸው?

- የደም አይነት ያለ ክፍያ ማወቅ ይቻላል።
- ሰዎች በ ደም እጥረት ምክንያት አይሞቱም።
- የጤና ጠቀሜታ እንዳለው በ አንዳንድ ምርምሮች ሲገለፅ ማለትም ከ ሌሎች ደም ከማይለግሱት የተሻለ በ heart attack  የመጋለጣቸው አድል አነስተኛ ነው።

ለበለጠ መረጃ፦ በ 0940512564 ይደውሉ

@TikvahethMagazine
ባለፉት አስራ ስድስት ቀናት በጉጂ፣ በምዕራብ እና ማዕከላዊ ኢትዮጵያ በተከሰረተ ጎርፍ የ14 ሰዎች ህይወት አለፈ

ባለፉት 16 ቀናት በምዕራብ ጉጂ፤ በሲዳማ፤ ማእከላዊ ኢትዮጵያ እና ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በተከሰተ የጎርፍ አደጋ የ14 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ከ106 ሺ ሰዎች በላይ መፈናቀላቸውን የአውሮፓ ኮሚሽን የአስቸኳይ ድጋፍ ማስተባበሪያ ማዕከል ባወጣው ሪፖርት አስታውቋል፡፡

በሪፖርቱ መሰረት ፦

- በምእራብ ጉጂ 120 ሺ 481 ሰዎች በጎርፍ ተጠቅተዋል፡፡ በተጨማሪም 102 ሺ 128 ሰዎች ተፈናቅለው የ5 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተመላክቷል፡፡ ከ 3ሺ በላይ ቤቶች በከፊል እና ሙሉ ለሙሉ መውደማቸው ሲገለጽ ከፍተኛ የምግብ ዋስትና ችግር እንዳለ ተመላክቷል፡፡

- በደቡብ ኢትዮጵያ ደግሞ 4ሺ ሰዎች በጎርፍ ተጠቅተው የ3 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተጠቁሟል፡፡

- በማእከላዊ ኢትዮጵያ 4ሺ 65 ሰዎች ሲፈናቀሉ የ6 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተመላክቷል፡፡

በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች በግጭቶችና ከአየር ንብረት ጋር በተያያዘ በሚደርሱ ድንገተኛ አደጋዎች ምክንያት አፋጣኝ ምላሽ ለማድረግ የሚያስችል የአቅም ውስንነት እንዳለ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር አሳውቋል፡፡

ፎቶ፦ ፋይል

@TikvahethMagazine
2024/05/18 01:59:56
Back to Top
HTML Embed Code: