Telegram Group Search
<< አንቱ ሰው መለያየት ማለት እንዴት ነው? >>
<< ምንም ትውስታ ማጣት ነው። >>
<< አንቱ ሰው አልገባኝም! >>
<< የኔ ልጅ ናፍቆት ትውስታ አለው። ትዝታ ትውስታ አለው። ሀዘን፣ ደስታ፣ ፍቅር፣ ሌላው ቢቀር ጥላቻ እንኳ ትውስታ አለው። ከሚወድህ ከምትወደው በአካል መራራቅ አይደለም መለያየት ማለት። አብረህ መኖር አለመቻል ማለት አይደለም መለያየት። መለያየት ማለት ትውስታ ማጣት ነው። ትዝታ አልባ መሆን። የኔ ልጅ ሰዎች እንደ ሰጠሀቸው ቦታ ያህል ነው ትውስታቸው። እንዳቀረብካቸው ያህል ነው ልብህ ላይ የሚመላለሱት። ለምታውቃቸው ሰዎች ትውስታ እስካለህ አልተለየሀቸውም። >>
<< አንቱ ሰው እወዶታለሁ! >>
<< የማይጠቅምህን ከማስታወስ ጌታዬ ይጠብቅህ! >>


@fezekiru
@fezekiru
«አንዳንድ ሰዎችን እጅግ እንወዳቸዋለን፣ እናከብራቸዋለን፣ የነሱን ደስታ እንጂ ምንም አይነት ክፉ ነገር መስማትም አንፈልግም። ነገር ግን የልባችንን ልናወራቸው አንደበታችን ይንተባተባል። ረጅም አመት አውቀናቸው፣ አብረናቸው ኖረን እንኳ በነፃነት እንደፈለግን ለማውራት ፈልገን የሆነ የሚያንቀን ነገር ይኖራል። ቁም ነገር seriously ማውራት ተራራ ይሆንብናል
ከነሱ በኋላ ከተዋወቅናቸው፣ ምናልባት ከነሱ ከማናስበልጣቸው ሰዎች ጋር ያሻንን እያወራን ከአንዳንድ ከምንወዳቸው ሰዎች ጋር ግን ወሬውም ይጠፋናል። ምክንያቱ ብዙ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን የሆነ ልባችን ላይ የሚመላለስ ነገር ሲኖር እንዲያ ለመሆኑ ያስጠረጥራል። ምናልባት እንቅጩን ላናውቀውም እንችላለን። በተለይ በመሀል ክፍተት ተፈጥሮ ከነበረ እንዲህ የመሆን እድሉ ከፍተኛ ነው።

በቃ እነዚህን ሰዎች እንወዳቸዋለን፣ እናከብራቸዋለን፣ ደስታቸውን እንፈልገዋለን እንጂ በደንብ ልናወራቸው የማናውቀው ምክንያት ይይዘናል። ይሄ እንዲሆን ግን ፈልገነው ላይሆን ይችላል።
አይታወቅም ምናልባት የሆነ ጊዜያችን ውስጥ "የእንደፈለግን የመግባባትና፣ የማውራት ነፃነታችን" የሆነ ቦታ ጠፍቶ አልያም ደንግጦ ይሆናል።
ብቻ ምንም ቢሆን ምን ማክበር መውደዳችን፣ መልካሙን ሁሉ ለነሱ መመኘታችን አይጥፋ። ይሄ ከጠፋ ግን ከመተዋወቅ ወደ አለመተዋወቅ፣ አለፍ ሲልም መረሳሳት ላይ ደርሰናል ማለት ነው። ያ ደግሞ ስሜት አልባነት ይሆናል፣ ከተጣሉ ሰዎችም ያነሰ አይነት ስሜት ነው ሚሆነው።»

በግንኙነታችሁ ውስጥ እንዲህ አይነት ክስተቶች አጋጥሟችሁ አያውቅም?

@fezekiru
@fezekiru
Forwarded from ሀላል መረዳጃ ዲላ (ye zd Lij)
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
በዲላ ከተማ "አኽላቅ ቶርናመንት" የምድር ገነት

የወንድማማችነት ሊግን ድምቀት ከሰጡት አንዱ የሸክ አደም ልዩ ዳእዋ ነበር ተሳስቦ መጫወት ተዋዶ መገናኘት ልዩ ደስታ አለው ድል ለሁላቹም

በሀላል በጎ አድራጎት አዘጋጅነት በደማቅ ሁኔታ እየተከናወነ ይገኛል እናመሰግናለን

https://www.tg-me.com/halale_merdaja_dilla

https://youtube.com/watch?v=BNN8n00PH9c&feature=share
እናመስግን!
.
.
መዝነን ያለፍናቸው. . .
አቅልለናቸው ያለፉ. ..
ድንገት ስናኮበኩብ፣
ሊያቆዩን የለፉ፣
ያውቁ ነበር. . .
አንድ ቀን እንደሚፀፅተን፣
ይቅርታ እንደምንሻ፣
ቁጭቱ ሲያቅተን!
.
አሉ ደሞ ሰዎች. . .
እነሱን ተክተው፣ወደ እኛ ሚመጡ፣
በገፋናቸው ሰዎች መንበር ሚቀመጡ፣
ስንቃጠል. . .
ስንበግን. . .
ያጣናቸውን ሰዎች ከልብ እናመስግን!

@fezekiru
@fezekiru
ሁሉም ነገር በምክንያት ነዉ ሚፈጠረው
የሂወት ዉበት ከማያምር ነገር ውስጥም ይታያል።

👇👇👇
@fezekiru
አንድ ትልቅ ሰው
‹የአደም ልጅ ንግግሩ ሁሉ ልክ ቢሆንና ስራው ጥሩ ቢሆን እንኳ ለኪሳራ ቅርብ ይሆን ነበር› አሉ።
‹እንዴት ይከስራል?› ሲባሉ
⟨በራሱ ይደነቃል አሉ። ⟩

Join @fezekiru
It's okay to be sad after making the right decision.°
@fezekiru
የትላንትህን ህመም እያስታወስከው የዛሬን ደስታ እንዳታጣው ።
👇👇👇
@fezekiru
ልቤ ከተኛ ስንት ዘመኑ
እሷ ስትመጣ
መንቃት ጀመረ ይኸው ካሁኑ።
እንድያው እንደቀልድ እያሳሳቀች
ልክ እንደ ውሀ እየወሰደች
ታሰጥመኝ ያዘች በምግባር ባህሯ
እሺ አንኳ ብላት ምንድን ነው መህሯ?

እያልኩ ብጨነቅ መቼ ሊጨንቃት
ልቤን ማግኘቱ በዝቶ እያብቃቃት።
ይኸው…
ፍቅር ክቡሩ አያሳይ የለ
ስታፈቅረኝ ነው
እኔም ያወቅኩት ሕይወት እንዳለ።

@fezekiru
@fezekiru
ፀሀይ ሁሌም አትኖርም አይደል… ሲጨልም ትጠፋለች። ጨረቃም ሁሌ አትኖርም… ጨለማውን ለማፍካት ሁሌም ከሰማዩ አትገኝም። ነገር ግን ከዋክብት አሉ… በጨለመ ጊዜ ሁሌም ከዋክብት አሉ። እነዚህን ከዋክብት ስመለከታቸው ጨለማ የዋጣቸውና የማይታዩ ይመስላሉ እነሱን ለማየት አትኩሮት ይፈልጋል ብርሃናቸው ሁሌም ልባችንን እንደ ጨረቃ አይስቡትም… ፈልገን እስካላየናቸው ድረስ።

እኚህ ከዋክብት፣ በችግሮቻቸው ጊዜ ልንመለከታቸው ያልቻልናቸው በጨለማችን ውስጥ ያሉ ኸይር ነገሮች ይመስሉኛል እኔ ...ያጋጠመን ነገር ለኸይር መሆኑን በዛ ውስጥ ኸይር እንደሚገጥመን ማመንና መጠበቅ ኸይር ነው ብሎ ኸይሩን መመልከት ሁሉም ሊያደርገው የሚችለው አይደለም…ግና ልክ በጨለማው ከዋክብትን ሁሉም ፈልጎ እንደማያያቸው አለመመረጥ ሳይሆን በኛ ቸልተኝነት ለማየት አለመምረጣችን ነው።
መርጦ ኸይሩን ማየት የቻለ ደግሞ ለጨለማው ከዋክብቱ እንደጨረቃ ይሆኑለታል።


Join @fezekiru
...ስትተወው ይተውሃል> የሚሉ መካሪ ቃላት፤ ከማጣት በኋላ የሚደውሉ የእድሜ ልክ ስንቅ ናቸው.... ሁሉም ነገር እንዲቆይ ሰበብ ይፈልጋል..... ስሩን ማጠጣት ያቆምክ ቀን ግንዱም ቀን ጠብቆ ይወድቃል..... ሁሉም ወዳጅም፣ ምግባርም....ኢማንም ልክ እንደዛው.... ያልተዘራ አይታጨድ ነገር...

..


@fezekiru
ሰላም ለነዛ በዱአቸዉ ለሚያስታውሱን
ስማችንን ጠርተዉ ያረብ ለሚሉ🥺

@fezekiru
A hidden connection is stronger than obvious one

@fezekiru
ህመሙ እየጠዘጠዘው ችሎ የኖረ ነው ወይስ የታማሚውን ህመም ያስመሰለ - ጥበበኛ? ለፍቅር የተገበረ ምስኪን ወይስ በቃል የሚራቀቅ - ጥበበኛ?
የሰው ህመምን እያስመሰሉ መሳለቅ ወይስ ወበቅን ለብቻ አዝሎ ፍግም ማለት - ጥበብ?
ስሜትን ረስቶ በዱንያ ልክ መጥበብ ወይስ ለፍቅር በጀ ብሎ ከአለም መላቅ - ጥበብ?

እንጃ! መዝገበ ቃላታችን እስካልጠራ የምንግባባ አልመሰለኝም።


Join @fezekiru
​​ባል 🙎‍♂:-  20 አመት ሙሉ በትዳር ስንኖር ሁሌም ከንግግሬ መሐል ስህተት  እንደፈለግሽ ነዉ ! 😢


ሚስት🙍‍♀ :-21 አመት ነው በትዳር የኖርነው ። 20 አደለም😁

እንዲም አይነት አለ !!!🤣🤣
👇👇👇
@fezekiru
ለዚህ ነበር?

.
የዘላለም ያህል ረዝሞ. . .
ዘጠኝ ወር አግቶኝ፤
ዘንቶ ለመቀመጥ፣
መወለድ አጓጉቶኝ፤
ሆዷን እረግጣለሁ፣
እጋላበጣለሁ. . .
"ውለጂኝ!" እላለሁ።
.
ማሕፀን ውስጥ አልቀረሁ፣
ተወለድኩ. . .
ተሰወርኩ!
.
ደርሶ ተከፈተ፣የመዓሲያው በር፣
"ኑሮ" በሚሉት የብላሽ አጎበር፣
በከረፋው ቀንበር፣
ታስሬ ልሰበር፣
ሆዷን የረገጥኩት፣ለዚህች ሕይወት ነበር?😔

@fezekiru
@fezekiru
2024/05/12 09:53:31
Back to Top
HTML Embed Code: