Telegram Group Search
አዲስ አበባ, ጎሮ ገብርኤል በተክርስቲያን አጠገብ የተፈጠረ የእሳት አደጋ

ትላንት ለሊት ከምሽቱ 6:30 ገደማ የተቀረፀ

ቪዲዮ 4 :- ዛሬ የተቀረፀ

ምንጭ:- ሀብታሙ
የአሳማ ኩላሊት በንቅለ ተከላ ለመጀመሪያ ጊዜ የተለገሰው ግለሰብ ህይወቱ አለፈ!

በዘረመል ምህንድስና የተሻሻለ የአሳማ ኩላሊት በንቅለ ተከላ ለመጀመሪያ ጊዜ የተለገሰው ግለሰብ ከህክምናው ሁለት ወራት በኋላ ህይወቱ ማለፉን ሆስፒታሉ አስታወቀ።የ62 ዓመቱ ሪቻርድ "ሪክ" ስላይማን ቀዶ ህክምናውን በመጋቢት ወር ከማድረጉ በፊት በከፋ የኩላሊት ህመም ይሰቃይ ነበር።

ህይወቱ ያለፈው በንቅለ ተከላው ምክንያት ስለመሆኑ ምንም ምልክት የለም ሲል የማሳቹሴትስ አጠቃላይ ሆስፒታል (ኤምጂኤች) እሑድ ዕለት አስታውቋል።በዘረመል ምህንድስና ከተሻሻሉ አሳማዎች የተገኙ ክፍሎችን ሌሎች የመተካት ሙከራ ቀደም ሲል አልተሳካም ነበር። የስላይማን ቀዶ ህክምና ግን ታሪካዊ ምዕራፍ ነው ተብሎ ተወድሷል።

ከኩላሊት ህመም በተጨማሪ ስላይማን የስኳር በሽታ እና የደም ግፊት ነበረበት።እአአ በ 2018 የሰው ኩላሊት ንቅለ ተከላ ቢያከናውንም ከአምስት ዓመታት በኋላ መሥራት ማቆሙ ተነግሯል።የአሳማ ኩላሊት ንቅለ ተከላውን ተከትሎ፤ አዲሱ ኩላሊቱ በጥሩ ሁኔታ እየሠራ በመሆኑ የኩላሊት እጥበት (ዳያሊሲስ) እንደማያስፈልገው ዶክተሮቹ አረጋግጠው ነበር።

"ስላይማን በዓለም አቀፍ ደረጃ ስፍር ቁጥር ለሌላቸው ህሙማን የተስፋ ብርሃን ፈንጣቂ ሆኖ ይታያል። ‘የዜኖትራንስፕላንቴሽን’ መስክን ወደፊት እንዲራመድ ላሳየው እምነት እና ፍቃደኝነት በጣም እናመሰግናለን" ሲል ሆስፒታሉ በሰጠው መግለጫ አስታውቋል።ዜኖትራንስፕላንቴሽን ህይወት ያላቸው ሴሎችን ወይም የአካል ክፍሎችን ከአንድ ዝርያ ወደ ሌላ ዝርያ መተካት ነው።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
የጋዜጠኞች መብት እንዳይጣስ የሚከራከር የህግ ባለሙያዎች ቡድን ሊቋቋም መሆኑ ተሰማ፡፡

ይህንን የህግ ባለሙያዎች ቡድን በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶች ህብረት እና ዩኔስኮ በጋራ በመሆን የሚቋቋሙት መሆኑ ተሰምቷል፡፡

አቶ መሱድ ገበየው በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶች ህብረት ዋና ዳይሬክተር የሚዲያ ተቋማት እና ጋዜጠኞች ስራቸውን በመስራታቸው ብቻ የሚደርስባቸውን ችግር ለመፍታት የህግ የባለሙያዎች ቡድንን እያቋቋምን እንገኛለን ብለዋል፡፡

ይህ ፕሮጀክት ሚዲያው ላይ ብቻ የሚሰሩ የህግ ባለሙያዎችን በማሰባሰብ የተለያዩ ጋዜጠኛውን የሚጎዱ ህጎች ላይ በመከራከር ጋዜጠኛውን መብቱን ማስጠብቅንም ያጠቃለለ ነው ብለዋል፡፡ጋዜጠኞቹ ሲታሰሩ መደበኛ ጥብቅናው እንዳለ ሆኗ የጋዜጠኞችን የዕውቀት ደረጃ ከፍ የሚያደርግ እና በእስር ላይ የሚገኙ የሚዲያ አካላትን በፋይናንስ መደገፍ የሚያስችል ተቋም ለመቋቋም መሰባቸውን ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶች ህብረት ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ መሱድ ይህ ለጋዜጠኞች መብት የሚሟጋት የህግ ባለሙያዎች ቡድን መላ የሚል ስያሜ እንደተሰጠውም ለጣብያችን ገልፀዋል፡፡ማህበሩ ዋና ዓላማ የህግ ባለሙያዎችን በማሰባሰብ ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብትን እንዲሁም የጋዜጠኞችን መብት ለማስጠበቅ የሚሰራ ነው ብለዋል።

[Ethio FM]
@YeneTube @FikerAssefa
ከሐዋሳ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ የነበረዉ አዉሮፕላን ዉስጥ ታይቷል የተባለዉ ጭስ በዉስጡ ያለዉ ዘይት በመቃጠሉ የተነሳ መሆኑ ተገለፀ!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሰሞኑ በአዉሮፕላኑ ላይ የተከሰተው ጉዳይን አስመለክቶ እንዳስታወቀው ከእሳት ወይም ከሌላ ነገር ጋር የተያያዘ ሳይሆን አዉሮፕላን ዉስጥ ያለዉ ዘይት ተቃጥሎ ነዉ በወቅቱ የተከሰተው ጭስ ሊፈጠር የቻለዉ ይህም አልፎ አልፎ የሚያጋጥም ችግር ነዉ ብሏል።

የአየር መንገዱ ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰዉ በተለይ ለካፒታል እንደተናገሩት " በአዉሮፕላኑ ዉስጥ ያለዉ ዘይት መጋጠሉ እና ከእርሱ ጋር ተያይዞ የተፈጠረ ጭስ ነዉ ይህ ደግሞ የተለመደ ነዉ ብለዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር ET154 ሚያዝያ 29፣ 2016 ከሀዋሳ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ እያለ በአውሮፕላን ውስጥ ጭስ መታየቱን አስታዉቆ እንደነበር ይታወቃል ።

[Capital]
@YeneTube @FikerAssefa
🌸m.shein.com  ከ Fashionnova.comAmazon.com ዌብሳይት ላይ  መግዛት የሚፍልጉትን እቃ ሊንኩን ወይም ፎቶውን ይላኩልን እኛ ከ15 እስከ 20 ቀን ውስጥ አስመጥተን እናስረክብዎታለን።

🌸ስልክ:- 0988747602 @Afufu98

🌸ክፍለሀገር በፖስታ ቤት እንልካለን::

ቴሌግራም ሊንክ:- https://www.tg-me.com/CFLqualityshop
ይህ ምንም ቅድመ ክፍያ ማዘዝ ይችላሉ
Forwarded from MneCreatives
📢🎉ለ12ኛ ማትሪክ እና ለመውጫ ፈተና ተፈታኞች!
ተማሪው መተግበሪያን ከፕለይስቶር በማውረድ ለፈተናዎ በቂ ዝግጅት ያድርጉ!

🔸ለ12ኛ ማትሪክ ተፈታኞች:- በመተግበሪያችን ከ አዲሱ የ12ኛ ክፍል ካሪኩለም የተወጣጡ ከ 2000 በላይ መለማመጃ ጥያቄዎችን ያገኛሉ።

🔸ለመውጫ ፈተና ተፈታኞች:-
🔹ለአካውንቲንግ
🔹ቢዝነስ ማኔጅመንት
🔹ኮምፒዩተር ሳይንስ
🔹ሆቴል ማኔጅመንት
🔹ማርኬቲንግ ማኔጅመንት
መለማመጃ ጥያቄዎችን ያገኛሉ።

በተጫማሪም መተግበሪያውን ለልጅዎ፣ ለቤተሰብዎ፣ ለዘመድዎ 🎁በስጦታ ማበርከት ይችላሉ።🎁
በሰሜን ሸዋ ዞን ሁለት ወረዳዎች ዉስጥ በሚገኙ ት/ት ቤቶች የድሮን ጥቃት መፈጸሙ የተነገረ ሲሆን በጥቃቱ ንጹሃን ገበሬዎች ሲገደሉ ፤ አንዲት መምህርት ተጎድታለች ተባለ

👉🏼 ጥቃቱ በቀወት እና ጣርማበር ወረዳዎች ተፈጽሟል

በትናንትናው ዕለት በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ቀወት ወረዳ ተሬ ቀበሌ ልዩ ስሙ ጉሎ ተብሎ በሚጠራ ስፍራ የድሮን ጥቃት መፈጸሙን ነዋሪዎች ለአል ዐይን አማርኛ ተናግረዋል፡፡

ለደህንነቱ በመፍራት ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ የተሬ ቀበሌ ነዋሪ እንዳለው “ትናንት ግንቦት 4 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 7፡30 ላይ በመንደራችን ከባድ ፍንዳታ ተፈጥሮ ነበር። እኔን ጨምሮ የሰፈራችን ነዋሪዎች ፍንዳታው ወደ ተሰማበት ስፍራ ስንሄድ ጥቃቱ ጉሎ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ላይ እንደተፈጸመ አየን” ሲል ተናግሯል፡፡

አስተያየት ሰጪው አክሎም “በዚህ የድሮን ጥቃት ሶስት አርሶ አደሮች ወዲያውኑ ህይወታቸው ሲያልፍ በትምህርት ቤቱ ውስጥ ትኖር የነበረች ሴት መምህር ከባድ ጉዳት ደርሶባት ወደ ሆስፒታል ተልካለች” ሲልም አክሏል፡፡

“አንድ ሌላ አርሶ አደር በተመሳሳይ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶበት ወደ ሆስፒታል መወሰዱን አውቃለሁ” ያለን ይህ የአይን እማኝ አንድ አርሶ አደር ደግሞ ቀላል ጉዳት እንደደረሰበትም ተናግሯል፡፡

በአካባቢው በመንግስት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ውጊያ ከተጀመረ አንድ ዓመት እንደሆናቸው የሚናገሩት እኝህ ነዋሪ የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች አልፎ አልፎ ብቅ እያሉ ንጹሃን ሰዎችን ፋኖን ትረዳላችሁ እያሉ ወጣቶችን ይገድላሉ ብሏል፡፡ በዚህ ምክንያት የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች መጡ ሲባል በተለይም ወጣቶች ወደ ጫካ እንደሚሄዱ እና እንደሚደበቁም ይህ አስተያየት ሰጪ ተናግሯል፡፡

በተመሳሳይ በዞኑ በጣርማበር ወረዳ በሚገኘው የመዘዞ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ላይ የድሮን ጥቃት መፈሙን ስማቸውን እንዳይጠቀስ የፈለጉ ነዋሪ ለአል ዐይን አማርኛ መናገራቸውን ዳጉ ጆርናል ከዘገባው ተመልክቷል። ነዋሪው እንደገለጹት በዚህ የድሮን ጥቃት በሰዎች ላይ ጉዳት ደርሷል።

ጥቃቱ ትናንት ግንቦት 5 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ ሰባት ሰአት ላይ መድረሱን የገለጹት እኝህ ነዋሪ በጥቃቱ የተጎዱ ሰዎች ወደ ጤና ጣቢያ ሲገቡ መመልከታቸውን ተናግረዋል። የሰሜን ሸዋ ዞን ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢ እና የሀገር መከላከያ ሰራዊት ተፈጸሙ ስለተባሉ የድሮን ጥቃቶች ያለውን ምላሽ ለማካተት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም ብሏል የዜና ምንጩ፡፡

በአማራ ክልል በተደጋጋሚ በተፈጸሙ የድሮን ጥቃቶች ንጹሃን ዜጎች መገደላቸውን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽንን ጨምሮ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተቋማት እና ምዕራባዊያን ሀገራት ባወጧቸው ሪፖርቶች ላይ ጠቅሰዋል፡፡እነዚህ ተቋማት እና ሀገራት የድሮን ጥቃቶች እንዲቆሙ ንጹሃን ዜጎችም ከጥቃት እንዲጠበቁ ቢጠይቁም የሀገር መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የድሮን ጥቃቱ እንደሚቀጥል እና ኢላማውን የጠበቀ ጥቃት ማድረሳችንን እንቀጥላለን ሲሉ ምላሽ መስጠታቸው አይዘነጋም፡፡

በክልሉ በፋኖ ታጣቂዎች እና በመንግስት ወታደሮች መካከል የተቀሰቀሰውን ግጭት ተከትሎ ከሐምሌ 28 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁ የሚታወስ ሲሆን ለተጨማሪ አራት ወራት የተራዘመ መሆኑ አይዘነጋም። ሆኖም ይህ አዋጅ አሁን ላይ ሊጠናቀቅ ሶስት ሳምንታት ቀርቶታል።

Via :- ዳጉ ጆርናል
@Yenetube @Fikerassefa
በሱዳን ጥገኝነት ለጠየቁ የቀድሞ ሰላም አስከባሪዎች ጥበቃ እንደሚያደርግ የስደተኞች ተቋሙ ገለጸ!

በሱዳን በጥገኝነት እየኖሩ ያሉ የቀድሞ የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ አባላት፣ ተፋላሚው የሱዳን "ፈጥኖ ደራሽ ኀይሎች"፣ በሰሞኑ መግለጫው ካቀረበው የጣልቃ ገብነት ክስ ጋራ ተያይዞ የደኅንነት ስጋት እንዳደረባቸው ገለጹ፡፡

ለደኅንነታቸው በመስጋት ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁን የትግራይ ተወላጅ የሰላም አስከባሪ አባላት፣ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት ቃለ መጠይቅ፣ የሱዳን "ፈጥኖ ደራሽ ኀይሎች" ባወጣው መግለጫ፣ የህወሓት ታጣቂዎች በሱዳኑ ጦርነት እየተሳተፉ እንደኾነ ያቀረበው ክስ፣ “በመጠለያ ጣቢያዎች ያለነውን ስደተኞች ለጥቃት እንዳይዳርገን ስጋት ፈጥሮብናል፤” ብለዋል፡፡

ስለ ጉዳዩ ለአሜሪካ ድምፅ በኢሜይል አስተያየት የሰጠው የተባበሩት መግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር በበኩሉ፣ “የስደተኞቹን የደኅንነት ስጋት እረዳለኹ፤ ኹኔታውን የተመለከተ መፍትሔም እያፈላለግኹ ነው፤” ብሏል፡፡

[VoA]
@YeneTube @FikerAssefa
በጅግጅጋ ከተማ የመኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካ ተመረቀ!

በጅግጅጋ ከተማ የመኪና መገጣጠሚያ ፋብሪካ በሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ ተመርቆ ስራ ጀምሯል።በ250 ሚሊየን ብር ካፒታል የተከፈተው ፋብሪካው በቀን እስከ 10 መኪኖችን የመገጣጠም አቅም እንዳለው ተገልጿል።

ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ ፋብሪካውን መርቀው በከፈቱበት ወቅት እንዳሉት በክልሉ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጎለበተ ይገኛል።

ፋብሪካው ለዜጎች የስራ እድል ከመፍጠር ባለፈ የውጭ ምንዛሬ ወጪን በመቀነስ ረገድ ፋይዳው የላቀ መሆኑን ጠቁመው የክልሉ መንግስትም ለግሉ ዘርፍ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ ይቀጥል ብለዋል።

[Walta]
@YeneTube @FikerAssefa
የቀድሞ ተዋጊዎችን ትጥቅ የማስፈታት እና ወደ ማህበረሰቡ መልሶ የማዋሃድ የቅድመ ማስጀመሪያ ምክክር በመቀለ ተጀመረ!

የቀድሞ ተዋጊዎችን ትጥቅ የማስፈታት፣መበተን እና ወደ ማህበረሰቡ መልሶ የማዋሃድ የቅድመ ማስጀመሪያ ምክክር በትግራይ መዲና መቀለ ተጀመረ።ትናንት ግንቦት 5/ 2016 ዓ.ም በተጀመረው በዚህ ምክክር ላይ የፌደራል መንግሥት ተወካዮች፣ የትግራይ ጊዜያዊ መንግሥት አመራሮች እና የአፍሪካ ኅብረት የስምምነት ክትትል፣ አረጋጋጭ እና አስከባሪ ኮሚቴ አባላት መገኘታቸውን የብሔራዊ ተሐድሶ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ተመስገን ጥላሁን በኤክስ ገጻቸው አስታውቀዋል።

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዚዳንቶች ጄነራል ታደሰ ወረደ እና ጄኔራል ጻድቃን ገብረትንሳኤን ጨምሮ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በዚህ ምክክር ላይ ተዋጊዎችን በመበተን እና ሁለንተናዊ በሆነ መልኩ ወደ ህብረተሰቡ ለማዋሃድ ፕሮግራም፣ ፕሮጀክቶች መንደፍ እንዲሁም የመጀመሪያው የትግበራ እቅድ ላይ ውይይት እንደሚደረግ ተጠቅሷል።

ኮሚሽነሩ በተጨማሪም “ተዋጊዎች የሚበተኑበት የተመረጡ ስፍራዎች የመስክ ጉብኝት እንደሚካሄድም” በትናንትናው ዕለት ባሰፈሩት የኤክስ መልዕክታቸው ጠቁመዋል።ለሁለት ዓመት የዘለቀውን ደም አፋሳሽ የቋጨው የፕሪቶሪያው ግጭትን በዘላቂነት የማስቆም ስምምነት እና የናይሮቢ የትግበራ ሰነድ የትግራይ ኃይሎች የከባድ መሳሪያ ማውረድ የሚካሄደው የውጭ እና የፌደራሉ መከላከያ ሠራዊት ያልሆኑ የክልል ኃይላት ከትግራይ በተመሳሳይ ወቅት ሲወጡ እንደሆነ ጠቅሷል።

ሙሉ ዘገባውን ለማንበብ:-

https://www.bbc.com/amharic/articles/cv2001z2zdxo

@YeneTube @FikerAssefa
ለድርጅትዎ የGOOGLE ማስታወቂያ ማሰራት ይፈልጋሉ?

ማስታወቂያዎት ደንበኛ ሊሆንዎት ከፍተኛ እድል ወዳላቸው ሰዎች(Potential
Customers) እንዲደርስስ?

-ጉግል ሰርች ላይ ለሚመጡ ማስታወቂያዎች፤
-በዩቲውብና ጂሜይል ለሚታዩ ማስታወቂያዎች፤
-በተለያዩ አፕሊኬሽኖች ላይ የሚታዩ ማስታወቂያዎችን በማሰራት ምርትና አገልግሎትዎን ለማሳደግ ከፈለጉ ያናግሩን።

ከዚህም በተጨማሪ ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም እና ኤክስን በመሳሰሉ የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ማስታወቂያ ማሰራትም ይችላሉ።

ቴሌግራም፡ @adsommar
ስልክ፡ 0954260423
በገጠር የመሬት ሽያጭ እና ግዢ የሚያከናውኑ ሰዎችን እስከ አምስት አመት በእስር የሚያስቀጣ አዋጅ በፓርላማ ጸደቀ!

የገጠር መሬትን በሸጠ ወይም በገዛ ማንኛውም ሰው ላይ እስከ አምስት ዓመት የሚደርስ ፅኑ እስራት ቅጣት የሚጥል አዋጅ በተወካዮች ምክር ቤት ጸደቀ። አዲሱ አዋጅ የግል፣ የወል ወይም የመንግስት ይዞታን በህገ ወጥ መንገድ ወርሮ ለተገኘ ሰውም ተመሳሳይ የእስራት ቅጣት ደንግጓል።

የተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ማክሰኞ ግንቦት 6፤ 2016 በነበረው መደበኛ ስብሰባው በሙሉ ድምጽ ያጸደቀው ይህ አዋጅ፤ ከ18 ዓመት በፊት የወጣውን የገጠር መሬት አስተዳደር እና አጠቃቀም አዋጅን ያሻሻለ ነው። አዲሱ አዋጅ አርሶ አደሮች፣ አርብቶ አደሮች እና ከፊል አርብቶ አደሮች በመሬት ላይ ያላቸውን መብቶች ያሻሻለ ሲሆን፤ የሴቶች እና ድጋፍ የሚሹ ሰዎችን የመሬት ተጠቃሚነት መብት ያረጋገጡ ድንጋጌዎችንም አካትቷል።

አዋጁ በረቂቅ ደረጃ ለፓርላማ ከቀረበ በኋላ ከተደረጉ ማሻሻያዎች መካከል፤ “የወንጀል ተጠያቂነት” በሚመለከተው የተጨመረው አንቀጽ ይገኝበታል። “ከመሬት ጋር ተያይዘው የሚፈጸሙ ወንጀሎች ላይ አስተማሪ እና ተመጣጣኝ ቅጣት ማስቀመጥ አስፈላጊ በመሆኑ” ምክንያት እንደተካተተ የተነገረለት ይህ ድንጋጌ፤ ከመሬት ወረራ እስከ መሬት ሽያጭ ድረስ ያሉ የህግ ጥሰቶች የሚያስከትሏቸውን ቅጣቶች ዘርዝሯል።

(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)
@YeneTube @FikerAssefa
🌸m.shein.com  ከ Fashionnova.comAmazon.com ዌብሳይት ላይ  መግዛት የሚፍልጉትን እቃ ሊንኩን ወይም ፎቶውን ይላኩልን እኛ ከ15 እስከ 20 ቀን ውስጥ አስመጥተን እናስረክብዎታለን።

🌸ስልክ:- 0988747602 @Afufu98

🌸ክፍለሀገር በፖስታ ቤት እንልካለን::

ቴሌግራም ሊንክ:- https://www.tg-me.com/CFLqualityshop
ይህ ምንም ቅድመ ክፍያ ማዘዝ ይችላሉ
📢🎉ለ12ኛ ማትሪክ እና ለመውጫ ፈተና ተፈታኞች!
ተማሪው መተግበሪያን ከፕለይስቶር በማውረድ ለፈተናዎ በቂ ዝግጅት ያድርጉ!

🔸ለ12ኛ ማትሪክ ተፈታኞች:- በመተግበሪያችን ከ አዲሱ የ12ኛ ክፍል ካሪኩለም የተወጣጡ ከ 2000 በላይ መለማመጃ ጥያቄዎችን ያገኛሉ።

🔸ለመውጫ ፈተና ተፈታኞች:-
🔹ለአካውንቲንግ
🔹ቢዝነስ ማኔጅመንት
🔹ኮምፒዩተር ሳይንስ
🔹ሆቴል ማኔጅመንት
🔹ማርኬቲንግ ማኔጅመንት
መለማመጃ ጥያቄዎችን ያገኛሉ።

በተጫማሪም መተግበሪያውን ለልጅዎ፣ ለቤተሰብዎ፣ ለዘመድዎ 🎁በስጦታ ማበርከት ይችላሉ።🎁
በመተማ ወረዳ ታጣቂዎች አደረሱት በተባለው ጥቃት አምስት ሰዎች ተገደሉ!

ከማዕከላዊ ጎንደር ዞን ጎንደር ከተማ ወደ መተማ ወረዳ በሚወስደው ዋና መንገድ ሲጓዙ በነበሩ ተሽከርካሪ ላይ ታጣቂዎች ፈፀሙት በተባለ ጥቃት፣ አምስት ሰዎች መገደላቸውንና አምስት ሰዎች መቁሰላቸውን የዐይን እማኞች ነን ያሉ ተናገሩ።ከጎንደር ከተማ ወደ መተማ ወረዳ ሲያመራ "ነጋዴ ባሕር" ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ወጣ ብሎ ልዩ ስሙ "ኩመር በር" በተባለ ስፍራ፣ ባለፈው ሳምንት ረቡዕ፣ ሚያዝያ 30 ቀን 2016 ዓ.ም. በታጣቂዎች ጥቃት ጉዳት በደረሰበት ተሽከርካሪ ውስጥ እንደነበር ገልፆ ለደኅንነቱ ስለሚሰጋ ስሙን እንዳንጠቅስ የጠየቀን ወጣት፣ በጥቃቱ እግሩ መመታቱን ተናግሯል።

ስለኹኔታ በስልክ የነገረን እና አኹን በመተማ ጠቅላላ ሆስፒታል በመታከም ላይ እንደሚገኝ የገለፀልን ይኸው ወጣት፣ በዕለቱ በጎንደር ከተማ ከሚኖሩት እናቱ ጋራ የፋሲካን በዓል አክብሮ ወደ መተማ በመመለስ ላይ እንደነበር ተናግሯል።በዕለቱ ከጫካ ውስጥ የወጡ ታጣቂዎች፣ በሚያልፉ ተሽከርካሪዎች ላይ በከፈቱት የተኩስ እሩምታ በርካታ ሰዎች መቁሰላቸውንና መኪኖቹም መቆማቸውን ገልጿል።

ታጣቂዎቹም ከቆሙት መኪኖች ውስጥ ተሳፋሪዎችን አስወርደው ወደወጡበት ጫካ ለመውሰድ ሲሞክሩ፣ "አንሔድም" በማለት የተቃወሟቸውን ተኩሰው ሲገድሏቸው መመልከቱን ወጣቱ የዐይን እማኝ አስረድቷል።

ከምዕራብ ጎንደር ዞን ትክል ድንጋይ ቀራንዮ መድኀኔዓለም ከተባለ ገዳም ተነሥተው ቤተሰቦቻቸውን ለመጠየቅ ወደ ቋራ በመጓዝ ላይ እያሉ በተሳፈሩበት ሚኒባስ ታክሲ ላይ የተተኮሰው ጥይት እጃቸውን ማቁሰሉን የነገሩን ሌላዋ የዐይን እማኝ፣ ታጣቂዎቹ እርሳቸው ይጓዙበት የነበረውን ሚኒባስ ታክሲ ጨምሮ ቢያንስ ዐሥር ተሽከርካሪዎችን አስቁመው መመልከታቸውን ተናግረዋል።አስተያየት ሰጪዎች የታጣዊዎችን ማንነት መለየት እንዳልቻሉ ተናግረዋል። በምዕራብ ጎንደር ዞን በመተማ ወረዳ እና አካባቢው፣ በንጹሐን ዜጎች ላይ ተደጋጋሚ ጥቃቶች እና እገታዎች ሲፈጸሙ መቆየቱን በየጊዜው መዘገባችን ይታወሳል።

የምዕራብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ቢክስ ወርቄ፣ ባለፈው ዓመት ሰኔ ወር ላይ፣ ከአሜሪካ ድምፅ ጋራ በነበራቸው ቆይታ፣ በአካባቢው ተደጋጋሚ ግድያ እና እገታ እንደሚፈጸም አምነው፣ አካባቢውን የሚያረጋጋ የመንግሥት የጸጥታ ኀይል ስምሪት ተደርጎ እንደነበር ተናግረዋል።የመተማ አጠቃላይ ሆስፒታል የድንገተኛ ክፍል አስተባባሪ አቶ ሰይፉ አሌ፣ ችግሩ በተደጋጋሚ እንደሚያጋጥም ገልጸው፣ መንግሥት ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ያመለክታሉ።

ያለፈው ሳምንት ረቡዕ ጥቃት ስለመፈጸሙ መረጃ እንደደረሳቸው የጠቀሱልንና ለጊዜው ስማቸውን በምስጢር እንድንይዝ የጠየቁን አንድ የዞኑ ከፍተኛ ባለሥልጣን፣ በዕለቱ ታጣቂዎቹ 30 ሰዎችንም ከቦታው አግተው እንደወሰዱ አስታውቀዋል።ኾኖም፣ የጸጥታ ኀይሎች ከአካባቢው ማኅበረሰብ ጋራ በመኾን ባደረጉት ርብርብ፣ ታጋቾቹን በማግሥቱ ለማስለቀቅ መቻሉን ባለሥልጣኑ ገልጸዋል።

Via VoA
@YeneTube @FikerAssefa
የነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን ሰዉ ሰራሽ የነዳጅ እጥረት እንዲፈጠር በሚያደርጉ ነዳጅ ማደያዎች ላይ ከማሸግ የዘለለ እርምጃ መዉሰድ የሚያስችለውን አዋጅ ማዘጋጀቱ ተነገረ!

ባለስልጣኑ ባዘጋጀው በዚህ አዋጅ ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት ሰው ሰራሽ የነዳጅ እጥረት በሚፈጥሩ ሕገ ወጦች ላይ እስራትና የገንዘብ ቅጣት እርምጃ መውሰድ የሚያስችሉ አንቀጾች መካተታቸውን ተጠቁመዋል።

አዋጁ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት መቅረቡን ተከትሎ በቅርቡ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸድቆ ወደ ስራ እንደሚገባ የተነገረ ሲሆን በነዳጅ ማደያዎች ነዳጅ እያለ እንደሌለ ማስመሰል፣ የነዳጅ ግብይትን በጥሬ ገንዘብ መሸጥ፣ ነዳጅን በተለያዩ ስፍራዎች ደብቆ ማስቀመጥና የመሳሰሉትን ህገወጥ አሰራሮችን ሊያስቀር እንደሚችል ካፒታል ከተቋሙ ያገኘው መረጃ ያመለክታል ።

Via Capital
@YeneTube @FikerAssefa
ቦይንግ በኢትዮጵያው አየር መንገድ አደጋ በወንጀል ሊከሰስ እንደሚችል አሜሪካ አስታወቀች!

ለ346 ሰዎች ህይወት እልቂት ለሆነው የኢትዮጵያው አየር መንገድ እና የኢንዶኔዥያው የ737 ማክስ 9 አውሮፕላን አደጋዎች ቦይንግን በወንጀል ለመክሰስ እያጤነው እንደሆነ የአሜሪካ የፍትህ መስሪያ ቤት አስታወቀ።ቦይንግ የሚያመርታቸውን አውሮፕላን ምርቶች ደኅንነት እና ጥራት ለማስጠበቅ ከሦስት ዓመት በፊት ከአሜሪካ የፍትህ ሚኒስቴር ጋር የገባውን የቁጥጥር መርሃ ግብር ስምምነት መጣሱንም መስሪያ ቤቱ ገልጿል።

ቦይንግ የቀረበበትን ስምምነት ጥሷል ክስ አስተባብሏል።በአቪዬሽን ኢንዱስትሪው አሰቃቂ በተባለው የቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን አደጋዎች በኢትዮጵያው 157 እንዲሁም በኢንዶኔዥያው አየር መንገድ 189 ሰዎች ህይወት ተቀጥፏል።

የአሜሪካ የፍትህ መሥሪያ ቤት በአውሮፕላንን አምራቹ ላይ ካደረገው የረዥም ጊዜ ምርመራ በኋላ ቦይንግ ለ737 ማክስ አውሮፕላኑ ፍቃድ ለማግኘት ሲል ሆን ብሎ የፌደራል አቪዬሽን አስተዳደር ተቆጣጣሪዎችን እንዳሳሳተ ደርሸበታለሁ በሚል “አሜሪካን ለማጭበርበር በማሴር” በሚል ከሦስት ዓመት በፊት ክስ መስርቶበት ነበር።

ቦይንግ ቺካጎ በነበረው የፍርድ ሂደት በአደጋው ሕይወታቸውን ላጡ መንገደኞች ቤተሰቦች ካሳ ለመክፈል ተስማምቶ በምላሹም የአሜሪካ የፍትሕ መሥሪያ ቤት ለአውሮፕላን አምራቹ ከ737 ማክስ ዲዛይን ጉድለት ጋር በተያያዘ በማጭበርበር ሴራ በወንጀል እንዳይከሰስ ከለላ ሰጥቶት ነበር።

የአውሮፕላን አምራቹ በአደጋው ለሞቱት ሰዎች ኃላፊነቱን እንደሚወስድ እና ተጠያቂነቱን ተቀብሎ ለአሜሪካ መንግሥት፣ አደጋ ለደረሰባቸው አየር መንገዶች እና ለተጎጂዎች የሚሆን 2.5 ቢሊዮን ዶላር የቅጣት ካሳ ለመክፈል ተስማምቷል።

ቦይንግ 2.5 ቢሊዮን ዶላር ለመክፈል ከአሜሪካ ዐቃቢያነ ሕጎች ጋር የደረሰው ስምምነት ኩባንያው በአደጋው ዙሪያ የሚካሄደው የወንጀል ምርመራ እንዲቀር የተስማማበት ነው።በወቅቱም የፌደራል ዐቃቢያነ ሕጎች ቦይንግ ለመጪው ሦስት ዓመታት ያህል ለስምምነቱ ተገዢ ከሆነ የወንጀል ክሱን ለመተው ተስማምተው ነበር።

ሆኖም ስምምነቱ ጊዜው ከማለፉ በፊት በአላስካው አየር መንገድ የቦይንግ ማክስ 9 በር በአየር ላይ ተገንጥሎ መውደቁን ተከትሎ የምርቶቹን ደህንንት እና ጥራት ለማስጠበቅ የገባውን የቁጥጥር መርሃ ግብር ስምምነቱን መጣሱን ማሳያ እንደሆነም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አመላክቷል።

በያዝነው ዓመት ታህሳስ ወር ከኦሬገን ግዛት ፖርትላንድ ከተማ ተነስቶ ወደ ካሊፎርኒያ ሲበር የነበረው አዲስ ሞዴል የሆነው ቦይንግ 737 ማክስ አውሮፕላን ከተነሳ በኋላ የኋላ በሩ በበረራ ላይ እያለ ተገንጥሎ መውደቁን ተከትሎ በአውሮፕላኑ ደኅነት ላይ ከፍተኛ ጥያቄዎች እየተነሱበት ይገኛል።

Via BBC
@YeneTube @FikerAssefa
የፕላስቲክ አምራቾች የወረቀትና የጨርቅ ከረጢቶችን በአፋጣኝ ማምረት እንዲጀምሩ ማሳሰቢያ ተሰጠ

አካባቢን ሊበክሉ የሚችሉ ስስ ፕላስቲኮችን የሚያመርቱ ድርጅቶች የአካባቢ ብክለትን የሚቀንሱ የወረቀትና የጨርቅ ከረጢቶች በአፋጣኝ ማምረት እንዲጀምሩ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን አሳሰበ፡፡

ፕላስቲክ በማምረት የተሰማሩ ድርጅቶችና ባለቤቶች ከተፈቀደላቸው 0.03 ማይክሮ ሜትር በታች ሲያመርቱ ከተገኙ፣ ከመዝጋታቸው ባሻገር፣ ከሦስት ዓመት እስከ አሥር ዓመት የእስር ቅጣት እንደሚያስከትልባቸው ሪፖርተር አስነብቧል።

በተጨማሪም ለኅብረተሰቡ ዳቦ የሚያከፋፍሉና ሌሎች ሸቀጦችን በፕላስቲክ ምርቶች ጠቅልለው የሚሸጡ ቸርቻሪዎችም ሆኑ አከፋፋዮች፣ ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ይደረጋል ተብሏል።

ሸማቾች ማንኛውንም ዕቃ ሲሸምቱ የፕላስቲክ ውጤቶችን ከመጠቀም ይልቅ፣ ከወረቀትና ከጨርቅ የተሠሩትን መጠቀም ይገባል በማለት ባለስልጣኑ አመልክቷል።

@Yenetube @Fikerassefa
የስሎቫኪያ ጠቅላይ ሚንስትር በጥይት ተመተው ሆስፒታል ገቡ!

የስሎቫኪያ ጠቅላይ ሚንስትር በጥይት ተመተው ሆስፒታል ገቡ።ባሳለፍነው ጥቅምት በተደረገ ምርጫ ወደ ስልጣን የመጡት የስሎቫኪያ ጠቅላይ ሚንስትር በጥይት ተመተው ሆስፒታል ገብተዋል ተብሏል።

ሮይተርስ የአይን እማኞችን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው ጠቅላይ ሚንስትር ሮበርት ፊኮ የካቢኔ ስብሰባ አድርገው ሲወጡ ከአንድ ግለሰብ በተተኮሰ ጥይት ተመተዋል።ፖሊስ ተጠርጣሪውን ወዲያውኑ በቁጥጥር ስር አውሎታል የተባለ ሲሆን በተጠርጣሪው ላይ ተጨማሪ ምርመራ በመካሄድ ላይ እንደሆነም ተገልጿል።

ጠቅላይ ሚንስትሩ ለህክምና ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል የተባለ ሲሆን የሀገሪቱ መንግሥት እስካሁን ስለ ጉዳዩ በይፋ ያለው ነገር የለም።ጠቅላይ ሚንስትር ፊኮ ኔቶን ጨምሮ ምዕራባዊያን ሀገራት ለዩክሬን የጦር መሳሪያ ድጋፍ ማድረግ የለባቸውም በሚል አቋማቸውም ይታወቃሉ።ዩክሬን ከሩሲያ ጋር እያደረገችው ያለው ጦርነት እንዲቆም ከተፈለገ ኪቭ ክሪሚያ የሩሲያ መሆኗን ማመን እና መቀበል እንዳለባት በተደጋጋሚ ሲናገሩ ይደመጣሉ።

Via Al-ain
@YeneTube @FikerAssefa
2024/05/16 01:49:53
Back to Top
HTML Embed Code: