Telegram Group Search
💒❤️💒

👰" #ውበት_ሐሰት_ነው፤ ደም ግባትም ከንቱ ነው #እግዚአብሔርን_የምትፈራ ሴት ግን እርሷ #ትመሰገናለች" (ምሳሌ ፴፥፴፩።)🙇‍♀

#እንኳን_አደረሳቹሁ_የእምየ_ተዋሕዶ_ልጆች

(፮🕯) እናታችን ቅድስት አርሴማ

#ጠብቂኝ_በዘንባባሽ🤲😢

#ጠብቂኝ_በቃልሽ ማሪኝ በዘንባባሽ
ከንቱ ሆኜ እንዳልቀር የማልረባ ርካሽ
አንቺው ጋሻ ሁኚኝ በፍቅርሽ እናቴ
#በረከት_ሙይልኝ በደሳሳ ቤቴ
ታምርሽን ልናገር እኔስ ለአለም
ክብሩን ገልፆብሻል #መድሀኒአለም
አርበኛ ሰማዕት ኮከብ ናት ፀሐይ
ከምድር ላይ ሁና ታየች በሰማይ
ለአንደበቴ ማር ነሽ ለከንፈሬ ወይን
#ነፍሴን_ደስ ይላታል ካንቺ ጋር ስሆን
ገድልሽን ባወራ ከእንቅልፌ ነቅቼ
በብርሀን ወጣሁ ጨለማውን ትቼ
#ፀበልሽን_ጠጣሁት ፀጋሽን አስቤ
ነፃሁኝ ከኃጢአቴ በደሌን ታጥቤ
ተጽፈሻል #አርሴማ_በልቤ

⛪️ #ቅድስት አርሴማ"#እግዚአብሔርን የምትፈራ በቅዱሳን #ሰማዕታት ማህበርና በገነት #በሮች የሕይወት#ፍሬ ያፈራች ሰማዕት ናት።

ፀሎት #ወበረከቷ የየኃሉ ምስሌነ
የእናታችን #የቅድስት_አርሴማ
ፀሎት በረከቷ ከእኛ ጋራ ፀንቶ #ለዘላለም ይኑር
#አሜን
#አሜን
#አሜን🤲💒
መልካም ቀን ቤተሰብ😍🙏😍@ortodox_27
Forwarded from 😭............
"ነገ ...7 ...🕯

አጋእዝተ ዓለም ቅድስት ሥላሴ ናቸው

የአብርሃሙ ሥላሴ ወቶ ከመቅረት ከክፉ ነገር ሁሉ ይሰውሩን🙏
@ortodox_27
የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መዝሙር 🇪🇹
Photo
. [ #ቅድስት_ሥላሴ ]

በሰባተኛይቱ ሰማይ ጽርሐ አረያም፣ በኪሩቤል ላይ ዙፋናቸው የተዘረጋ ነው! አይመረመሩም ድንቅ ነው፣ እንደተነገረ ከንፋስ ነፍስ፣ ከነፍስም መላእክት እንደሚረቁ፣ #ሥላሴ ከሰው ህሊና! ከመላእክትም ሃሳብ እጅጉን ይረቃሉ! ወደ እነርሱ መቅረብ የሚቻለው ማንም የለም! ሁሉን ፈጠሩ፣ አከናውነው አበጃጁት፣ በሰማይ እና በምድር ሁሉ ከእነሱ የተገኘ ነው! መሰወሪያቸው የእሳት መጋረጃ፣ ዙፋናቸውም የእሳት ነበልባል ነው! በላይ እና በታች ጠፈር እና መሠረት እነርሱ ናቸው!

[አብ] የእራሱ ገጽ፣ የእራሱ አካል፣ የእራሱ መልክ አለው! [ወልድም] የእራሱ ገጽ፣ የእራሱ አካል፣ የእራሱ መልክ አለው፣ [መንፈስ ቅዱስም] የእራሱ ገጽ፣ የእራሱ አካል፣ የእራሱ መልክ አለው።

ሶስት አካል፣ ሶስት ስም፣ ሶስት ግብር ሲኖራቸው፣ አንዲት ባህሪ፣ አንዲት ስልጣን፣ አንዲት አገዛዝ አላቸው! ለግዛታቸውም ወሰን እና ልክ ያለው አይደለም፣ ዓለም እና መላዋ በውስጧ ያለው ሁሉ ግዛታቸው ነው! ከእነርሱ ሊሰወር የሚቻለው ማንም የለም! በ "99"ኙ ነገደ መላእክትም የሚመሰገኑ ናቸው! እልፍና አእላፋትም ምስጋናቸውን ያበዛሉ! በምድርም ልባቸው ከቀና ከደቂቀ አዳም ምስጋና ይቀርብላቸዋል! ምስጋናቸውም የሚቋረጥበት ጊዜ እና ዘመን የለም! ዘመናትን አልፎ ይሻገራል እንጂ!

ከፍ ብሎ በላይ በሰማይ የሚኖር ይህንን የመለኮት አኗኗር እንመረምር ዘንድ አይቻለንም፤ ከክብራቸው በጥቂት እናውቅ ዘንድ እነርሱ ገለፁልን እንጂ፤ ይህም የአንድነታቸው እና የሶስትነታቸው ነገር ነው! #አብ ልብ ነው፤ በአብ ልብነት ያስባሉ! #ወልድ ቃል ነው፤ በወልድ ቃልነት ያከናውናሉ! #መንፈስ_ቅዱስ እስትንፋስ ነው፤ በመንፈስ ቅዱስ እስትንፋስነትም ያፀናሉ!!

ቅድስት ሥላሴ በበረከት አይለዩን!

[ አሜን ]

. #ይቆይ//
🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁

⛪️ #ሳናቋርጥ_የሦስቱን_ምስጋና አንድነት እንናገራለን፥ #ፍጹም_አሸናፊ አንድ አምላክ #እግዚአብሔር_አብ_ወልድ_መንፈስ ቅዱስ ኾይ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ ተብለኽ የምትመሰገነው #ምስጋናኽ_በሰማይ በምድር ምሉዕ ነው፡፡"
(#ሃይማኖተ_አበው_ዘጎርጎርዮስ)

#እንኳን_አደረሳቹሁ_የእምየ_ተዋሕዶ_ልጆች

ለአጋእዝተ ዓለም ቅድስት ሥላሴ

🕯🦋 #ቅድስት_ሥላሴ ⛪️❤️

የሥላሴ ዙፋን #አሰቦት_ገዳም
የመምሬ አድባር ነሽ ቤቱ ለአብርሐም ።
ጌታ ቀራንዮ
#አርብ_እለት ተሰቅሎ ከፈሰሰ ደሙ ፣
ቃል ኪዳን ቢረጨሽ ዑራኤል በስሙ ፤
ደብረ ወገግ #ታየ_ብርኅን ለአለሙ ።
ቅዱሳን አባቶች የተሰወሩብሽ ፣
ፃድቃን #ሰማእታት_የተሰየፉብሽ
ኪሩቤል ተነጥፈው የተጋረዱብሽ ፤
የመላዕክት ዜማ የያሬድ ውዳሴ ፣
ሠርክ የሚሰዋብሽ ስብሐት ለሥላሴ ፣
የደናግል አምባ #የመናኞች_ዋሻ
ሀገረ እግዚአብሔር የክብሩ መንገሻ ፤
የአራዊቶች ድንኳን የበረሀ ገነት ፣
እነ አባ ሳሙኤል ያነፁሽ ሰገነት ።
የብርሐን አንባ ምስራቅ ፀሐይ ፋና ፣
#የድንግል_ማርያም ልጅ ያረገሽ ገናና ፣
እሳት የከበበሽ ታቦር ደብረ ሲና ፣
የስላሴ ምድር ጥንታዊ መዲና ፤
አንቺ ነሽ #ኢትዮጵያ የፈጣሪ መና ።
አርማሽ አስጊጦት በሦስቱ ቀለም ፣
አንድ አርጎሻል ቃሉ #እስከ_ዘላለም

#ሥላሴ_ምሕረቱን ከእኔ ያላራቀ አምላኬ ይክበር ይመስገን። በእውነት የክርስቲያኖች አምላክ ታላቅ ነው። በእርሱ የሚደገፉ ልዑሉንም #መጠጊያ_የሚያደርጉ ታላቅና ዘላለማዊ ክብር ይጠብቃቸዋል። የእጁ ስራዎች የሆኑት ይጠፉ ዘንድ ፈቃዱ አይደለምና። እግዚአብሔር ምስጉን ነው። #የአብ_የወልድና_የመንፈስ ቅዱስም አንዲት መንግስት የተቀደሰች ናት።(ቅዱስ ኒፎን)


አጋእዝተ ዓለም ቅድስት ሥላሴ ናቸው

የአብርሃሙ ሥላሴ ወቶ ከመቅረት ከክፉ ነገር ሁሉ ይሰውሩን🙏

ወስብሐት #ለእግዚአብሔር

🤲 🤲 🤲
#አሜን......... 🧡 ......... #አሜን
#አሜን🙏³

🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁🍁@ortodox_27
ግንቦት 7 ቀን
💌💌💌💌
ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ
💌💌💌💌💌💌
በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ከሐዋርያት ቀጥሎ የቅዱስ አትናቴዎስን ያህል
ስለ ሃይማኖት የተዋጋ ቅዱስ ፈልጐ
ማግኘት አይቻልም::
💌💌💌💌💌💌
ቅዱስ አትናቴዎስ ማን ነው?
የግንቦት ስንክሳር ስለ ቅዱሱ ምን ይነግረናል?
ሊንኩን ሲጫኑ ሙሉ ታሪኩን ያደምጣሉ
ሞት የሌለበት ህይወት
https://youtu.be/G6igdhVO1D8?si=Gjiho_nXWo4UAQ0G
____☝️☝️☝️☝️☝️☝️ .........
💌💌💌💌💌💌💌💌💌
ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ
https://youtu.be/FGcPNFEXrvo?si=5fG8HnJlJrWcMeod
☝️☝️☝️☝️☝️☝️
💌💌💌💌💌💌💌💌
የተለያዩ አስተማሪ መልዕክቶችን ለማግኘት፥ ዩቲዩብ ቻናላችንን ይቀላቀሉ

@ortodox_27

Join
አዲስ ዝማሬ "ቅድስት ሥላሴ"ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ
"ቅድስት ሥላሴ"

ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ

ገጼን አማትቤ

ገጼን አማትቤ ልጀምር ውዳሴ
በትምህርተ መስቀል በስመ ሥላሴ
ይርቃል ከጎኔ ጠላት ዳቢሎስ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ

ከትቢያ ከአፈር አንስቶ የሰራኝ
በአፉም እስትንፋስ ህይወትን ያደለኝ
የሥላሴ ስራ ድንቅ ነው ጥበቡ
ከአይምሮ በላይ ነው የእግዚአብሔር ሀሳቡ

አዝ_

እክህደከ ሰይጣን ጠላቴን ክጃለው
ለዚህም ምስክር ማርያም ናት ብያለው
በቤተክርስትያን ቆሜ በመቅደሱ
ለቅድስት ሥላሴ ዘመርኩ ለንጉሱ

አዝ_

አልነበረም ዘመን እሱ ያል ነበረበት
ዳግመኛም አይኖርም እርሱ ማይኖርበት
የህይወቴ ጣእም ክብርና ሞገሴ
የማይሾሙት ንጉስ ዘላለም ሥላሴ

አዝ_

ኪሩቤል ሱራፌል ኃይላት ሊቃናት
መናብርት ስልጣናት ቆመው በአንድ ነት
ያላንዳች ዝምታ ይሉታል በክብር
ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ እግዚአብሔር

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

     🔸 @ortodox_27
🔸🔹🔸 @ortodox_27
     🔸 @ortodox_27

✍️Comment @Tewahdo27
የመስቀሉ ኃይል እንደ ምን ይደንቅ? በሰው ልጆች ዘንድ በመስቀሉ ኃይል የኾነው የተደረገው ለውጥ እንደ ምን ይረቅ? ከድቅድቅ ጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃን አውጥቶናልና፤ ከሞት ወደ ዘለዓለም ሕይወት መልሶናልና፤ ከዘለዓለም ጥፋት ወደ ዘለዓለም ልማት አሸጋግሮናልና፡፡
በመስቀሉ ያልተደረገልን በጎ ነገርስ ምን አለ? ምክንያቱም በመስቀሉ ርትዕት ሃይማኖትን ዐወቅን፤ የእግዚአብሔር የጸጋውን ብዛት ተረዳን፡፡ በመስቀሉ ስለ እግዚአብሔር እውነት የኾነውን ዐወቅን፡፡ በመስቀሉ፥ ርቀን የነበርን እኛ ሕዋሳተ ክርስቶስ እስከ መኾን ደርሰን የቀረብን ኾንን፡፡ በመስቀሉ ከመንፈስ ቅዱስ ጸጋ ተካፋይ የመኾን መብት (ሥልጣን) አገኘን፡፡
በመስቀሉ የፍቅርን ኃያልነት ዐወቅን፡፡ በመስቀሉ ለሌሎች መሞትን ተማርን፡፡ በመስቀሉ ንቀት፣ ውርደት፣ መከራ ማለት ምን ማለት እንደ ኾነ ዐወቅን፡፡ ጊዜያዊ ያይደለ የዘለዓለም በረከት ምንጭ መኾኑን ተረዳን፤ የማይታየውን እንደሚታይ አድርገን ተቀበልን፡፡
በመስቀሉ የተሰቀለው ይሰበካል፤ በእግዚአብሔር ማመንን እውነትም ለዓለም ኹሉ ይነገራል፡፡ በመስቀሉ የተሰቀለው ክርስቶስ ይሰበካል፤ በትንሣኤ ማመንንና በላይ በሰማያት ያለችውንም ሕይወት መንግሥተ ሰማያትም በእውነት ያለ ሐሰት ያለ ጥርጥር ይሰበካል፡፡
ከመስቀሉ በላይ የከበረ፣ ለነፍስም ድኅነትን የሚሰጣት ምን አለ? መስቀል አጋንንት ድል የተነሡበት ነው፡፡ መስቀል የኃጢአት ድል መንሻ የጦር ዕቃ ነው፡፡ መስቀል ጌታችን እባቡን የመታበት ሰይፍ ነው፡፡
መስቀል የአብ ፈቃድ፣ የወልድ ክብር፣ የመንፈስ ቅዱስ ደስታ፣ የመላእክት ጌጥ፣ የቤተ ክርስቲያን አጥር፣ የቅዱስ ጳውሎስ ውዳሴ፣ የቅዱሳን ጋሻ፣ የዓለምም ብርሃን ነው፡፡

https://www.tg-me.com/ortodox_27
«ወደ እግዚአብሔር የምንጸልየው፥ መረጃ ወይም መመሪያ ልንሰጠው ሳይሆን፥ ወደ እርሱ እንድንቀርብና ከእርሱ ጋር ኅብረት ያለን እንድንሆን ነው።»
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
እግዚአብሔር የሚጠላቸው ስድስት ነገሮች ናቸው፥ ሰባትንም ነፍሱ አጥብቃ ትጸየፈዋለች፦
፩ኛ. ትዕቢተኛ ዓይን፥
፪ኛ. ሐሰተኛ ምላስ፥
፫ኛ. ንጹሕን ደም የምታፈስስ እጅ፥
፬ኛ. ክፉ አሳብን የሚያበቅል ልብ፥
፭ኛ. ወደ ክፉ የምትሮጥ እግር፥
፮ኛ. በሐሰት የሚናገር ሐሰተኛ ምስክር
፯ኛ. በወንድማማች መካከልም ጠብን የሚዘራ።

ምሳሌ 6÷16-19

@ortodox_27
የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መዝሙር 🇪🇹
Photo
⛪️ #ጻድቅስ_ከመ_በቀልት ይፈሪ ወይበዝኀ ከመ ዘግባ ዘሊባኖስ ትኩላን #እሙንቱ_ውሰተ_ቤተ_እግዚአብሔር
(መዝ/ዳዊት ፺፪ ፥፲፪)🙏

#እንኳን_አደረሳቹሁ_የእምየ_ተዋሕዶ_ልጆች

( ፰🕯) ለጻዲቁ አባ ኪሮስ🦋

አባ ኪሮስ አባቱ #ንጉስ_ዮናስ_እናቱ_አንስራ ይባላሉ፡፡ ሀገሩ ሮም ነው፡፡ ወላጆቹ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ደጋግ ቅዱሳን ነበሩና አቡነ ኪሮስ በታህሳስ 8 ወለዱ፡፡ አቡነ ኪሮስ የመጀመሪያ ስሙ #ዲላሶር ይባል ነበር፡፡ በኋላ አባቱ ከሞተ በኋላ ሀብቱን ከወንድሙ ተካፍሎ ለድሆች መጽውቶ ዓለምን ንቆ መንኖ ሄደ፡፡ ከአባ በቡነዳ ገዳም ገባ፡፡
በ17 ዓመቱ #ሥርዓተ ምነኩስናን ተማረ፡፡ በአባ በቡነዳ እጅ መነኮሰ፡፡ #ከዚህ_በኋላ በጾም በጸሎት ተወስኖ ኖረ፡፡ስለ ዓለም መከራ ለ40 ዘመን ተኝተው ሲጸልዩ እላያቸው ላይ ሳር በቅሎባቸው ሳለ #መላእክት_መጥተው ተነስ ቢሉት አዳም የፍጡር ቃል ሰምቶ ወድቀዋል ጌታዬ ድምጹን ያሰማኝ አላቸው በኋላ ኪሩቤል አንስቶ ወስዶ ገነት አሳይተውት #ጌታችንም ቃል ኪዳን ሰቷቸዋል።

⛪️ #አባ_ኪሮስ_አባቴ 🕯
በእግዚአብሔር ትዕዛዝ ወደ #ገዳም_ገብተህ
በሀዘን ስሜት ውስጥ እንባህን አፍሰስህ
እመቤቴ ጠራህ አትለይኝ ብለህ
ሰባት መቶ ስግደትን ለእመ አምላክ ሰግደህ
ምህረትን አገኘህ እንደ እንግዳ ሆነህ
ወደ እግዚአብሔር ፀለይክ በሽተኛ ልታድን
#መላእክትም_መጡ ካንተ ጋር ለመሆን
እልፍ አዕላፋት እንዲሁም ጌታችን
ለችግረኞች ተስፋ የሆነው አምላካችን
ልክ እንደ አብርሀም እንደ #ፃድቁ_ሰው
ሰው ስትቀበል በሰላም በፍቅር ነው
የራስ ፀጉር እንደ በረዶ የነጣ
የፂምህ ውበት ነጭ ሆኖ የወጣ
አሟሟትህ ይገርማል ለሰማው የደንቃል
#እግዚአብሔር ተቀበሎ ለሚካኤል ሰጣት
በመቃብርህ ላይ መስቀሉን ተከሉት
ነፍስህን ከአምላክ ጋር እንዲ አሳረጓት
እርሷም በተሰጣት #ክብር_ደስ እያላት

❤️ወስብሐት #ለእግዚአብሔር 🦋

"ወር በገባ በ8 ፃድቁ አባታችን ቅዱስ አቡነ ኪሮስ ናቸው ።

ካልታሰበ አደጋ ወቶ ከመቅረት ይሰውሩን በቃል ኪዳናቸው ያስምሩን🙏

መልካም ቀን 🙏ቤተሰብ በስላም ያውለን

🤲 🤲 🤲
#አሜን......... 🧡 ......... #አሜን
#አሜን🙏³⊹
የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መዝሙር 🇪🇹
Photo
. [ #ነገረ_ምስለ_ፍቁር_ወልዳ ]

"ነገረ ምስለ ፍቁር ወልዳ" ማለታችን ጌታችን እንዳቀፈች በሚታየው በእመቤታችን ስዕል ዙሪያ ያሉትን ምስጢራት የሚያብራራ ጽሕፈት ስለሆነ ነው! እንግዲህ ይህ content ከወጣ ጊዜ ጀምሮ ለመማሪያ እንዲሆነን ለ "5"ኛ ጊዜ ደግመን ፖስተነዋል! ይህም በእመቤታችን ምስለ ፍቁር ወልዳ ዙሪያ ያሉትን ምስጢራት ሁላችንም እንድንረዳው ስለሚየስችለን፣ ይህን ታሳቢ በማድረግ በማሳጠር በአጭር አማርኛ የተጻፈ እና ሌሎች ትርጓሜዎችም ያሉት መሆኑን አንባቢው ያስተውል!! በተጨማሪም ለአረዳድ ያመች ዘንድ በስዕሉ ላይ ቀስትን ከቀስት ለይቶ መመልከት ተገቢ ነው!

#ሀ > አክሊለ ብርሃን፦ የቅድስና ምልክት ሲሆን ይህም በሁሉም የቅዱሳን አናት ላይ ተደርጎ የሚሳል እና ቅድስናቸውን፤ መንፈስ ቅዱስ ያደረባቸው ( ማህደረ መንፈስ ቅዱስ ) መሆናቸውን የሚያመለክት ነው!

#ለ > የእመቤታችን ከውስጥ የምትለብሰው ቀይ ልብስ፦ አረጋዊ ስምዖን በነፍስሽ ሰይፍ ያልፋል እንዳላት ጌታን ከፀነሰች ጀምሮ ከእርሱ ጋርም የደረሰባትን ሀዘን፤ ጭንቁን፤ መከራዋን ሁሉ የሚያመለክት ሲሆን አንድም እሳተ መለኮትን በውስጧ የተሸከመች መሆኗን ያመለክታል!!

#ሐ > በእመቤታችን በስተ ቀኝ ትከሻዋ ላይ ያለው ኮከብ፦ ጊዜ ፀኒስ ድንግል መሆኗን ያመለክታል!

#መ > የጌታ ሁለቱ ጣቶች፦ ሁለቱን የጌታ ልደታት ማለትም፦
1) ቅድመ ዓለም ከአብ ያለ እናት፤
2) ድኅረ ዓለም ያለ አባት ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም መወለዱን ያመለክታል!

#ሠ > እመቤታችን በእጇ የምትይዘው መሐረብ ወይም ሰበን፦ ለቶማስ የስጠችውን እና አባቶች በእጅ መስቀላቸው ላይ የሚይዙት የሰበኗ ምሳሌ ነው!

#ረ > እመቤታችን ከላይ የምትለብሰው ሰማያዊ ልብስ፦ አንድም እንደ ሰማያዊያን በፍፁም ቅድስና የተገኘች እና አንድም ሰማይና ምድር የማይወስኑትን አምላክ በማህፀኗ የተሸከመች ዳግሚት ሰማይ መሆኗን ያመለክታል!

#ሰ > የእመቤታችን ሁለቱ ጣት፦ በነፍስም በሥጋም በሁለት ወገን ድንግል (ድንግል በክልኤ) መሆኗን ያመለክታል!

#ሸ > ከእመቤታችን ከእራስ ላይ ያለው ኮከብ፦ ቅድመ ፀኒስ ድንግል መሆኗን ሲያመለክት በተመሳሳይ ጌታ በተቀመጠበት በስተ ግራዋ አቅጣጫ ትከሻዋ ላይ ባማይታይ መልኩ ከውስጥ አንድ ኮከብ አለ፤ ይህም ድኅረ ፀኒስ ድንግል መሆኗን ያመለክታል!

#ቀ > በእመቤታችን እራስ ላይ ያለው ዘውድ፦ አባቷ ዳዊት " የወርቅ ልብሷን ተጎናፅፋና ተሸፋፍና ንግስቲቱ በቀኝህ ትቆማለች " እንዳለ ጌታን በመውለዷ የሰማይም የምድርም ንግስት መሆኗን ያመለክታል!

#በ > በእምቤታችን በልብሶቿ ላይ ያለው የወርቅ መጎናፀፊያ፦ ቀድሞ በብሉይ ታቦተ ፅዮን በወርቅ ትለበጥ እንደነበረ፤ እንዲሁ አማናዊት ታቦት እመቤታችን በንፅህና እና በቅድስና ያጌጠች የተለበጠች መሆኗን ያመለክታል!

#ተ > በጌታ እጁ ላይ ያለው መፅሐፍ፦ ጌታ እየዞረ ያስተማረው የወንጌል ምሳሌ፤ አንድም ቸር እውነተኛ መምህርም እርሱ መሆኑን የሚያመለክት ነው!!

[ የእመቤታችን ዘላለማዊ አማላጅነቷ በነፍስም በስጋም አይለየን አሜን ]


Oô Màryâm Lâmmà Sëbèktânï
[ ግንቦት - 6 - 2016 ]

#ቆዩ_በሰናይ//
◈ እስትንፋሰ ክርስቶስ ◈
✞ ጋሜል - ዘ ኦርቶዶክስ ✞
✞ እስትንፋሰ ክርስቶስ ✞

የደብረ አስጋጁ ተጋዳይ ነህ የእግዚአብሔር አገልጋይ
እስትንፋሰ ክርስቶስ ሐዋርያ ጸልይ ለኢትዮጵያ [፪]

ቅዱስ ሚካኤል አሳደገህ
እየቀደመ ከፊት መራህ
ብሉይና ሐዲስ ድርሳናቱን
ሁሉን አውቀሃል መጻሕፍቱን

     አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
አርባዉን መአልት አርባ ለሊት
ተወስነሃል በጾም ጸሎት
በብዙ ድካም በብዙ ጻማ
ከመከራ አልፈህ ደረስክ ከራማ

     አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
እንደ ኢያሱ ፀሐይ አቁመህ
ከመነኮሳት ብልጫ አለህ
የኢትዮጵያ ቅዱሱ ፍሬ
እስትንፋሰ ሆይ ይላል ከንፈሬ

     አዝ▸▸▸▸▸▸▸▸▸▸►
ከባህር ገብተህ ዘጠኝ ዓመት
ለኢትዮጵያ ጸለይክላት
ቃል ኪዳን አለህ ለዘልዓለም
ዛሬም ስለኛ ለምልጃ ቁም

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥

ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች👇
                •➢ ሼር // SHARE

https://www.tg-me.com/ortodox_27
https://www.tg-me.com/ortodox_27
https://www.tg-me.com/ortodox_27

✥••┈┈••●◉ ✞ ◉●••┈┈••✥
#እናቴ_ሆይ "ደስ ብሰኝ ባንቺ ደስ እሰኛለሁ፤ ባዝንም ባንቺ እፅናናለሁ፤ መከራና ችግርም ቢያገኘኝ ወዳንቺ እጮሃለሁ።"

(#አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ - በመጽሐፈ አርጋኖ)

@ Ortodox_27 ❤️
@ Ortodox_27 💛
@ Ortodox_27 💚

👆👆👆👆
Join
ግንቦት 10
" ኢየሱስ ናትናኤልን ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ ስለ እርሱ። ተንኰል የሌለበት በእውነት የእስራኤል ሰው እነሆ አለ።ናትናኤልም። ከወዴት ታውቀኛለህ? አለው። ኢየሱስም መልሶ። ፊልጶስ ሳይጠራህ፥ ከበለስ በታች ሳለህ፥ አየሁህ አለው።ናትናኤልም መልሶ። መምህር ሆይ፥ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ ነህ፤ አንተ የእስራኤል ንጉሥ ነህ አለው። "ዮሐ 1:48-49
ግንቦት 10 የሐዋርያው ናትናኤል  ወርሐዊ የመታሰቢያ  በዓሉ ነው።
ከሐዋርያው በረከት አይለየን
💌💌💌💌💌💌💌💌

።።።።።።።።።።።።
ሂዱ ንገሩ አውሩ ለዓለም
ተነስቷል በዚህ የለም መድኅኔዓለም
💌💌💌💌💌💌💌👎👎👎👎
ዝማሬውን ለሁሉ ያድርሱ የምስራች ነውና እናመሰግናለን
https://youtu.be/JJ7NoZ_9DcU?si=GcE56tvf5r5vniIm
☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️
💌💌💌💌💌💌💌💌💌
ዩቱዩብ ቻናሉን #Share በማድረግ ለሁሉም እናዳርስ! #Like በማድረግም ድጋፋችንን እናሳይ! 
💌💌💌💌💌💌💌💌💌
ሰው ሆኖ ሰው አደረገኝ
የትንሳኤ ስጦታችን
https://youtu.be/JJ7NoZ_9DcU?si=GcE56tvf5r5vniIm
☝️☝️☝️☝️☝️☝️☝️
💌💌💌💌💌💌💌💌
ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን ዩቱዩብ ቻናል👉በላይክ👉 ሼር👉 ሰብስክራይብ👉ሱፐር ቻት 👉ሜምበር በመሆን ሚዲያችንን በቅንነትእናበረታታ  እናመሠግናለን
💚@ortodox_27 💚
💛@ortodox_27 💛
❤️@ortodox_27 ❤️
🙏🙏🙏🙏🙏
2024/05/19 02:50:47
Back to Top
HTML Embed Code: